Euro Cup Amharic News

Euro Cup Amharic News

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Euro Cup Amharic News, Sports Event, Addis Ababa.

28/04/2020

https://ytimoney.xyz/942845735698938/

ሰው ጊዜውን የሚያጠፋው Facebook ወይም telegram ላይ ነው። ከሚያጠፉት ጊዜ ላይ ቀንሰው business መስራት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ከላይ ያለውን ሊንክ በመጫን አሁኑኑ register ያድርጉ🏦 እረፍት ስትሆኑ ወይም በትርፍ ጊዜአችሁ እቤታችሁ ቁጭብላችሁ ገንዘብ ምታገኙበት website ልጠቁማችሁ
https://ytimoney.xyz/942845735698938/
✅ መጀመሪያ ከላይ ያለውን link ንኩት

✅ Website ውስጥ ሲከታቹ register የሚል ፈልጉና ንኩት

✅ username ፣ email ወይም ስልክ ቁጥራችሁን መሙላት፣ password ከዛ መጨረሻ ላይ ሚሰጣችሁ ቁጥር ሙሉና register በሉት success ይላል

✅ Start watching payed ads ሚለውን ንኩት

✅ ከላይ ሚፅፍላችሁን ቁጥር እየሞላችሁ Continue እያላችሁ ገንዘባችሁን ማጠራቀም ያጠራቀማችሁትን የገንዘብ መጠን ከጎን ይፅፍላችሆል ከዛ

✅ 150$ ሲደርስላችሁ ከስር withdrawal ሚለውን ስትነኩት የምትኖሩበትን ሀገር 🇪🇹 እና ገንዘቡን መላኪያ መንገድ ይነግራችሆል ገንዘቡን መቀበያ መንገድ wester union በሚለውን ነክታችሁ አስልኩት እዚ https://ytimoney.xyz/942845735698938/ በማንኛውም ባንክ መቀበል ትችላላችሁ
g
👉👉 በመጨረሻም ስለዚ ልንገራችሁ viewing payed advertising በማስታወቂያዎች ላይ ሚሰራ ድርጅት ነው ትልልቅ ስም ያላቸው
ጅርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራል ለምሳሌ nike ፣adidas፣ barcelona club ...
👉 እናንተ የምሞሉት ቁጥር ለድርጅቱ ስራ እየሰራችሁላቸው ነው ለዛ ነው ድርጅቱ በ% ሚከፍላችሁ 10ጊዜ ቁጥሩን ስሞሉት 1ትችላላችሁ ዶላር ይከፍላችሆል

😱 ለየት የሚያረገው ደግሞ ካፓኒው አንዴ ካወቃችሁ ሌሎች business ሊያሠራችሁ ይችላል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ytimoney.xyz

Photos from Euro Cup Amharic News's post 28/09/2016

ዕለተ እሮብ ምሽት አጫጭር ስፖርታዊ ዜናዋች በ የቀረበ

ሁሌም ፖስቶቹን ላይክ ሳያደርጉ አይለፉ።ላይክ ማድረጋችሁ ለኛ ብቻሳይሆን ለናንተም እንዲደርሳችሁ ነው።



የ25 ዓመቱ ዩጋንዳዊ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ኪሪዚስቶም ንታምቢ የፕሪምየር ሊጉን አዲስ ክለብ ጅማ አባቡናን እንደተቀላቀለ የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።ተጫዋቹ ያለፈውን ዓመት በደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ዲቪዝዮን ለሚወዳደረው ቫስኮ ደጋማ ክለብ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን በተመሳሳይ የአንድ ዓመት ውል ነው ለጅማ አባቡና የፈረመው።
ጅማ አባ ቡና ጀማል ጣሰው ፣ ቢንያም አሰፋ ፣ መሃመድ ናስር እና በድሉ መርዕድን የመሳሰሉ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በማስፈረም ስብስቡን ማጠናከር ችሏል፡፡



የማንቺሰተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ስፔናዊውን የመሀል ተጫዋች ሁዋን ማታን አዲስ ኮንትራት ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል።

የኢንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አስተዳደር ሳም አልራዳይስን ከ አሰልጣኝነታቸው አሰናብቶዋቸል።ሳም አላርዳይስ የኢንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተደርገው የተሾሙት ከ 68 ቀን በፊት ነበር።

የመድፈኞቹ አለቃ አርሰን ዌንገር ቅዳሜ ምሽት ከቼልሲ ጋር በነበራቸዉ የፕሪሜርሊግ ጨዋታ ላይ ጉዳት ስለገጠመዉ አማካያቸዉ ኮክለን ተጠይቀዉ ከሶስት ሳምንት ቦሀላ እንደሚመለስ አረጋግጠዋል "ነገ ከምናደርገዉ የቻምፒዮንስሊግ ጨዋታዉጪ ነዉ ሆኖም የጉዳት መጠን አሳሳቢ አይደለም ከሶስት ሳምንት ቦሀላ ይመለሳል"ብለዋል።

ዌስትሃም ዩናይትዶች ከ48 ዓመቱ የክለቡ አሰልጣኝ ስላቨን ብሊች ጋር ሊያደርጉት አቅደው የነበረውን የኮንትራት ድርድር የክለቡን ደካማ አቁአም ተከትሎ ለግዜው እንዲቆም አድርገውታል።

ኤቨርተኖች ከ23 ዓመቱ አጥቂ ሮሚዮ ሉካኩ ጋር የኮንትራት ውል እድሳት ለማድረግ ንግግር ጀመሩ። የመርሲሳይዱ ክለብ ቤልጂየማዊ ኢንተርናሽናልን በክለቡ የረጅም አመት ኮንትራት ማስፈረም ይፈልጋሉ።

ከአርሰናል በውሰት ቦርንስማውዝ እየተጫዋተ ሚገኘው ጃክ ዊልሸር በዐመቱ መጨረሻ በቋሚነት እዚው ቦርንስማውዝ ሊፈርም እንደሚችል ነው ዘ ሰን የገለፀው።

አንቶንዮ ኮንቴ የበርንሌዩን ወጣት ተከላካይ ኪንን በጥሩ የዝውውር መስኮት ማስፈረም ይፈልጋሉ።

ማንቺስተር ሲቲዋች የጁቬንቱሱን ተከላካይ ቦኑቺን አሁንም እንደሚፈልጉት ነው ስካይስፖርት የገለፀው።

ማንቸስተር ዩናይትዶች የ24 ዓመቱን ተከላካይ ፊል ጆንስ ለመልቀቅወስነዋል። አርሰናል እና ሊቨርፑሎች የእንግሊዛዊውን ፊርማ ለማግኘት ይፈልጋሉ ተብሎአል።

መድፈኞቹ የጥር ወር የተጫዋቾች የዝዉውር መስኮት ሲከፈት የአሲ ሚላኑን አጥቂM.baye niange ለማስፈረም አቅደዋል፣ተጫዋቹም ቢሆን በቅርቡ ከ Gazzettadelo sport ጋር በነበረዉ ቆይታ "ፕሪሜርሊጉ ለኔ ትክክለኛ ቦታ ነዉ አንድ ቀን ወደዛ መጏዜ አይቀርም"ማለቱ ይታወሳል።

ዩናይትዶች 42 ሚልየን ፓውንድ በማውጣት የሪያል ማድሪዱን ሰርጂዮ ራሞስን ማስፈረም ይፈልጋሉ።

ፒኤስጂዋች በጥሩ የዝውውር መስኮት አይናቸውን ወደ ኤስሚላኑ አጥቂ ባካ እንደሚያዞሩ የተገለፅው።


ሪ.ማድሪድ (ሮናልዶ፣ቫራኔ) 2- 2 ዶርትሙንድ (ኦበመያንግ፣ሹርሌ)
ባ.ሊቨርኩሰን (ሀርናንዴዝ) 1- 1 ሞናኮ(ግሊክ)
ቶተንሀም (ሰን) 1- 0 ሲኤስኬ ሞስኮ
ሌስተር (ሲለማኒ) 1-0 ፖርቶ
ጁቬንቱስ (ሴምፐር፣ፒጃኒክ፣ሂግዌን፣ዲይባላ) 4-0 ዛግሪብ
ስፖርቲንግ (ርዊዝ፣ዶስት) 2- 0 ዋርስዛዋ
ኮፐንሀገን (ዴንስዊል፣ድሌኒ፣ሳንታደር፣ጃርገንሰን) 4- 0 ክለብ ብሩጅ
ሲቪልያ (ቤንየደር) 1- 0 ሊዮን


•ባ.ሙኒክ ከ አ.ማድሪድ 3:45ማታ
•አርሰናል ከ ባዜል 3:45 ማታ
•ቦ.ሞንቼግላድባክ ከ ባርሰሎና 3:45
•ቤስኪታሽ ከ ዳይናሞ ኬቭ 3:45 ማታ
•ሴልቲክ ከ ማንቺስተር ሲቲ 3:45 ማታ
•ናፖሊ ከ ቤኔፊካ 3:45 ማታ
•ፒኤስቪ ከ ሮስቶቭ 3:45 ማታ
•ፒኤስጂ ከ ሊዶጎሬ

