Foot Ball Live 107.8 እግር ኳስን በቀጥታ

Foot Ball Live 107.8 እግር ኳስን በቀጥታ Foot ball Live streaming on radio.

10/07/2026
😮 No caption Needed 👋
07/07/2026

😮 No caption Needed 👋

ሞከርኩ ሞከርኩ ሊሆንልኝ አልቻለም በሜት ላይፍ የተጀመረው ጉዞዬ በሜት ላይፍ ይቋጫል
05/07/2026

ሞከርኩ ሞከርኩ ሊሆንልኝ አልቻለም
በሜት ላይፍ የተጀመረው ጉዞዬ በሜት ላይፍ ይቋጫል

Why Always Me Haaland 7Kylian 7Messi 7This World Cup keep delivering 🤩
05/07/2026

Why Always Me
Haaland 7
Kylian 7
Messi 7
This World Cup keep delivering 🤩

23ተኛው የአለም ዋንጫ አጓጊነቱ ጨምሮ የመጀመሪያ ዙር መርሀ ግብራቸውን 48ቱንም አገራትን ተመልክተናል የትኛው ብሔራዊ ቡድን አስገረማችሁ የትኛውስ ተጫዋች??ተጠባቂዎቹ ከዋክብት በብዛት በደ...
18/06/2026

23ተኛው የአለም ዋንጫ አጓጊነቱ ጨምሮ የመጀመሪያ ዙር መርሀ ግብራቸውን 48ቱንም አገራትን ተመልክተናል የትኛው ብሔራዊ ቡድን አስገረማችሁ የትኛውስ ተጫዋች??

ተጠባቂዎቹ ከዋክብት በብዛት በደመቁበት በመጀመሪያው ዙር ምባፔ ሀቨርትዝ ሀላንድና ኬን በተጠበቁበት ደረጃ ሲጀምሩ የአለም ሻምፒዮኑ ሜሲ አሁንም በ39 አመቱ ለአገሩ እግሮቹ እንዳልከዱት በአለም ዋንጫ የመጀመሪያ ሀትሪኩ በሶስት ጐሎች አሸብርቋል በመጀመሪያ ጐሉ የገርድ ሙለርን ጐሎች መጠን ሲጋራ በሁለተኛ ጎሉ ከR9 በሶስተኛ ግቡም የአለም ዋንጫ ላይ በአንደኛነት የተቀመጠውን ሚሮስላቭ ክሎሰን ታሪክ ተጋርቷል በ6 አለም ዋንጫ ውድድሮች በመሳተፍም ቀዳሚው ነበር ተቀናቃኙ ሮናልዶ በቀጣዩ ቀን እስኪከተለው ምናልባትም የሜሂኮዎ ኡቾዋ ይቀላቀላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል::

በውድድሩ አዘጋጇ አሜሪካ ባሎጉንን ምልክት አድርጋ ስትጀምር የፖች አጨዋወት ተጨብጭቦለታል የአባቱ አገር ላይ ሁለት ድንቅ ግቦችን ያስቆጠረው ኣያሪ ደስታውን በተቆጠበ መልክ የገለፀው ስዊድናዊ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን አሰልጣኝ ሳብሪ ላሙቺ ሻንጣቸውን በአንድ ጨዋታ እንዲሸክፉና ልማደኛው ሄርቬ ሬናርድ እንዲተኴቸው ምክንያት ሆኗል::

ለውድድሩ አዳዲሶቹ ኡዝቤኪስታን ጆርዳንና ኩራሳኦ የመጀመሪያ ግባቸውን ቢያስቆጥሩም ከመሸነፍ አልዳኑም ተአምረኛዋ ኬፕ ቬርዲ ግን ግብ ባታስቆጥርም በ40 አመቱ ግብ ጠባቂዋ ጆሲሜር ዲያዝ ቮዚንሃ ድንቅ ውሎ ለዋንጫ ተጠባቂዋን ስፔንን ነጥብ በመቀማት አለም ዋንጫውን አጣፍጣለች ቮዚንሃም በአንድ ቀን ምሽት አቋሙ 44ሺ የነበረው የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዩ እንደ ሮኬት በመወንጨፍ 9 ሚሊየን ተሻግሯል

ሃላንድ ለ28 አመት ከመድረኩ የራቀችውን አገሩን አንገት ቀና ሲያደርግ የቫይኪንጐቹ ደጋፊዎች በመላው አሜሪካ በጋራ የፈጠሩት የቀዘፋ ሞገድ የአሜሪካን ማዕበል በግረው እንዲደምቁ አስችሏቸዋል::

