17/01/2021
ጎልልል ፋሲል ከነማ
❖ ሀድያ 0 - 1 ፋሲል
'
❖ ደቂቃ 85'
በየቀኑ አዳዲስ የባህር ማዶ እና የሀገር ዉስጥ ስፖርታዊ ዜና?
17/01/2021
ጎልልል ፋሲል ከነማ
❖ ሀድያ 0 - 1 ፋሲል
'
❖ ደቂቃ 85'
17/01/2021
♦ ሀድያ 0 - 0 ፋሲል
ደቂቃ 65'
Share
17/01/2021
♦ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል
❖ ሀድያ 0 - 0 ፋሲል
ደቂቃ 45'+2'
Share
17/01/2021
♦ ሀድያ 0 - 0 ፋሲል
ደቂቃ 20'
Share
17/01/2021
♦ ሀድያ 0 - 0 ፋሲል
ደቂቃ 10'
17/01/2021
♦ ሀድያ ሆሳዕና Vs ፋሲል ከነማ
ቀጥታ የጨዋታ ስርጭት
13/01/2021
ረዕቡ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ!
ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት።
═════════════════════════
ባርሴሎና በቀጣዩ ክረምት ከማንችስተር ሲቲ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ሰርጂዮ አጉዌሮን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።( Sun Sport)
════════════════════════
ዶርትመንድ አሁን ጄደን ሳንቾን ለመሸጥ ተዘጋጅቷል የስቱት ጋርቱን የፊት መስመር ተጫዋች ታንጉይ ኳሊባሊን ለመተካት እየተመለከቱ ነው ተብሏል።(France Football)
════════════════════════
የቸልሲው ባለቤት ሮማን አብራሃምኦቪች የቀድሞ የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ የነበረውን አቭራሃም ግራንትን የአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ምክትል አሰልጣኝ አድርገው ወደ ስታምፎርድብሪጅ ለማምጣት እያጤኑ እንደሚገኙ ተዘግቧል። (Sky Sports)
═════════════════════════
ሬያል ማድሪድ ፈረንሳያዊውን የ 22 አመት አጥቂ ኬለን ምባፔን በቀጣዩ በቀጣዩ ክረምት ወደ ሳንቲያጎ በርናበው ለማምጣት 6 ተጫዋቾችን የመሸጥ እቅድ እንዳላቸው ተነግሯል።ጋሬዝ ቤል፣ማርሴሎ፣ሉካ ዮቪች፣ኢስኮ፣ሴባዮስ እና ብራሂም ዲያዝ ናቸው።(AS - in Spanish)
═════════════════════════
የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ቲሞቲ ፎሱ ሜንሳ በቀያይ ሴጣኖቹ የቀረበለትን አዲስ ኮንትራት አልፈርም በማለት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ በ £1.5m ወደ ጀርመኑ ክለብ ባየርሊቨርኩሰን ሊዘዋወር መሆኑ ተዘግቧል።(Manchester Evening News)
═════════════════════════
አሰልጣኝ ኑኖ ሳንቶስ ስፕሪንቶ የአጥቂ ክፍል ችግራቸውን ለመቅረፍ ከቸልሲ ኦሊቨር ዤሩድን እና የሊቨርፑሉን አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊን እንዲጉለት እንዲገዙላቸው ለክለቡ ቢነግሩም ክለቡ ግን በጥሩ የዝውውር መስኮት ምንም አይነት ገንዘብ ለተጫዋቾች ለመመደብ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ነግረውታል። (Mirror)
═════════════════════════
ባየርሙኒክ በክረምቱ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የሬዲንጉን የ 22 አመቱን ተከላካይ ኦማር ሪቻርድስን ቅድመ ኮንትራት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።ኤቨርተን እና ዌስትሃም የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው ተብሏል።(Guardian)
═════════════════════════
የናፖሊው ተከላካይ ካሊዶ ኩሊባሊ ስሙ በስፋት ከሊቨርፑል፣ከማንችስተር ሲቲ እና ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል የኔፕልሱ ክለብም £100m የሚያቀርብለት ክለብ ካለ በዚህ በጥሩ የዝውውር መስኮት የ 29 አመቱን ሴኔጋላዊ ለመሸጥ ዝግጁ ናቸው ተብሏል።(Talksport)