እነዚህን ጨዋታዋች በተለያዩ ምክንያቶች ማየት ያልቻላችሁ በዚህ ፔጅ ከ 3:45ጀምሮ በቀጥታ መመልከት ይችላሉ።





ዜናዎቹን አንብበው ሲጨርሱ አስተያየት መስጠቶን አይርሱ።

Photos from Euro Cup Amharic News's post 22/09/2016

~>የእለተ ሀሙስ የስፖርት መረጃወች

¤ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ አማካይ ዳኒ ድሪንክወተርን ዳግም በ £30 million ወደ ኦልትራፎርድ በጥሩ የዝውውር መስኮት ለመመለስ አስበዋል:: (sun)
:
¤የቼልሲው አማካይ ጆን ኦቢ ሚካኤል እንደተናገረው ከሌላ ክለብ ጋር በጥሩ ዝውውር እነጋገራለው አሁን በእስታምፎርድ ብርጅ ያለኛ ኮንትራት በዚሂ ሲዝን ያልቃል ብሉዋል:: (goal)
:
¤ዌስትሀም ፈረንሳያዊውን የመስመር ተጫዋች ዲሚትሪ ፓዬትን PSG እና ማድሪድ ስለ ወደፊቱ ለማውራት ቢፈልጉም ውድቅ አድርገውባቸዋል:: (squawka)
:
¤የዩናይትዱ የመስመር ተጫዋች አንቶኒዮ ማርሻል እሁድ በዋትፎርድ 3-1 ሲሸነፉ በጭንቅላት መጋጨት ምክንያት ተጎድቶ ከሜዳ ወቶ ነበር ነገር ግን የ 20 አመቱ ፈረንሳያዋዊ እንደተናገረው በጥሩ ሁኔታ በማገገም ላይ እገኛለው ብሉዋል:: (mirror)
:
¤በፔፔ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የአርሰናሉን ተከላካይ የሄክተር ቤላሪን የኮንትራት ሁኔታ እየተከታተሉ ይገኛሉ ተጫዋቹን ወደ ኢትሀድ ለማምጣት:: (mirror)
:
¤ኢንተር ሚላን ዲያጎ ሲሞኔን ወደ ሳንሴሮ ማምጣት ይፈልጋሉ እስከ 2018 በቪሴንቴ ካልዴሮን የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም ኢንተሮች ከወዲሁ አስፈርመውት መጠበቅ ይፈልጋሉ:: (AS)
:
¤ማንችስተር ዩናይትድ አሁንም ከሊውስ ቫንሀል ሀንጎቨር አልነቃም ብለዋል ጆሴ ሞሪኒዮ:: (mirror)
:
¤የማንችስተር ሲቲው ተጫዋች ጉንዶጋን የርገን ክሎፕ ምርጥ እና አስገራሚ አሰልጣኝ ነው ነገር ግን ፔፔ ጋርዲዮላ ጂኒየስ ነው በማለት ተናግሯል:: (four two)
:
¤ ፔፔ ጋርዲዮላ ሳኔ ቀጣይ ከስዋንሲ ጋር ባላቸው ጨዋታ ላይ ሙሉ ለሙሉ ይሰለፋል በማለት ተናግሯል:: (manchster evening)
:
¤ የቶተንሀሙ ተጫዋች ዴሊ አሊ በቶተንሀም የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል
:
¤የሪያድ ማድሪዱ ተጫዋች ጀምስ ሮድሪጌዝ የልጅነት አይዶል ተጫዋቼ ዚነዲን ዚዳን ነው በማለት ተናግሯል:: (as)
:
¤የቀድሞ የቸልሲ ተጫዋች ማካሌሌ የቸልሲውን የመሀል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ የአለማችን ምርጡ ተጫዋች ነው በማለት አሞግሶታል:: (mirror)
:
¤ሪፖርቶች እንደሚገልፁት ከሆነ ማንችስተር ዩናይትድ እሁድ ዕለት ስፖርቲንግሊዝበን ከ rio ave በነበረው ጫወታ መልማዮቹን ልኮ የፖርቹጋላዊውን አማካይ የዊልያም ካርቫሮን አቅም ተመልክተዋል:: (Abola)
:
¤አርሰናል እና ሌስተር ሲቲ የላስ ፓልማሱን አማካይ roque mesaን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ሁለቱም ክለቦች የ 27 አመቱን አማካይ የማግኘት እድል አላቸው:: (cadena copa)
¤ማንችስተር ሲቲ በክረምት ያያ ቱሬን የመሸጥ እድል አጊንተው ውድቅ አድርገዋል:: (mirror)
:
¤አርሰን ቬንገር በሊግ ካፕ ኖቲንጋሀምን 4-0 ካሸነፉ ቡኃላ ስለኒኮላስ ቤንድትለር አስተያየት ሰተዋል እሱ ለክለቡ ታማኝ ተጫዋች ነው አሁንም ሙሉ አቅም አለው ገና 28 አመቱ ነው ወደ ቀድሞ ቶፕ አቁዋሙ ይመለሳል ብዬ አምናለው ብለዋል ::
:

¤ሊዮኖቺ ከሊቨርፑል በነፃ ዝውውር ኒስን የተቀላቀለውን ማርዮ ባላቶሊን ማዘዋወር ይፈልጋሉ::

¤የቦርሲያ ዶርትመንዱ አማካይ ማርዮ ጎትዜ በባየርሙኒክ ያልተሳካ ግዜን አሳልፏል ማለት አይቻል ብሉዋል ወኪሉ::

¤አርጀንቲናዊው አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ አንድም ቀን ከኢንተር ለመውጣት አስቤ አላውቅም ብሉዋል::

¤ፔፔ ጋርዲዮላ በያያ ቱሬ እና በወኪሉ ደስተኛ አደለም:: ጋርዲዮላም ያያ ቱሬ ማሰልፈው ዲሚትሪ ሴሉክ እኔን እና የቡድኑ ተጫዋቾችን ይቅርታ ሲጠይቅ ነው ብለዋል::

Photos 02/09/2016

Happy New Year!!!

Photos 28/08/2016

የትምህርት ጥራት...

ከስልካችን ላይ ፎቶ, ቪዲዮ, ኦዲዮ ተሳስተን ዲሌት ብናደርግ በዚህ መሰረት መልሰን ማግኘት እንችላለን 18/06/2016

ከስልካችን ላይ ፎቶ, ቪዲዮ, ኦዲዮ ተሳስተን ዲሌት ብናደርግ በዚህ መሰረት መልሰን ማግኘት እንችላለን ከስልካችን ላይ ፎቶ, ቪዲዮ, ኦዲዮ ተሳስተን ዲሌት ብናደርግ በዚህ መረጃ መሰረት በቀላሉ መልሰን ማግኘት እንችላለንከስልካችን ላይ ፎቶ, ቪዲዮ, ኦዲዮ ተሳስተን ዲሌት ብናደርግ በዚህ መሰረት መልሰን ማግኘት እንችላለን

Photos from Euro Cup Amharic News's post 09/06/2016

ውድ የፔጃችን ታዳሚዎች እነሆ የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ሰአታት እድሜ ቀርቶታል እነሆ በቃላችን መሰረት ስለ አውሮፓ ዋንጫ በሰፊው እናወራለን። ታዲያ ዛሬ በዚህኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ዳሰሳ ሰፋ ባለና ባማረ አቀራረብ ይዘን መተናል አብራቹን ቆዩ።
ሁሌም ፖስቶቹን ላይክ ሳያደርጉ አይለፉ።
ላይክ ማድረጋችሁ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለናንተም እንዲደርሳችሁ ነው።
✡✡✡የዩሮ 2016 የምድብ ዳሰሳ✡✡✡
✡✡✡[ምድብ አንድ ]✡✡✡
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
❀✿❀✿❀✿❀✿
ይህ ምድብ አዘጋጇ ፈረንሳይን የያዘ ምድብ ሲሆን በተጨማሪም ሩማንያ ፣አልባኒያና ሲውዘርላንድ የምድቡ ተፎካካሪዎች ናቸው፡፡
# ፈረንሳይ
የዩሮ 2000 እና ዩሮ 1984 ሻምፒዮን በመሆን ለሁለት ጊዜያት ያህል የአውሮፓ ንግስናን ያሳካችው ፈረንሳይ ከሜዳ ውጪ እየተከሰቱ ያሉ ጉዳዮች እየረበሿት ይገኛሉ፡፡የካሪም ቤንዜማን ከተጫዋች ዝርዝር መውጣት ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰጡ ሲሆን ከቫልቡኤና ጋር በተያያዘው የወሲብ ቪድዮ ቅሌት ምክንያት ሳይሆን በአሰልጣኙ የዘረኝነት ችግር ምክንያት ነው የተቀነሰው የሚል ሀሳብ እያየለ መምጣቱ በቡድኑ ውስጥ ያለውን የአንድነት መንፈስ እንዳይረብሸው ያሰጋል፡፡ ከዚህ በፊት የ 1984 የአውሮፓ ዋንጫንና የ 1998 የዓለም ዋንጫን በማሰናዳት እዛው ያስቀረችው ፈረንሳይ በዚህም የአውሮፓ ዋንጫ በደጋፊዎቿ ፊት መጫወቷ ዋንጫውን ለማሸነፍ በትልቁ እንደሚረዳት ይጠበቃል፡፡ የአማካይ ክፍሉ የቡድኑ ዋነኛ ጥንካሬ ሲሆን በአለም እግር ኳስ ላይ ትልቅ ስም ካላቸው ወጣት አማካዮች ዋነኛው በሆነው ፖል ፖግባ ይመራል፡፡ በተጨማሪም በውድድር አመቱ ምርጥ ብቃት ማሳየት የቻሉት ብሊስ ማቱዲ ፣ አንቶኒ ማርሻል ፣ ሁጎ ሎሪስ ፣ አንቶኒ ግሪዝማንና የመሳሰሉት ተጫዋቾች በከፍተኛ ደረጃ ተጠባቂ የሆኑ ናቸው፡፡
# ሩማንያ
ከኦስትሪያና ሲውዘርላንዱ የዩሮ 2008 ተሳትፎ በዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በትልቅ ውድድር መድረክ የቀረበችው ሩማንያ በማጣሪያው የደረሳት ቀለል ያለ ምድብ ለዚህ ተሳትፎ እንዳበቃት ትታማለች፡፡ የጆርጅ
ሀጂዋ አገር ሩማንያ በማጣሪያው ሁለት ጎሎችን ብቻ
ያስተናገደ ጥሩ የተከላካይ ክፍል አላት ፤ ቡድኑ በባለልምዱ የ 34 ዓመት ተጫዋች ራዝቫን ራት የሚመራ ሲሆን ከጆርጅ ሀጂ በዋላ ለአገሪቱ እግር ኳስ
የተፈጠረው ትልቅ ተስዕጦ የሚባልለት ሉቺያን ሳንማርቲን ተጠባቂ ተጫዋቿ ነው፡፡የቡድኑ አሰልጣኝ በጆርጅ ሀጂ በተመራው የሮማንያ ወርቃማ ትውልድ አባል የነበረው አንሄል ኢዮርዳኔሹ ብሔራዊ ቡድኑን ከመያዙ በፊት የፖለቲካ ተሳትፎ የነበረው ሲሆን በአገር አቀፉ ሴኔት ውስጥም መቀመጫ ነበረው፡፡
# አልባኒያ
ትንሿ የባልካን አገር አልባኒያ ከኮሚኒዝም ስርዓት መውደቅና ከሶቭየት መፈራረስ በዋላ
ለመጀመሪያ ጊዜ በትልቅ የእግር ኳስ መድረክ ለመቅረብ የተሰናዳች ሲሆን ማጣርያውን
ባለፈችበት ቅጽበት በአገሪቱ የነበረው የደስታ አገላለጽ የተለየ ነበር፡፡ ለፈረንሳዩ ናንትስ የሚጫወተውና ከዛ
በፊት በፒ ኤስ ጂ፣ ማርሴይ ፣ ጋላታሳራይ ፣ ሰንደርላንድና ላዚዮ ቆይታ የነበረው ሎሪክ ካና የቡድኑ
አምበልና የተከላካይ ክፍሉ ልብ ሲሆን በዚህ ሻምፒዮና ለአገሩ የቻለውን ሁሉ ከማድረግ እንደማይቆጠብ ሲናገር ተስተውሏል፡፡
ሌላኛው በጣልያን ሁለተኛ ዲቪዝዮን ለፔስካራ የሚጫወተውና ታታሪነት መለያው የሖነው ሌዲያን ሜሙሻይ ለአልባኒያ ተስፋ መጣያ ነው፡፡ የቡድኑ አሰልጣኝ ጣልያናዊው ጂዮቫኒ ደ ቢያሲ ሲሆን ቡድኑን ከያዘበት የዛሬ አምስት አመቱ ጀምሮ በአገሩ ላይ በዘረጋው ዘመናዊ የእግር ኳስ በተመልካቾችና በተጫዋቾች ይወደሳል፡፡ ሆኖም ልምድ በሌላቸው ተጫዋቾቹ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ተቋቁሞለተሻለ ውጤት መብቃቱ አጠራጣሪ ነው፡፡
# ስዊዘርላንድ
ከስምንት አመት በፊት የተካሄደውን የዩሮ 2008 ከኦስትሪያ ጋር በጥምረት አሰናድታ የነበረችው ስዊዘርላንድ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምድቧ የምታልፍበትን ዕድል ለማሳካት ተስፋ ሰንቃለች፡፡ በአሰልጣኝ ቭላድሚር ፔትኮቪች አመራር የሚታይ እመርታና ለውጥ ያመጣችው ሲውዘርላንድ በፊፋ የአገራት የደርጃ ሰንጠረዥ ምርጥ ሀያዎቹ ውስጥ እስከመካተት ደርሳለች፡፡ በባየርን ሙኒክና ኢንተር ሚላን የተጫወተውና በአለም ዋንጫ ላይ ሁለት ጊዜ አገሩን የመወከል ልምድ ያለው ዤርዳን ሻኪሪ የአገሪቱ ምርጥ ተጫዋች ነው፡፡ ይህን የውድድር አመት በእንግሊዝ ስቶክ ሲቲ ያሳለፈው ተጫዋቹ በሻምፒዮናው አገሩን ለተለየ ክብር ያበቃል የሚል እምነት የብዙ ሲውዘርላንዳውያን ነው፡፡ ሌላኛው ተጠቃሽ ደግሞ በጀርመን ቡንደስ ሊጋ የሚጫወተውና በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከታላላቆቹ ክለቦች አንዱን እንደሚቀላቀል የሚጠበቀው ሪካርዶ ሮድሪጌዝ
ለሲውዝ እምቅ ኃይል ነው፡፡

