02/09/2026
!!⚽⚽⚽
👉በዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ክላስተር ወጣቶችና ስፖርት ዩኒት አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ2018 ዓ/ም የክረምት የውስጥ ለውስጥ የእግርኳስ ውድድር።
👉 የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተደርገው ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ አራት ክለቦች ታውቀዋል።
👉የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች።
#ከነዓን #ኢንቬስተር Vs #በይቱልሂክማ
#ኢዛ #ፕሪንቲንግ Vs #ዲኤስቲቪ
👉የሩብ ፍፃሜ ጫወታ ውጤቶች።
👉ቅዳሜ 9:30
5 - 0 #አጋም
👉እሁድ 9:30
3 - 0
👉ማክሰኞ 9:30
#ሰላም 1 - 1 #በይቱል ሂክማ
በመለያ ምት በይቱል ሂክማ 5-3 ሰላም ሄቦት
👉እሮብ 9:30
1 - 1 #ገቴ
በመለያ ምት ዲኤስቲቪ 4-2 ገቴ በየቡ
!!⚽⚽
በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን
02/09/2026
መልካም ዜና ለዳሎቻ ከተማና ወረዳ ስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ!
በዳሎቻ ከተማና ወረዳ በጋራ በመሆን አዲስ የፉትሳል እግር ኳስ ውድድር ልንጀምር ስለሆነ መሳተፍ የምትፈልጉ ስፖርተኞች ምዝገባ መጀመሩን እንገልጻለን።
የምዝገባ መስፈርቶችና መረጃዎች፡
* የቡድን አባላት ብዛት፡ አንድ ቡድን 10 ስፖርተኞችን ብቻ ያቀፈ የስም ዝርዝር ማቅረብ ይኖርበታል።
* የምዝገባ ቦታ፡ [ቡራቅ ፎቶ
በይቱል ሂክማ መጻፍ ቤት ]
የምዝገባ ጊዜ፡ [ከ 1-13-2018 እስከ 5-13-2018
* የመመዝገቢያ ክፍያ (1500
ለተጨማሪ መረጃ
* 📞 0982100100
* 📞 0954201324 ማረላ ሲርበላ
0928760116 አ/ሰላም መሐሙድ
+251934699069 ዘሃብ ኦርመንጎ
ማሳሰቢያ፡
* የምዝገባ ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ቀድመው በመመዝገብ ቦታዎን ያረጋግጡ
02/09/2026
የ2018 የሁልባራግ ወረዳ የሴክተሮች ጤና ካፕ የውስጥ ለውስጥ ውድድር ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ ቀጥሏል
እንሁ የፊታችን ኡሁድ ለዋንጫ እና ለደረጃ የሚደረጉ ተጠባቂዉ እና አጓጊዉ ጫወታዎች
በእለተ ኡሁድ በቀን ጳግሜ 1/2018
የደረጃ ጫወታ 🥈🥈🥈🥈
ከጥዋት 4:00⏰
ፖሊስ Vs ጤና ለሁሉም
የዋንጫ ጫወታ 🏆🏆🏆
በእለተ ኡሁድ በቀን ጳግሜ 1/2018
ከሳአት 8:00⏰
ፋይናንስ Vs ማዘጋጃ
30/08/2026
የራጋ ካፕ ውድድር በአዲሱ ስታዲየም መጀመሩ የተለየ ምዕራፍ ነው፦ አቶ ኡስማን ተሰማ
==============================
ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም (የማ/ል/ወ/መ/ኮ)፦ ቆሼ
የማረቆ ልዩ ወረዳ 4ኛው ዙር የራጋ ካፕ ውድድር በቆሼ ከተማ በሚገኘው አዲሱ ሁለገብ ስታዲየም በይፋ ተጀምሯል።
የማረቆ ልዩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ተሰማ በመክፈቻው ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ውድድሩ በአዲሱ ስታዲየም መጀመሩ ለማረቆ ልዩ ወረዳ የስፖርት እንቅስቃሴ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን ያመላክታል ብለዋል።
አቶ ኡስማን፣ ቀደም ሲል የነበሩ የስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች በመቀነሳቸው ስፖርተኞች በተሻለ ሁኔታ ለውድድር እንዲዘጋጁና ችሎታቸውን እንዲያሳዩ የተሻለ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው፣ አዲሱ ስታዲየም ለስፖርተኞች ብቻ ሳይሆን ለወጣቶችና ለማህበረሰቡ የስፖርት ተሳትፎን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የስፖርት ቦታዎች መሻሻላቸው ወጣቶች በተሰጥኦአቸው ላይ እንዲሰሩና ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድጉ የሚያበረታታ መሆኑንም አመልክተዋል።
አቶ ኡስማን፣ የራጋ ካፕ ውድድር ዋና ዓላማው ዋንጫ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ወጣቶችን በስፖርት ማሳተፍ፣ ተሰጥኦአቸውን ማውጣትና በመካከላቸው የሚፈጠረውን ማህበራዊ ትስስር ማጠናከር መሆኑን ጠቁመዋል።
ስፖርት ወጣቶችን በጋራ በማሰባሰብ ሰላምንና አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንዳለው ያመለከቱት አቶ ኡስማን፣ በውድድሩ የሚሳተፉ ቡድኖችና ደጋፊዎች ለስፖርታዊ ሥነ-ምግባር ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰይፈ አለሙ፣ የራጋ ካፕ ውድድር ወጣቶች ተሰጥኦአቸውን የሚያሳዩበትና ወደ ተሻለ የስፖርት ደረጃ የሚሸጋገሩበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
በስፖርት ዘርፍ የሚደረግ የመሠረተ ልማት ልማት ስራ የስፖርተኞችን ተሳትፎና ውጤት ለማሻሻል ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ሰይፈ አዲሱ ስታዲየምም የስፖርት እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ጠቃሚ መሠረተ ልማት መሆኑን አመልክተዋል።