═════════════════════════
ብራዚላዊው አማካይ ካስሜሮ በአሁን ሰዓት በሬያል ማድሪድ ከሚገኙ ተጫዋቾች አሁን ባለው ገበያ ውዱ ተጫዋች ነው ሲል የ audit Specialists KPMG ሪፖርት ያሳያል። (Mundo Deportivo - in Spanish)
═════════════════════════
የ 24 አመቱ ስፔናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ጁኔሮ ፊሪፖ በተለያዩ ክለቦች ቢፈለግም በዚህ የዝውውር መስኮት የመልቀቅ ፍላጎት ስለሌለው በካምፕኑ መቆየት ምርጫው ነው ተብሏል። (Marca)
═════════════════════════
ሚሱት ኦዚል ከቲውተር ተከታታዮቹ ጥያቄ እና መልስ እያደረገ ነበር በዚህ ግዜ ለቶተንሃም ከመፈረም እና ጫማክን ከመስቀል የተኛውን ትመርጣለክ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ኦዚል "ለ ቶትንሃም ከምፈርም ጫማየን ብሰቅል ይሻለኛል" ሲል መለሰ ይህን ጋዜጠኞች ጆሴን ሲጠይቋቸው ጆዜ ሞሪኒሆ "ማነው ቶትንሃም ሊአስፈርምህ ይፈልጋል ብሎ የነገረው ሲል ጥያቄ በሚመስል መልኩ በነገር ሸንቆጥ አድርገውታል። (The Sun)
═════════════════════════
ኤስሚላን የ 23 አመቱን እንግሊዛዊ የመሀል ተከላካይ ፊካዮ ቶሞሪን እስከ ሲዝኑ መጠናቀቅ ድረስ በውሰት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።(The Guardian)
═════════════════════════
የሌስተር ሲቲው አልጄሪያዊ አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ለመዘዋወር የጤና ምርመራ እያደረገ ይገኛል። (Sky Sports)
═════════════════════════
የአርቢላይፕዚኩ ፈረንሳያዊ ተከላካይ ዳዮት አፕሜካኖ በባየርሙኒክ እየተፈለገ ይገኛል፤ቸልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድም የተከላካዮ ፈላጊ ክለቦች ናቸው። (Marca)
═════════════════════════
ቶተንሃም፣ሼፊልድ ዩናይትድ፣ሬንጀርስ እና ሴልቲክ የ 19 አመቱን አጥቂ ኬየል ጆሴፍን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።(Mirror)
═════════════════════════
ዌስትሃም £7m በመደብ ከማርሴ ጋር እየተፎካከረ ይገኛል የ 26 አመቱን ፖላንዳዊ አጥቂ አርካዲዝ ከናፖሊ ለማስፈረም።(Radio Kiss Kiss via SportWitness)
═════════════════════════
የሞናኮ የቀኝ መስመር ተከላካይ ጂብሪል ሲዲቤ በክሪስታል ፓላስ እና ኒውካስል ቢፈለግም ወደ እንግሊዝ የመምጣት ፍላጎት ስለሌለው አሁን ባለበት ፈረንሳይ መቆየት ምርጫው ተብሏል። (France Football via Sport Witness)
═════════════════════════
ቶተንሃም ሆስፐር የ 22 አመቱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ከሬያል ማድሪድ በውሰት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው፤ሮማ፣ኤስ ሚላን እና ኢንተር ሚላንም ተጫዋቹን በውሰት በመውሰድ እንደብቃቱ በቋሚነት ለመግዛትም እቅድ አላቸው ተብሏል።(Corriere dello Sport - in Italian)
═════════════════════════
የስፐርሱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪኒዮ ሊድስ እና ዩቬንቱስን በመቀላቀል የስቱት ጋርቱን የ 22 አመት አርጀንቲናዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኒኮላስ ጎንዛሌዝን ከወዲሁ ለቀጣዩ ክረምት ኢላማቸው አድርገውቷል።(Athletic subscription required)
═════════════════════════
ቫሌንሺያ የ 24 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ሀሪ ዊንክስን በውሰት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ተብሏል።(Football London)
