02/11/2025
በቀን 23/02/2081 ዓ.ም.በቻይና በተካሄደው የማራቶን ውደድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ።
በቻይና በቤጂንግ እና ሆንዙ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሆንዙ የማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ በ2:24:29 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች።
በወንዶች አትሌት ጫሉ ደሶ በ2:11:15 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል።
በተመሳሳይ በቤጂንግ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2:08:10 በመግባት ሲያሸንፍ÷ አትሌት ደሳለኝ ግርማ ሁለተኛ ወጥቷል።
በሴቶች አትሌት አንቻሉ ደሴ በ2:26:06 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ÷ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ቁፍቱ ጣሂር ሦስተኛ ወጥታለች።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
30/10/2025
Female Out of Stadium Athlete of the Year nominee ✨
Like to vote for Tigst Assefa 🇪🇹 in the .
Voting closes on Sunday 2 November at 11:59 PM CET.
30/10/2025
Male Out of Stadium Athlete of the Year nominee ✨
Like to vote for Yomif Kejelcha 🇪🇹 in the .
Voting closes on Sunday 2 November at 11:59 PM CET.
19/10/2025
አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ የግማሽ ማራቶን አሸነፈ።
በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል።
ጥቅምት 9, 2018 ዓ.ም.
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት 01 ሰኮንድ ከ21 ማይክሮ ሰኮንድ ፈጅቶበታል፡፡
በሴቶች ዘርፍ በተደረገ ውድድር ደግሞ አትሌት መስከረም ማም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በሌላ ዜና በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት ጸጋዬ ጌታቸው 2ኛ እንዲሁም አትሌት ጌታነህ ሞላ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
አትሌት ጸጋዬ ጌታቸው ባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
16/10/2025
ዛሬም ይናገራል ፎቶ !!!
ያዮትን ሲክዱ ሰምተው ላለመስማት ፤
እውነትን ጨፍልቀው በውሸት ለማማት ።
ያለፈውን ክደው አሁን ሲያሽቃብጡ ፤
ከርሞ እንደለመዱት ዛሬንም ሊንጡ ፤
አወዳደሩና ከዳቦና ሊጡ ፤
ይሻለናል ሲሉ ከድጡ የማጡ ፤
በወቅቱ ባይችልም ትናጋው ተከቶ ፤
ለምን አይናገር ይናገራል ፎቶ ፤
ሕይወት ከዘራበት ሉሌ ድንገት መጥቶ።
6 ጥቅምት 2018
ዘላለማዊ ክብር ለክብርት አትሌት
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፤
የሷን ፈለግ ተከትለው ኢትዮጵያን ላኮሩ አትሌቶች በሙሉ
ልዑልሰገድ እሸቱ
15/10/2025
♦️" ሽልማቱን ለእናቴ በቃላት ለማይገለፀው ውለታዋ ማስታወሻ ይሁንልኝ..."
♦️"መሸለሜን ተወውና የትዝታው ንጉስ ከሆነው ከጋሽ መሀሙድ አህመድ ጋር የእኔም ፎቶ አብሮ ወጥቶ ሳየው እጅግ ከፍተኛ ደስታም ድንጋጤም ነበር የተሠማኝ..."
♦️"...ዶክተር ጋሻው የሀገርን ስም የሚያስጠራ፣ከሩጫም በላይ ፋይዳ ያለውን ስራ በመስራቱ ሁላችንም ልናመሠግነው፣ልናግዘው ይገባል..."
♦️"...እኔ ከፊት ሆኜ ልሸለም እንጂ ባለቤቴ የዚህ ሽልማት ተጋሪ ነውና አመሠግነዋለሁ..."
