ስለ እግር ኳስ

ስለ እግር ኳስ

Share

አጫጭር እና ወቅታዊ እግር ኳስን የተመለከቱ መረጃዎችን ያገኙ

04/10/2025

በለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ዌስትሀም ዩናይትድ
************

አርሰናል በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ከዌስትሀም ዩናይትድ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

11 ሰዓት ላይ በኢምሬትስ በሚደረገው ጨዋታ መድፈኞቹ ሊቨርፑል እስኪጫዎት ድረስ ሊጉን ለመምራት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ከዌስትሀም በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፈው አርሰናል ሦስት ነጥብ ለማግኝት ወደ ሜዳ በሚገባበት ጨዋታ ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

ከግርሀም ፖተር ስንብት በኋላ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶን አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ዌስትሀም ዩናይትድ በአራት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ቶተንሀም ሆትስፐር ከሜዳው ውጭ ከሊድስ ዩናይትድ ይጫወታል፡፡

04/10/2025

ቦርንማውዝ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠበትን ውጤት አስመዘገበ
*************

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ7ኛ ሳምንት ጨዋታ ቦርንማውዝ ፉልሀምን 3 ለ 1 አሸንፏል።

በቪታሊቲ ስቴዲየም በየደረገው ጨዋታ ፉልሃም ሪያን ሴሲኞ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ ቢሆንም ለመሸነፍ ተገዷል።

አንቶኒ ሴሜኒዮ የቦርንማውዝን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጀስቲን ክላይቨርት አንድ ግብ አስቆጥሯል።

በውድድር ዓመቱ 4ኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦርንማውዝ በ14 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

29/09/2025

ዌስትሃም በዚህ አመት በፕርሚየር ሊጉ ከ5ጨዋታ በአራቱ ተሸንፎ 1ብቻ አሸንፏል እሱም ኖቲንግሃምን ሲሆን በወቅቱ የጫካዎቹ አሰልጣኝ የነበረውን ኑኖ ኤስፔሬቶን ደሞ ቅዳሜ ዋና አሰልጣኝ አድርገው ሾመዋል

29/09/2025

ጆዜ ሞሪኒዮ ሰለ ትላንቱ የማድሪድ ሽንፈት

"የትናንቱ የሪያል ማድሪድ ጨዋታ ውጤት ምንም አልገረመኝም! በደረትህ ላይ ያለው አርማ ምን እንደሆነ ገና ካልገባህ እና እንደፈሪዎች ስትጫወት ይህ እንደሚሆን ግልጽ ነው!"

"በትላንትናው እለት ከሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች መካከል አንዳቸውም የሪያልነት ስሜት አልነበራቸውም ፣ ሱፐርስታርስ የሚባሉ ተጫዋቾች ያለ ምንም ከፍ ያለ ስሜት በሜዳው ላይ ለጤና የሚጫወቱ ነበር የሚመስለው። እኔ ራሴ አትሌቲኮ ከአምስት በላይ ያስቆጥራል ብዬ አስቤ ነበር ፤ ትላንት በይፋ ለሪያል ማድሪድ የክህደት ቀን ነበር።"

"ሪያል ማድሪድ ለዚህ አርማ ህይወቱን የሚሰጥ ሰው ይፈልጋል"

23/09/2025

ለ8 ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

23/09/2025

የላሚን ያማልን ባሌንዶር ተስፋ ውሃ የቸለሰበት ተጨዋች።

23/09/2025

🚨የደምበሌ ለቅሶ ምክንያቱ ምን ነበር?

ኦስማን ዴምቤሌ ስሜታዊ ንግግሩን ሲያደርግ ሲያለቅስ የነበረው ሰው ሙስጠፋ ዲያታ ይባላል።

ሁለቱ ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚተዋወቁ ሲሆን በወጣት ቡድኖች ውስጥ የቡድን አጋሮች ነበሩ። ኦስማን ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆነ። ሙስጠፋ ግን ህልሙን ሳያሳካ በጉዳት ምክንያት ከእግርኳስ ተገለለ።

🇫🇷 ኦስማን ደምበሌ🎙" ይህ ለአንተም ነው ምርጥ ጓደኛዬ። እኔ እና ሙስጠፋ ዲያታ የልጅነት ጓደኛሞች ነን። በሚገርም ሁኔታ ሙስጠፋ ከአራት አመት ጀምሮ የማውቀው ጓደኛዬ ነው። አንድ ጊዜ ሙስጠፋ አንድ ነገር ነገረኝ። አንድ ቀን በዓለም ላይ ምርጥ ተጫዋች ትሆናለህ። ሁሉንም ነገር አንድ ላይ አድርገናል። ቡዙ ነገር አጋጥሞናል። እሱ ሁልጊዜ ይደግፈኛል። እናም እስከ መጨረሻው ድረስ እሱ እና እኔ አብረን እንሆናለን።"

ሙስጠፋ እና ኡስማን የባሎንዶርን አሸናፊ መሆኑን ካወቁ በኋላ አብረው ማልቀስ ጀመሩ! 🥹

22/09/2025

የዓመቱ ምርጥ ክለብ፡-ፒኤስጂ
**************
የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፒኤስጂ የዓመቱ ምርጥ ክለብ ሆኖ ተመርጧል፡፡

ለባሎንዶር በርካታ ዕጩዎችን ያስመረጠው ክለቡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ያሳካውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ ጨምሮ አምስት ክብሮችን አሸንፏል፡፡

የክለቡ ፕሬዝደንት ናስር አልከሊፋ ሽልማቱን ተረክበዋል፡፡

22/09/2025

የ2025 ባሌንዶር አሸናፊ ኦስማን ደንቤሌ።

እንኳን ደስ አለህ!