═════════════════════════
ብራይተን የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ የነበረውን ኢኳዶራዊውን አማካይ ሞይስ ካይሴዶን ከኢንዲፔንዴንቴ ኒውካስልን በመርታት እንደሚያስፈርሙት እርግጠኛ ናቸው። (Talksport)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቸልሲ ደግሞ የ 19 አመቱን አማካይ ካይሴዶን ማስፈረም የሚፈልጉት በውሰት ብቻ መሆኑ ተነግሯል።(Mail)
═════════════════════════
አርሰናል ከብራይተን የ 24 አመቱ ማሊያዊ አማካይ ዩቪስ ቤሳውማን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ኢላማቸው አድርገውታል። (Football London)
═════════════════════════
የሊዮኑ ፈረንሳያዊ አጥቂ ሙሳ ዴንቤል ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሰዋል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዮቹ ቀናት ዝውውር ይፋ እንደሚደረግ ተዘግቧል።ዝውውሩ ይህ ሲዝን እስከሚጠናቀቅ በውሰት ይሆን እና ከወደዱት ደግሞ በ €35m የውሰት ውሉ በአመቱ መጨረሻ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭም ማካተታቸው ተዘግቧል። (Telefoot via Sky Sports)
═════════════════════════
DEAL DONE: ሮብ ሆልዲንግ በአርሰናል እስከ 2024 የሚያቆየውን የረጅም ግዜ ኮንትራት መፈረሙ ተረጋግጧል።(Arsenal)
════════════════════════
ኬቨን ስትሩትማን ከማርሴ በመልቀቅ ወደ ጄኖዋ በቋሚ ዝውውር ለመዘዋወር ወደ ጣልያን ማምራቱ ተዘግቧል።(DiMarzio)
════════════════════════
ሰርቢያዊው አጥቂ ሉካ ዮቪች በሬያል ማድሪድ ያልተሳካ ግዜን እያሳለፈ መሆኑን ተከትሎ ወደ ቀድሞ ክለቡ ኢንትራንክፍራንክፈርት እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ሊያመራ መሆኑ ተራግሯል።( GOAL)
════════════════════════
ሜሱት ኦዚል ስለ ሰርጂዮ ራሞስ :
"ሰርጂዮ ራሞስ በእኔ ጊዜ ካሉ ተከላካዮች ምርጡ ተከላካይ ነው" ሲል ተናግሯል።
═════════════════════════
አርሰናል ኢላማ ያደረገውን የ 24 አመቱን አርጀንቲናዊ አማካይ ኤሚሊ ቡዌንዲያን በዚህ በጥሩ የዝውውር መስኮት የማስፈረም እድል የለውም ተብሏል ምክንያቱ ደግሞ የተለጠፈበት የዝውውር ዋጋ £40m በመሆኑ ነው ተብሏል። (Express)
═════════════════════════
የቸልሲው አማካይ ቲሞ ባካዮኮ ወደ ጣልያን በሄደበት ናፖሊ መልካም የሚባል ግዜ እያሳለፈ በመገኘቱ የጣልያኑ ክለብ ተጫዋቹን በቋሚነት የግሉ ለማድረግ ተዘጋጅቷል።(Star)
═════════════════════════
ትላንት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና በስፔን ላሊጋ የተደረጉ ጨዋታዎች
🏴 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
ወልቭስ 1-2 ኤቨርተን
ሼፊልድ 1-0 ኒውካስትል
በርንሌይ 0-1 ማንችስተር ዩናይትድ
🇪🇸 በስፔን ላሊጋ
ግራናዳ 2-0 ኦሳሱና
አትሌቲኮ ማድሪድ 2-0 ሴቪያ
════════════════════════
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
🏴 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
03:00 | ማንችስተር ሲቲ ከ ብራይተን
05:15 | ቶተንሀም ከ ፉልሀም
🇪🇸 በስፔን ሱፐር ካፕ
05:00 | ሪያል ሶሲዳድ ከ ባርሴሎና
🇮🇹 በኮፓ ኢታልያ
11:00 | ፊዮሬንቲና ከ ኢንተር
01:45 | ናፖሊ ከ ኢምፖሊ
04:45 | ዩቬንቱስ ከ ጄኖዋ
════════════════════════
👍) ከተመቻቹህ ላይክ ያድርጉ
✍🏾አሳብ አስተያየት ካላቹህ ኮመንት ላይ ፃፉልን ፣
👌ለሌሎች ጎደኞቻቹህ እዲድርስ ሸር ያድርጉ፣
08/01/2021
አርብ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ!
ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት።
═════════════════════════
አትሌቲኮ ማድሪድ ከሊዮን ፈረንሳያዊውን አጥቂ ሙሳ ዴንቤሌን በውሰት ለመውሰድ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ እንዳልቀረ ተዘግቧል።የክለቡ ባለስልጣናት ሩዲ ጋርሺያ እና ጁኒኒዮ የመልቀቁን ሀሳብ አልተቃረኑትም ሲል L’Equipe ዘግቧል።
═════════════════════════
አዲሱ የፒኤስጂ አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቸቲኖ በቀጣዩ ክረምት ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቀውን አርጀንቲናዊውን አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮን የማስፈረም እቅድ እንዳላቸው ተዘግቧል።(Canal+)
═════════════════════════
ኮትዲቫራዊው አጥቂ ሴባስቲያን ሄለር በ €25m ከዌስትሀም በመልቀቅ ወደ ሆላንዱ ክለብ አያክስ ለማድረግ የጤና ምርመራ ማድረጋቸው ተዘግቡዋል።በቀጣዮቹ ሰዓታት ውስጥም ዝውውሩ እንደሚጠናቀቅ ተዘግቡዋለ።(FabrizioRomano)
═════════════════════════
 DEAL DONE:ራቢ ማቶንዶ ከሻልካ እስከ ሲዝኑ መጠናቀቂያ ድረስበውሰት ስቶክ ሲቲን መቀላቀሉ ተረጋግጧል። (stokecity)
═════════════════════════
ዌስትብሮም ስኮትላንዳዊውን አማካይ ሮበርት ስኖድግራስን ከዌስትሃም ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።( Sky Sports)
═════════════════════════
ባየርሙኒክ ለግራ መስመር ተከላካያቸው አልፎንሶ ዴቪስ ባካፕ እንዲሆናቸው በቀጣዩ ክረምት ከሬዲንግ ጋር ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቀውን ኦማር ሪቻርድስን ለማስፈረም ከወዲሁ በጥልቀት እየተወያዩ ይገኛሉ።(David_Ornstein)
═════════════════════════
 DEAL DONE: ማንችስተር ዩናይትድ አይቬሪኮስታዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች አማዶ ዲያሎን በ £37m ከአትላንት ማስፈረማቸውን አረጋግጠዋል ።በኦልትራፎርድም እስከ 2025 የሚያቆየውን የ 4 አመት ኮንትራት ፈርሟል እንደ ብቃቱ እየታየም ዩናይትድ ኮንትራቱን በፈለገ ሰዓት የአንድ አመት ኮንትራት የማስፈረም መብት አላቸው። (ManUtd)
═════════════════════════
በዛሬው ዕለት በአስቶን ቪላ እና በሊቨርፑል መካከል ሊደረግ የነበረው የ FA CUP ጨዋታ ቁጥራቸው ያልተጠቀሰ የ አስቶን ቪላ ተጫዋቾች በ ኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው ጫወታው ተሰርዟል።
═════════════════════════
በተመሳሳይ ነገ ቅዳሜ ቀን ሳውዝሃምፕተን እና ከ ሽዌርስበሪ ጋር የሚያደረገው የ FA Cup 3ተኛ ዙር ጨዋታ እንደተሰረዘ ይፋ ተደርጓል።
═════════════════════════
የባርሴሎናው ተጫዋች ካርልስ አሌና በውሰት ውል ጌታፌን መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል። ተጫዋቹም እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ በጌታፌ ይቆያል ተብሏል።
═════════════════════════
አርሰናል የኸርታ በርሊኑን ወጣት ተከላካይ ኦማር ረቂቅን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።ለአርሰናልምፈ በጥሩ የዝውውር መስኮት የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ነው። ተጫዋቹም በስቲቭ ቦልድ በሚመራው የአርሰናል ከ 23 አመት በታች ቡድንን መቀላቀል ችሏል።
═════════════════════════
እንግሊዛዊው የአስቶንቪላ አማካይ ጃክ ግሪሊሽን ማስፈርም የሚፈልግ ማንኛውም ክለብ £90 ሚሊዮን መክፈል እንደሚኖርበት The Athletic በዘገባው አስፍሯል።
═════════════════════════
እንግሊዛዊው አጥቂ ፍሎሪን ቦሉንጋ በአርሰናል ያለውን ኮንትራት የሚያራዝም ከሆነ የመጫወቻ ሰዓት ሊሰጠው ነገር ግን የማይፈርም ከሆነ በቂ የሆነ የመጫወቻ ግዜ እድል ላይሰጡት እንደሚችል ተዘግቧል።በተለያዩ 15 ክለቦችም ተጫዋቹ ይፈለጋል።(FabrizioRomano)