አትሌት መሠረት ደፋር(ከአሜሪካ)
✍✍በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
| የኦሎምፒክ እና የአለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊና ሪከርድ ሠባሪዋ ጀግናዋ አትሌታችን መሠረት ደፋር፤ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ለሀገሯ ብሎም ለአፍሪካ ላበረከተችው ከፍተኛ አስተዋፅኦና ብዙ ታዳጊዎች ላይ በጎ ተፅእኖ በማሳረፍዋ ክብርና ዕውቅና አግኝታለች።ባለውለኘተኞችን በህይወት እያሉ ለመልካሙ ስራቸው ዕውቅናና ክብር በመስጠት ተለይቶ የሚታወቀውና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ኖቫ ኮኔክሽን ጀግናዋን አትሌት በአትሌቲክስ ላበረከተችው የላቀ አስተዋፅኦ የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚ አድርጓታል።የሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያሉ ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ አትሌት መሠረት ደፋር ከሠጠመችበት የደስታ ባህር ሳትወጣ በስልክ ሞገድ አሳብሮ ሀሎ በማለት በሽልማቱ ዙሪያ አናግሯት ከዚህ በታች ባለው መልኩ አጠናክሮታል።
🎤መሲዬ እንዴት ነሽ...?...ለሀገር ለዋልሽው ውለታ በአደባባይ ክብርና ዕውቅና ሲሠጥሽ አይተን ደስ ብሎናል፤የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በአትሌቲክስ ዘርፍ ተሸላሚ በመሆንሽ እንኳን ደስ አለሽ...?...
📌...እንኳን አብሮ ደስ አለን፤ከኢትዮጵያ ደውለህ ደስታዬን ስለተጋራኸኝም በጣም አመሠግናለሁ፤...
🎤...የዚህ ትልቅ ሽልማት አሸናፊ በመሆንሽ በውስጥሽ የተፈጠረውን የደስታ ስሜት እንዴት ነው የምትገልጪልኝ...?...
📌...ኡኡኡ...የደስታ ስሜቴን እንዴትና በምን ቃል እንደምገልፅልህ አላውቅም፤እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፤እኔ እንግዲህ እንደምታውቀው የተለያዩ ሽልማቶችን በተለያዩ የውድድር ዘርፎች አግኝቼ አጣጥሜያለሁ፤የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በአትሌቲክስ ዘርፍ ተሸላሚ በመሆኔ ግን በቃላት መግለፅ የማልችለው ልዩ የደስታ ስሜት ነው የተሠማኝ፤አሁንም ድረስ የደስታው ስሜት አብሮኝ ነው ያለው፣በቀጣይም አብሮኝ ነው የሚኖረው፤ከሩጫው ከወጣሁ በጣም ረዥም ጊዜ ሆኖኛል፤ነገር ግን ለሀገሬ የሠራኹትን ስራ መለስ ብሎ አስታውሶ ሽልማቱ፣ክብሩ ይገባሻል የሚል ተቋም ተፈጥሮ በጣም ትልቅ ስራ ከሠሩ ታላላቅ ሠዎች ጋር አንቺም አንዷ ነሽ ተብዬ መሸለሜ በቃላት መግለፅ የማልችለው ከፍተኛ ክብርም ኩራትም እንዲሠማኝ አድርጓል...
🎤...ከሀገር ውጪ ያውም በአሜሪካ በበርካታ ኢትዮጵያዊያንና ታላላቅ ሠዎች ፊት መሸለሙስ የሚፈጥረው የተለየ ስሜት አለው...?...
📌...በጣም አለው...የዘንድሮው ሽልማት ለአምስተኛ ጊዜ ነው፤የሽልማቱ ደረጃና ዕውቅናው በየጊዜው እያደገ ነው፤በዕውነት ለመናገር ደረጃውን የጠበቀ ትልቅ ፕሮግራምም ነው፤ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣አፍሪካዊያንና አሜሪካዊያን በዛ ላይ ደግሞ በሠሩት ስራ አንቱ ከተባሉ የተከበሩ ሠዎች ጋር በአንድ መድረክ ለዚህ ክብርና ዕውቅና በመብቃቴ የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል፤ለሀገርህ የሠራኸው ስራ ዋጋ እንዳለው እንደሚያስከብርህ ያረጋገጥኩበት መድረክም ሆኖ ነው ያገኘሁትና ከምገልፅልህ በላይ እጅግ ደስ ብሎኛል...
🎤....በዘንድሮው የአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ ከአንቺ ሌላ ተወዳጁ ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ፣የመዝናኛ ሾው አዘጋጁና በበርካታ በጎ ስራዎቹ የምናውቀው ሠይፉ ፋንታሁንና የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ቸርነትም ተሸላሚ የሆኑበት መድረክ ላይ አብረሽ መሸለምሽና ዕውቅና ማግኘትሽን እንዴት ነው የምትገልጪው...?...
📌...በአንድ መድረክ አብሬ ቆሜ መሸለሜን ተወውና ገና ከኢትዮጵያ ሳንሄድ ከእነዚህ ታላላቅና ለሀገር ትልቅ ውለታ ከዋሉ የተከበሩ ሠዎች የ2025 ተሸላሚዎች በሚል ይፋ ሲደረግና የኔንም ፎቶ ከእነሱ ጋር ሳየው በራሱ የሆነ የማላውቀው የተለየ ስሜት ነው የተሠማኝ፤በተለይ በተለይ የትዝታው ንጉስ ከሆነው ከጋሽ መሀሙድ አህመድ ጋር የእኔም ፎቶ አብሮ ወጥቶ ሳየው እጅግ ከፍተኛ ደስታም ድንጋጤም ነበር የተሠማኝ፤ምክንያቱም እኔ ጋሽ መሀሙድ አህመድን ከሚያክል ህያው ሌጀንድ ጋር እኩል የምቆም ሠው ነኝ ብዬ ስለማላስብ በጣም ነበር የተደሠትኩት፤የሀገራችንን የሙዚቃ ታሪክ የቀየረ፣በሙዚቃው የሁላችንንም ቤትና ልብ ያንኳኳው፣ደስታችን፣ተስፋችን፣ሁሉነገራችንን በሙያው ከገለፀው ሌጀንድ ጋር አብሬ ለዚህ ክብር መብቃቴና መሸለሜ የትልቅ ታሪክ ባለቤት አድርጎኛል ብቻ ሳይሆን በህይወት ዘመኔ ሁሉ ሳስታውሠው የምኖረው ሽልማት አድርጎታል፤ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ....
🎤...(ድንገት አቋረጥኳትና)...ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ምን...?....
📌...ሠይፉ ፋንታሁንን ብትወስደው በሙያው(በሚዲያ)ሀገር ላይ ትውልድ ላይ አሻራውን ያሳረፈ፣የብዙዎችን ህይወትና ቤት የለወጠ፣በተለይ ደግሞ በቅርቡ ሙያውን ተጠቅሞ መቄዶኒያ ላይ ሁላችንንም ያስገረመ ስራን የሠራ፤እንደ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን እንደ አፍሪካ የምንኮራበትን ግዙፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከሚመሩት መስፍን ጣሠው ጋር አብሬ መሸለሜና ዕውቅና ማግኘቴ ለእኔ ትልቅ ታሪክና ክብር በመሆኑ በጣም ተደስቻለሁ የተለየ ቦታ የምሠጠውም ታሪካዊ ሽልማት ነው ለኔ...
🎤...በዚህ ደረጃ የገለጥሽውን ሽልማት ማስታወሻነቱን ለማን ትሠጪያለሽ ብልሽ ምን ትመልሺልኛለሽ...?...
📌...በሽልማቱ ዕለትም መናገር እየፈለኩ በጣም ስሜታዊ(ነርቨስ)በመሆኔ ስሜቴን ሳልገልፅ ወረድኩ እንጂ ማስታወሻነቱን መሆን ከሚገባት በላይ ሆና ላሳደገችኝ ውዷ እናቴ ይሁንልኝ ለማለት ፈልጌ ነበር እንዳልኩህ መድረክ ላይ በጣም ስሜታዊ(ነርቨስ)ሆኜ ስለነበር የውስጤን አልተናገርኩም፤አንተም ይሄን ዕድል ስለሠጠኸኝ በጣም እያመሠገንኩ የዚህን ታሪካዊ ሽልማት ማስታወሻነት በሩጫው አለም ትልልቅ ውጤቶችና ስኬቶችን አሳክቼያለሁ፤የእነዚህ ስኬቶቼ ትልቁ መሠረቴ ለፍታ ያሳደገችኝ እናቴ ናትና ሽልማቱን ለእናቴ በቃላት ለማይገለፀው ውለታዋ ማስታወሻ እንዲሆንልኝ ማበርከት ነው የምፈልገው...
