31/05/2026
ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በውጤት የደመቁበት የ2026 የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።
ካሳለፍነው አርብ ጀምሮ በኬኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የካራቴ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ በውድድሩ ኢትዮጵያውያ ስፖርተኞች አኩሪ ድል አስመዝግበዋል።
በዚህም መሰረት በሻምፒዮናው በሴቶች ኢትዮጵያን በብቸኝነት የወከለችው እፁብ ድንቅ በላይ በነጠላ ካታ የወርቅ እና በነጠላ ፋይት የነሃስ ሜዳሊያ በማስመዝገብ ደማቅ ታሪክን ፅፋለች።
በወንዶች የነጠላ ፋይት ምርጥ ብቃቱን ያሳያው ፀጋዘአብ ጎሳ የወርቅ ሜዳሊያን ሲያሰገኝ, በሲኒየር የነጠላ ካታ እዮብ አለሙ የነሀስ ሜዳሊያን አስመዝግቧል።
የወርቅ ሜዳሊያ እና ዋንጫ ከተገኘበት የወጢቶች የቡድን ፋይት በተጨማሪ
ያብስራ አሰፋ, እዮብ አለሙ እና አህመድ ጡሃ በቡድን የሲኒየር ካታ ብርቱ ፉክክር አድርገው 2ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።
ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በቡድን ካስመዘገቡት ግሩም ውጤት በተጨማሪ በግል ፋይት ለሚ ሎሊ የወርቅ, ናትናኤል ሀብታሙ የብር እና ኑር ሙሀመድ የነሀስ ሜዳሊያ ለአገራቸው ኢትዮጵያ አስገኝተዋል።
በግል የወንዶች ሲኒየር ፋይት እልህ አስጨራሽ ፉክክር ያደረገው አህመድ ጡሃ የነሃስ ሜዳሊያን አስመዝግቦ አጠናቋል::
በሻምፒዮናው የተሳተፈው የኢትዮጵያ ካራቴ ልዑክ ቡድን ነገ ወደ አገሩ ይመለሳል::
# # # ማሳሰቢያ:
በምንም መልኩ የምንጽፋቸው ጽሑፎች እና መጣጥፎች እንድሁም ልጥፎች የተለያዩ የራሳቸው ሀሳብ እና ህመም ያለባቸውን ግለሰቦች ለማሳዘን ወይም የግል ጥቅማቸውን ለማሳጣት ሳይሆን፣ የካራቴን ህብረተሰብ ለማነቃቃት እና ባልተለመደ መልኩ ካራቴን ለማስተዋወቅ መሆኑ እንዲታወቅልን ! በአክብሮት እናሳስባለን 🙏
# # # JKS ኢትዮጵያን ይከታተሉ!
የJKS ኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች፣ ዜናዎች፣ የስልጠና መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተዘረዘሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይጎብኙ፦
* ቴሌግራም: [https://t.me/JKSEthiopia](https://t.me/JKSEthiopia)
* ድረ-ገጽ: [https://jkskarateethiopia.com/](https://jkskarateethiopia.com/)
* ዩቲዩብ: [https://www.youtube.com/](https://www.youtube.com/)
* ፌስቡክ: [https://www.facebook.com/JKSEthiopia/](https://www.facebook.com/JKSEthiopia/)
* ቲክቶክ: [https://www.tiktok.com/](https://www.tiktok.com/)
* 𝕏: [https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09](https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09)
30/05/2026
የድል ዜና፡ የኢትዮጵያ ካራቴ ቡድን በኬንያው ውድድር ታላቅ ድል ተቀዳጀ!