═════════════════════════
አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ በአመቱ መጨረሻ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ሊለቅ እንደሚችል ፍንጭ ሰቷል።(GOAL)
═════════════════════════
ሊቨርፑል በክረምቱ የዝውውር መስኮት በነፃ ዝውውር የባየርሙኒኩን ኮከብ ዴቪድ አላባን በ £9m አመታዊ ክፍያ በመክፈል ከሬያል ማድሪድ ጋር ተፎካክሮ ለማስፈረም ተፋጠዋል።( Daily Express)
═════════════════════════
ሊቨርፑል በክረምት ከሬያል ማድሪድ ጋር ያለው ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ሰርጂዮ ራሞስን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገልፁዋል።(El Chiringuito)
═════════════════════════
OFFICIAL: ወልቭስ ሜክሲኳዊውን አጥቂ ራውል ሂሚኔዝን በጉዳት ለረጅም ግዜ ማጣቱን ተከትሎ በውሰት ለፊዮረንቲና የሰጡትን ፓትሪክ ኩትሮኔን መጥራታቸውን አረጋግጠዋል።(Wolves)
═════════════════════════
የፌነርባቼው አሰልጣኝ ኤሮል ቡሉት ክለባቸው የአርሰናሉን አማካይ ሚሱት ኦዚልን ዝውውር ዙሪያ በቀጣዮቹ ቀናት ነገሮች ግልፅ እንደሚሆን ተናግሯል። (Mirror)
═════════════════════════
ማንችስተር ሲቲ ትንሹ ሜሲ እየተባለ ያለውን የ 17 አመቱን አርጀንቲናዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዳሪዮ ሳርሚኒቶን ከአርጀንቲናው ክለብ ስቱዴንቴ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።(Talksport)
═════════════════════════
ኒውካስል ዩናይትድ የሞናኮውን ፈረንሳያዊ የመስመር ተከላካይ ጂብሪል ሲዲቤን ለማስፈረም ግንኙነት መፍጠራቸው ተዘግቧል።(Foot Mercato - in French)
═════════════════════════
የበርንሌው አሰልጣኝ ሺያን ዳች ለተጫዋቾች ለኮሮና ቫይረስ ተብሎ የተዘጋጀው መድሀኒት በቶሎ ቢሰጣቸው ሲል ተናግሯል እንደምክንያት ደግሞ የገለፁት ለኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ተብሎ የሚወጣው ገንዘብ ለማዳን ሲሉ ገልፀዋል። (Guardian)
═════════════════════════
አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ሰርጂዮ ሮሜሮ ከዩናይትድ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ኦልትራፎርድ ተመልሷል ስለወደፊት ቆይታው ለመወያየት።(Sky Sports)
═════════════════════════
የዋትፎርዱ አዲሱ አሰልጣኝ ዤስኮ ሞኖዝ ቅዳሜ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በ FA CUP በሚያደርጉት ጫወታ እንደ እንስሳ ነው የሚፋለሙት ሲል ተናግሯል።(Evening Standard)
═════════════════════════
ጀርገን ክሎፕ በዋይናልደም ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ነገሮችን መናገር እደማይፈልግ አሳወቀ
የሊቨርፑል አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ ስለ ሁኔታው ብዙም የሚናገሩት ነገር እንደሌለ አሳውቀዋል የዋይናልደም የኮንትራት ድርድር ወደ መቋጫ መድረሱን በስፍት እየተዘገበ ነው፡፡
ክሎፕ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት እንዲህ ብሏል “በእውነቱ ምንም ማለት አይቻልም እኔ ተጫዋቹን ምን ያህል እንደሚያስፈልገኝ ሁሉንም ነገር የተናገርኩ ይመስለኛል።ይህ ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ዜና እደሚሆን አላቅም፡፡”
═════════════════════════
የባርሴሎናው እጩ ፐሬዝዳንት ኦግስቲ ቤኔዲቶ ሊዮናል ሜሲ ኮንትራቱ በሰኔ 2021 ሲጠናቀቅ በካምፕኑ ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ይፈርማል ብለው እንደማይጠብቁ ተናግሯል። (Goal)
═════════════════════════
፡
👍) ከተመቻቹህ ላይክ ያድርጉ
✍🏾አሳብ አስተያየት ካላቹህ ኮመንት ላይ ፃፉልን ፣
👌ለሌሎች ጎደኞቻቹህ እዲድርስ ሸር ያድርጉ፣
20/10/2020
.
