Yegna Manchester United - የኛ ማንቸስተር ዩናይትድ

Yegna Manchester United - የኛ ማንቸስተር ዩናይትድ ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ሁሉም መረጃ ለማግኘት ፔጁን(Like Page ) በማረግ ቤተሰብ ይሁኑኑ ይወዱናል ሁሌም ማንቼን ብቻ
❤

Fabrizo Romano:-ማንቸስተር ዩናይትድ እና ትራብዞንስፖር ለኦናና ኮንትራት ሁሉንም ሰነዶች ተፈራርመዋል ሁሉም ነገር  አልቋል ፣ አንድሬ ኦናና ከማችስተር ዩናይትድ በውሰት ትራብዞንስፖ...
08/09/2025

Fabrizo Romano:-ማንቸስተር ዩናይትድ እና ትራብዞንስፖር ለኦናና ኮንትራት ሁሉንም ሰነዶች ተፈራርመዋል ሁሉም ነገር አልቋል ፣ አንድሬ ኦናና ከማችስተር ዩናይትድ በውሰት ትራብዞንስፖርን ተቀላቅሏል።

ከዚ የተሻለ ዜና የትም አታገኙም ማንቼዎች ላይክ/ሼር እና ፎሎ አርጉን🤩

👉ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ ቢመለስ እና በ ስድስት ቁጥር ቦታ ቢሰለፍ ከ ማኑኤል ኡጋርቴ እንዲሁም ከካሴሚሮ የተሻለ ብቃት ሊያሳየን ይችላል ማርቲኔዝ በአጨዋወቱ ፈጣን ፣ በባህሪው...
07/09/2025

👉ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ ቢመለስ እና በ ስድስት ቁጥር ቦታ ቢሰለፍ ከ ማኑኤል ኡጋርቴ እንዲሁም ከካሴሚሮ የተሻለ ብቃት ሊያሳየን ይችላል ማርቲኔዝ በአጨዋወቱ ፈጣን ፣ በባህሪው እልኧኛ እና ኳስን ለመቀማት (ፕሬስ ለማድረግ) የማይታክት ተጫዋች ነው ጨዋታዎችን በሚገባ ያነባል ፣ በሜዳ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ይገምታል ፣ እናም ታክሎችን ለመግባት የማይፈራ ተጫዋች ነው ጥሩ በሚባል ደረጃ ኳስን ተቆጣጥሮ የመጫወት ችሎታ አለው ፣ በግፊት ውስጥ ሆኖ ኳስን መስጠት እና ማቀበል ይችላል ፣ የረጅም ኳስ አሰጣጡ ጥሩ የሚባል እና ብዙ ግዜ የሚሳካ ነው ፣ እናም ለመሀል ሜዳ ክፍሉን መነቃቃትን ያመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
እኔ አሞሪምን ብሆን ከኡጋርቴ እና ሳሴሜሮ ቀድሜ እሱን አሰልፈዋለሁ በክለባችን ሲፈለግ የነበረው ካርሎስ ባሌባ ከሚያቀርበው አገልግሎት ውስጥ ማርቲኔዝ 85% ያህሉን ሊሰጥህ ይችላል። ኳስ መንጠቅ ላይ ጠንካራ ተጫዋች ነው ፣ ወደፊት የሚደረጉ ቅብብሎሾችን እና በተከላካይ አማካይ ስፍራ የሚያስፈልገውን አገልግሎት ሁሉ ይሰጣል ባለፈው እንደነገርኳችሁ ተጫዋቹ በአያክስ ቤት እያለ የ 6 ቁጥር ሚናን ይዞ በርካታ ጨዋታዎችን ማድረጉ አይዘነጋም የ 6 ቁጥር ቦታ ላይ እሱ ቢጫወት እና የእሱን የተከላካይ ክፍል ሉክ ሾው የሚጫወት ይሆናል የቡድናችን አሰላለፍ በምስሉ ላይ እንዳለው ይሆናል ማለት ነው ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ ስለ እዚህ ነገር ?

ሼር/ላይክ/ፎሎ እያረጋቹ ቤተሰብ ሁኑን

እንኳን ደስ አላቹ እርስ በርስ ተባባሉ እንጂ 👇👇👇🤩
07/09/2025

እንኳን ደስ አላቹ እርስ በርስ ተባባሉ እንጂ
👇👇👇🤩

በአባቱ አዝኖበታል!!
03/09/2025

በአባቱ አዝኖበታል!!