የካራቴ ጥበብ እና የኢትዮጵያዊነት ኩራት በኬንያ መድረክ ደመቀ።
የኢትዮጵያ ካራቴ ቡድን በኬንያ ባደረገው አራት ሀገራት የተሳተፉበት የምስራቅ አፍሪካ የውድድር መድረክ አስደናቂ አፈጻጸም በማሳየት ሀገራችንን በክብር አስጠርቷል። ይህ ድል የጀግኖች ስፖርተኞቻችን የጥረት፣ የትዕግስት እና የጽኑ አገር ፍቅር ውጤት ነው።
በውድድሩ ላይ የተሳተፉት የJKS ኢትዮጵያ አባላት፣ በተለይም የሴንሴ ቢንያም ልጆች የጊኒሩ ጀግኖች፣ በታየው ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ በብቃት በመወዳደር ተጋድሏቸውን በወርቅ ሜዳሊያዎች አክብረዋል። የJKS ኢትዮጵያ ዳኞች ሀላፊ በሆኑት በሴንሴ ቢንያም የሚሰለጥኑ ለውድድር የቀረቡት እነዚህ ጀግኖች፣ ተጋድሏቸውን "ወርቅ በወርቅ" በማድረግ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርገውታል።
የJKS ኢትዮጵያ ኦፕሬሽን ማናጀር ወይዘሮ አብነት አለበል በጉዳዩ ላይ ሲናገሩ፡**
እንኳን ደስ አላችሁ! ይህ ድል የጥረት፣ የትዕግስት እና የአገር ፍቅር ውጤት ነው። ሀገራችንን በክብር አስጠራችሁ፤ ይህ ድል መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። በራሳችሁ ወጪ እና ጥረት በወጣትነት እድሜያችሁ ሀገራችሁን ለማስጠራት ያሳያችሁት ቁርጠኝነት ለእኛ ትልቅ ኩራት ነው። በጣም ኮርተናል!"* ብለዋል።
ይህ ድል ለወደፊትም ለሌሎች ወጣቶች አርአያ የሚሆን ታላቅ ስኬት ነው።
**ለጀግኖቻችን ክብር ይገባል! እንኳን ደስ አላችሁ!
ማሳሰቢያ:
የJKS ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች፣ መጣጥፎች እና ልጥፎች የካራቴ ስፖርትን ለማነቃቃት፣ ለማስተዋወቅ እና የዲጂታል ሚዲያ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ታቅደው የሚዘጋጁ ናቸው። ማንኛውንም ግለሰብ ለመጉዳት ወይም የሌላውን ጥቅም ለመንካት የተጻፉ አለመሆናቸውን በአክብሮት እንገልጻለን።
የሁላችንም ዓላማ የካራቴ ቤተሰቡን በአንድነት በማሰባሰብ ስፖርቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ነው። በኢንተርናሽናል ደረጃም ሆነ በሀገር ውስጥ በለለ የግለሰቦች የደቦ ሀሳብና ህግ አትሌቶች በግለሰቦች አድሏዊ አመለካከት ወይም በማንኛውም አግባብነት በሌለው መንገድ ከስፖርቱ እንዲገለሉ እዲቀጡ ማድረግ የጋራ ግባችንን የሚጎዳ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ አካሄዶችን በጥብቅ እንቃወማለን። የካራቴ ስፖርት የክብርና የአንድነት መድረክ ነው።"
JKS ኢትዮጵያን ይከታተሉ!
የJKS ኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች፣ ዜናዎች፣ የስልጠና መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተዘረዘሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይጎብኙ፦
ቴሌግራም: [https://t.me/JKSEthiopia](https://t.me/JKSEthiopia)
* ድረ-ገጽ: [https://jkskarateethiopia.com/](https://jkskarateethiopia.com/)
* ዩቲዩብ: [https://www.youtube.com/](https://www.youtube.com/)
* ፌስቡክ: [https://www.facebook.com/JKSEthiopia/](https://www.facebook.com/JKSEthiopia/)
* ቲክቶክ: [https://www.tiktok.com/](https://www.tiktok.com/)
* 𝕏: [https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09](https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09)
29/05/2026
በራስ ጥረት እና በመልካም ሰወች እገዛ ለሀገር ክብር፤ የኢትዮጵያ ካራቴ ቡድን በኬንያ ለሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ናይሮቢ ገብቶል
በኬንያ ናይሮቢ ከግንቦት 22 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የካራቴ ቡድን፣ በታላቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ወደ ስፍራው አቅንቷል።
በዚህ ውድድር ላይ ከሚሳተፉት አትሌቶች መካከል የJKS ኢትዮጵያ ስድስት አባላትን ጨምሮ አብዛኞቹ አትሌቶች፣ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ በራሳቸው በመሸፈን፣ ወጣትነታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ለሀገር ክብር ሲሉ አውለዋል።
እነዚህ የካራቴ ስፖርት አፍቃሪዎችና አትሌቶች፣ ለኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት በግል እና በክለብ ደረጃ የሚያደርጉትን የላቀ ስልጠና ለማሳየት እና የካራቴ ስፖርትን ከማሳደግ ባለፈ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በአፍሪካ መድረክ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ተነሳሽነት አሳይተዋል።