♦ የአውሮፓ ቻምፕዮን ስሊግ እና የኢሮፓ ሊግ ከዛሬ እስከ ሀሙስ ድረስ ይካሄዳል እነዚህንም መረሃግብሮች ለናንተ በሚመች መልኩ አቅርበናል ስለዚህም ገፃችን ላይክ እና ሼር እንድታደርጉ እንጠይቃችዋለን ሁሌም አዳዲስ መረጃ እንዲደርሳችሁ ከፈለጋችሁ።
═════════════════════════
ማክሰኞ| ዜኒት 1 : 55 ክለብ ብሩጅ
ማክሰኞ| ዳይናሞ ኬቭ 1:55 ዩቬንቱስ
ማክሰኞ| ቸልሲ 4:00 ሴቪያ
ማክሰኞ| ሬንስ 4:00 ክራስኖዳር
ማክሰኞ| ላዚዮ 4:00 ቦርሲያዶርትመንድ
ማክሰኞ| ባርሴሎና 4:00 ፌርኒካቫሮስ
ማክሰኞ| ፒኤስጂ 4:00 ማንችስተር ዩናይትድ
ማክሰኞ| አርቢላይፕዚክ 4:00 ኢስታንቡ ባሳክሼር
ረቡዕ| ሳልዝበርግ 1:55 ሎኮሞቲቭ ሞስኮ
ረቡዕ| ሬያል ማድሪድ 1:55 ሻካታር ዶኔስኪ
ረቡዕ| ባየርሙኒክ 4:00 አትሌቲኮ ማድሪድ
ረቡዕ| ኢንተር ሚላን 4:00 ቦርሲያሞንቸግላድባክ
ረቡዕ| ማንችስተር ሲቲ 4:00 ፖርቶ
ረቡዕ| ኦሎምፒያኮስ 4:00 ማርሴ
ረቡዕ| አያክስ 4:00 ሊቨርፑል
ረቡዕ| ሚትላንድ 4:00 አትላንታ
═════════════════════════
ኢሮፓ ሊግ
ሀሙስ| ያንግ ቦይስ 1:55 ሮማ
ሀሙስ| ሴስኬ ሶፊያ 1:55 ክለብ ክሉጅ
ሀሙስ| ዱንላክ 1:55 ሞልደ
ሀሙስ| ራፒድ ቬና 1:55 አርሰናል
ሀሙስ| ባየርሊቨርኩሰን 1:55 ኒስ
ሀሙስ| ሀፖል ቤርሼባ 1:55 ስላቪያ ፕራ
ሀሙስ| ስታንዳርድ ሌዥ 1:55 ሬንጀርስ
ሀሙስ| ሊቼ ፖዘን 1:55 ቤኔፊካ
ሀሙስ| ፒኤስቪ 1:55 ግራናዳ
ሀሙስ| ፓኦኬ 1:55 ኦሞኒያ ኒኮሲያ
ሀሙስ| ናፖሊ 1:55 አዜድ አልካማር
ሀሙስ| ሬጂካ 1:55 ሬያል ሶሲዳድ
ሀሙስ| ስፖርቲንግ ብራግ 4:00 ኤኬ አቴንስ
ሀሙስ| ሌስተር ሲቲ 4:00 ዞርያ ሉዋንስክ
ሀሙስ| ስፓርታ ፕራህ 4:00 ሊል
ሀሙስ| ሴልቲክ 4:00 ኤስሚላን
ሀሙስ| ማካቢብ ቴላቪቭ 4:00 ቃራባግ
ሀሙስ| ቪያርያል 4:00 ሲቫስፖር
ሀሙስ| ቶተንሀም ሆስፐር 4:00 ላስክ
ሀሙስ| ሉዶጎሬት 4:00 አንቲዊርፕ
ሀሙስ| ዳይናሞ ዛግሬብ 4:00 ፌኖርድ
ሀሙስ| ወልፍስርግ AC 4:00 ሲኤስኬ
ሀሙስ| ሆፈንሄም 4:00 ክሬቬ ዝቬዝድያ
ሀሙስ| ስሎቫን ሌቤርካ 4:00 ጄንት
═════════════════════════
የአውሮፓ ቻምፕዮን ሊግ ምድብ ድልድል
ምድብ A
✅ ባየር ሙኒክ
✅ አትሌቲኮ ማድሪድ
✅ ሳልስፐርግ
✅ ሎኮሞቲቭ ሞስኮ
ምድብ B
✅ ሪያል ማድሪድ
✅ ሻካታር ዶኔስክ