🎤...ከዚህ በላይ ጊዜሽን መውሰድ አልፈልግምና በመጨረሻ የምታስተላልፊው መልዕክት ካለሽ ዕድሉን ልስጥሽ...?...
📌...በመጨረሻ ሁለት ነገሮችን ማንሳት እፈልጋለሁ...የመጀመሪያው በሠው ሀገር ይሄንን ከሩጫም በላይ የሆነን ትልቅ ቁምነገር ያለው ስራን እየሠራ የሚገኘውን ዶክተር ጋሻው አብዛንና አብረውት የሚደክሙትን በሙሉ ማመስገን እወዳለሁ፤ዶክተር ጋሻው የሀገርን ስም የሚያስጠራ፣ከሩጫ በላይ ፋይዳ ያለውን ስራ በመስራቱ ሁላችንም ልናመሠግነው፣ልናግዘው ይገባል፤ሩጫውን ጨምሮ ሁለት ግዙፍ ነገሮችን ያውም በሠው ሀገር በስኬት፣በድምቀት በማጠናቀቁ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ፣የሚያስደንቅ ስራ በመሆኑ ትልቅ ክብር ይገባዋል፤በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፍቅራቸውን፣ናፍቆታቸውን የሚገልፁበት፣ባህላቸውን፣ቋንቋቸውን፣ታሪካቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ከመሆን ባለፈ በአሜሪካ የኢትዮጵያ መገለጫ ወይም ምልክት ተደርጎ የሚወሠድ ሀገርንም አፍሪካዊያንን የሚያኮራ በመሆኑ ይበልጥ
እንዲያድግ ሁላችንም ከዶክተር ጋሻው አብዛ ጎን በመቆም ልናግዘው፣ልንደግፈው ልናበረታታው ይገባል እላለሁ...
🎤...ሁለተኛውስ...?....
📌...ሁለተኛውና የመጨረሻው ደግሞ ምስጋና ነው፤ቅድም ማስታወሻነቱን በተመለከተ የእናት ነገር ምትክ የሌለው በመሆኑ አስቀደምኩ እንጂ ባለቤቴ ቴዎድሮስ የምስጋናው ፀበል ሊደርሠው በጣም ላመሠግነው ይገባል፤በሩጫ ህይወቴ ሁለት አስርት አመታትን አሳልፌያለሁ፤በእነዚህ ዓመታት ሁሉ በውጣውረዶቼ፣በፈተናዎቼ፣በውድቀቴም፣በስኬቴም አብሮኝ የለፋው፣መከራዬንም ደስታዬንም የተጋራው የረዳኝ፣የደገፈኝ ያገዘኝ፣ባለቤቴ ቴዲ ነው፤ቴዲ ባለቤቴ ብቻ ሳይሆን ወንድሜ፣ጓደኛዬ፣አባቴም ብቻ ሁሉም ነገሬ ስለሆነ እኔ ከፊት ሆኜ ልሸለም እንጂ እሱም የዚህ ሽልማት ተጋሪ ነውና በዚህ አጋጣሚ ላደረገልኝና ለከፈለልኝ መስዋዕትነት፣አብረን ላሳለፍነው ሁሉ በአደባባይ ከፍ አድርጌ ላመሠግነው እወዳለሁ፤ቴዲዬ ያለአንተ ድጋፍ ለዚህ ክብር አልበቃም ነበርና ከፍ አድርጌ አመሠግንሀለሁ...