ይህ በራስ ጥረት እና በግል የገንዘብ አቅም ሀገርን ለማስተዋወቅና ለማስጠራት የተደረገው ጥረት፣ የካራቴ ስፖርት በኢትዮጵያ ያለውን ተስፋ እና የአትሌቶቹን የላቀ የሀገር ፍቅር የሚያሳይ ታላቅ ማሳያ ነው።
የJKS ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል፣ በአሁኑ ወቅት በኬንያ የሚገኙትን የJKS አባላት እና መላው የኢትዮጵያ የካራቴ ልዑክ ቡድን በውድድሩ የላቀ ውጤት በማምጣት ሀገራቸውን በድል እና በክብር እንዲያስጠሩ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
JKS ኢትዮጵያ ሚዲያ
ማሳሰቢያ:
የJKS ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች፣ መጣጥፎች እና ልጥፎች የካራቴ ስፖርትን ለማነቃቃት፣ ለማስተዋወቅ እና የዲጂታል ሚዲያ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ታቅደው የሚዘጋጁ ናቸው። ማንኛውንም ግለሰብ ለመጉዳት ወይም የሌላውን ጥቅም ለመንካት የተጻፉ አለመሆናቸውን በአክብሮት እንገልጻለን።
የሁላችንም ዓላማ የካራቴ ቤተሰቡን በአንድነት በማሰባሰብ ስፖርቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ነው። በኢንተርናሽናል ደረጃም ሆነ በሀገር ውስጥ በለለ የግለሰቦች የደቦ ሀሳብና ህግ አትሌቶች በግለሰቦች አድሏዊ አመለካከት ወይም በማንኛውም አግባብነት በሌለው መንገድ ከስፖርቱ እንዲገለሉ እዲቀጡ ማድረግ የጋራ ግባችንን የሚጎዳ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ አካሄዶችን በጥብቅ እንቃወማለን። የካራቴ ስፖርት የክብርና የአንድነት መድረክ ነው።"
JKS ኢትዮጵያን ይከታተሉ!
የJKS ኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች፣ ዜናዎች፣ የስልጠና መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተዘረዘሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይጎብኙ፦
ቴሌግራም: [https://t.me/JKSEthiopia](https://t.me/JKSEthiopia)
* ድረ-ገጽ: [https://jkskarateethiopia.com/](https://jkskarateethiopia.com/)
* ዩቲዩብ: [https://www.youtube.com/](https://www.youtube.com/)
* ፌስቡክ: [https://www.facebook.com/JKSEthiopia/](https://www.facebook.com/JKSEthiopia/)
* ቲክቶክ: [https://www.tiktok.com/](https://www.tiktok.com/)
* 𝕏: [https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09](https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09)
26/05/2026
የጄኬኤስ ፍሪ ካንኩ ካራቴ ክለብ (JKS Free Kanku Karate Club) ታሪክ በሰራበት ደማቅ ስነ-ስርዓት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ችሎ ያዘጋጀውን የህፃናት ካራቴ ውድድር በታላቅ ድምቀት አካሂዷል።
ይህ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ውድድር እድሜያቸው ከ7 እስከ 15 ዓመት የሆኑ 70 ታዳጊ ህፃናትን ያሳተፈ ሲሆን፣ ታዳጊዎቹ በዕለቱ የነበራቸውን ከፍተኛ ስፖርታዊ ጨዋነት እና ክህሎት በተግባር አሳይተዋል።
🏆 የዕለቱ ታላቅ አሸናፊ
በውድድሩ ላይ ብርቱ ፉክክር ሲደረግ የሰነበተ ሲሆን፣ በመጨረሻም ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩት የታዳጊዎች ስብስብ የነበረው ጎሮ ካምፓስ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ እና የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ታሪካዊ ድሉን ተቀናጅቷል።
🎤 የጄኬኤስ ኢትዮጵያ አበረታች መልዕክት
በዚህ ደማቅ መርሃ-ግብር ላይ የጄኬኤስ ኢትዮጵያ ኦፕሬሽን ማናጀር ወ/ሮ አብነት አለበል በቦታው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ማናጀሩ በንግግራቸው፡
ክለቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ችሎ እንዲህ አይነት ሰፊ ውድድር በማዘጋጀቱ የተሰማቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ታዳጊዎቹ በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ አበረታትተዋል።
ለዝግጅቱ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና እና እውቅና ሰጥተዋል።
የዕለቱ መልዕክት፦
ይህ ውድድር የህፃናቱን ስፖርታዊ ክህሎት ማሳደግ ብቻ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ የካራቴ ስፖርት የወደፊት ተስፋዎች ላይ ትልቅ አሻራ ጥሎ ያለፈ ደማቅ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል።
ለጄኬኤስ ፍሪ ካንኩ ካራቴ ክለብ እና ለአጠቃላይ አሸናፊው ጎሮ ካምፓስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን!