✅ ኢንተር ሚላን
✅ ሞንቼግላድባህ
ምድብ C
✅ ፖርቶ
✅ ማንችስተር ሲቲ
✅ ኦሎምፒያኮስ
✅ ኦሎምፒክ ማርሴ
ምድብ D
✅ ሊቨርፑል
✅ አያክስ
✅ አታላንታ
✅ ሚጂትላንድ
ምድብ E
✅ ሲቪያ
✅ ቼልሲ
✅ ክራስኖዳር
✅ ሬንስ
ምድብ F
✅ ዜኒት ፒተርስፐርግ
✅ ቦርሲያ ዶርትሞንድ
✅ ላዚዮ
✅ ክለብ ብሩጅ
ምድብ G
✅ ጁቬንቱስ
✅ ባርሴሎና
✅ ዳይናሞ ኬቭ
✅ ፍራስቬቫኖስ
ምድብ H
✅ ፓሪሰን ዠርመን
✅ ማንችስተር ዩናይትድ
✅ አርቢ ሌፕዚንግ
✅ ኢስታንቡል ባሳክሺር
═════════════════════════
👍ከተመቻቹህ ላይክ ያድርጉ
✍🏾አሳብ አስተያየት ካላቹህ ኮመንት ላይ ፃፉልን ፣
👌ለሌሎች ጎደኞቻቹህ እዲድርስ ሸር ያድርጉ፣
14/10/2020
✔ አምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር።
═══════════════════════════
👍 ከተመቻችሁ ላይክ እድርጉት!
🔄 ጓደኞችዎ እንዲያነቡት ሼር ማድረጋችሁንም አትርሱ!
📆 ሃሳብ አስተያየታችሁንም አካፍሉን።
09/10/2020
=================================
🔵የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ መስከረም ምርጥ ተጫዋቾች እና አሰልጣኝ ከሰዓታት በፊት ይፋ ሆኗል ።
🔴በውድድር አመቱ በፕሪምየር ሊጉ ኤቨርተንን ይዘው ድንቅ ጅማሮ አድርገው ያደረጓቸውን ሁሉንም የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ድል ያደረጉት ጣልያናዊው ታክቲሽያን ካርሎ አንቼሎቲ የወሩ ምርጥ መባል ችለዋል።
🔵በኤቨርተን ድንቅ ጅማሮ በግብ ማግባቱ ትልቁን ሚና ሲወጣ የነበረው ጨራሽ አጥቂያቸው ዶሚኒክ ካልሸርት ሌዊን ባደረጋቸው 4 ጨዋታዎች 6 ግብ ከመረብ ማሳረፍ መቻሉ የወሩ ምርጥ አስብሎታል።
🔵የሌስተር ሲቲው ኮከብ ጀምስ ማዲሰን ማንችስተር ሲቲ ላይ ያስቆጠረው ጎል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመስከረም ወር ምርጥ ጎል ተብሎ ተመርጧል ።
📍ካርሎ አንቼሎቲ - የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ
📍ካልቨርት ሌዊን - የወሩ ምርጥ ተጫዋች
📍ጀምስ ማዲሰን - የወሩ ምርጥ ጎል አሸናፊ
02/10/2020
♦ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