✡✡✡ [ ምድብ ሁለት ]✡✡✡
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
❀✿❀✿❀✿❀✿❀
የብሪታንያ ደርቢ በእንግሊዝና በዌልስ መካከል የሚካሄድበት ይህ ምድብ በተጨማሪም ስሎቫኪያና ሩሲያ ይፎካከሩበታል፡፡
# እንግሊዝ
ከ 20 ዓመታት በፊት ራሷ ባዘጋጀችው የዩሮ 1996 ላይ ያሳካችው ግማሽ ፍጻሜ የውድድሩ ከፍተኛ ውጤቷ ነው ፤ ለበርካታ ጊዜያት በውድድሩ ተጠባቂ ሆና ከሄደች በዋላ በደካማ ውጤቶች ስትመለስ የቆየችው እንግሊዝ ድልና ዝናን በተራቡ ኮከቦቿ ተስፋ አድርጋ ተዘጋጅታለች፡፡ በውድድር አመቱ ምርጥ ብቃታቸውን ማሳየት በቻሉ ወጣቶች የተሞላችውእንግሊዝ የተከላካይ ክፍሏ ድክመት ዋጋ እንዳያስከፍላት ያሰጋል፡፡ ሆኖም ከተከላካዮቹ ፊት ለፊት በአማካይ ተከላካ ስፍራ የሚጫወተው ኤሪክ ዳየር ይህን ክፍተት በሚገባ ይደፍነዋል የሚል እምነት በእንግሊዛውያን ዘንድ አለ፡፡ በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ በጋራ 49 ጎሎችን ማምረት የቻሉት አጥቂዎቿ ሀሪ ኬንና ጂሚ ቫርዲ የቡድኑ ፊት አውራሪዎች ሲሆኑ በውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታዎች በአማካይ ስፍራ ላይ የተሻለ መንቀሳቀስ የቻለው ዌይን ሩኒ ከወጣቱ ዴሊ አሊ በመሆን የቡድኑን የማጥቃት ኃይል የመጨመር ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጫዋቾች
ምርጫቸው ከፍተኛ ትችትና ቅሬታን ያስተናገዱት አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን የተቺዎቻቸውን አፍ ለማዘጋት በመረጧቸው ተጫዋቾቻቸው ላይ ተስፋን ሰንቀዋል፡፡ራሄም ስተርሊንግ ፣ ጀምስ ሚልነር ክሪስ ስሞሊንግና ሌሎቹም አገራቸውን በታሪክ የማጻፍ ትልምን አንግበው ፈረንሳይ ላይ ይከትማሉ፡፡
# ሩስያ
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት የተመዘገቡ ውጤቶች ሁሉ በሩስያ ስም እንዲቀየሩ ከወሰነ በዋላ የ 1960ውን የመጀመሪያ የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮንነት ጨምሮ ሶስት ጊዜ የፍጻሜ ተፋላሚ እና ሁለት ጊዜ ደግሞ የግማሽ ፍጻሜ ተካፋይ በመሆን የሚያኮራ ታሪክ ያላት ሩስያ ማጣሪያውን ሁለት ጊዜ ብቻ አቻ ወጥታ ምንም ሳትሸነፍ ጨርሳለች፡፡
በአንጋፋ ተጫዋቾች የተሞላው የተከላካይ ክፍሏ ዋጋ እንደሚያስከፍላት ቢያሰጋም የፊት አጥቂው አርተም ዚዩባ መተማመኛዋ ነው፡፡ በተጨማሪም የጨዋታ አቀጣጣዩ ሮማን ሺሮኮቭ ቡድኑን ቢያንስ ወደቀጣዩ
ዙር የማሳለፍ ስኬትን በማስመዝገብ ይረዳታል የሚል ግምት አለ፡፡ የተከላካይ ክፍሉ በቀድሞው የቸልሲ ተጫዋች ዩሪ ዚርኮቭ የሚመራ ሲሆን ጠንካራው ግብ ጠባቂ አኪንፊቭ በሁለቱ ብረቶች መሀል ቆሞ አገሩን የሚወክል ይሆናል፡፡
# ስሎቫኪያ
በዚህ ውድድር ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስመዘግቡ የሚችሉበት ዕድል እንዳላቸው የተወራላቸው ስሎቫኪያዎች በማጣሪያው ስፔንና ዩክሬንን ማሸነፍ
መቻላቸው ግምቱን እንዲያገኙ አስችሏል፡፡ ነጻ አገር ከሆነች በዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ዋንጫ የመሳተፍ እድልን ያገኘችው ስሎቫኪያ በናፖሊው የመሀል ሜዳ ኮከብ ማሬክ ሀምሲክ ትልቁን ኃላፊነት
ጥላለች፡፡ የቡድኑ ጠንጋራ ጎን የተከላካይ ክፍሉ ሲሆን
የሚመራውም በሊቨርፑሉ ስከርትል ነው፡፡
# ዌልስ
በክሪስ ኮልማን አመራር ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ዋንጫ ያለፈችውና ከ 1958 የዓለም ዋንጫ በዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በትልቅ ውድድር የመሳተፍ አጋጣሚውን ያገኘችው ዌልስ ሌላኛዋ የሻምፒዮናው
አስደናቂ አገር የመሆን ግምት ያገኘች ሆናለች፡፡ በማጣሪያው ከቤልጅየም ጋር ተደልድላ የነበረችውና የነሀዛርድና ሉካኩን አገር በሁለቱም ጨዋታ መቋቋም
የቻለችው ዌልስ የዚህ ትልቅ ጨዋታን የመቋቋም ልምዷ ከእንግሊዝ ጋር ለምታደርገው የብሪቴን ደርቢ ይረዳታል ተብሎይታሰባል፡፡በጋሬዝ ቤል ላይ ጥገኛ እንደሆነ የሚነገርለት የዌልስ ብሔራዊ ቡድን በማጣሪው ካስቆጠረቻቸው 11 ጎሎች ሰባቱን በቤል አማካኝነት ማግኘቱ የዚህ አስጊ ሁኔታ ማሳያ ነው፡፡ በሊቨርፑሉ ጆ አለንና በአርሰናሉ አሮን ራምሴይ የተገነባው የአማካይ ክፍሏ ወደቀጣዩ ዙር መሸጋገር ካስቻሏት ለዌልስ እንደትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው፡፡

