Ethiopian Amateur Boxing With Cazo 24/7

Ethiopian Amateur  Boxing  With Cazo 24/7

Share

እኛ ምርጥ የእምዬ ኢትዮጵያ ልጆች

Cazo Boxing 24/7 is a global boxing media platform dedicated to promoting amateur and professional boxing worldwide.

We share fight news, athlete spotlights, training clips, interviews, and exclusive boxing content 24/7 https://youtube.com/channel/UCcrk4m8FU4-J8hEg9X25FyA

Photos from Ethiopian Amateur  Boxing  With Cazo 24/7's post 05/06/2026

"ለሁሉም ክፍት ከ17 አመት በላይ የክ/ከተሞች ቦክስ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ይካሄዳል"

በአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በመዲናችን አዲስ አበባ ለሁሉም ክፍት የሆነ በ ኤ እና ቢ ተከፍሎ በሁለቱም ፆታዎች የክፍለ ከተሞች እና የቡድኖች ውድድር በአራዳ ፓርክ ፒያሳ አሬና ስፖርት ማዕከል ይካሄዳል::

ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 6/2018ዓ.ም በሚካሄደው ውድድር በርካታ ቦክሰኞች ይሳተፋሉ::

በዚህ ለሁሉም ክፍት የክ/ከተሞች ውድድር በሁለት ጎራ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን በ ኤ በቢ እንዲሁም በሴቶች ውድድሩ ይካሄዳል::

ውድድሩ በእያንዳንዱ ካታጎሪ ከአንድ ቡድን በየካታጎሪያቸው በኤ አንድ እንዲሁም በቢ አንድ ቡጢኛ ብቻ የሚያሳትፉ ይሆናል::

በዚህ ውድድር የምትሳተፉ በየክፍለከተሞቹ ያላቹ አሰልጣኞች የተወዳዳሪዮቻቹን ስም ዝርዝር እስከ ፊታችን እሁድ ግንቦት 30/2018ድረስ በዚህ+251918096107 የቴሌግራም ቁጥር ማስገባት ትችላላቹ::

"Open Boxing Tournament for All"
Organized by the Addis Ababa Boxing Federation, an open boxing tournament for all projects, sub-cities, and teams will be held in our capital city, Addis Ababa, at Arada Park – Piassa Arena Sports Center.
The competition will take place from Sene 2 to Sene 6, 2018 E.C. (Ethiopian Calendar) and is expected to be an exciting and vibrant event. 🥊🏆

Photos from Ethiopian Amateur  Boxing  With Cazo 24/7's post 05/06/2026

ሞሞ ቦክስ (Momo Box)

ሞ የራሱን MoMo Boxing ብራንድ በመገንባት ላይ በሚያደርገው ጉዞ ሁሉ መልካም ዕድል እንመኝለታለን።

እንዲሁም በኢትዮጵያ ባለው ጂሙ ውስጥ በቦክስ አማካኝነት ልጆችን በመደገፍ የሚያከናውነውን ዋጋ ያለው ስራ እንዲቀጥል እንመኛለን፤ እንዲሁም በTikTok የሙያ ጉዞው የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን መልካም ምኞታችንን እናቀርባለን!!

Momo Box dropped in for a quick session and to show off his ever increasing collection of bling.
We wish Mo the very best of luck moving forward building his MoMo Boxing brand and continuing his valuable work supporting kids through boxing back at his gym in Ethiopia and of course furthering his TikTok career!!
🇬🇧🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿🏴‍☠️
www.rebelsfitness.uk

05/06/2026

ኢትዮ ፋይት ናይት ውድድር ተሰናድቷል በ23" ኢቲኤፍሲም በ*23

ሁለቱም ውድድሮች ግን በተመሳሳይ ቀን መሆናቸውን ትደግፋላቹ ሀሳብ አስተያየታቹን አካፍሉን!?

አወዳዳሪዮች መብዛታቸው እርግጥ ነው ስፖርተኛውን ይጠቅማል!

