01/04/2026
የአለም ዋንጫ ምድብ ይህን ይመስላል
ቼልሲን በተመለከት ዜና፣ውጤት፣የተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ታሪክ እና የዝውውር ወሬ በስፋት ይቀርባል።
01/04/2026
የአለም ዋንጫ ምድብ ይህን ይመስላል
01/04/2026
ሮም እንደወደቀች ሁሉ ጣሊያንም ወደቀች🙆።ጣሊያን ለ3ተከታታይ ግዜ የአለም ዋንጫ መሳተፍ ሳትችል ስትቀር ቦስኒያ በታሪኳ ለሁለተኛ ግዜ የአለም ዋንጫ ለመሳትፍ ትኬት ቆርጣለች።
big respect to dire police🙏🙏
የቸርነት ጉግሳ ጎል⚽
31/03/2026
የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ
ጨዋታው ተጀምሯል
🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-0 ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ 🇸🇹
ድምር ውጤት: 3-0
30/03/2026
ካፍ የሀሳብ ለውጥ አድርጓል። በዚህም መሰረት በዝግ ስቴዲየም እንዲካሄድ ተወስኖ የነበረው የኢትዮጵያ እና የሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ለተመልካች ክፍት እንዲሆን ፈቅዷል።
በዚህም መሰረት 10,000 ተመልካቾች በቦታው መታደም ይችላሉ። ጨዋታው ነገ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ስቴዲየም ይካሄዳል።
መልካም ዕድል ለብ/ቡድናችን!!
27/03/2026
#ጋዜጠኛ አሉላ ፍሬው የኦርቶዶክስን እምነት የምትከተል እና ማንቺስተር ዩናይትድን የምትደግፍ ሴት አገባለሁ ማለቱ ሊመሰገን እንጂ ከስራው ሊታገድ እና ሊከሰስ አይገባውም።
27/03/2026
#ዋሊያዎቹ በሞሮኮ ምድር ድል ቀንቷቸዋል!
የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን በሞሮኮ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።
ግቦቹ:-
• 22' ደቂቃ ከነዓን ማርክነህ — በመጀመሪያው አጋማሽ መሪነቱን ያስጨበጠች ግብ ከመረብ አሳረፈ።
• 31' ደቂቃ አቤል ያለው — ልዩነቱን በማስፋት የዋሊያዎቹን ብልጫ አረጋገጠ።
• 78' ደቂቃ አቤል ያለው — በሁለተኛው አጋማሽ ድንቅ ብቃቱን በመድገም ለቡድኑ ሦስተኛውንና የራሱን ሁለተኛ ግብ አስቆጠረ።
ይህ ድል ለቀጣዩ የማጣሪያ ጉዞ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ ሲሆን፣ ተጫዋቾቻችን ሜዳው ላይ ላሳዩት አስደናቂ ትጋት ትልቅ አድናቆት ይገባቸዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ! ድል ለዋሊያዎቹ! 🇪🇹💪
27/03/2026
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን የሚገጥመው የኢትዮጵያ አሰላለፍ
ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አርሴናል በህጻናት ላይ የሚያደርሰውን የስነ ልቦና ስብራት ሊያቆም ይገባል🤗☺
24/03/2026
Too late