31/12/2021
በቦታው እንድትገኙ የአአ ስፖርት ኮሚሽን ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ጥሪውን አስተላልፏል።
It is a health and fitness trainers Association in the City of Addis Ababa established by fitness tr
31/12/2021
በቦታው እንድትገኙ የአአ ስፖርት ኮሚሽን ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ጥሪውን አስተላልፏል።
14/12/2021
ጥሩ ጊዜ
የሁለተኛ ደረጃ የአካል ብቃት ስልጠና መውሰድ የምትፈልጉ ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ምዝገባ ጀምሯል።
28/02/2021
የመላው ጥቁር ህዝብ ድል አድዋ በአካል ብቃት ደምቆ ታስቧል። የአዲስ አበባ አካል ብቃት አሰልጣኞች ማህበር እንቅስቃሴዎችን አሰርቷል።
27/10/2020
ኮሚሽነር ዮናስ ለነበረን የአብሮነት ጊዜ ማህበራችን ከልብ እናመሰግናለን ። ኮሚሽነር በላይ ደጀኔ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን።
11/10/2020
ዛሬ በቦሌ ክ/ከተማ የተደረገው እንቅስቃሴ እንዲሁም መንገድ ለሰው እንቅስቃሴዎች ላይ የማህበራችን አባላት አካል ብቃት በማሰራት ትልቁን ሚና ተጫውቷል።
07/09/2020
ለመላው የአዲስ አበባ ጤናና አካል ብቃት አሰልጣኞች ማህበር አባላት እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ ከልብ ይመኛል።
ማህበሩ
27/07/2020
10/05/2020
የቦሌ ክ/ከተማ ስፖርት ጽ/ቤት ከክ/ከተማው የጤና ጽ/ቤቶች እና ከአዲስ አበባ አካል ብቃት አሰልጣኞች መህበር ጋር በመተባበር በክ/ከተማው ስር በሚገኙ በርካታ የህብረተሰብ ክፍል በሚገኙባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰቡ አካላት በሀገራችን በተከሰተው የኮቪድ 19 ስርጭትን ተከትሎ
የህብረተሰብ ክፍሎች እቤታቸው በመቀመጥ የበሽታውን ወረርሺኝ እራሳቸውን ለመከላከል በሚያደረጉት ጥረት ከጭንቀት፣ከድብርት እንዳይጋለጡ በተመረጡ ዋና ዋና ስፍራዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ግንቦት 02/9/2012 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ሳይት የህብረተሰቡም ተሳትፎ ጥሩ የሚባል ነበር፡፡
06/05/2020
ሚያዚያ 27/ 2012 ዓ.ም ( ኮንደሚኒየም ) የሚኖሩ ነዋሪዎች በቤታቸው በረንዳ እና በግቢው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአካል ብቃት አሰልጣኞች እየታገዙ ሰርተዋል ።
በዚህ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጋራ መኖሪያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ጋር አብረው የሰሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ የኮረና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ከቫይረሱ ለመከላከልና ለመጠበቅ በቤታቸው ሆናችሁ ይህን ክፉ ቀን ለማሳለፍ የምታደርጉትን ጥረት ከተማ አስተዳደሩና ኮሚሽኑ አክብሮቱን ይገልፅላችዋል ብለዋል ።
ኮሚሽነር ዮናስ አያይዘውም ይህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመኖሪያችሁ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ይኖርባችዋል ለዚህም ከፊት ሆነው ሚና ለተጫወቱ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ ለቦሌ ክ/ ከተማ የስፖርት ፅህፈት ቤትና በተግባር እያሰሩ ላሉ ለአካል ብቃት አሰልጣኞችና ነዋሪዎች ምስጋናዬን አቀርባለው ብለዋል ።
ዛሬም በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በበረንዳቸው ወጣ ብለው አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው በሚል መሪ ቃል እየሰሩ ናቸው ።
ተፈላጊነቱ በነዋሪው እየጨመረ መምጣቱና ነዋሪዎች በቤታቸው ሲውሉ ከጭንቀት ፣ ከድብርትና ካልተፈለገ በሽታ ለመታደግ በቤት ውስጥ ሁሉ የአካል እንቅስቃሴ መሠራቱ የዐለም የጤና ድርጅትም ካስቀመጠው መርህዎች አንዱ ነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ውጤታማ ስራ እየሰራ ይገኛል በመሆኑም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጤናማ ህብረተሰብ ለመፍጠር በጋራ መኖሪያ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ይገኛል ይህም ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
የኮንዶሚንየም የጋራ መኖሪያ ሳይት ነዋሪዎች በአካል ብቃት እንቅስቃሴው እንዲሳተፉ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ባለሙያዎች አስቀድመው ዝግጅት ማድረጋቸውም ታውቋል
03/05/2020
የአዲስ አበባ ጤናና አካል ብቃት ማህበር በዛሬው እለት በተለያዩ ክ/ከተሞች በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍል ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በቦታው በመገኘት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሰሩ ሲሆን በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስን እንዴት መከላከል እንደሚችልና በፍጹም ህዝቡ በኮሮና ዙሪያ መዘንጋት እንደሌለባቸው መልእክቶችን አስተላልፈዎል።
ሁሌም በማህበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ማህበሩ የአካል ብቃት ባለሙያዋችን ያመሰግናል።
የአ.አ.ጤ.አ.ብ.አ.ማ