✡✡[ ምድብ ሦስት ]✡✡✡
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
የዓለም ሻምፒዮኖቹ ጀርመናውያን የሚገኙበት ይህ ምድብ በተጨማሪም የሌዋንዶውስኪዋን ፖላንድን ፣ ዩክሬንንና ሰሜን አየርላንድን ያቀፈ ነው፡፡
# ጀርመን
አርጀንቲናን አሸንፈው የዓለም ሻ ምፒዮንነታቸውን ካወጁበት 2014 በዋላ የማሽቆልቆል ምልክቶችን ያሳዩት ጀርመኖች ከሁለት አመት በፊት የነበራቸውን
አስተማማኝ ብቃት ያጡት ይመስላል፡፡ ፊሊፕ ላሀም ፣ ሚሮስላቭ ክሎሰና ፔር ሜርትሳከርን የመሳሰሉት ተጫዋቾች ከአለም ዋንጫው በዋላ ራሳቸው ከብሔራዊ ቡድኑ ያገለሉ ሲሆን አምበሉ ባስቲያን ሸዌይንስታይገርና ወደባየርን የተዘዋወረው ተከላካይ ማትስ ሀመልስ ከጉዳት ጋር እየታገሉ ወደሻምፒዮናው
ተቀላቅለዋል፡፡ በዘንድሮው አመት በቱርክ ቤሽኪታሽ ምርጥ አቋሙን የመለሰው አጥቂ ማሪዮ ጎሜዝ የጎል ማስቆጠር ስራውን የሚወጣ ሲሆን የማርኮ ሪዩስን ጉዳት ተከትሎ እድሉን እንደሚያገኝ የሚጠበቀው አንድሬ ሸርለ አጋጣሚውን እንደሚጠቀምበት ይጠበቃል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአርሰናል ምርጥ ብቃቱን ያሳየው ሜሱት ኦዚል የቡድኑ መሰረት ሲሆን ቶማስ ሙለር ፣ ማኑኤል ኑዌርና ዤሮም ቦአቴንግ የጥንካሬ መገለጫዎቹ ናቸው ፤ የዮሀኪምሎው ጀርመን ከምድቧ ቅለት አንጻር ወደቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሏ የሰፋ እንደሆነ ይታመናል፡፡
# ዩክሬን
በአሰልጣኝ ሚካይሎ ፎሚንኮ የምትመራው ዩክሬን አገሪቱን ያመሳትን ፖለቲካዊቀውስ ተቋቁማ ለውድድሩ የበቃች ሲሆን በ 4-5-1 አሰላለፍ አካላዊ ጥንካሬን መሰረት ባደረገው አጨዋወቷ ትታወቃለች፡፡ ላለፉት አምስት የትልልቅ ውድድሮች ማጣሪያ ላይ እርግማን በሚመስል መልኩ የመጨረሻ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ እየተሸነፈች ከውድድሩ ውጪ ስትሆን የነበረችው ዩክሬን በዚህኛው ግን ስሎቫንያ በጥሎ ማለፉ በማሸነፍ አልፋለች፡፡ ቡድኑ በሲቪያው ድንቅ አማካይ የቨን ኮኖፕሊያንካ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ለዳይናሞ ኪየቭ የሚጫወተው አንድሬይ ያርሞሌንኮ የፊት አውራሪ በመሆን ጎል የማስቆጠሩን ኃላፊነት ይወጣል፡፡
# ፖላንድ
በዚህ ምድብ ጀርመንን ለመፎካከር የተሻለ አቅም ያላት የተባለችው ፖላንድ በአሰልጣኝ አዳም ናዋልካ ትመራለች፡፡ በውድድሩ ማጣሪያ ወቅት ከጀርመን ጋር
በአንድ ምድብ የነበረችው ፖላንድ በሜዳዋ የአለም ሻምፒዮኖቹን በማሸነፍ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ ይሆናታል፡፡ በመልሱ ጨዋታ በጀርመን የደረሰባት ሽንፈት ባለፉት ሁለት አመታት የደረሰባት ብቸኛ ሽንፈት ሲሆን በባየርኑ ኮከብ ሮበርት ሌዋንዶውስኪና በአያክሱ አርካዱዝ ሚሊክ የሚመራው የጥቃት ወረዳዋበማጣሪያው 33 ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ነው፡፡ የቡድኑ ደካማ ጎን የተከላካይ ክፍሉ ሲሆን በማጣሪያው 10 ጎሎችን አ ስተናግደዋል፡፡ የተከላካይ ክፍሉን የመምራት ስራ በቶሪኖው ተከላካይ ከሚል ግሊክ ላይ የወደቀ ሲሆን የሲቪያው ግሪዝጎሪዝ ክሪቶዋይክ ከቡድኑ ከዋክብት አንዱ ነው፡፡
# ሰሜን አየርላንድ
ዝቅተኛ የተሰጣትና በሁለተኛና ሶስተኛ ዲቪዚዮን ተጫዋቾች የተሞላችው ሰሜን አየርላንድ ምናልባትም በከፍተኛ የማሸነፍ ስሜት ተጫውታ ምድቡን በማለፍ
ልታስደንቀን ትችላለች፡፡ የሚካኤል ኦኔሏ ሰሜን አየርላንድ በአካላዊ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ አጨዋወትን የምትተገብር ሲሆን ጎል ላለማስተናገድ የሚደረግ ተጋድሎ መለያዋ ነው፡፡ ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎች በዚህ መልኩ ለመጨረስ
መሞከር ከባድ ቢሆንም እግር ኳስ ነውና ሰሜን አየርላንዳውያንም በከፍተኛ ትጋትና ወኔ አገራቸውን ለመጥቀም ፈረንሳይ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከቡድኑ ኮከብ ተጫዋች እንጥራ ከተባለ በእንግሊዝ ለበርሚንግሀም ሲቲ የሚጫወተውና በማጣሪያው ሰባት ጎሎችን ያስቆጠረው አጥቂ ካየል ላፈርቲ ነው ።
✡✡✡ [ ምድብ አራት ]✡✡✡
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
የምድቡ ኃያል ሻምፒዮኗ ስፔን ስትሆን ቼክ ሪፐብሊክ ፣ ቱርክና ክሮሺያ የሚጋፈጧት ይሆናሉ፡፡
# ስፔን
የምርጥ ተጫዋቾች ባለጸጋ የሆነችው ስፔን በሽግግር ላይ እንደሆነች ቢታመንም አሁንም ምርጥ እና ጥራት ባላቸው ተጫዋቾች የተሞላች ናት፡፡ አሰልጣኝ ቪሴንቴ
ዴል ቦስኬ ለመምረጥ እጅጉን እንደተቸገሩ ባሳበቀ መልኩ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ላይ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ሳይመርጡ ቀርተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ዲዬጎ ኮስታ ፣ ሁዋን ማታ ፣ ዣቪ ማርቲኔዝ ፣ ፈርናንዶ ቶሬስና አንደር ሄሬራ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የዓለምና የአውሮፓ ሻምፒዮን መሆን በቻሉት ነባር ከዋክብትና ድልን በተራቡ አዳዲስ ተጫዋቾች የተገነባው ስፔን በውድድሩ ብዙ ርቀት የመጓዝ አቅም
አለው፡፡ ባለልምዱ አንድሬስ ኢንዬስታ ከባየርኑ ወጣት ቲያጎ አልካንታራ ጋር የመሀል ሜዳ ጥምረት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ የፊት አጥቂነት ሚናውን የአትሌቲኮ ቢልባኦው አሪትዝ አዱሪዝ እንደሚመራው የሚጠበቅ ሲሆን የማንችስተር ዩናይትዱ ዴቪድ ደሂያ የግቡ ዘብ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በጉዳት በተገለለው የቀኝ መስመር ተከላካይ ዳኒ ካራቫያል ቦታ ላይም የአትሌቲኮ ማድሪዱ ታታሪ ተከላካይ ሁዋንፍራን
ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል ፤ የ 2008 እና የ 2012 አውሮፓ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት ስፔናውያን ይህን ዩሮ 2016 ካሳኩ በቀላሉ የማይደፈር ክብረወሰን ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡
# ክሮሺያ
በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ከሩብ ፍጻሜ የዘለለ ታሪክ የሌላት ክሮሺያ የዘንድሮው ቡድኗ ከዛ ያለፈ ውጤት ያመጣል የሚለው እምነት በደጋፊዎች ልብ ተሰንቋል፡፡
በተለያዩ ታላላቅ የመሀል ተጫዋቾች ለተሞላው ቡድናቸው የሚመጥን አሰላለፍ ማግኘት የአሰልጣኝ አንቴ ካሲች ከባዱ ስራ ነው፡፡ በማጣሪያው ላይ ማስቆጠር ከቻሏቸው 20 ጎሎች አንዷን ብቻ በስሙ ያስመዘገበው የጁቬንቱሱ ማሪዮ ማንዙጊች ያለውን አቅም እንዲጠበቅ መርዳት ሌላኛው ኃላፊነታቸው ይሆናል፡፡ ቡድኑ ደረጃቸውን በጠበቁና የትልልቅ ልምድና አቅም ባለቤት በሆኑ አማካዮች የተገነባ ሲሆን የሪል ማድሪዱ ሉካ ሞድሪች የጀርባ አጥንታቸው ነው፡፡ በአመቱ በባርሴሎና ጥሩ ብቃቱን ያሳየው ኢቫን ራኪቲች ሌላኛው ተጠባቂ ሲሆን ፔርሲችና ብሮዞቪች እንዲሁ ለክሮሺያውያን የተስፋ ስንቅ ናቸው፡፡
# ቱርክ
በሻምፒዮናው ማጣሪያ ከቼክ ጋር በአንድ ምድብ ተደልድላ የነበረችው ቱርክ ምድቧን በሶስተኝነት ብትጨርስም በጥሩ 3ኛነት ማለፏ ይታወሳል፡፡ በዋናው
ዩሮ 16 በድጋሚ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር በአንድ ምድብ የተገናኙ ሲሆን ማጣሪያው ላይ አንድ አንድ ጊዜ በመሸናነፋቸው ተመጣጣኝ ፉክክር አንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ የአሰልጣኝ ፋቲህ ተሪም ስብስብ ጥራት ባላቸው ተጫዋቾች የተሞላ ሲሆን በ2008 የአውሮፓ ዋንጫ የደረሱበትን የግማሽ ፍጻሜ ገድል ለመድገም
አልመዋል፡፡ የፊት አጥቂው ቡራክ ይልማዝ በምርጥ አቋሙ ላይ መገኘት የቱርካውያንን የማጥቃት ፍላጎት የሚያነቃቃው ሲሆን የባርሴሎናው አርዳ ቱራን
ያለጥርጥር የአገሪቱ ዋነኛ ኮከብ ነው፡፡ ለጀርመኑ ባየርን ሊቨርኩሰን የሚጫወተውና የታላላቅ ክለቦች ዐይን ማረፊያ የሆነው አማካይ ሀካን ካልሃኖግሉ
በሻምፒዮናው ጎልተው መውጣት እንደሚችሉ ከተነገረላቸው መካከል ሲሆን የቡድኑ ደካማ ጎን የመከላከል ወረዳው ነው፡፡
# ቼክ ሪፐብሊክ
ጥሩና ጤናማ ፉክክር እንደሚኖራቸው ከሚጠበቁት ምድቦች አንዱ በሆነው በዚህ ምድብ የምትገኘው ሌላኛዋ አገር ቼክ ሪፐብሊክ ናት ፡፡ አሰልጣኙ ፓቬል ቨርባ እንደቀድሞው የቼክ ሪፐብሊክ ትውልድ በከዋክብት የተሞላ ቡድን ባያገኙም ለማሸነፍ አዳጋች የሆነውን ቡድን ገንብተዋል፡፡ በቀድሞው ምርጥ ቡድኗ የዩሮ 2004 ሻምፒዮን የመሆን ዕድሏን በግሪክ ምክንያት ያጣችው ቼክ በዚህኛው የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ምድቧን በበላይነት በመጨረስ ለውድድሩ በቅታለች፡፡ ሆኖም በማጣሪያው አንድም ጨዋታ እንኳን ጎል ሳይቆጠርባት መጨረስ አለመቻሏ የተከላካይ ክፍሏ መሻሻል እንደሚያሻውና ለግብ ጠባቂው ፒተር ቼክ የተጠናከረ ሽፋን እንደሚያስፈልገው ማሳያ ነው፡፡ ቶማስ ሮዚስኪ ባለልምዱ ተጫዋቻቸው ሲሆን የፊት አጥቂው በማቴይ ቪያድራና ዴቪድ ላፋታ ላይ ወድቋል፡፡ በአማካይ ስፍራ ላይ ቭላድሚር ዳሪዳ የጨዋታ አቀጣጣይነት ሚናውን ይወጣል፡፡