እናንተ የወሩ ምርጥ ማን ነበር??ዮሮ ዴሊት ኤምቤሞ 👇👇ኮሜንት አርጉልን
02/09/2025

እናንተ የወሩ ምርጥ ማን ነበር??

ዮሮ
ዴሊት
ኤምቤሞ
👇👇ኮሜንት አርጉልን

ስለ አዲሱ ኮርቷና ዴቪድ ዴህያ ሴን ላመንስ: ከፒተር ሽማይክል መልቀቅ በኋላ ክለባችን ዩናይትድ በፈረንሳዊው ፋቢያን ባርቴዝ እና በአሜሪካዊው ቲም ሃዋርድ ለአመታት ሲቸገር ቆይቷል። በነዚህ ...
02/09/2025

ስለ አዲሱ ኮርቷና ዴቪድ ዴህያ

ሴን ላመንስ: ከፒተር ሽማይክል መልቀቅ በኋላ ክለባችን ዩናይትድ በፈረንሳዊው ፋቢያን ባርቴዝ እና በአሜሪካዊው ቲም ሃዋርድ ለአመታት ሲቸገር ቆይቷል። በነዚህ ወቅቶች ሰር አሌክስ ከ2001/06 ድረስ ፕሪሚየር ሊጉን ማንሳት ናፍቋቸው አልፏል ሆኖም በአያክስ ደምቆ፣ በጣልያን ምድር ደብዝዞ ለንደን ፉልሃም የከተመውን ቫን ደርሳርን ካስፈረሙ በኋላ ህይወት ሰምራ ስኬትን ተሞሽራ ማንቸስተርን ቀይ አድርጋታለች።
በዴቪድ ዴሂያ የቀይነት ጅማሮዎች ላይም ቅጥነቱ፣ የአየር ላይ ኳስ ደካማነቱ እና አይኑ ላይ የነበረበት የሩቅ እይታ ችግር ጅማሮውን ቢያከብድበትም የዩናይትድ ዋልታ ለመሆን የፈጀበት ጊዜ ግን አንድ አመት ብቻ ነበር ሴን ላመንስም ክለባችን ለገባበት የግብ ዘብ አሁናዊና ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሆነናል። ላመንስ የአጭርና መካከለኛ ርቀት ፓሶቹ፣ የሚመቱ ኳሶችን የማስቆም ልዩ ችሎታው እና በክሮስ በሚላኩ ፍልሚያዎች ያለው ብቃት ክለባችንን ከፈተና ይታደገዋል ዩናይትድን ለማሸነፍ ከቆመ ኳስ እንዲሁም ከመስመሮች አሻሙ ብሎም እድል ካለ ወደ ጎል ሞክሩ የሚለው የተቃራኒ ቡድን አሰልጣኞች ምክር ከሴን ላመንስ መፈረም በኋላ ስልታቸው የሚሰራላቸው አይመስልም። ምንም እንኳን ክለባችን ጫና ውስጥ ቢሆንም ላመንስ ከዚህ ጫና የሚያልፍበት አንድ መንገድ አለይኸውም; ባለፉት 3 ጨዋታዎች ያሳየነው እንቅስቃሴ ነው። በ3ቱ ጌሞች ያስተናገድነው ሙከራ ብዛት 24 ብቻ ሲሆን በአንጻሩ 60 ሙከራዎችን አድርገናል። ካስተናገድነው ሙከራ ውስጥ ጥቂቶቹ ነበሩ ኦን ታርጌቶቹ። እናም ላመንስ ብዙ ሙከራ ባላስተናገደ እና የሚደረጉትንም ጥቂት ሙከራዎች ማክሸፍ ከቻለ ሳይቸገር ሃገሩን፣ አየሩን፣ ሊጉን ብሎም የኮቹን ሃሳብ ተላምዶ ለመተግበር የሚያስችለውን ፋታ ያገኛል።


#ፔጁንፎሎአርጉልን
#ማንችስተርዩማይትድ

?ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ ምሽቱን በተጠናቀቀው የዝውውር መስኮት ከሞላ ጎደል የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ለማለት ያስደፍራል የቀያይ ሰይጣኖቹ ባለስልጣናት በዝውውሩ መስኮቱ ጅማሬ አሳይተ...
01/09/2025

?ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ ምሽቱን በተጠናቀቀው የዝውውር መስኮት ከሞላ ጎደል የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ለማለት ያስደፍራል የቀያይ ሰይጣኖቹ ባለስልጣናት በዝውውሩ መስኮቱ ጅማሬ አሳይተው የነበረው እንቅስቃሴ በብዙ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ ሲያስተቻቸው የቆየ ቢሆንም ...የኋላ ኋላ ከተኙበት የነቁ ይመስል በጊዜ ሂደት ቁልፍ ዝውውሮችን መፈፀም ችለዋል ክለባችን አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ከመቀላቀሉ በተጨማሪ በርከት ካሉ ነባር ተጨዋቾቹ ጋር በይፋ ተለያይቷል የላንክሻየሩ ክለብ በተገባደደው የዝውውር መስኮት በአጠቃላይ #ስምንት የሚደርሱ ተጨዋቾቹን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ ሰጥቷል ከነዚህም ውስጥ ጆኒ ኤቫንስ ፣ ክርስቲያን ኤሪክሰን እና ቪክተር ሊንደሎፍ በክለባችን የነበራቸው ኮንትራት በማብቃቱ ክለባችንን በነፃ የለቀቁ ተጨዋቾች ናቸው በተቃራኒው ደግሞ ክለባችን በውሰት እና በቋሚ ሽያጭ ተጨዋቾቹን የለቀቀ ሲሆን :

በዝርዝርም ...
አሌሀንድሮ ጋርናቾ - በ40 ሚሊየን ፓውንድ
አንቶኒ - በ21.6 ሚሊየን ፓውንድ
ራስመስ ሆይሉንድ - [ በውሰት ]
ማርከስ ራሽፎርድ - [ በውሰት ]
ጄደን ሳንቾ - [ በውሰት ]

ሌሎች ክለባችንን የለቀቁ ተጨዋቾች ሆነዋል

#ፔጁንፎሎአርጉልን

01/09/2025

ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት 3 አመታት አማካኝ ሳያስፈርም የዝውውር መስኮቱ ተዘግቶ አያውቅም ነበር:

በ 24/25 - ኡጋርቴ
በ 23/24 - አምራባት
በ 22/23 - ኤሪክሰን እና ካሴሚሮ

ዘንድሮስ?

Ben Jacobs ሩበን አሞሪም በዚህ ክረምት ከአማካኝ በተጨማሪ ፉልባክ ለማስፈረም እቅድ ነበረው... ለዚህም የብራይተኑን የግራ መስመር ተመላላሽ ኢስቱፒናንን እንዲፈርም ፈልገው ነበርነገርግ...
01/09/2025

Ben Jacobs

ሩበን አሞሪም በዚህ ክረምት ከአማካኝ በተጨማሪ ፉልባክ ለማስፈረም እቅድ ነበረው... ለዚህም የብራይተኑን የግራ መስመር ተመላላሽ ኢስቱፒናንን እንዲፈርም ፈልገው ነበርነገርግን ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ንግግር ለመግባት ፍቃደኛ አልነበሩም።

የኤሚ ዝውውር ለምን ተቋረጠ በFabrizio Romanoኤሚ ከክለባችን ጋር የነበረው ስምምነት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበር የማንቸስተር ዩናይትድ ሀሳብ የነበረውም ጄዶን ሳን...
01/09/2025

የኤሚ ዝውውር ለምን ተቋረጠ በFabrizio Romano

ኤሚ ከክለባችን ጋር የነበረው ስምምነት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበር የማንቸስተር ዩናይትድ ሀሳብ የነበረውም ጄዶን ሳንቾ እና ኤሚ ማርቲኔዝን በቋሚ ስምምነት ያለ ምንም ገንዘብ የልውውጥ ዝውውር ማድረግ ነበር ነገርግን ሳንቾ በውሰት ብቻ መልቀቅ በመፈለጉ እና ቋሚ ዝውውርን ባለመቀበሉ ይህ ስምምነት ሊሆን አልቻለም በአጠቃላይ ሳንቾ በዩናይትድ ቤት እያገኘ ያለውን £300,000 ፓውንድ ማጣት አልፈለገም።

Address

ኢትዮጵያዊ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yegna Manchester United - የኛ ማንቸስተር ዩናይትድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yegna Manchester United - የኛ ማንቸስተር ዩናይትድ:

Shortcuts

Share