ጀርመን ከሁለት ተከታታይ የአለም ዋንጫ የውድቀት ጉዞ በኋላ በምትታወቅበት ማደባየት ስትመለስ ትንሿን ኩራሳኦን ተጭና ነው ስዊድንና ኖርዌይም የሰሜኑን ንፍቀ ክበው ወክለው ከፍ ብለው ጀምረዋል::

ሞሮኮ በተጫነችበት ጨዋታ ሴሌሳኦ ደብዝዘው ሲያመሹ ብራዚል በምትታወቅበት የበላይነት ላይ ለመመለስ ብዙ ብዙ ይቀራታል
ያማል፣ ሮናልዶ፣ ሞድሪች በተጠበቁበት ያልተገኙ ኮከቦች ሆነው ሲከርሙ ካታር በምድሯ ያላሳካችውን ነጥብ ሳትጠበቅ ከስዊዝ ስትቀማ በትርምስ ያለችው ኮንጎም በስኳድ ጥራት ምርጦቹን አይቤሪያዎች ፖርቱጋልን አስደንግጣለች ቤልጂየም ወርቃማ ትውልዷ ተመናምኖ ሽማግሌ ስብስቧ ነጥብ ለመጋራት እንኳን በራስ ላይ የተቆጠረ ጐል አስፈልጓታል
ኦራንጄም በጨዋታው ሳሙራዮቹን ብትመራም ተስፋ የማይቆርጡት ጃፓኖች የሳሙራይ ስለታቸውን ስለው ነጥብ ተጋርተዋል::

ሳውዝ አፍሪካ እጅግ ደካማ ሆና በጀመረችበት ስታድዮ አዝቴካ በመክፈቻ ሁለት ተጫዋች በቀይ ስታጣ ሶከሩስ ሳይገመቱ ጠንካራዋን የሞንቴላን ተርኪዬ አንገት አስደፍተዋል::
ዛሬም ምሽት 1:00 ሁለተኛው ዙር ሲጀምር በመጀመሪያው ዙር የቀናቸው ወደቀጣይ ዙር ሊንደረደሩ የደከሙትም እድላቸውን ሊያቃኑ ለቀጣይ አንድ ሳምንት ይፋለማሉ

የትኛው አስገረማችሁ ካቦ ቨርዲ ወይስ ሊዮ ሜሲ የቫይኪንግ ሞገድ ወይስ ያልተጠበቁ ቡድኖች ድል

የእግር ኳስ ፍቅር ሱስም እስከሞት 23ተኛው የአለም ዋንጫ ከተጀመረ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል ብዙ አስገራሚ ነገሮችንም ከነውዝግቡ እያስመለከተን ይገኛል በመክፈቻው ጨዋታ 3 ቀይ ካርዶችን ስን...
14/06/2026

የእግር ኳስ ፍቅር ሱስም እስከሞት

23ተኛው የአለም ዋንጫ ከተጀመረ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል ብዙ አስገራሚ ነገሮችንም ከነውዝግቡ እያስመለከተን ይገኛል በመክፈቻው ጨዋታ 3 ቀይ ካርዶችን ስንመለከት ትላንት ምሽት የመጀመሪያው ፍፁም ቅጣት ምት ተቆጥሯል እስካሁን 19 ጎሎችን ስንመለከት አዘጋጇ አሜሪካ ደቡብ ኮሪያና ሞሮኮ አስደሳች አጀማመር አሳይተውናል
በአፍሪካ ሆነን ውድድሩን ለምንከታተል የጨዋታ ሰአት ልዩነቱ ርቀት አራት ጨዋታዎች ያለ እንቅልፍ እንድከታተል ግዴታ ጥሎብናል የምንወደው ውድድር ነውና አያስችለንም ሆኖም የእግር ኳስ ልክፍት መጠኑን ካለፈ ጤና ሊያዛባ ብሎም ህይወት ሊያሳጣም ስለሚችል ጥንቃቄ ያሻናል
ነገሩ እንዲህ ነው በ2012 የአውሮፓ ሻምፒዮና በፖላንድና ዩክሬን ሲዘጋጅ አንድ ቻይናዊ የ26 አመት ወጣት ዢያንግ ዢያዎሻን ሲሰኝ በጉጉት ይጠብቀው የነበረውን የአውሮፓ ሻምፒዮና አንድም ጨዋታ ሳያልፈው ለማየት ቆረጠ ችግሩ ግን በምስራቅ አውሮፓና በቻይና መሀል የ7 ሰአታት ልዩነት ነበርና ጨዋታዎቹ የሚጀምሩት እኩለ ለሊትና ከዚያ በኋላ ነበር በዚያ ላይ ሲነጋ እንዲቀለው ያህል ተጣጥቦ ወደ ስራ ገበታው ይመለሳል ጨዋታውንም ሲመለከት ለመነቃቃት ትኩስ መጠጦችን ዘና ለማለት አልኮል ይጎነጫል በዚህ ሂደት 11 ቀናት ከተጓዘ በኋላ በጁን 18 የኢታሊና የሰሜን አየርላንድን ጨዋታ ከተመለከተ በኋላ ከአቅሙ በላይ ስለሆነ መተኛት ተገደደ ነገር ግን አልተነሳም እስከ ወዲያኛው አሸለበ የሞቱ መንስኤም ከልክ ያለፈ ድካም መሆኑ በህክምና ባለሙያዎች ተረጋገጠ እናም አራት አመት ጠብቀን የምናገኘው ውድድር አጓጊና ተናፉቂ ቢሆንም የጤናችን ጉዳይ ቀዳሚ መሆኑ አይዘንጋ