✡✡✡ [ ምድብ አምስት ]✡✡✡
✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
❀✿❀✿❀✿❀✿❀✿
የሞት ምድብ በተባለለት በዚህ ምድብ በከዋክብት የተሞላችው ቤልጅየም ፣ ጠንካራዋ ጣልያን ፣ እንዲሁም ስውዲንና አየርላንድ ይገኛሉ፡፡
# ቤልጅየም
ቀያዮቹ ቤልጅየማውያን ከምንጊዜውም በተሻለ በምርጥና ባለልምድ ተጫዋቾች
የታጀበ ምርጥ ስብስብ የያዘ ሲሆን የ 2014 የዓለም ዋንጫ መጥፎ ትውስታን ለመቀየር ዕድሉ ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ኤደን ሃዛርድ ፣ ኬቨን ደ ብሩይን ፣ሮሜሎ ሉካኩና ቲቡ ኮርቱዋ የመሳሰሉ ተጫዋቾችን የያዘችውና የከዋክብት እጥረት የሌለባት ቤልጅየም እነዚህን ምርጥ ተጫዋቾች አቀናብሮ ምርጥ ቡድን የመስራትን ቀመር ማግኘት ለአሰልጣኝ ማርክ ዊልሞት ከባዱ የቤት ስራ ነው፡፡ የመሐል ተከላካዮቹ ቪንሰንት ኮምፓኒና ቶማስ ቨርማለን ፣ እንዲሁም የመስመር
ተከላካዮቹ አልደርዊልድና ዣን ቬርቶኸን በወረቀት ላይ አስደናቂ የተከላካይ መስመር ጥምረት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ሆኖም የኮምፓኒ በጉዳት መገለልና የቶማስ ቨርማለን በውጣ ውረድ የተሞላ የውድድር ዓመት የተከላካይ ክፍሉን ማሳሳቱ የማይቀር ሲሆን በሻምፒዮናውም የአገሪቱ ድክመት እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ለዩሮ 16 ከፍተኛ ግምትን ካገኙ አገራት አንዱ ከሆነው ቡድናቸው ድልን የሚጠብቁ ቤልጅማውያን ቁጥር ጥቂት አይደለም ፤ በአራት ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ ተሳትፎአቸው በ 1980ው ሻምፒዮና ለፍጻሜ የቀረቡበት ምርጥ ውጤታቸው ሲሆን የ 1972 እንዲሁም የ ዩሮ 2000 አዘጋጅ መሆን ችለው ነበር፡፡
# ጣልያን
በረጅም ጊዜ የውድድሩ ተሳትፎዋ አንድ ጊዜ ብቻ (በ 1968) ሻምፒዮን የሆነችው ጣልያን ከአራት አመት በፊት በተካሄደው የዩሮ 2012 የፍጻሜ ተፋላሚ ነበረች፤ ከወትሮው በተለየ ብዙም ነጥረው የወጡ ከዋክብትን በቡድኗ ባታካትትም ለአመታት የሚታው በትልልቅ ሻምፒዮናዎች ላይ የሚፈጠር ጠንካራ የአሸናፊነት መንፈስ በዘንድሮውም ውድድር ጣልያንን ብዙ ሊያስጉዛት ይችላል፡፡ከሻምፒዮናው መጠናቀቅ
በዋላ የቼልሲ ኃላፊነትን የሚረከቡት አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ባማረ አጨራረስ ብሔራዊ ቡድኑን ለመልቀቅ ያለመ ይመስላል፡፡ በጆርጂዮ ቼሊኒ እና ሊዮናርዶ ቦኖቺ የተገነባው የመከላከል ወረዳ የቡድኑ ጥንካሬ ቢሆንም ጠንካራው የአንድነት መንፈሱ ግን ረጅም ርቀት ሊያስኬዳት የሚችል ቁልፍ ነው፡፡ በሚቀጥለው የ 2018 የዓለም ዋንጫ 40 አመት የሚሞላው አንጋፋው ግብ ጠባቂ ጂያንሉዊጂ ቡፎን
ምናልባትም የመጨረሻው ትልቅ ውድድሩ ሊሆን ይችላል፡፡
# ስዊዲን
በዚህ ሻምፒዮና የተለየ ግምት ባታገኝም ምርጥ የውድድር አመትን ባሳለፈ አጥቂዋ ዝላታን ኢብራሂሞቪች እገዛ ለተሻለ ውጤት ልትበቃ ትችላለች ተብሎ ይገመታል፡፡ ራሷ ካስተናገደችው ዩሮ 1992 በዋላ ከሩብ ፍጻሜ ተሻግራ የማታውቀው ሲውድን
በተጨማሪም ያለፉት ሁለት የአለም ዋንጫዎች አምልጠዋታል፡፡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ሀምረን የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ የሚወራለት ጠንካራ ጎኑ በ 34 አመቱ
ዝላታን የሚመራው የአጥቂ ክፍሏ ሲሆን በማጣሪያው ወቅት ያሳየውን ድንቅ ብቃት መድገም ከቻለ በፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ 35ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ አገሩን ከፍ ወዳለ ደረጃ ሊያበቃ ይችላል፡፡
# አየርላንድ
በመጨረሻው የማጣሪያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ( play off ) ቦስኒያን 2 ለ0 በማሸነፍ ወደውድድሩ ያለፈችው አየርላንድ በቀደመው ዩሮ 2012 ተሳታፊ የነበረች
ሲሆን ምድቧን ማለፍ ግን አልቻለችም፡፡ ባሰለጠኗቸው ክለቦች በውጤታማነት የሚታወቁት
ማርቲን ኦኔል የቡድኑ አሰልጣኝ ሲሆኑ በአውሮፓው ዋንጫ ላይም ይህን ውጤታማነት
እንዲያስቀጥሉ የአየርላንዳውያን ምኞት ነው፡፡ቡድኑ ጎልቶ የወጣ ኮከብ ባይኖረውም በበርካታ ባለጥሩ ብቃት ተጫዋቾች የተሞላ እንደመሆኑ ወደቀጣዩ ዙር
ለማለፍ የቤልጅየምና የጣልያን ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ከስውዲን ጋር እንደማድረጉ ያንን ጨዋታ በድል መወጣት ከቻሉ የማለፍ እድላቸውን ማስፋት ይችላሉ::