22/09/2025

ሚኬል አርቴታ እና ፔፕ ጋርዲዮላ በአርሰናል እና በማንቸስተር ሲቲ መካከል አሰልቺ ጨዋታዎችን ለመፍጠር አዳዲስ መንገዶችን እንዴት እንደሚያገኙ ስናይ መደነቅ አለብን።

በችሎታ የታጨቁ ተጨዋቾች አሏቸው - ይልቁንስ በኤምሬትስ 1-1 መለያየታቸው ሌላ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ጉዳይ ነበር።

እነዚህ አስልጣኞች መከላከያቸውን ሲያጠናክሩ…መከላከላቸውን በማጠናከር ምላሽ ሲሰጡ ተስተውለዋል።

የዚህ ውድድር እውነተኛ አሸናፊዎች ፍጹም ተቃራኒ አቀራረብ ያላቸው ሊቨርፑሎች ነበሩ።

Photos from ስለ እግር ኳስ's post 22/09/2025

“አትሌቲክሳችን በባል ተሰልጥኖ አሁንም ውጤት አይመጣም” አትሌት ፋንቱ መጌሶ

መስከረም 12 ፣ 2018 ዓ.ም ሀገሬ ቴቪ :- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤት ማጣት ዋናው ምክንያት በባል እና በወንድም መሰልጠኑ ነው፤በእኛ ግዜ አርንጓዴ ጎርፍ ስያሜ እንዳልተሰጠው አሁን ላይ ለተሳትፎ መሄዳችን እጅግ ያሳዝናል ስትል የቀድሞ የ800 ሜትር ሯጭ አትሌት ፋንቱ መጌሶ ለሀገሬ ስፖርት ተናግራለች፡፡

ትናንት በተጠናቀቀው የቶኪዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የሩጫ ውድድር ርቀቶች ሁሉ ያልተሳካ ውጤት አስመዝግባ በዚህም በአራት ሜዳሊያ ወርቅ ሳታገኝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳቧን የሰጠችው የቀድሞ የ800 ሜትር ሩጫ ተወዳዳሪ፤በርቀቱ በሴቶች ፈር ቀዳጅ እና ኢትዮጵያን በአለም አደባባይ ማስጠራት የቻለችው አትሌት ፋንቱመጌሶ ከሀገሬ ስፖርት ጋር በነበራት ቆይታ “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በባል እና በወንድም እየተመራ የትም አይደርስም ስትል ተናግራለች፡፡

ፋንቱ እንደምትለው ለአትሌቲክሳችን መበላሸት ዋናው ምክንያት አብዛኛው አትሌት በባል እንዲሁም በወንድም እና በእህት መሰልጠን ነው፤እንዴት ውጤት ለማምጣት እንጠብቃለን፤ይሄ በጣም የሚያሳፍር ነው ብላለች፡፡

አሁን ላይ የፋን ኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መስራች እና ዋና አዘጋጅ የሆነችው አትሌት ፋንቱ እንደምትለው “በቀጣይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደ ተቋም እራሱን ገምግሞ ካልሰራ አሰቸጋሪ ነው የሚሆነው፤አትሌቲክስ አይናችን ነው ስትል ሀሳቧን ገልጻለች፡፡

ፋንቱ እንደምትለው በእኛ ግዜ አርንጓዴ ጎርፍ ስያሜ እንዳልተሰጠው አሁን ላይ ለተሳትፎ መሄዳችን እጅግ ያሳዝናል፤ፋን ኢትዮጵያም በሩጫው መስክ ታዳጊዎችን ለማፍራት የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ለሀገሬ ስፖርት ጨምራ ተናግራለች፡፡

በማሕበራዊ መገናኛዎቻችን መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ

21/09/2025

ሜሲ ቦአቲንግን ዘርሮ ስላስቆጠረው ግብ ማኑኤል ኑዌር ሲናገር .....

"ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም በመልበሻ ክፍል ውስጥ ቦአቴንግ በድንጋጤ ተውጦ ነበር።

ፔፕ ጋርዲዮላም ወደ ክፍሉ ገብቶ እሱን ሲመለከተው በጣም ተጨንቆ ስለነበር እንዲህ አለው "ጀሮም ትሰማኛለህ ምንም የጥፋተኝነት ስሜት እንዳይሰማህ ፤ይህ ሜሲ በሁሉም ሰው ላይ የሚያደርገው ነገር ነው።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa
1000