EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

Share

EBC Sport is one of Ethiopian Broadcasting Corporation social media focusing on Sports.

Photos from EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት's post 03/09/2026

“የባሎንዶር ሽልማት ለፒኤስጂ ተጫዋቾች ሊሰጥ ይገባል” - ሉዊስ ኤንሪኬ
*****************

ከቀናት በፊት የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ዓለም ዋንጫን የመሰሉ ውድድሮችን ማሸነፍ የባሎንዶር የዓለም ኮከብነት ሽልማትን ለማግኘት ብቸኛ መስፈርት ሊሆን እንደማይገባ መናገራቸው ይታወሳል።

በዚህ ሳያበቁም በዓለም ዋንጫ ታሪክ 22 ግቦች በማስቆጠር የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የተሰኘው ኪሊያን ምባፔ ሽልማቱን ሊያገኝ ይገባል የሚል ሃሳብም ሰንዝረው ነበር።

ሉዊስ ኤንሪኬ ደግሞ ከዚህ የሞሪንሆ ሃሳብ ተቃራኒውን ሰንዝረዋል። አሰልጣኙ በግለሰብ ደረጃ እከሌ ማሸነፍ አለበት ብለው ስም ባይጠቅሱም፣ ተጫዋቾቻቸው በቀደመው የውድድር ዘመን በክለብም ሆነ በብሔራዊ ቡድኖቻቸው ያስመዘገቧቸው ስኬቶች ለዚህ ሽልማት ብቁ የሚደርጋቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከፒኤስጂ ጋር ያነሱትን ኡስማን ዴምቤሌ እና ክቪቻ ክቫራኬሊያን ጨምሮ፣ ከስፔን ጋር የዓለም ዋንጫን ያሳካውን ፋቢያን ሩዊዝን በመጥቀስ የቡድን አባሎቻቸውን ለሽልማቱ ተገቢ መሆን አብራርተዋል።

ኤንሪኬ “የሽልማቱ አሸናፊ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን አልያም ፒኤስጂ መሆኑ ግዴታ አይደለም” ለሚለው የጆዜ ሞሪንሆ ሃሳብ ምላሽ በሚመስል መልኩ ነው ይህን አስተያየት የሰነዘሩት።

“በዓለም ላይ በአሁን ሰዓት ከ12 ያላነሱ ታላላቅ ተጫዋቾች አሉ፤ ከነዛ ውስጥ ከአራት ያላነሱት ሪያል ማድሪድ ነው የሚገኙት” የሚለው የሞሪንሆ ሙግት ሌላኛው ነጥብ ነው።

70ኛው የባሎንዶር ሽልማት በህዳር ወር ለንደን ላይ ይካሄዳል።

በእድሪስ አህመድ

03/09/2026

ኢቲቪ ስፖርት ምሽት - አረንጓዴ ጎርፍ - የአበበ ቢቂላ የባዶ እግር ድል ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ምን አበረከተ?

03/09/2026

የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ እጩ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር ይፋ ሆነ
*********************

መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በሚካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዝዳንታዊ ምርጫ በዕጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ጅራ የቀረቡ እጩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ተጠባባቂ አባላትን ስም ዝርዝር ፌዴሬሸኑ ይፋ አደርጓል።

Photos from EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት's post 03/09/2026

ኔይማር ጁኒየር ተጨማሪ ጉዳት አጋጠመው
**************

በእግር ኳስ ታሪክ ከታዩ እና በተደጋጋሚ ጉዳት ከተፈተኑ ኮከቦች አንዱ ኔይማር ጁኒየር ነው። በቅርቡ በተካሄደው 23ኛው የዓለም ዋንጫም ተጫዋቹ ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን የሚጠበቅበትን እንዳያደርግ ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ጉዳት ነው።

የ34 ዓመቱ ኔይማር አዲሱ ጉዳት ያጋጠመው በብራዚል ዋንጫ ክለቡ ሳንቶስ ፓልሜራስን ገጥሞ 3 ለ 0 በተረታበት ጨዋታ ነው። ኔይማር ጉዳቱ ያጋጠመው ከመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቅ በፊት ቢሆንም፣ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ተጫውቶ ለእረፍት ሜዳውን በእንባ ታጅቦ ለቆ ወጥቷል።

ከዓለም ዋንጫው በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ያገለለው ኔይማር፣ በዚህ የውድድር ዓመት ለሳንቶስ በ24 ጨታዎች ላይ ተሰልፎ 8 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።

በብራዚል እግር ኳስ ስኬታማ ከሆኑ ቡድኖች አንዱ የሆነው ሳንቶስ የሊጉን ዋንጫ ለ8 ጊዜያት ያክል አንስቷል። ሆኖም ይህ ፔሌን ጨምሮ በርካታ የዓለም እግር ኳስ ክዋክብት ተጫውተው ያለፉበት ክለብ የብራዚልን ሴሪአ ዋንጫ ካነሳ 22 ዓመታት ተቆጥረዋል።

በዘንድሮው የውድድር ዓመትም ከወራጅ ቀጠናው በአራት ነጥቦች ብቻ ርቆ በ29 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በእድሪስ አህመድ

EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

Photos from EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት's post 03/09/2026

በሊቨርፑል የተጫዋቾች ዝውውር እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆናቸውን አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ ተናገሩ
********************

በአዲሱ የውድድር ዓመት ሊቨርፑልን የተረከቡት አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ ክለቡ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ባስፈረማቸው ተጫዋቾች ደስተኛ መሆናቸውን፣ ይህም ቡድኑን ለማጠናከር በእጅጉ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።

ሊቨርፑል በዚህ የዝውውር መስኮት አራት ዋና ዋና ዝውውሮችን ያደረገ ሲሆን፣ በ123 ሚሊዮን ፓውንድ ከፓሪስ ሴንት ዘርሜን ያስፈረሙት ብራድሊ ባርኮላ በጉልህ ይጠቀሳል።

ምንም እንኳ ተጨማሪ ተጫዋቾችን የማስፈረም አማራጮችን ለመውሰድ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም፣ አሁን ባሏቸው ተጫዋቾችም ቢሆን ክለቡን የማጠናከር ስራ እንደሚሰሩና በውድድር ዓመቱ ጠንካራ ተፎካካከሪ ለመሆን ከተጫዋቾቻቸው ጋር ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

አዲሱ ፈራሚ ብራድሊ ባርኮላ ነገ ሊቨርፑል ከኢፕስዊች ታውን ጋር በሚያደርገው የሦስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሊሰለፍ እንደሚችል ይጠበቃል።

ሊቨርፑል ባለፈው የውድድር ዓመት 5ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ በተያዘው የውድድር ዓመት በሁለቱ ሳምንታት፣ ሁለቱንም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቆ በ2 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በእድሪስ አህመድ

03/09/2026

ስለ ስፖርት
*****

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ብቸኛው እጩ ተወዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ጅራ የ‘ስለ ስፖርት’ እንግዳ ናቸው።

አቶ ኢሳያስ ለአዲሱ የምርጫ ዘመን ምን አዲስ ሃሳብ ይዘዉ መጡ?
በአስተዳር ጊዜያቸዉ እግር ኳሱ የደረሰበት ስኬት እና የገጠሙት ፈተናዎች እና
በምርጫዉ ዙሪያ እየተነሱ ያሉ ሃሳቦች ይዳሰሳሉ።

በእነዚህና ሌሎች ከምርጫው ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ከአቶ ኢሳያስ ጅራ ጋር ቆይታ
እናደርጋለን።

ቅዳሜ ከ3፡00 – 5፡00 ሰዓት በኢቲቪ መዝናኛ እና በዶት ስትሪም አማራጮች ይጠብቁን!

03/09/2026

የ1954ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ድል ትውስታ እና አሁን የተሰነቀው ተስፋ
************************

የኢትዮጵያ እግር ኳስ በአፍሪካ መድረክ የነገሠበት፣ ሰንደቅ ዓላማዋ በአኅጉሪቱ ትልቁ የስፖርት መድረክ ላይ ከፍ ብሎ የተውለበለበበት ብሎም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምታልም ሳትሆን የዋንጫው ባለቤት የነበረችበት ወርቃማ የታሪክ ምዕራፍ ነበር።

ጥር 13 ቀን 1954 ዓ.ም አዲስ አበባ የአፍሪካ እግር ኳስ መናኸሪያ ሆና 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታስተናግድ፣ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ለፍጻሜው ደረሰች። በኢትዮጵያ እና በታሪካዊው ድል መካከል የቆመው ደግሞ የወቅቱ ሻምፒዮን የነበረው የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ነበር።

በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ስታዲየም (የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) የተሰበሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ ትልቁን ድንቅ ምዕራፍ ለመመልከት ታደሙ። ፍልሚያው ግን እጅግ ፈታኝ ነበር።

በ35ኛው ደቂቃ ባዳዊ አብደል ፈታሕ ግብ አስቆጥሮ ግብጾችን መሪ አደረገ። በሁለተኛው አጋማሽ ግርማ ተክሌ አቻ ቢያደርግም፣ ባዳዊ በ75ኛው ደቂቃ ሁለተኛ ግቡን በማስቆጠር ኢትዮጵያን ከሽንፈት አፋፍ ላይ አድርሷት ነበር። ሆኖም 84ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈርጥ መንግሥቱ ወርቁ ባስቆጠራት አስደናቂ ግብ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2 ለ 2 ተጠናቅቆ ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ።

በጭማሪው ሰዓት የታሪክ ገጾች ለኢትዮጵያ በደማቁ ተጻፉ። በ101ኛው ደቂቃ ኢታሎ ቫሳሎ ኢትዮጵያን መሪ ሲያደርግ፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት መንግሥቱ ወርቁ ለራሱ ሁለተኛዋን ግብ በማስቆጠር ውጤቱን 4 ለ 2 አደረገው። የዳኛው የመጨረሻ ፊሽካ ሲሰማ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆኗ ታወጀ።

በዕለቱ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የነበረው ደስታ እና ሕዝቡ በሬዲዮ ዙሪያ ተሰብስቦ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይከታተልበት የነበረው ስሜት ወደር አልነበረውም።

ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዋንጫውን ለአንበሉ ሉቺያኖ ቫሳሎ ሲያስረክቡ የታየው ምሥል የሀገር ብሔራዊ ኩራት መገለጫ ሆኖ ለትውልድ ተላልፏል።

ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የ1949ኙ የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ፣ በ1951ዱ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ካጠናቀቀች በኋላ ነው በ1954ቱ በግማሽ ፍጻሜው ቱኒዚያን 4 ለ 2 እንዲሁም በፍጻሜው ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 በማሸነፍ በሁለት ጨዋታዎች 8 ግቦችን አስቆጥራ ታሪካዊውን ዋንጫ ወደ ቤቷ ያስገባችው።

ያ ድል ለሀገራቸን ከ64 ዓመታት በኋላ ዛሬም ድረስ ብቸኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሆኖ ይገኛል። የእግር ኳስ ዓለም ተቀይሯል፤ ውድድሩም በገንዘብ፣ በስታዲየሞች ደረጃ እና በታክቲክ እጅግ የበለጸገ ሆኗል።

ነገር ግን የመንግሥቱ ወርቁ፣ የሉቺያኖ ቫሳሎ፣ የኢታሎ ቫሳሎ እና የግርማ ተክሌ አሻራ በታሪክ መዝገብ ውስጥ ሕያው ሆኖ ይኖራል።

ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ዳግም ለማስተናገድ እና ወደ አኅጉሩ የውድድር መድረክ በድምቀት ለመመለስ በምታልምበት ወቅት፣ ይህንን ታሪካዊ ድል ማስታወስ ለወደፊቱ ጉዞ ትልቅ ብርታት ነው።

ምክንያቱም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ማማ ላይ ነበር፤ ሀገራችን ዋንጫውንም አሸንፋለች።

በመሆኑም ወደፊት የአፍሪካ መድረክ ላይ ስኬታማ ለመሆን የሚደረገው ጥረት የነገ ሕልም ብቻ ሳይሆን፣ ትናንት በተግባር የተረጋገጠ የታሪክ እውነት ጭምር ነው።

በእሱባለው ተሾመ

Photos from EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት's post 03/09/2026

ለሊዮኔል ሜሲ በመላው አርጀንቲና የክብር ስንብት ሊደረግለት ነው
************************

ከቀናት በፊት ከብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ራሱን ያገለለው ሊዮኔል ሜሲ፣ በመላው አርጀንቲና ደማቅ የሽኝት እና የምስጋና ስነ-ስርዓት እንደተዘጋጀለት የአርጀንቲና እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል።

በቀጣይ ሳምንት በመላው አርጀንቲና በሚገኙ በሁለቱም ፆታ የትኛውም እርከን በሚካሄዱ ውድድሮች በመጀመሪያው አጋማሽ 10ኛው ደቂቃ ላይ እንደሚቋረጡ ነው የእግር ኳስ ማህበሩ ያስታወቀው። 10ኛው ደቂቃ የተመረጠውም ሊዮኔል ሜሲ ይለብስ የነበረውን 10 ቁጥር መለያ ለማሰብ ነው።

10ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ ጨዋታዎቹ በዳኞች ፊሽካ እንዲቆሙ ይደረጋል። ከዚያም ተጫዋቾችን ጨምሮ በስታዲየሞች ውስጥ የታደሙ ሁሉ በጭብጨባ ለሜሲ ያላቸውን አክብሮት እና ስንብት ይገልፃሉ።

እንደ እግር ኳስ ማህበሩ ገለጻ ከ10ኛው ደቂቃ የጨዋታ መቋረጥ በተጨማሪ፣ ከጨዋታዎቹ መጀመር በፊት የሚሲን ስንብት የሚገልፁ የምስል መልዕክቶች እንደሚተላለፉም ተገልጿል።

በእግር ኳስ ታሪክ ከተሰሙ የስንብት ዜናዎች ከቀዳሚዎቹ የሚመደበው የሜሲ ስንብት፣ በስታዲየሞች ውስጥ በሚኖር ደማቅ ህብረ-ዝማሬ እንደሚደምቅም ይጠበቃል።

የ39 ዓመቱ ሜሲ ከ20 ዓመታት በላቀ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቆይታው በ207 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 125 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።

በእድሪስ አህመድ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
3344