✡✡✡[ምድብ ስድስት]✡✡✡
የክርስቲያኖ ሮናልዶዋ ፖርቱጋል የምድቡ አባት ስትሆን አይስላንድ ፣ ሀንጋሪና ኦስትሪያ ሌሎቹ ተፎካካሪ ናቸው፡፡
# ፖርቱጋል
ከአራት አመታት በፊት በተካሄደው 14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ከጀርመን ፣ ከዴንማርክና ከኔዘርላንድ ጋር በከባድ ምድብ ተደልድላ የነበረችው ፖርቱጋል በዘንድሮ እድሏ የተካሰች ይመስላል፡፡ በቤልጅየምና ሀፐላንዱ ዩሮ 2000 ሳትጠበቅ በምርጥ ብቃት ታጅባ ለግማሽ ፍጻሜው መብቃት የቻለችውና በቀጣዩ ዩሮ 2004 በራሷ አስተናጋጅነት ፍጻሜን አሳክታ የነበረችው ፖርቹጋል ለዘንድሮው ስኬቷ የሶስት ጊዜው የዓለም ኮከብ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምርጥ እንቅስቃሴ የግድ አስፈላጊ ይሆንባታል፤ ሮናልዶ በአምበልነት በሚመራው በዚህ ስብስብ በፔፔና በ ብሩኖ አልቬስ የተገነባው የተከላካይ ክፍል የተሻለ አቅም ያለው ሲሆን ለፈርናንዶ ሳንቶሱ ቡድን የጥንካሬ መሰረት ነው፡፡ በማጣሪያው ላይ በምርጥ ብቃት ከምድባቸው መሪ ሆነው ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደቀድሞው አቋሙ የመመለስ ምልክቶችን እያሳየ ያለው ሪካርዶ ኳሬዝማ እንዲሁም የቀድሞው
የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጫዋች ሉዊስ ናኒ ሌሎቹ ተጠባቂ ተጫወቾች ናቸው፡፡ ቡድኑ ይህን ምድብ ቀዳሚ ሆኖ የመጨረስ ብቃቱ ያለው ቢሆንም
ከከባዱና ቤልጅየም ፣ ጣልያን ፣ስውዲንና አየርላንድን ካቀፈው ምድብ አምስት የሁለተኛ ደረጃ አገር ጋር የመጫወት ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡ አይስላንድ ምንም እንኳን በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሳተፉም ሚጢጢዋን አይስላንድ ዝቅ አድርጎ መመልከት ከስህተት ሊዳርግ ይችላል፡፡ እነ አርያን ሮበን ፣ ሮበን ቫንፐርሲንና ሜምፊስ ዴፓይን የመሳሰሉ
ሆላንዳውያንን ሻምፒዮናውን በቴሌቭዥን እንዲከታተሉ ያስገደደ ውጤትን በማጣርያው ያስመዘገቡ ናቸው፤ ሁለት ጊዜ ሆላንድን ማሸነፍ ከመቻላቸው ካደረጉት 10 የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች በስድስቱ ጎል ሳይቆጠርባት መውጣት የቻለች ጠንካራ ቡድን ናት፡፡ በተከላካይ ክፍል ጥንካሬው የሚታወቀው ይህ ቡድን ሬንጀር ሲጉርሰን
የተከላካይ አመራርነት እንዲሁም በስዋንሲ ሲቲው የቅጣት ምት ስፔሻሊስት ጊልፊ ሲጉርሰን ጨዋታ አቀጣጣይነት ወደሜዳ ይገባል፡፡ የቀድሞው ዝነኛ የባርሴሎናና የቼልሲ አይቂ ኤይዶር ጉድዮንሰን የፊት
አጥቂነት ሚናውን እደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ በቀድሞው የስውድን አሰልጣኝ ሀንስ ላገርባክ የምትመራው አይስላንድ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከፖርቱጋል ጋር የምታደርግ ሲሆን ከጨዋታው ነጥብ የምታገኝ ከሆነ ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርላታል፡፡ ሀንጋሪ በጥሎማለፍ ማጣሪያው ኖርዌይን ጥለው ለዚህ ቢበቁም ምድቡን ተቋቁመው ያልፋሉ የሚለው ግምት አናሳ ነው፡፡ በቀድሞው የጀርመን ተጫዋች በርናድ ስቶርክ የሚሰለጥነው የሀንጋሪ ብሄራዊ ቡድን ምናልባትም ምድቡን በሶስተኝነት ጨርሶ በጥሩ ሶስተኝነት የማለፍ ዕድል
ሊኖራት እንደሚችል ይጠቀሳል፡፡ ቡድኑ በተለያየ ቅርጽና ተቀያያሪ የአሰላለፍ ዘይቤው የሚታወቅ ሲሆን የቀድሞው የፉልሀም ተጫዋች አንጋፋው ዞልታን ጌራ አሁንም ለቡድኑ ምርጥ ግልጋሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ሌላኛው ምርጥ ተጫዋቻቸው ባላዝ ሱድዝሳክ የሚባል ሲሆን በግል ክእሎቱና ጨዋታ አቀጣጣይነቱ የታወቀ ነው፡፡ኦስትሪያ በዚህ ሻምፒዮና ሳይጠበቁ አስገራሚ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ የሚል ግምት ከተሰጣቸው አገራት ግንባር ቀደሙ የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ነው፡፡በማጣርያው ምንም አይነት ሽንፈት ያላስተናገዱ ሲሆን አንድነትና ቡድናዊ ስሜት የቡድኑ መገለጫ ነው፡፡ በጋራ መከላከልና አስገራሚ የመልሶ ማጥቃት ቡድኑ የሚከተለው ዘይቤ ሲሆን ይህ አጨዋወቱ ለብዙዎች ስጋት አድርጎታል፡፡ በቡድኖ ንጅጉን ጎልቶ የወጣ ኮከብ አለመገኘቱ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ያመዘነ ይመስላል፤ 11 ተጫዋቾች እንደ ቡድን ሜዳ ላይ ከፍ ባለ ወኔ የሚጫወቱ ሲሆን ለዚህም
ባለፉት አራት አመታት በቡድኑ ላይ እምብዛም ለውጥ ሳደረግበት አብረው መቆየታቸው እንደረዳቸው ይታመናል፡፡ አለማችን ላይ ካሉ ምርጥና ወጣት ተስፈኞች ዋነኛ የሆነው የባየርን ሙኒኩ ዴቪድ አላባ ከፍተኛ ግምት ያገኘ ሲሆን ግዙፉ አጥቂ ማርክ ጄንኮ የፈት መስመር ኃላፊነቱን ይረከባል፡፡ ጄንኮ በማጣርያው ወቅት ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ከምርጥ አስቆጣሪዎች አንዱ የነበረ ሲሆን ይህን ብቃቱን ፈረንሳ ላ መድገም ከቻለ ለተከላካዮች ራስ ምታት መሆኑ አይቀርም፡፡
# በ15ኛውየአውሮፓዋንጫ አውነታዎች
# Euro2016
♠ ለአስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ 24 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ተመድቧል፡፡
♠ ከ90ሺ በላይ የፀጥታ ኃይሎች ይሰማራሉ፡፡
♠ እስከ 1.49 ቢሊዮን ዩሮ መዋዕለ ንዋይ ይንቀሳቀሳል፡፡
♠ 301 ሚሊዮን ዩሮ የሽልማት ገንዘብ ቀርቧል፡፡
♠ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እስከ 500 ሚሊዮን ዩሮ ትርፍ ይጠበቃል፡፡
♠ የሚሳተፉት 552 ተጨዋቾች እስከ 4.72 ቢሊዮን ዩሮ የዋጋ ተመን አላቸው፡፡
♠ 1 ጨዋታ በአማካይ 150 ሚሊዮን ተመልካች በዓለም ዙርያ ያገኛል፡፡
♠ 15ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አዘጋጇ ፈረንሳይ ከሮማንያ በስታድ ደ ፍራንስ በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል፡፡
♠ ፈረንሳይ የአውሮፓ ዋንጫን የምታስተናግደው በውድድሩ ታሪክ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን ሁለቱን ያስተናገደችው በ1960 እኤአ እና በ1984 እኤአ ነበር፡፡
♠ የአሜሪካ መንግስት የአውሮፓ ዋንጫው ለሽብር ጥቃት የተጋለጠ መሆኑን ከወር በፊት ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ አዘጋጇ ፈረንሳይ 51 ግጥሚያዎች በሚካሄድባቸው 10 ከተሞች እና 10 ስታድዬሞች ከ90ሺ በላይ የፀጥታ ኃይል በማሰማራት ከፍተኛ ጥበቃ እና ክትትል ታደርጋለች፡፡
♠ የአውሮፓ ዋንጫውን ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች በስታድዬሞች በመገኘት እንደሚከታተሉት የሚጠበቅ ሲሆን 1.5 ሚሊዮን ያህሉ በእንግድነት በፈረንሳይ የተለያዩ ከተሞች የሚገቡ ቱሪስቶች ናቸው፡፡
♠ የፈረንሳይ መንግስት በአገሪቱ ያለውን ፀጥታ ለማጠናከር ሲተገብር የቆየውን ልዩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአውሮፓ ዋንጫውም ላይም እንደሚቀጥል ያመለከተ ሲሆን ለአስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ 24
ሚሊዮን ዩሮ በጀት መመደቡን ለማወቅ ተችሏል ፡፡
♠ ፈረንሳይ 15ኛውን የአውሮፓ ዋንጫ እንድታስተናግድ የተመረጠችው ከ6 ዓመታት በፊት ሲሆን ጣሊያንና ቱርክ መስተንግዶውን ለማግኘት ተፎካካሪዎቿ ነበሩ፡፡
♠ የአውሮፓ ዋንጫውን በ10 የፈረንሳይ ከተሞች ቦርዶ፤ ሌንስ፤ ሊል፤ ሊዮን፤ ማርሴይ፤ ኒስ፤ ፓሪስ፤ ሴንት ዴኒስ፤ ሴንት ኢተንና ቱሉስ የሚገኙ 10 ስታድዬሞች የሚስተናገድ ሲሆን ሁሉንም ስታድዬሞች በአዲስ መልክ በመገንባት በማደስ እስከ 1.6 ቢሊዮን ዩሮ ወጭ ተደርጓል፡፡
♠ 15ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በ24 ቡድኖች መካከል መካሄዱ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሆን፤ ለመጀመርያ ጊዜ የሚሳተፉት አምስት አገራት አልባንያ፤ አይስላንድ፤ ሰሜን አየርላንድ ፤ ስሎቫኪያ እና ዌልስ ናቸው፡፡
♠ ተሳታፊዎቹ 24 ብሄራዊ ቡድኖች በ6 ምድቦች የተደለደሉ ሲሆን ከየምድቡ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ የሚያገኙት እንዲሁም ከስድስቱ ምድቦች ጥሩ ሶስተኛ የሆኑት 4 ብሄራዊ ቡድኖች ወደ ጥሎ ማለፍ ምእራፍ
ይሸጋገራሉ፡፡
♠ አዘጋጇ ፈረንሳይ፤ 13ኛውና 14ኛውን የአውሮፓ ዋንጫዎችን በተከታታይ ያሸነፈችው ስፔን፤የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመንና በአዲስ ትውልድ የተዋቀረው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድኖች ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት ያገኙ ሲሆን በርካታ ምርጥ ተጨዋቾችን ያሰባሰበው የቤልጅዬም ብሄራዊ ቡድንም ለዋንጫው ፉክክሩ የታጨ ሆኗል፡፡
♠ የአውሮፓ ዋንጫው ላይ በርካታ ምርጥ ብቃት ያላቸው አጥቂዎች በብዛት በመኖራቸው በጎሎች ብዛት እንደሚደምቅም ግምት አለ፡፡ በተለይ በኮከብ ግብ አግቢነቱ ፉክክር ደግሞ የጀርመኑ ቶማስ ሙለር፤ የፈረንሳዩ አንቶኒ ግሪዝማን፤ የፖርቱጋሉ ክርስትያኖ ሮናልዶ፤ የእንግሊዙ ሃሪ ኬን እንዲሁም የፖላንዱ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ እንደሚፎካከሩ ቅድሚያ ግምት
ተሰጥቷቸዋል፡፡
♠ ክርስትያኖ ሮናልዶ በፖርቱጋል ብሄራዊ ቡድን በመሰለፍ በ4 የአውሮፓ ዋንጫዎች ግብ ያስቆጠረ ተጨዋች ለመሆን የሚያነጣጥር ሲሆን ለተመሳሳይ
ታሪክ የስዊድኑ ዝላታን ኢብራሞቪች የሚፎካከረው ይሆናል፡፡ ሁለቱ ተጨዋቾች በተሳተፉባቸው ያለፉት ሶስት የአውሮፓ ዋንጫዎች እኩል 6 ጎሎችን ለብሄራዊ ቡድኖቻቸው አስመዝገበዋል፡፡
♠ በየብሄራዊ ቡድኖቻቸው ሳይመረጡ በመቅረታቸው የአውሮፓ ዋንጫው ካመለጣቸው ተጨዋቾች መካከል ፊሊፕ ሴንድሮስ ከስዊዘርላንድ፤ ጃቪ ማርቲኔዝ ከስፔን፤ ዳኒ ድሪን ዎተር ከእንግሊዝ፤ ሃቴም ቤን አርፋ ከፈረንሳይ፤ ማርዮ ባላቶሊ ከጣሊያን፤ ዲያጎ ኮስታ ከስፔን፤ ካሪም ቤንዜማ ከፈረንሳይ እና ፈርናንዶ ቶሬስ
ከስፔን ይጠቀሳሉ፡፡
♠ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በ2012 እኤአ ላይ ፖላንድ እና ዩክሬን አዘጋጅተው ከነበሩት 14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በ50 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ገቢን ከ15ኛው የአውሮፓ ዋንጫእንደሚጠብቅ ገልጿል፡፡
♠ የአውሮፓ ዋንጫው በ24 ብሄራዊ ቡድኖች መካሄዱ ከ10 በላይ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን በስፖንሰርሺፕ በማቀፍ ዳጎስ ያለ ጥቅም የሚያስገኝ ሲሆን እሰከ 1.49 ቢሊዮን ዩሮ መዋዕለንዋይ ይንቀሳቀስበታል፡፡
♠ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በዝርዝር እንዳስታወቀው ከአውሮፓ ዋንጫው ከ450 እስከ 500
ሚሊዮን ዩሮ ትርፍ ይጠበቃል፡፡ ከትኬት ሽያጭ እና መስተንግዶ 500 ሚሊዮን ዩሮ፤ ከቴሌቭዥን ስርጭት መብት እስከ 1 ቢሊዮን ዩሮ ገቢ እንደሚገኝ ነው፡፡