የማረቆ ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤትኃላፊ አቶ ከድር መሐመድ በበኩላቸው፣ የራጋ ካፕ ውድድር ስፖርትን ከባህል ስፖርትና ፌስቲቫል ጋር በማቀናጀት የአካባቢውን ባህልና እሴት ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ልዩ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
ኃላፊው በ4ኛው የራጋ ካፕ ውድድር በዲቪዚዮን አንድ 23 ቡድኖች እና በዲቪዚዮን ሁለት 18 ቡድኖች በድምሩ 41 ቡድኖች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።
በመክፈቻው ዕለት ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ያሜ ቤቶ ከአዲስ አዳጊው ዲዳ ሀሊቦ ጋር ባደረገው የመክፈቻ ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ ውድድሩን በድል ጀምሯል።
በመክፈቻ ስነስርዓቱ የልዩ ወረዳው ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ሻምበል ደበሮ፣ የልዩ ወረዳው ብልጽግና ጽህፈት ቤት የፖለቲካ አቅምና ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደርጉ ቡሉቆን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልልና የልዩ ወረዳው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአቢ ለምቢኮ
30/08/2026
🔴 LIVE | በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!
የኢትዮ ሰመር ስልጤ ዞን ጦራ ካፕ — ተጠባቂው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ!
የስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደርን እያደመቀ የሚገኘው የኢትዮ ሰመር ጦራ ካፕ አሁን ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ዛሬ እሁድ (ነሐሴ 24) የብዙዎችን ቀልብ የሳበው ታላቅ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በታላቅ ግርማ ይካሄዳል!
🔥 የዕለቱ ተጠባቂ ግጥሚያ:
ጨዋታ: ፋያ Gold 🆚 አልከሶ
ቀን: እሁድ (ነሐሴ 24)
ሰዓት: ከቀኑ 9:00 ጀምሮ
ቦታ: ጦራ ከተማ አስተዳደር
ማን አሸንፎ የፋይናል ትኬቱን ይቆርጣል? ማንስ በግማሽ ፍፃሜው ጉዞው ይገታል?
ይህንን አስደሳችና ውጥረት የሞላበት ጨዋታ ከእነ ተንታኞቻችን ትንታኔ ጋር በቀጥታ ስርጭት (Livestream) በገጻችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን! እንዳያመልጥዎ!
30/08/2026
በወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የክረምት ወራት የበጎ የጤና የእግርኳስ ዉድድር በሀይር አንዚ ሜዳ እንደቀጠለ ነው ።
ወራቤ ሆስፒታል ከ BDS የሚያደርጉት ጫወታ የመሀል ዳኛው ባሰማው ፊሽካ ጫወታው ጀምሯል ።
30/08/2026
ሸይቴ እንግዳ ማረፊያ — ጦራ ከተማ
በጦራ ከተማ ለሥራ፣ ለእረፍት ወይም ለንግድ ጉዳይ መጥተው የሚያርፉበት ምቹና ንጹሕ ቦታ ይፈልጋሉ?
ሸይቴ እንግዳ ማረፊያ ሞቅ ባለ እንግዳ ተቀባይነት ይጠብቅዎታል!
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
👉ንጹሕና ዘመናዊ መኝታዎች: ለጽዳት ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው ምቹ ክፍሎች
👉ሙሉ እረፍት የሚያገኙበት ጸጥተኛና አስተማማኝ ጥበቃ ያለው
👉በፍቅርና በትህትና የሚቀበልዎት ፈጣን አስተናጋጅ
አድራሻ: ጦራ ከተማ
ለበለጠ መረጃና ቦታ ለመያዝ: 0950444634
ምቾትዎ እና እረፍትዎ የኛ መለያ ነው!
29/08/2026
🥊 በወራቤ ከተማ ሊካሄድ የታቀደው ታሪካዊው "Werabe Fight Night" የቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ!
በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በቅርቡ ለሚከናወነው "Werabe Fight Night" አጓጊ የቦክስ፣ የሚክሲድ ማርሻል አርት ስፖርት ውድድር አዘጋጆች እና ባለድርሻ አካላት በሲሃም ሞል በመገኘት የቅድመ ዝግጅት ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ የዝግጅቱን ሂደትና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ አስመልክቶ ሰፊ ምክክር የተደረገ ሲሆን፤ ከውድድሩ ጋር የተያያዙ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማድረስ በቅርቡ የመጀመሪያ ዙር ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ መሆኑን በቦታው የነበረው ጡርቤ ስፖርት ሚዲያ ዘግቧል።
👉 ለስፖርቱ አፍቃሪዎች የሚሰጡ ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎችን እና ዝርዝሮችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ይቆዩ!
#ጡርቤስፖርት