እኛም
ይህንን ቃለመጠይቅ በማድረግ የ 2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዋን የአትሌት መሰረት ደፋርን ስሜት ያጋራንን ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይን እናመሰግናለን።
14/10/2025
የማንቂያ ደወል
በአትሌት መሰረት ደፋር የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ዙሪያ ለሰራነው ገንቢ ዘገባ ትምህርት ወስዶ እራስን እንደማስተካከል፤ በተለያዮ ሰዎች ስም እየተጠቀሙ መሳደብ ለጀመሩ ሰዎች ይህንን የማንቂያ ደወል ለፌድሬሽኑ ለመደወል ተገደናል።
ሲጀመር ስለአትሌት መሰረት ደፋር ያቀረበውን ዜና የፌዴሬሽኑ ባለሙያ ተብዬ - ከጌጡ ተመስገን ቃል በቃል ገልብጦ ነው ከነፎቶው የተጠቀመው። በዚህም የሙያ ጥሰት ከመፈፀም ባሻገር እራሱን ችሎ ዜና የሚሰራ ባለሙያ ፌድሬሽኑ እንደሌለው በግልፅ አሳይቷል። ቀጥሎም መረጃውን ያገኘበትን ምንጭ እንኳን ሳይጠቅስ ዜናውንና ከሽልማቱ የሚዲያ አጋር ከአርትስ ቲቪ የወሰደውን ፎቶግራፎች ጭምር የራሱ አስመስሎ በማቅረቡ ሳያፍር ስህተትህን አርም በተባለ እኛን መሳደብ ጀምሯል። እኛ ደግሞ እውነትን መግለጥ እንጂ ስድብ ስለማናውቅ ጉዳዮን በደንብ ገላልጠነዋል።
የፌድሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ብስራት ለፌድሬሽኑ ባገለገለባቸው አመታት ፤ ፌድሬሽኑ ከየትኛውም ተቋም የማይዋስ፤ የማይገለብጥ እንዲያውም ለጋዜጠኞች እንኳን ሪፈረንስ የሚሰጥ ጥርት ባለ የቋንቋ አጠቃቀም ፍሰትና፤ ያልተቀላቀለን መረጃ ለይቶ በመስጠት የተመሰከረለት ዜናና ዘገባዎችን በመፅሔት፤ በዮቲዮብ እንዲሁም በዚህ የፌስቡክ ገፅ በማቅረብ የታወቀ ነበረ።ፌድሬሽኑ በፌስ ቡክ ገፁ ከ 180 ሺህ በላይ ተከታይ የመኖር ሚስጢሩ ደግሞ በዚያን ጊዜ የነበረው የኮሙኒኬሽን ቲም ስራ እንጂ አሁን የተጨመረ ነገር እንደሌለ ገሀድ ነው።
አሁን ግን ጭራሽ ከሌላ ምንጭ ሙሉ ዜናው ተሰርቆና የራስ አስመስሎ ለቀረበ ዘገባ ትክክል ነኝ እያሉ መከራከርና መሳደብ ተጀምሯል። የምን አይነ ደረቅ .....አሉ።
ሁለተኛ - ዜናው የተሰረቀ ቢሆንም እንኳን የአትሌት መሰረት ደፋር የአፍሪካ ኢምፓክት ሽልማትና የአትሌቷ የአለም አትሌቲክስ ሪከርድ ተለይቶ በቦታና በጊዜ ተጠቅሶ ባለመቅረቡ ነው ስህተት ያልነው። ለምን ቢባል ዜና ሲቀርብ ለሁሉም አይነት አድማጭ ተመልካች፤ ለአሁኑም ለበፊቱም ስለሆነ ሾላ በደፈናው የሚባል አዘጋገብ ስለሌለ ነው።
ይህም የአሁኑ ጉዳይ ለአትሌቲክሱ ማህበረሰብ ግልፅ ያደረገው ነገር ቢኖር ፌድሬሽኑ ተቋሙን የሚመጥን ልምድና እውቀት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ እንደሚያስፈልገው ነው።
ፌድሬሽኑ በሚቀጥለው የሪፎርም ስራው ይህንንም ክፍተት በደንብ ፈትሾ ለአትሌቲክሱ ሁለንተናዊ እድገት በኮሙኒኬሽን ያለውን ባዶነት እንዲሞላ ደወሉን ደውለናል።
14/10/2025
ጉድ ጉድ ጉድ !!! ለማሽቃበጥም ልክ አለው። ዜና ለመዘገብም ትክክለኛ መረጃና እውቀት ያስፈልጋል። ዛሬ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሙኒኬሽን ስለአትሌት መሰረት ደፋር ሽልማት የሰራውን እውቀት አልባ ዘገባ ተመልከቱ።
ትክክለኛው መረጃና ዜና ይኼውላችሁ።
በየአመቱ ስኬትንና የላቀ ስራ የሰሩ ልዩ ተሸላሚዎች ከስፖርት፣ ከኪነጥበብ፣ ከቢዝነስ ዘርፍ ተመርጠው ላደረጉት በጎ አስተዋፅኦ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን ዘንድሮ በአትሌቲክሱ የኦሊምፒክ እና ዓለም ሻምፒዮና አሸናፊ አትሌት መሰረት ደፋር ተሸለማለች።
አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት የተካሄደ ሲሆን ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣የዲባባ ቤተሰብና አትሌት ስለሺ ስህን ፣አትሌት ትዕግስት አሰፋና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ተሸላሚ ነበሩ።
መሲ እንኳን ደስ አለሽ!!!