♠ የአውሮፓ ዋንጫው በመላው ዓለም በ230 የስርጭት ቀጠናዎች በቴሌቭዥን የቀጥታ ሽፋን የሚያገኝ ሲሆን አንድ ጨዋታ በአማካይ 150 ሚሊዮን የቲቪ ተመልካች እንደሚኖረው ተገምቷል፡፡
♠ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለአውሮፓ ዋንጫው ያቀረበው የሽልማት ገንዘብ ከ301 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ሲሆን ካለፈው የአውሮፓ ዋንጫ በ194 ሚሊዮን ዩሮ
ጭማሪ አሳይቷል፡፡
♠ በውድድሩ ተሳታፊ ሚሆኑ 24 ብሄራዊ ቡድኖች በተሳትፎ ብቻ በነፍስ ወከፍ 8 ሚሊዮን ዩሮ ሲከፋፈሉ በየምድብ ጨዋታው ለሚያሸንፍ 1 ሚሊዮን ዩሮ እንዲሁም አቻለሚወጣ 500ሺ ዩሮ ይታሰባል፡፡ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ 16 ብሄራዊ ቡድኖች 1.5 ሚሊዮን ዩሮ፤ ሩብ ፍፃሜ የሚደርሱ 8 ብሄራዊ ቡድኖች 2.5 ሚሊዮን፤ ለግማሽ ፍፃሜ የሚበቁ 4 ብሄራዊ ቡድኖች 4 ሚሊዮን ዩሮ ሲሰጣቸው በዋንጫ ጨዋታው ለሁለተኛ ደረጃ 5 ሚሊዮን እንዲሁም ለሻምፒዮኑ አገር 8 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚበረከትም ለማወቅ
ተችሏል፡፡ ዋንጫውን የሚያሸንፍ ብሄራዊ ቡድን እስከ 27 ሚሊዮን ዩሮ፤በሁለተኛው ደረጃ የሚያጠናቅቀው እስከ 24 ሚሊዮን ዩሮ የሚያገኙ ሲሆን ለደረጃ የሚጫወቱት ሁለት ብሄራዊ ቡድኖች በነፍስ ወከፍ እስከ 19 ሚሊዮን ዩሮ ከሽልማት ገንዘቡየሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡
♠ ከ15ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በፊት ስፔን እና ጀርመን እያንዳንዳቸው እኩል 3 ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን የከፍተኛ ውጤት ክብረወሰኑን ሲጋሩ ፈረንሳይ በ2 ጊዜ
አሸናፊነት ትከተላለች፡፡
♠ እያንዳንዳቸው እኩል አንዴ ሻምፒዮን ለመሆን የበቁት ስምንት ቡድኖች ደግሞ የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት፤ ጣሊያን፤ ቼክ ሪፖብሊክ፤ ሆላንድ ዴንማርክ እና ግሪክ ናቸው፡፡
♠ ጀርመን በአውሮፓ ዋንጫ የተሳትፎ ታሪኳ 43 ጨዋታዎችን በማድረግ ፤
23 በማሸነፍ እና 65 ጎሎች በማስቆጠር ግንባር ቀደም ትሆናለች፡፡
♠ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ 9 ጎሎች በማግባት የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የሚመራው
የፈረንሳዩ ሚሸል ፕላቲኒ ሲሆን፤ የማጣርያ ጨዋታዎችን ጨምሮ ከዋናው ውድድር ጋር 26 ጎሎች
በማስመዝገብ የፖርቱጋሉ ክርስትያኖ ሮናልዶ ተጠቃሽ ይሆናል፡፡
♠ በ24ቱ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች የሚሰለፉ 552 ጨዋታቸው የዝውውር ገበያ የዋጋ ተመን 4.972 ቢሊዮን ዩሮ ነው፡፡
♠ በአውሮፓ ዋንጫው
በሚሳተፉ 24 ብሄራዊ ቡድኖች ተጨዋቾቻቸውን ላቀረቡ ከ580 በላይ ክለቦች የሚከፈልም 150
ሚሊዮን ዩሮ ተዘጋጅቷል፡፡
♠ በአውሮፓ ዋንጫው 12 ተጨዋቾችን ለየብሄራዊ
ቡድኖቻቸው በማሰለፍ ግንባር ቀደም የሆኑት የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል እና የጣሊያኑ ክለብ ጁቬንትስ ሲሆኑ ሌላው የእንግሊዝ ክለብ ቶትንሃም 11 ተጨዋቾች በማሳተፍ ይከተላል፡፡ የስፔኑ ባርሴሎና እና የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እያንዳንዳቸው 9፤ ሪያል ማድሪድ 8፤ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ፓሪስ ሴንትዠርመን 4 ተጨዋቾችን በአውሮፓ ዋንጫው
ያካፍላሉ፡፡ ሌሎቹ የእንግሊዝ ክለቦች አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ እያንዳንዳቸው 10 ተጨዋቾችን ፤ ማንችስተር ሲቲ 7፤ ቼልሲ 6 እንዲሁም በርካታ የፕሪሚዬር ሊጉ እና የአንደኛ ዲቪዝዮን ክለቦች ለአውሮፓ ዋንጫው ከሌሎች የአውሮፓ ክለቦች በላቀ ብዛት በመልቀቅ ይጠቀሳል፡፡
በፈረንሳዩ ዩሮ-2016 ላይ የሚሳተፉ ዉዱ 8ቱ ተጨዋቾች
1. ክርስቲያኖ ሮናልዶ (Portugal) – £86m
2. ጋሬዝ ቤል (Wale) – £63m
3. ቶማስ ሙለር (Germany) – £59m
4. ሮበርት ሊዋንዶውስኪ (Poland) – £59m
5. ኤዲን ሀዛርድ (Belgium) – £55m
6. ፖል ፓግባ (France) – £55m
7. አንቶንዮ ግሬዝማን (France) – £55m
8. ሜሱት ኦዚል (Germany) – £47m
እስቲ 24ቱም ብሔራዊ ቡድኖች እያንዳንዱ ብሔራዊ ቡድን ስንት ያወጣል
;;;;;
24 ሀንጋሪ =£27.3M
23 ኖርዝ አየርላንድ =£35.9M
22 አልባኒያ =£40.9M
21 አየስላንድ =£41.6M
20 ሮማኒያ=£56M
19 ቼክሪፐብሊክ=£64.5M
18 ሲውዲን=£86.9M
17 ሪፐብሊክ ኦፍ አየርላንድ=£89.3M
16 ስሎቫኪያ=£91.1M
15 አውስትራሊያ=£128.4M
14 ዩኩሬን=£128.7M
13 ራሽያ=£133.5M
12 ዌልስ=£168.6M
11 ሲውዘርላንድ=£172.5M
10ፖላንድ=£175.5M
9 ቱርክ=£186.1M
8 ጣልያን=£272M
7 ክሮሽያ=£273.3M
6 ፖርቹጋል=£321.7M
5 እንግሊዝ=£446M
4 ፈረንሳይ=£454M
3 ቤልጄም=£460.9M
2 እስፔን=£557.5M
1 ጀርመን=£562M
የአውሮፓ ዋንጫ የጨዋታ መርሃ ግብር በሃገራችን ቀንና ሰአት አቆጣጠር ጋር ⚽
♞ ♞ መንሱር አብዱልቀኒ
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ አርብ ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም
ምድብ ሀ
ፈረንሳይ 4፡00 ሮማኒያ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም
አልባኒያ 10፡00 ስዊዘርላንድ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
ምድብ ለ
ዌልስ 1፡00 ስሎቫኪያ
እንግሊዝ 4፡00 ሩሲያ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ እሁድ ሰኔ 4 ቀን 2008 ዓ.ም
ምድብ ሐ
ፓላንድ 1፡00 ሰሜንአየርላንድ
ጀርመን 4፡00 ዩክሬን
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
ምድብ መ
ቱርክ 10፡0 ክሮሺያ
☞ ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም
ስፔን 10፡00 ቼክሪፐብሊክ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
ምድብ ሠ
አየርላንድ 1፡00 ስዊዲን
ቤልጂየም 4፡00 ጣሊያን
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2008 ዓ.ም
ምድብ ረ
ኦስትሪያ 1፡00 ሃንጋሪ
ፓርቱጋል 1፡00 አይስላንድ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ረቡዕ ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም
ሩሲያ 10፡00 ስሎቫኪያ
ሮማኒያ 1፡00 ስዊዘርላንድ
ፈረንሳይ 4፡00 አልባኒያ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ሀሙስ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም
እንግሊዝ 10፡00 ዌልስ
ዩክሬን 1፡00 ሰሜንአየርላንድ
ጀርመን 4፡00 ፖላንድ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ አርብ ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም
ጣሊያን 10፡00 ስዊዲን
ቼክሪፐብሊክ 1፡00 ክሮሺያ
ስፔን 10፡0 ቱርክ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ቅዳሜ ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ.ም
ቤልጂየም 10፡00 አየርላንድ
አይስላንድ 1፡00 ሃንጋሪ
ፓርቱጋል 4፡00 ኦስትሪያ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣ ,
☞ እሁድ ሰኔ 11 ቀን 2008 ዓ.ም
ሮማኒያ 4፡00 አልባኒያ
ስዊዘርላንድ 4፡00 ፈረንሳይ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2008 ዓ.ም
ሩሲያ 4፡00 ዌልስ
ስሎቫኪያ 4፡00 እንግሊዝ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣ ,
☞ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም
ሰሜንአየርላንድ 1፡00 ጀርመን
ዩክሬን 1፡00 ፖላንድ
ክሮሺያ 4፡00 ስፔን
ቼክሪፐብሊክ 4፡00 ቱርክ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ረቡዕ ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ.ም
ሃንጋሪ 1፡00 ፓርቱጋል
አይስላንድ 1፡00 ኦስትሪያ
ጣሊያን 4፡00 አየርላንድ
ስዊዲን 4፡00 ቤልጂየም
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2008 ዓ.ም
የ16ቱ ቡድኖች ጨዋታ
የምድብ”ሀ”2ኛ 10፡0 የምድብ”ሐ”2ኛ
የምድብ”ለ”1ኛ 1፡00 የምድብሀ/ሐ/መ3ኛ
የምድብ”መ”1ኛ 4፡00 የምድብለ/ሠ/ረ3ኛ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም
የምድብ”ሀ”1ኛ 10፡0 የምድብሐ/መ/ሠ3ኛ
የምድብ”ሐ”1ኛ 1፡00 የምድብሀ/ለ/ረ3ኛ
የምድብ”ረ”1ኛ 4፡00 የምድብ”ሠ”2ኛ
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም
የምድብ”ሠ”1ኛ 1፡00 የምድብ”መ”2ኛ
የምድብ”ለ”2ኛ 4፡00 የምድብ”ረ”2ኛ
የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ሀሙስ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ1 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ2
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ አርብ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ3 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ4
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ5 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ6
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ እሁድ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ7 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ8
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2008 ዓ.ም
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
የግማሽፍፃሜአላፊ1 4:00 የግማሽፍፃሜአላፊ2
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
☞ ሀሙስ ሰኔ 29 ቀን 2008 ዓ.ም
የግማሽፍፃሜአላፊ3 4፡00 የግማሽፍፃሜአላፊ4
★★★★★★★★★
⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
# የፍፃሜ_ጨዋታ_FINAL
☞ እሀድ ኃምሌ 2 ቀን 2008 ዓ.ም
የፍፃሜአላፊ1 4፡00 የፍፃሜአላፊ2