ከሶስቱ አዘጋጆች ካናዳ የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ነጥቧን ስታሳካ አሜሪካ በሎስ አንጀለስ ሜክሲኮ በአዝቴካ በድል በመጀመር ከኳታር ውጭ ሁሉም አዘጋጆች በመክፈቻ አዘጋጅ ሆነው ያልተሸነፉበት ሪ...
13/06/2026

ከሶስቱ አዘጋጆች ካናዳ የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ነጥቧን ስታሳካ አሜሪካ በሎስ አንጀለስ ሜክሲኮ በአዝቴካ በድል በመጀመር ከኳታር ውጭ ሁሉም አዘጋጆች በመክፈቻ አዘጋጅ ሆነው ያልተሸነፉበት ሪከርድ ቀጥሏል

England becomes World champs after 60 years of waitሶስቱ አናብስት የአለም ሻምፒዮንስ
08/06/2026

England becomes World champs after 60 years of wait
ሶስቱ አናብስት የአለም ሻምፒዮንስ

የአለም ዋንጫ እስከ ፍፃሜ ጉዞ እንግሊዝ ከ60 አመት በኋላ የአለም ሻምፒዮን ትሆናለችWorld Cup ...

እለቱን በአለም ዋንጫ ታሪክ ስናስታውስበዛሬው እለት ጁን 08-1990 ከ36 አመት በፊት በሳንሲሮ የመክፈቻ ጨዋታ እለት የማይበገሩት አንበሶች በማይረሳው ውድድር ጊዜያቸው የውድድሩን አሸናፊን...
08/06/2026

እለቱን በአለም ዋንጫ ታሪክ ስናስታውስ

በዛሬው እለት ጁን 08-1990 ከ36 አመት በፊት በሳንሲሮ የመክፈቻ ጨዋታ እለት የማይበገሩት አንበሶች በማይረሳው ውድድር ጊዜያቸው የውድድሩን አሸናፊን የዲዬጎዋን አርጀንቲናን የረቱበት አጋጣሚ በልዩነት ይታወሳል ዘግየት ብሎም ቴራንጋ አንበሶቹ የወቅቱን አሸናፊን ፍራንስን ረትታ አለምን ስታስደነግጥ የካሜሩንን ገድል በማስታወስም ጭምር ነበር በእለቱ ኦማር ቢክ በጭንቅላት ያስቆጠራት ግብ የጨዋታው ልዩነት ስትሆን ወንድሙ ጀግና በነበረበት ጨዋታ ታናሹ አንድሬ ካና ቢክ ግን በቀይ ካርድ መሰናበቱ አነጋጋሪ ነበር እንዲሁም የአርጀንቲናውን ድንቅ ተጫዋች ካኒዢያን ከባድ ጉዳት ያደረሰበት ቤንጃሚን ባሲንግም በቀይ ተሰናብቶ በተለየ መልክ ከሚታወሱ የአለም ዋንጫ መክፈቻዎች መሀል ይጠቀሳል

Address

Adiss Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251910819677

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Foot Ball Live 107.8 እግር ኳስን በቀጥታ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category