# # ማሳሰቢያ:
በምንም መልኩ የምንጽፋቸው ጽሑፎች እና መጣጥፎች እንድሁም ልጥፎች የተለያዩ የራሳቸው ሀሳብ እና ህመም ያለባቸውን ግለሰቦች ለማሳዘን ወይም የግል ጥቅማቸውን ለማሳጣት ሳይሆን፣ የካራቴን ህብረተሰብ ለማነቃቃት እና ባልተለመደ መልኩ ካራቴን ለማስተዋወቅ መሆኑ እንዲታወቅልን ! በአክብሮት እናሳስባለን 🙏
# # # JKS ኢትዮጵያን ይከታተሉ!
የJKS ኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች፣ ዜናዎች፣ የስልጠና መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተዘረዘሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይጎብኙ፦
* ቴሌግራም: [https://t.me/JKSEthiopia](https://t.me/JKSEthiopia)
* ድረ-ገጽ: [https://jkskarateethiopia.com/](https://jkskarateethiopia.com/)
* ዩቲዩብ: [https://www.youtube.com/](https://www.youtube.com/)
* ፌስቡክ: [https://www.facebook.com/JKSEthiopia/](https://www.facebook.com/JKSEthiopia/)
* ቲክቶክ: [https://www.tiktok.com/](https://www.tiktok.com/)
* 𝕏: [https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09](https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09)
18/05/2026
የJKS ኢትዮጵያ ሚድያ ልዩ የዜና መግለጫ
በUSA ሰማይ ስር አዲስ ታሪክ ጻፈ፤ ሴንሴ ሀይለሚካኤል አሰፋ (ዳዲኮፍ) የድል ሜዳሊያዎችን ለሀገሩ አበረከተ!
የፍልሚያው (የኩሚቴው) ንጉሥ፣ የJKS ኢትዮጵያ መስራችና ዋና አሰልጣኝ ሴንሴ ሀይለሚካኤል አሰፋ (ዳዲኮፍ) በስደትና በናፍቆት፣ በትምህርትና በጊዜ ጥበት ውስጥ ሆኖም ለሀገሩና ለቤተሰቡ ያለውን ክብር በተግባር አስመስክሯል። በትናንትናው ዕለት (ሜይ 17/2026) በሜሞሪያል ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፉ WKF MIAMI OPEN KARATE INTERNATIONAL CHAMPIONSHIP በድል ተጠናቋል።
በዚህ 17 ሀገራት በተሳተፉበት ታላቅና ብርቱ መድረክ ላይ ዳዲኮፍ ሁልጊዜም በሚታወቅበትና በለመደበት የኩሚቴ (ፍልሚያ) ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆን የቻለ ሲሆን፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ካለው የጊዜ ጥበት ጋር እየታገለ በካታ (Kata) ጭምር በመወዳደር 3ኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ተጎናጽፏል። በዚህም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በኩራት በዓለም መድረክ ላይ ከፍ አድርጎ አውለብልቧል።
ዳዲኮፍ ከድሉ በኋላ በግል የፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈውና ለአገሩ ወጣቶች ታላቅ አርአያ የሚሆን፣ በስሜትና በናፍቆት የተሞላ መልዕክት ለኢትዮጵያ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እንዲህ ሲል ገልጿል
ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም እንደሚባለው፤ በካታም በኩሚቴም ሁለት ወርቅ ማምጣት ባልችልም፣ 17 ሀገራት በተሳተፉበት በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ የሀገሬን ስም ከፍ አድርጌያለሁ። እምዬ ኢትዮጵያ ሆይ! ሀገሬ ባንድራሽን ስለብሰው ሀዘንም ደስታም የተቀላቀለበት የስሜት እባ አይኔ ይሞላዋል.