ዳሰሳው ይህን ይመስላል በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ ፔጁን ⇨ ላይክ ፓስቱን ሼር ማድረጎን አይዘንጉ።
አስተያየት እና ምስጋና ካሎት ኮመንት ይስጡን። ስላነበቡት እናመሰግናለን
ይመቻችሁ!!!

Photos 06/06/2016

4 ቀናት ብቻ ቀረው።
ካሁኑ ፔጁን ላይክ እና ሼር በማድረግ ለFrance Euro 2016 ዜናዎች ቅርብ ይሁኑ።
➡ ➡ በሰኔ ወር ለሚጀመረው የ euro 2016 ፍራንስ ላይ⬅ ⬅
♠ የጨዋታ ቅድመ ትንታኔዋች
♠ የጨዋታ ሰዐቶችና ፕሮግራሞች
♠ ከጨዋታ በሁላ ሰፍ ያለ ትንታኔ
♠ የጉዳት ዜና
♠ የጨዋታ የቀጥታ ስርጭቶች
♠ የጨዋታ ውጤቶች ከ ሙሉ ትንታኔ ጋር
እናም ሌላም ሌላም እርሶ ብቻ ፔጁን ላይክ እና ሼር ያርጉ።
እናመሰግናለን

Photos 28/05/2016

.......ይገምቱ ይሸለሙ.....
♠ ውድ የፔጃችን ተከታዮች ዛሬ ቅዳሜ 3:45pm በ አ.ማድሪድና በ ሪ.ማድሪድ ሚደረገውን የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በመገመት የ100ብር ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ። በአጭሯ ጊዜ የተጠቀመ አሸነፈ። ታዲያ ይሄን። ሽልማት ለመውሰድ የግድ
በመጀመርያ ፔጁን ላይክ ያርጉ
በመቀጠል ፔጁን ለወዳጅ ዘመድዋ ሼር እና invite ያርጉ
በመጨረሻም በኮመንት ሳጥን ውስጥ ግምትዋን ያስቀምጡ።
አለበለዚያ ሽልማቱን አንሰጥም።
♥ ማሳሰቢያ መገመት ሚቻለው ፔጁ ላይ ብቻ ነው።ሽልማቱን ደሞ ለ 5 ሰዋች ብቻ ነው ምንሸልመው።
♣ ታዲያ ምን ይጠብቃሉ አሁኑኑ ይገምቱ!!!!!

Photos from Euro Cup Amharic News's post 27/05/2016

ሰኔ 2 በፈረንሳይ የሚጀመረው የአውሮፖ ዋንጫ ሙሉ ፕሮግራም እነሆ
ሁሌም ፖስቶቹን ላይክ ሳያደርጉ አይለፉ።ላይክ ማድረጋችሁ ለኛ ብቻ ሳይሆን
ለናንተምእንዲደርሳችሁ ነው።
አርብ ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም
♠ ምድብ ሀ
ፈረንሳይ 4፡00 ሮማኒያ
♦ ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም
አልባኒያ 10፡00 ስዊዘርላንድ
♠ ምድብ ለ
ዌልስ 1፡00 ስሎቫኪያ
እንግሊዝ 4፡00 ሩሲያ
እሁድ ሰኔ 4 ቀን 2008 ዓ.ም
♠ ምድብ ሐ
ፓላንድ 1፡00 ሰሜንአየርላንድ
ጀርመን 4፡00 ዩክሬን
ምድብ መ
ቱርክ 10፡00 ክሮሺያ
♦ ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም
ስፔን 10፡00 ቼክሪፐብሊክ
♠ ምድብ ሠ
አየርላንድ 1፡00 ስዊዲን
ቤልጂየም 4፡00 ጣሊያን
♦ ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2008 ዓ.ም
♠ ምድብ ረ
ኦስትሪያ 1፡00 ሃንጋሪ
ፓርቱጋል 1፡00 አይስላንድ
♦ ረቡዕ ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም
ሩሲያ 10፡00 ስሎቫኪያ
ሮማኒያ 1፡00 ስዊዘርላንድ
ፈረንሳይ 4፡00 አልባኒያ
♦ ሀሙስ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም
እንግሊዝ 10፡00 ዌልስ
ዩክሬን 1፡00 ሰሜንአየርላንድ
ጀርመን 4፡00 ፖላንድ
♦ አርብ ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም
ጣሊያን 10፡00 ስዊዲን
ቼክሪፐብሊክ 1፡00 ክሮሺያ
ስፔን 10፡0 ቱርክ
♦ ቅዳሜ ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ.ም
ቤልጂየም 10፡00 አየርላንድ
አይስላንድ 1፡00 ሃንጋሪ
ፓርቱጋል 4፡00 ኦስትሪያ
♦ እሁድ ሰኔ 11 ቀን 2008 ዓ.ም
ሮማኒያ 4፡00 አልባኒያ
ስዊዘርላንድ 4፡00 ፈረንሳይ
♦ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2008 ዓ.ም
ሩሲያ 4፡00 ዌልስ
ስሎቫኪያ 4፡00 እንግሊዝ
♦ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም
ሰሜንአየርላንድ 1፡00 ጀርመን
ዩክሬን 1፡00 ፖላንድ
ክሮሺያ 4፡00 ስፔን
ቼክሪፐብሊክ 4፡00 ቱርክ
♦ ረቡዕ ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ.ም
ሃንጋሪ 1፡00 ፓርቱጋል
አይስላንድ 1፡00 ኦስትሪያ
ጣሊያን 4፡00 አየርላንድ
ስዊዲን 4፡00 ቤልጂየም
♦ ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2008 ዓ.ም
♠ የ16ቱ ቡድኖች ጨዋታ
የምድብ”ሀ”2ኛ10፡00 የምድብ”ሐ”2ኛ
የምድብ”ለ”1ኛ 1፡00 የምድብሀ/ሐ/መ3ኛ
የምድብ”መ”1ኛ 4፡00 የምድብለ/ሠ/ረ3ኛ
♦ እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም
የምድብ”ሀ”1ኛ 10፡00 የምድብሐ/መ/ሠ3ኛ
የምድብ”ሐ”1ኛ 1፡00 የምድብሀ/ለ/ረ3ኛ
የምድብ”ረ”1ኛ 4፡00 የምድብ”ሠ”2ኛ
♦ ሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም
የምድብ”ሠ”1ኛ 1፡00 የምድብ”መ”2ኛ
የምድብ”ለ”2ኛ 4፡00 የምድብ”ረ”2ኛ
♠ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች
♦ ሀሙስ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ1 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ2
♦ አርብ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ3 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ4
♠ ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ5 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ6
♠ እሁድ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ.ም
የሩብፍፃሜአላፊ7 4፡00 የሩብፍፃሜአላፊ8
♠ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2008 ዓ.ም
የግማሽፍፃሜአላፊ1 4፡00 የግማሽፍፃሜአላፊ2
ሀሙስ ሰኔ 29 ቀን 2008 ዓ.ም
የግማሽፍፃሜአላፊ3 4፡00 የግማሽፍፃሜአላፊ4
♠ የፍፃሜ ጨዋታ
እሁድ ኃምሌ 2 ቀን 2008 ዓ.ም
የፍፃሜአላፊ1 4፡00 የፍፃሜአላፊ2
♦ መረጃውን አንብበው ሲጨርሱ ላይክ ኮመንት ሼር ማረጎን አይርሱ።
ምንጭ፦
መልካም ቀን!!!!

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa