19/09/2022
Ethiopian Coffee F.C Daily News
Official page for the Ethiopian coffee sports club
19/09/2022
Ethiopian Coffee F.C Daily News
19/09/2022
Ethiopian Coffee F.C Daily News
የ16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ መስከረም 9/2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና ከዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ አዳጊ ቡድን ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ከቀኑ 10:00 ሰዓት ያደርጋል።
17/09/2022
ተጠናቀቀ
ኢትዮጵያ ቡና 1 -0 ኢትዮ ኤሌትሪክ
26' አንተነህ
17/09/2022
⚽16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ መስከረም 7/2015 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።
👉 ክለባችን የኢትዮጵያ ቡና የውድድሩን የመክፈቻ ጨዋታ ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን ዳግም ከተቀላቀለው ኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር በ8:00 ሰዓት ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
🎯 ስድስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ቡና የቤተሰብ ሩጫ የመሮጫ ትኬቶች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ዙሪያ በቦታው በሚገኝ መኪና ውስጥ እና አስተባባሪ ደጋፊዎች ጋር የሚሸጥ ይሆናል።
ድል ለታላቁ የኢትዮጵያ ቡና‼
16/09/2022
Ethiopian Coffee F.C Daily News
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ 23 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸውን ተጫዋቾች ብሩክ በየነ፣ መስፍን ታፈሰ፣ መሐመድኑር ናስ፣ ጫላ ተሺታ፣ አብዱልከሪም ወርቁ እና ሀ/ሚካኤል አደፍርስን ዛሬ የፊፋ ሕግ በሚያዘው መሰረት ወደ ብሔራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ወደ ቦታው ልኳል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ 23 ዓመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድናችን መልካም የውድድር ጊዜ እንዲሆንለት ምኞቱን ይገልፃል::
ድል ለብሔራዊ ቡድናችን!!
14/09/2022
👉 ለ16 ኛ ጊዜ የሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ዋንጫ ከፊታችን መስከረም 7-15/2015 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በስድስት ቡድኖች(የኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ መቻል እና ለገጣፎ ለገዳዲ) መካከል ይካሔዳል።
👉 ክለባችን የኢትዮጵያ ቡና በምድብ ሀ ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ እና ለገጣፎ ለገዳዲ ተደልድሏል።
👉 የመጀመሪያውን ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌትሪክ ቅዳሜ መስከረም 7/2015 ዓ.ም በ8:00 ሰዓት ላይ የሚያደርግ ይሆናል
👉 ውድድሩን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሁሉንም ጨዋታዎች በቀጥታ ያስተላልፋል
👉 የስታዲየም የመግቢያ ዋጋዎች ፦
ሚስማር ተራ 20 ብር
ካታንጋ 30 ብር
ከማንአንሼ 50 ብር
ጥላፎቅ 100 ብር
ክቡር ትሪቢውን 200 ብር
👉 50% የሚሆነው ጥቅላላ ገቢ ለክለቦች በሽልማት መልክ ይከፋፈላል።
11/09/2022
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ለፅ/ቤት ሠራተኞች፣ ለደጋፊ ማህበር አመራሮች፣ ለክለባችን አሰልጣኞች ፣ ለክለባችን ተጫዋቾች እና ለታላቁ እና ታማኙ '12' ቁጥር ለባሾቹ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እንኳን ለ2015 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
08/09/2022
Ethiopian Coffee F.C Daily News
07/09/2022
ዛሬ ጳግሜ 2/2014 ዓ.ም ሐዋሳ ላይ ከልምምድ በኋላ የክለባችን የስራ አመራር ቦርድ ፕሬዝደንት እና የክለባችን ስራ አስኪያጅ ከቡድኑ ጋር በጋራ ፎቶግራፍ ተነስተዋል።
በቀጣይ
👉 ትላንት ምሽት የክለባችን አመራሮች ከቡድኑ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እና
👉 የቡድኑን አጠቃላይ ሁነት የምንመለስበት ይሆናል።
07/09/2022
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት መ/አለቃ ፈቃደ ማሞ እና የክለባችን ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ሐዋሳ ልምምድ በሚሰራበት ቦታ በመገኘት ቡድኑን አበረታተዋል።
አጠቃላይ በቡድኑ ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን።
06/09/2022
ስድስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች ዓመታዊ ሩጫ መስከረም 29/2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የምዝገባ ሂደቱም ከነሐሴ 1–30/2014 ዓ.ም ድረስ በቡና ባንክ፣ በክለቡ ጽ/ቤት በደጋፊ ማህበር ጽ/ቤትና በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የደጋፊ አስተባባሪዎች ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በዚህም በወቅቱ ለተመዘገቡ ደጋፊዎቻችን ያለንን ክብርና ምስጋና በዚህ አጋጣሚ እየገለፅን፣ በተለያየ ምክንያት (ከበዓል ጋር ተያይዞ እንዲሁም የትምህርት ቤት ምዝገባ መኖሩን ተከትሎና በሌሎችም ምክንያት) ምዝገባው እንዲራዘም ደጋፊዎቻችን በተደጋጋሚ ጠይቀውናል፡፡
የክለቡ ፅ/ቤትና የደጋፊ ማህበር አመራሮች ነሐሴ 30/2014 ዓ.ም ከደጋፊ አስተባባሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ምዝገባው መራዘም እንዳለበት ተስማምተዋል፡፡
በመሆኑም በዕቅድ የያዝነው ቁጥር ላይ ለመድረስና ደጋፊዎቻችን ተደራሽ ለማድረግ እስከ መስከረም 20/2015 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለፅን፣ ከዚህ ቀን በኋላ ግን ምንም ዓይነት ምዝገባ የማይካሄድ መሆኑን አጥብቀን እንገልፃለን፡፡