Abyssinia sport/ አቢሲኒያ ስፖርት

Abyssinia sport/ አቢሲኒያ ስፖርት ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

ብዙ ኮሚኒቲ ሺልድ ማን አሸነፈ ? አንጋፋው የእንግሊዝ ኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ጨዋታ ወደኋላ 117 አመታትን ያስቆጠረ ታሪክ አለው። 1898 ኮሚኒቲ ሺልድ በሚል ስያሜ የጀመረው ውድድሩ 1908 ...
16/08/2026

ብዙ ኮሚኒቲ ሺልድ ማን አሸነፈ ?

አንጋፋው የእንግሊዝ ኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ጨዋታ ወደኋላ 117 አመታትን ያስቆጠረ ታሪክ አለው።

1898 ኮሚኒቲ ሺልድ በሚል ስያሜ የጀመረው ውድድሩ 1908 ቻሪቲ ሺልድ የሚል መጠሪያ አግኝቷል።

የመጀመሪያው የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ በማንችስተር ዩናይትድ እና ኪውፒአር መካከል ነበር የተካሄደው።

ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታውን በማሸነፍ በዋንጫው ላይ ስሙን ያፃፈ የመጀመሪያው ክለብ ነው።

በውድድሩ ታሪክ ማንችስተር ዩናይትድ 2️⃣1️⃣ ጊዜ ዋንጫውን በማሸነፍ ቀዳሚው ክለብ ሆኗል።

አርሰናል 1️⃣7️⃣ እንዲሁም ሊቨርፑል 1️⃣6️⃣ ዋንጫዎችን በማሸነፍ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

ቀያዮቹ ሰይጣኖች ለመጨረሻ ጊዜ ውድድሩን ያሸነፉት ከአስር አመታት በፊት 2016 ነበር።

ኢንተር ሚያሚ ከናሽቪል ጋር ባደረጉት ጨዋታ የናሽቪል ደጋፊዎች በጨዋታው ወቅት ይህንን ባነር አሳይተዋል።
16/08/2026

ኢንተር ሚያሚ ከናሽቪል ጋር ባደረጉት ጨዋታ የናሽቪል ደጋፊዎች በጨዋታው ወቅት ይህንን ባነር አሳይተዋል።

25/05/2026

🔴 "ሻምፒየንስ ሊጉን እናሸንፋለን!" — ሚኬል አርቴታ

​የፕሪሚየር ሊጉ አዲስ አሸናፊ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ቀጣዩ ትልቅ ዓላማቸው ክለቡን የአውሮፓ ሻምፒዮን ማድረግ እንደሆነ በይፋ ገልጸዋል።

​አርቴታ ለታሪካዊው የፍፃሜ ጨዋታ ያላቸውን እምነት ሲናገሩ፦

​💬 "አሁን ቀጣዩን አንድ ጨዋታ ካሸነፍን የአውሮፓ ሻምፒዮን መሆን እንችላለን። ለፍፃሜው ጨዋታ ከነገ ጀምሮ ሙሉ ዝግጅታችንን እንጀምራለን፤ ሻምፒየንስ ሊጉን አሸንፈን በዚህ ታላቅ ክለብ ውስጥ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ለመክፈት እጅግ ጓጉተናል።"

​አሰልጣኙ ከሊጉ ዋንጫ ድል በኋላ በውስጣቸው ስላለው ስሜት ሲገልጹ፦

​"በአሁኑ ሰዓት የሚሰማኝን ጥልቅ ስሜት በቃላት ለመግለጽ እቸገራለሁ። እጅግ ከፍተኛ ደስታ፣ ስሜታዊነት እና ትልቅ ኩራት በውስጤ ይመላለሳል..."

​በመጨረሻም ለአውሮፓው ክብር ስላላቸው ፍጹም እምነት ሲናገሩ፦

​"የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን እናሳካዋለን፤ እንደምናደርገውም ሙሉ በሙሉ አምናለሁ!"

24/05/2026

🔴 "አንዱ ኢላማችን ገና ይቀራል!" — ስታን ክሮንኬ

​የአርሰናል ባለቤት ስታን ክሮንኬ፣ ክለቡ ለእነሱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው በመግለጽ ከታሪካዊው የፕሪሚየር ሊግ ድል በኋላ ለስካይ ስፖርት (Sky Sports) አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

​ክሮንኬ በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው የሚከተለውን ተናግረዋል፦

​💬 "ከዓላማዎቻችን መካከል አንዱን (የሊጉን ዋንጫ) አሳክተናል። ነገር ግን አሁንም ገና ሌላኛው ትልቅ ዓላማችን ይቀራል!"

​አክለውም ቡድኑ ወደ ቀጣዩ ታሪካዊ ምዕራፍ ስላለው ዝግጅት ሲገልጹ፦

​"ከነገ ጀምሮ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጠንካራ ስራችንን እንጀምራለን።"

​ባለቤቱ ለክለቡ ስላላቸው ቁርጠኝነት እና ቀጣይ ኢንቨስትመንት ሲናገሩ፦

​"በሁሉም በኩል ኢንቨስት አድርገናል። ይህንን ክለብ ከልባችን እንወደዋለን፤ አሁንም ድጋፋችን ይቀጥላል፣ ስራችንም ነገ ይቀጥላል!"

24/05/2026
23/05/2026

🔴 "ወደ አርሰናል መምጣቴ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር" — ዴክላን ራይስ

​የአርሰናሉ አማካይ ዴክላን ራይስ ወደ ኤምሬትስ ለመዘዋወር የወሰነው ውሳኔ ፍጹም ትክክለኛ እንደነበር ገለጸ። ከዝውውሩ በፊት ከአሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ጋር ስለነበረው ንግግር ሲናገር፦

​"አርቴታ እቅዱን የሚገልፅበት መንገድ የተለየ ነው። ከመጣሁ በኋላ ደግሞ የተናገራቸው ነገሮች በሙሉ ወደ ተግባር ተቀይረው እውነት ሆነዋል፤ ይህ በጣም ያስደንቃል።"

​ራይስ አክሎም በወቅቱ ሌሎች አማራጮች እንደነበሩት አስታውሶ፣ ከአርቴታ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ግን ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ መለወጡን እንዲህ ሲል ገልጿል፦

​"ሌሎች አማራጮች ነበሩ፤ ነገር ግን ከአርቴታ ጋር ካወራን በኋላ ጠፉ። በጨዋታ እና በአሰልጣኝ ላይ እንደዚህ አይነት እምነት ኖሮኝ አያውቅም፤ ወደ አርሰናል መዘዋወሬ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር።

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abyssinia sport/ አቢሲኒያ ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abyssinia sport/ አቢሲኒያ ስፖርት:

Shortcuts

Share

Category