22/09/2026
አርሰናልን ከአናት ለማውረድ ከሊጉ ጥምረት ሰብሳቢ ማይክል ካሪክ የተሰጠ ለግለጫ፦ ለፈገግታ ነው ደሞ
የአምባገነኑን የአርሰናል የበላይነት ለመስበር ከተመሰረተው የሊጉ ክለቦች ህልውና ትብብር የተሰጠ መግለጫ!
የሚኬል አርቴታ አምባገነናዊ አገዛዝ ከተንሰራፋበት ጊዜ ጀምሮ፣ በየሳምንቱ ባካሄዳቸው የኮርና እና የሴት ፒስ ጥቃቶች ምክንያት መላው የሊጉ ክለቦች በማያቋርጥ የደስታ ማጣት አዙሪት ውስጥ ይገኛሉ። የውጭ ተጫዋቾችን እና ቫርን በመቅጠር ህዝቤ በሚለው ደጋፊ ላይ በሰነዘረው የ90 ደቂቃ አሰልቺ ጥቃት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሌሎች ክለብ ደጋፊዎች ሳቅ እና ፈገግታቸውን አጥተዋል፤ ቅዳሜና እሁድን በፍርሃት የሚያሳልፉ ሆነዋል። በዚህም ምክንያት በሊጉ የተለያዩ ክፍሎች (ቼልሲ፣ ሊቨርፑል፣ ስፐርስ) እራሳቸውን ከደረጃ ሰንጠረዥ መውረድ ለመከላከል እና ህልውናቸውን ለመጠበቅ ታግሎ ነጥብ መጋራት አስገዳጅ አማራጭ ሆኗል!
አርቴታ እና አገዛዙ የሌሎችን ክለቦች ነጥብ ለመዝረፍ በማሰብ በሲቲ፣ በኒውካስል እና በሌሎችም ሜዳዎች የሚደረጉትን የህልውና ትግሎች ለማኮላሸት ቲም ቶክ እና Dark Arts የተሰኙ ዘዴዎችን በመጠቀም የደጋፊዎችን አንጀት በማሳረር ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ እውነተኛዎቹ የታሪክ ባለቤቶች የአርቴታን እኩይ ተንኮል በመረዳት አጠቃላይ የእንግሊዝን እግር ኳስ ከተጋረጠው አስልቺ ጨዋታ እና የእኩልነት አደጋ ለማዳን በዕውቀት እና በትዕግስት ሌት ተቀን በመስራት ዛሬ የሊጉ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና በመመስረት የአርሰናልን የካራባኦ እና የፕሪሚየር ሊግ ሴራ ለማክሸፍ ችለዋል።
እኛ ቀያይ ሰይጣኖች የሊጉ ህልውና ትብብር መመስረቱን እውነተኛ ኳስ ለናፈቀው የእግር ኳስ ህዝብ ታላቅ የምስራች መሆኑን እያበሰርን ለተመሰረተው ትብብር ሙሉ ድጋፋችንን እና አጋርነታችንን እንገልፃለን፡፡ አርሰናልን ከደረጃ ሰንጠረዡ አናት ለማውረድ በሚደረገው የጋራ ትግልም ስኬትን እንመኛለን።
በመጨረሻም ይህንን አምባገነን የ3 ነጥብ ዘራፊ ለማስወገድ ብቸኛው መንገድ የመላው ክለቦች አንድነት መሆኑን በማመን፤ ዛሬም በድጋሚ በሰንጠረዡ አናት ላይ ያለውን አምባገነን አገዛዝ ለማስወገድ እና ሊጋችን እንደገና ሳቅና ጨዋታ የሰፈነበት የተጋነነ ጭማሪ ሰዓት የሌለበት ማህበራዊ ሚዲያችን ከታይተል ሬስ ጭቅጭቅ ነፃ የሆነበት ለማድረግ በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን!
ቀያይ ሰይጣኖች መስከረም 2026 ዓ.ም