Photos from Ethiopian Amateur  Boxing  With Cazo 24/7's post 04/06/2026

"ኢትዮ ፋይት ናይት ፣ የተሰኘ የMMA ዉድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው"

በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተዘጋጁት ታላቅ የንኪኪ ስፖርታዊ ዝግጅቶች “ኢትዮ ፋይት ናይት” በሚል መጠሪያ በ3 ጥምር አዘጋጀች ፣ በአዲስ አበባ ኪክ ቦክስ ፌዴሬሽን ፣ በአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም በአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ትብብር ነሀሴ 23/2018 እኤአ Aug 29/2026 ታላቅ የMMA እና የቦክስ ስፓርት ዉድድር በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ የድብልቅ ማርሻል አርት ዘርፍ በአለም አቀፍ እዉቅና ያላቸዉ የዉጭ አገር ዜጓች መካከል ፍልሚያ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያን በመወከል ከሚሳተፉ መካከል በዋናነት ቢኒያም ሽብሬ፣ ክብሮም ንጉሴ እንዲሁም ሀገረሰላም አርባ የሚገኙበት ሲሆን በጠቅላላው ከ 6 እስከ 8 የሚደርሱ የተለያዩግጥሚያዎች ይካሄዳሉ ።

ሁሉም ተወዳዳሪዎች የተመረጡት በውድድር መዝገቦች (fight card )፣ በኢንተርናሽናል ውድድሮች ልምድ፣ የአካል ብቃትና ጤንነት ፣ ማራኪ ግጥሚያዎችን ለማቅረብ ባላቸው ችሎታ ላይ በመመስረት ነው።

አትሌቶች በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት የግዴታ የህክምና ምርመራ፣ የክብደት መለኪያ እና የፍቃድ አሰጣጥ ሂደቶችን ያለፉ ሲሆኑ በቅርቡ የሁሉም ተወዳዳሪዎች የክብደት መጠንና ዜግነት ይፋ ይሆናል።

በዚህ ታሪካዊ ዝግጅት ከ8,000 እስከ 10,000 የሚደርሱ የስፓርት አፍቃሪያን ተመልካቾችንይህንን ድንቅ ዉድድር ለመመልከት የሚታደሙ ሲሆን የስፓርት ችሎታዎችን ለአፍሪካ እና ለአለም የሚያሳይ አስተማማኝ፣ ሙያዊ እና አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ የስፖርት ዝግጅት ለማቅረብ ዝግጅታችንን አገባደናል።
የዝግጅቱ አላማ ፣ የንክኪ ስፖርቶችን ማጎልበት እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት መዝናኛ መድረክ ከመፍጠር ባለፈ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሙያዊ መድረክ በመፍጠር፣ ወጣት አትሌቶችን ለማነሳሳት፣ ኢትዮጵያንና አዲስ አበባን በስፖርት ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ እና የአለም አቀፍ የንክኪ ስፖርታዊ ውድድሮች መዳረሻ ለማድረግ የታለመ ነው።

የዝግጅቱ ስፍራ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር (AICC) ደረጃውን በጠበቀ የኤሌክትሮኒክስ የምስልና የድምፅ መገልገያ መሳሪያዎች የተሟላ በመሆኑ የስፓርት መዝናኛ ለማቅረብ ፣ምቹና ፣ ተስማሚ ያደርገዋል።

ገራሚ ኢቨንትስ የዝግጅቱን ፕሮዳክሽን ማኔጅመት በመምራት ከ3ቱ ባለቤቶች ጋር በጣምራ የሚሰራ ሲሆን፣ በአትሌቶች ዝግጅት፣ የውድድር ቦታ ፣ በደህንነት፣ እና ሎጂስቲክስ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ተመድቧል።

ይህ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በተከታታይ ለማካሄድ የታቀደ ሲሆን የዝግጅቱን ጥራት ከፍ ለማድረግ እና የአትሌቶችን እድገት ለመደገፍ አገር በቀል እና አለም አቀፍ ስፖንሰሮች በቦታ ብራንዲንግ፣በሚዲያ ሽፋን፣በዲጂታል
ግብይት፣በብሮድካስት፣ቪአይፒ ተሳትፎ እና በማህበረሰብ ተፅእኖ ተነሳሽነት የምርት እይታን በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ተደራሽ በማድረግ እንዲሰሩ ይጋብዛል።

የመግቢያ ትኬቶችን ዋጋና የእይታ ሰፊ ሽፋንን ለማረጋገጥ ከሚዲያ አጋሮች ጋር አብረን እየሰራን ስንሆን የቴሌቭዥን እና የዲጂታል መድረኮችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች
በቅርቡ ይፋ ይደረጋሉ።

ስፓርት ለሁሉም! እናመሰግናለን!

Photos from Ethiopian Amateur  Boxing  With Cazo 24/7's post 04/06/2026

ኢትዮ ፋይት ናይት ፣ የተሰኘ የMMA ዉድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ።

በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተዘጋጁት ታላቅ የንኪኪ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ግንባር ቀደም የሆነው “ኢትዮ
ፋይት ናይት” በሚል መጠሪያ በ3 ጥምር አዘጋጀች ፣ በአዲስ አበባ ኪክ ቦክስ ፌዴሬሽን ፣ በአዲስ አበባ ቦክስ
ፌዴሬሽን እንዲሁም በአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ትብብር ነሀሴ 23/2018 እኤአ Aug 29/2026 ታላቅ የMMA
እና የቦክስ ስፓርት ዉድድር በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ የድብልቅ ማርሻል አርት ዘርፍ በአለምአቀፍ እዉቅና ያላቸዉ የዉጭ አገር ዜጓች መካከል ፍልሚያ
የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያን በመወከል ከሚሳተፉ መካከል በዋናነት ቢኒያም ሽብሬ፣ ክብሮም ንጉሴ እንዲሁም
አገረሰላም አርባ የሚገኙበት ሲሆን በጠቅላላው ከ 6 እስከ 8 የሚደርሱ የተለያዩ ግጥሚያዎች ይካሄዳሉ ።
ሁሉም ተወዳዳሪዎች የተመረጡት በውድድር መዝገቦች (fight card )፣ በኢንተርናሽናል ውድድሮች ልምድ፣ የአካል
ብቃትና ጤንነት ፣ ማራኪ ግጥሚያዎችን ለማቅረብ ባላቸው ችሎታ ላይ በመመስረት ነው።አትሌቶች በፌዴሬሽኑ
ደንብ መሰረት የግዴታ የህክምና ምርመራ፣ የክብደት መለኪያ እና የፍቃድ አሰጣጥ ሂደቶችን ያለፉ ሲሆኑ በቅርቡ
የሁሉም ተወዳዳሪዎች የክብደት መጠንና ዜግነት ይፋ ይሆናል።
በዚህ ታሪካዊ ዝግጅት ከ8,000 እስከ 10,000 የሚደርሱ የስፓርት አፍቃሪያን ተመልካቾችንይህንን ድንቅ ዉድድር
ለመመልከት የሚታደሙ ሲሆን የስፓርት ችሎታዎችን ለአፍሪካ እና ለአለም የሚያሳይ አስተማማኝ፣ ሙያዊ እና
አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ የስፖርት ዝግጅት ለማቅረብ ዝግጅታችንን አገባደናል።
የዝግጅቱ አላማ ፣ የንክኪ ስፖርቶችን ማጎልበት እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት መዝናኛ መድረክ
ከመፍጠር ባለፈ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሙያዊ መድረክ በመፍጠር፣ ወጣት አትሌቶችን ለማነሳሳት፣
ኢትዮጵያንና አዲስ አበባን በስፖርት ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ እና የአለም አቀፍ የንክኪ ስፖርታዊ ውድድሮች መዳረሻ
ለማድረግ የታለመ ነው።
የዝግጅቱ ስፍራ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር (AICC) ደረጃውን በጠበቀ የኤሌክትሮኒክስ የምስልና የድምፅ
መገልገያ መሳሪያዎች የተሟላ በመሆኑ የስፓርት መዝናኛ ለማቅረብ ፣ምቹና ፣ ተስማሚ ያደርገዋል።
ገራሚ ኢቨንትስ የዝግጅቱን ፕሮዳክሽን ማኔጅመት በመምራት ከ3ቱ ባለቤቶች ጋር በጣምራ የሚሰራ ሲሆን፣
በአትሌቶች ዝግጅት፣ የውድድር ቦታ ፣ በደህንነት፣ እና ሎጂስቲክስ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ተመድቧል።
ይህ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በተከታታይ ለማካሄድ የታቀደ ሲሆን የዝግጅቱን ጥራት ከፍ ለማድረግ እና
የአትሌቶችን እድገት ለመደገፍ አገር በቀል እና አለም አቀፍ ስፖንሰሮች በቦታ ብራንዲንግ፣በሚዲያ ሽፋን፣በዲጂታል
ግብይት፣በብሮድካስት፣ቪአይፒ ተሳትፎ እና በማህበረሰብ ተፅእኖ ተነሳሽነት የምርት እይታን በተለያዩ የሚዲያ
አውታሮች ተደራሽ በማድረግ እንዲሰሩ ይጋብዛል። የመግቢያ ትኬቶችን ዋጋና የእይታ ሰፊ ሽፋንን ለማረጋገጥ
ከሚዲያ አጋሮች ጋር አብረን እየሰራን ስንሆን የቴሌቭዥን እና የዲጂታል መድረኮችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች
በቅርቡ ይፋ ይደረጋሉ።

ስፓርት ለሁሉም! እናመሰግናለን!

Via gerami event

04/06/2026
03/06/2026

«እባካችሁ አትግደሉን!» — ይህ በአሁኑ ሰዓት በአርሲ ምድር በእምነታቸው ብቻ ተለይተው በግፍ እየተጨፈጨፉ ያሉ ንጹሃን ወገኖቻችን ልብ ሰባሪ ጩኸት ነው። 💔

በአርሲ ዞን አሰኮ እና ሺርካ ወረዳዎች ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት፣ ከ10 በላይ ንጹሃን መገደል እና ከ100 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የታሪካዊው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ አመድ መሆን መላውን ኢትዮጵያውያንን በጥልቅ ሃዘን ውስጥ ጥሏል። ንጹሃን ማረፊያ አጥተው እየተሳደዱ ባሉበት በዚህ አስከፊ ወቅት፣ ዝምታን መምረጥ ከገዳዮች ጎን መቆም ነው።

03/06/2026

አንዳንዶች በተፈጥሮ ከተሰጥኦ ጋር ይወለዳሉ ሌሎች ደሞ በትግል ይቀረፃሉ።
ጓንቱ የቆዳህ አካል ሲሆን፣ ያ ሁሉም መከራና ፈተና ወደ ጥንካሬ መቀየሩን ያሳያል።
ውጊያው በውስጥህ ይኖራል፣ ታላቅነትም ከዚያ ይጀምራል። 🥊

03/06/2026

another ጦር*ነ *ት what a gr8 fight አስደናቂው የ67ኪ.ግ ቦክስ ፍፃሜ ጨዋታ!

ወርቅ ለመውሰድ የተደረገ ትንቅንቅ ቀይ ማዕዘን አቡበከር ሰፋን (ማረሚያ) ከ ሰማያዊ ማዕዘን አድማሱ አጥናፉ ኦሜድላ ያደረጉት ዕልህ አስ ራሽ ቦክስ ጨዋታ;;

unbelievable Boxing Fight

Give us your commente &feed back

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Kolfe
Addis Ababa
24/7