ለትክክለኛ መረጃና ዘገባ
ይህንን ዜና ከሰራን በኋላ በአንዳንድ ሰዎች ስም በመጠቀም ምንድነው ስህተቱ ብለው የሰደቡን ቢኖሩም እኛም አላዋቂነታቸውን ሳንንቅ ይህን መልዕክት ጨምረናል።
ከመሳደብ በፊት የዜና አዘጋገብንና የቋንቋ አጠቃቀምን ማወቅ አስፈላጊ ነው። በማንኛውም ጉዳይ ላይ ስለምን ዜና እያወራህ እንደሆነ ጠንቅቀህ አውቀህ በዘገባው ፍሰት ውስጥ ተጨማሪ መረጃ መስጠት ከፈለግህ ፤ ሁነቱን ጊዜውንና ቦታውን በትክክል ገልፀህ ትዘግባለህ እንጂ ሰውን በማሳሳት በአፍሪካ ኢምፓክት የተሸለመች የመጀመሪያ ሴት አትሌት አስመስለህ ሰው ካሳሳትክ በኋላ ፤ ስለአፍሪካ ኢምፓክት እያወራህ ያወራሁት ስለአለም ኮከብ ነው ብለህ የማምለጫ መንገድ መፈለግ በስህተት ላይ ሌላ ስህተት መደረብ ስለሆነ ለወደፊቱ የዜናና ዘገባ አፃፃፍ መርሆችንና
የቋንቋ አጠቃቀም ሥርዓቶችን እንዲሁም የሙያ ሥነምግባሮችን መማር ለፈለገ በነፃ ኦንላይን ኮርስ እንሰጣለን። አሁንም
12/10/2025
ሀዊ ፈይሳ የቺካጎ ማራቶን 2025 አሸናፊ ሆናለች።
በቺካጎ ማራቶን በሴቶች ምድብ ያሸነፈች 8ኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ናት።
ሀዊ ፈይሳ በቺካጎ ማራቶን የገባችበት ሰዓት የምንግዜም የዓለማችን 5ኛው ፈጣን ሰዓት ሲሆን ከኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደግሞ የምንግዜም 2ኛው ፈጣን ሰዓት ነው።
1. ትግስት አሰፋ 2:11.53
2. ሀዊ ፈይሳ 2:14.56
3. አማኔ በሪሶ 2:14.58
4. ወርቅነሽ ደጋፋው 2:15.51
5. ሱቱሜ አሰፋ 2:15.55 በመሮጥ በኢትዮጵያዊያን የሴት አትሌቶች የማራቶን ታሪክ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ከአንደኛ እስከ 4ኛ ደረጃ የተቀመጡት በአሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ እና ፤ በከሊል የሚሰለጥኑ ሲሆኑ 5ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሱቱሜ በአሰልጣኝ ብርሀኑ መኮንን ትሰለጥናለች!!!