በመቀጠልም በትምህርትና በስደት ህይወት ውስጥ ሆኖ ለሀገር ክብር ለመወዳደርና ራስን ለማዘጋጀት እጅግ በጣም ከፍተኛ ትዕግስት፣ ጽናትና መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ እንዲሁም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያደክም ገልጿል። በተለይም በውድድር ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በካታ (Kata) ዘርፍ ለመቅረብና ለመዘጋጀት ብዙ እንደደከመና እንደጣረ በሰፊው አስረድቷል።
ምናልባት በፈለግኩት ልክ ባልሆንልኝም፣ ባንዲራሽን ግን በኩራት አውለብልቤያለሁ። በነበረኝ አቅም ሁሉ ስምሽን ከፍ ለማድረግ ጥሬያለሁና 'ይቅር በይኝ' ባልልም 'ደስ ይበልሽ' እላለሁ።"ብሏል።
ሴንሴ ዳዲኮፍ በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የJKS ዓለም አቀፍ አሰልጣኞችን አብሮ በማግኘቱ የተሰማውን ታላቅ ደስታ የገለጸ ሲሆን፣ ውድድሩን በዚህ መልኩ በድልና በታሪክ እንዲያጠናቅቅ ለረዳው ፈጣሪውም *"ላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አምላከ አበው ተመስገን!"* በማለት ምስጋናውን በቁጭትና በደስታ አቅርቧል።
ይህ ድል የሴንሴ ሀይለሚካኤል አሰፋ (ዳዲኮፍ) የግል ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ለJKS ኢትዮጵያ ቤተሰቦችና ለሀገራችን የማርሻል አርት ስፖርት ትልቅ ኩራት ነው። በየትኛውም የዓለም ጥግ እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ፣ በትምህርትና በስደት ጫና ውስጥም ሳይበገሩ የሀገርን ስም ከፍ ማድረግ እንደሚቻል ለወጣቱ ትውልድ በተግባር ያሳየበት ታላቅ አርአያነት ነው!
የJKS ኢትዮጵያ ሚድያ ክፍል ለመላው የስፖርቱ አፍቃሪያንና ለሀገራችን ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ ለዋና አሰልጣኛችን ለሴንሴ ዳዲኮፍ የላቀ ምስጋናና ክብር ያቀርባል።
ኦስ (Oss)!
JKS family ሺድዮ ሌሉሎች ኢንሰትግራም ላይ ከለቀቁት የቆረጥኩት ነው መሉወ እደደረሰኝ የምለቀው ይሆናል
JKS ኢትዮጵያ ሚድያ
16/05/2026
JKS Ethiopia Extends Heartfelt Congratulations on the Success of the JKS Union South Africa National Championships
Following the spectacular conclusion of the JKS union South Africa National Championships, JKS Ethiopia, led by its Chief Instructor and Senior Technical Director, extends its warmest congratulations to the organizing team and the entire JKS South Africa family.
Events of this magnitude are a testament to the power of teamwork, commitment, and sacrifice. JKS Ethiopia wishes to express deep appreciation to everyone who worked behind the scenes—from the General Secretary and President to the referees, medical teams, and the talented media professionals at Celsus Imago and Visually Spoken—for capturing the spirit of our karate community so beautifully.
Special Recognition for Instrumental Mentorship
In a special note of gratitude, JKS Ethiopia highlights the vital role played by two distinguished leaders whose mentorship has been fundamental to the professional growth of our Chief Instructor (Dudikoff) and the overall strengthening of our federation:
Sensei Andre:For his exceptional leadership in organizing this event and his unwavering guidance that has helped JKS Ethiopia reach its current technical standards.
Sensei Lourensian: For his immense contribution to the technical and moral preparation that ensures JKS karate continues to thrive across the continent.
The dedication of these instructors acts as a cornerstone for the growth of JKS Ethiopia, and their continued support is deeply valued.
The Future of JKS Africa
This championship has once again proven that the future of karate in our region is bright. **There is no doubt that JKS Africa will continue to grow exponentially, and the entire JKS Africa family stands ready and united to prepare for this journey of expansion and excellence.
JKS Ethiopia remains committed to strengthening its bond with our South African brothers and sisters. Together, we will continue to build a disciplined, respectful, and confident generation through the spirit of JKS Karate.
Together, we continue to build the future of JKS Karate!