እግር ኳሳዊ ዜና Eger Kuwasawi Zena

እግር ኳሳዊ ዜና Eger Kuwasawi Zena

Share

እግር ኳሳዊ ዜናዎች በአማርኛ እናቀርብላችሁዋለን

Photos from እግር ኳሳዊ ዜና Eger Kuwasawi Zena's post 30/05/2026

ሰበር
=====
🔴ሊቨርፑሎች አሰልጣኛቸው አርኔ ስሎትን ማሰናበታቸው ይፋ ሆኗል።

በተያያዘ በአርኔ ስሎት ቦታ የበርንማውዙን አንዴ ራዮላን ለመቅጠር ንግግር መጀመራቸው ታውቋል ለሊቨርፑል ሑነኛው ሰው እሱ ነው ብለው በማሰባቸው ሌላ አማራጮችን ማየት አይፈልጉም ቀጣዩ የቀዮቹ አሰልጣኝም ራዮላ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ፋብሪዚዮ ሮማኖ
===========
እግርኳሳዊ ዜናዎች

29/05/2026

ሰበር
===
🔵🔴ባርሴሎናዎች የኒውካስል ዩናይትዱን እንጊሊዛዊ የመስመር አጥቂ አንቶኒ ጎርደንን በ69 ሚሊየን ፓውንድ ማስፈረማቸው ተረጋግጧል።

ተጫዋቹ በባርሳ ቤት ለአምስት ዓመት የሚያቆየውን ውል ለመፈራረም ከስምምነት ደርሷል።
======
እግርኳሳዊ ዜናዎች

22/05/2026

ሰበር
====
💎ማንችስተር ሲቲዎች ለምንግዜም ምርጡ አሰልጣኛቸው ፔፕ ጋርዲዮላ የስታዲየሙን ደቡባዊ መቀመጫ በስሙ እንዲሑም በስታዲየሙ ዙሪያ ሃውልት በማቆም ለአሰልጣኙ ያላቸውን ክብር ሊገልጹለት ነው።
==========
እግርኳሳዊ ዜናዎች

22/05/2026

የተረጋገጠ
=======
💎ማንችስተር ሲቲዎች አሰልጣኛቸው ፔፕ ጋርዲዮላ በይፋ ክለቡን መልቀቃቸውን አረጋግጠዋል አሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ በ10 ዓመት ቆይታቸው 20 ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል።
=======
እግርኳሳዊ ዜናዎች

20/05/2026

እንኳን ደስ አላችሑ መድፈኞች 🏆🎉
===================
🚨የ22 ዓመታት ጥበቃ ለ22 ዓመታት አትችሉም መባል ኮከቦቻቸውን በተቀናቃኞቻቸው ዓይናቸው እያየ ሲወሰዱ ልባቸው እየቆሰለ የተመለከቱ ውብ እግር ኳስን እንግሊዝ ውስጥ ሲያስመለክቱ ኖረው ለዛ ውለታቸው ግን ስድብና ዘለፋን ያስተናገዱት አርሰናሎች በመጨረሻም ቀኑ ደርሶ እግር ኳስ ካሳቸው።

የ2008 አስገራሚ ውብ እግርኳስ ማንም በማያቃቸው ከአካዳሚና በእርካሽ ገንዘብ በተገዙ ወጣቶች በነ ሴስክ ፋብሪጋዝ በነ ፣አልክሳንደር ህሌብ ሮሰዝስኪ ፣ኤድዋርዶ ፣ፍላሚኒ በተባሉ ልጆች ለአራት ዋንጫ እየተጫወቱ ማንም ያለረገውን ሳንሲሮ ድረስ ሄደው በወቅቱ ገናና የነበረውን ኤስሚላን በሜዳውና በደጋፊው ፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ያንበረከኩ ከሊጉ ጫፈሰ ተቃርበው በካራባኦ ካፕ ጨዋታ ኤድዋርዶን በአሰቃቂ ሑኔታ በጉዳት በማጣታቸውና አብዛኛው የቡድኑ አባላት ልጆች በመሆናቸው ያንን ጉዳት ካዩ በኋላ በስነልቦና በመጎዳታቸው የሚገባቸውንና የለፉበትን ዋንጫዎች አተው የተሳቀባቸው።

ላለፉት ሶስት ዓመታት ከማንም በላይ ለሊጉ ተፎካክረው ዋንጫዎችን ስላጡ እንደ ቀሽም የተቆጠሩ ቦትለርስ ሚዜ የመሳሰሉ ቅጽል ስም የወጣላቸው አርሰናሎችና በጽናት ሑሉንም ችለው የቆሙት ደጋፊዎች በመጨረሻም ሚኬል አርቴታ በተባለ ጀነራል እየተመሩ ፔፕ ከተባለ የዋንጫ ቀበኛ አስጨናቂ አሰልጣኝ እጅ ፈልቅቀው የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ለ14ኛ ጊዜ መሆን ችለዋል።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሑ🎉🎊

እግርኳሳዊ ዜናዎች
===========

Photos from እግር ኳሳዊ ዜና Eger Kuwasawi Zena's post 19/05/2026

ሰበር
=====

🚨 ሳውዝሃምፕተን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ከሚደረገው የፕሌይ-ኦፍ ጨዋታ ውጪ ተደርጓል :: ለቀጣዩ የውድድር ዘመንም የ4 ነጥብ ቅነሳ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። ይህ የሆነው ሰሞኑን ይፋ በተደረገው በተቃራኒ ቡድኖች ላይ በሰሩት እና ባመኑት የስለላ ተግባር ነው ።

ሳውዛምፕተኖች ሚድልስቦሮዎችን አሸንፈው የነበረ ቢሆንም በስለላቸው ከመጨረሻ ጥሎ ማለፉ ሊታገዱ ችለዋል።

በዚህም መሰረት ኃል ሲቲ ቅዳሜ ዕለት በዌምብሊ በሚደረገው የፕሌይ ኦፍ ፍፃሜ ጨዋታ ሚድልስብሮን የሚገጥም ይሆናል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Haile Gebre Selase Avenue
Addis Ababa