Bekalu

Bekalu

Share

ልሳነ ግእዝ -->ልሳነ ኢትዮጵያ 2050 Stadium, Arena & Sports Venue

08/05/2025
07/05/2025

ዕረግ ውስተ ደብረ ናባው ዘውስተ ምድረ ሞአብ ዘመንገለ ገጸ ኢያሪኮ ወርእያ ለምድረ ከናአን እንተ እሁቦሙ ለደቂቀ እስራኤል ይምልክዋ፤
ዘዳግም 32÷49

19/01/2024

እንኳን ለበዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ! እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን ሮሜ ፮፣፬
ጥምቀት ከደዌ ሥጋ እና ከደዌ ነፍስ የሚፈውስ ፍቱን መድኃኒት ብቻ ሳይሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንመስልበት ትልቅ የልጅነት ጸጋችን ነው። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች እንዳለው “ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሣ እንዲሁ እኛ በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን” (ሮሜ. 6፡3-4) በጥምቀቱ ምክንያት ብዙዎች በአዲስ ሕይወት ተመላልሰዋል፤ ከመርገመ ስጋም ሆነ ከመርገመ ነፍስ ተፈውሰዋል። በተጨማሪም የጥምቀት በዓል ለኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሠላሳ (፴) ዓ.ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የምናስታውስበት ደማቅ ዓመታዊ በዓላችንም ነው። መጠመቅ ከክርስቶስ ልደት በፊትም ሆነ በኋላ ደዌ ስጋን ይፈውስ እንደነበር እና ብዙዎች (ንዕማን፣ ኢዮብ፣ ቅዱስ ጳውሎስ...) አዲስ ሕይወት በጥምቀተ ማይ እንዳገኙ ምሳሌ ማየት እንችላለን።
ንዕማን (መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ ፭፣፲)
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ፤ ደግሞም ጽኑዕ ኃያል ነበረ፥ ነገር ግን ለምጻም ነበረ። (፪ኛ ነገሥት ፭፣፩)
በሶርያ አደጋ ጣዮች ተማርካ ከእስራኤል ምድር የመጣች አንድ ታናሽ ብላቴና ፤ የንዕማንንም ሚስት ታገለግል በነበረበት ወቅት ለምጹን አይታ “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ኤልሳዕ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር አለቻት። ንዕማንም ከብላቴናዋ የተነገረውን መረጃ ሳይንቅ ወደ ኤልሳዕ ሔደ። ምንም እንኳ የቢዩ የነገረውን ነገር ላለመቀበል የደማስቆ ወንዞች አባና እና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉም በማለት ሞግቶ የነበረ ቢሆንም በወዳጆቹ ምክር የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ። ለምጽ የነበረው ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ” ይላል። እንደተጨማሪ ሌሎችንም ማየት ይቻላል። ዮሐንስ 9፥7 “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።”
የሐዋርያት ሥራ 22፥16 “አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።” ተብሎ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስም ታዝዟል።
ዛሬም ላይ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የልጅነት ጥምቀት “ልጅነት የምታሰጠዋ ጥምቀት አንዲት ናት” (ኤፌ 4፡4-5) በተባለው መሰርት አንድ ጊዜ ወንዶች በ፵ ቀናችን ሴቶች በ፹ ቀናቸው አስቀድመን በሥጋ ከእናትና አባታችን በዘር በሩካቤ እንደተወለድንና የሥጋ ልጅነትን እንዳገኘን ሁሉ በማየ ገቦ ስንጠመቅ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ እንወለዳለን፡፡ ይህንን አስመልክቶ ጌታችን “ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” በማለት (ዮሐ.3፥3 እና 6) በምሥጢረ ጥምቀት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ስለመገኘቱ አስተምሯል፡፡ ሐዋርያውም በጥምቀት ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ አስመልክቶ ሲናገር “አባ አባት ብለን የምንጮኸበትን (የምንጣራበትን) የልጅነትን መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈስ ጋር ይመሰክራል” ብሏል (ሮሜ.8፥15-16)፡፡ ይላል።
ይህም በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ሊፈጸም ይችላል ።
 የውሃ ጥምቀት በካህናት አማካኝነት በተጸለየበት ውሃ ውስጥ በሥላሴ ስም ተጠምቀን በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከእግዚአብሔር የምንወለድበት ነው (ዮሐ 3፡3-6)
 የእሳት ጥምቀት በፍጹም ልብ የክርስትናን ትምህርት አምነው ከመጠመቃቸው በፊት በሰማዕትነት የሚያርፉ ሰማዕታት እግዚአብሔር ባወቀ የልጅነትን ጥምቀት ከመንፈስ ቅዱስ ወይም ከእሳት ይቀበላሉ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማለት ደግሞ በውሃ ሳንጠመቅ እግዚአብሔር በፍቃዱ ጸጋውን በመላክ የሚሰጠን ልደት ነው። ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ቅዱሳን ሐዋርያት የተጠመቁት ጥምቀት ነው (ሉቃ 3፡16 ፡ ሐዋ 1፡5 ፡ ሐዋ 2፡1-4 ፡ 1ኛ ቆሮ 12፡13)፡፡
 የደም ጥምቀት ሲሆን ይህ የሰማዕታት የጥምቀት ዓይነት ነው። የክርስትናን እምነት በመማር ላይ ሳሉ ወይም ተምረው ሳይጠመቁ ወይም ሁለቱንም ሳያውቁ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ብለው መሥዋዕት መሆናቸውን ተመልክተው “በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምነው እና መስክረው በሰማዕትነት የሚሞቱ ሰዎች ደማቸው /ስቃያቸው/ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ጥምቀት ይቆጠርላቸዋል። ልጅነትን ያገኙበታል፤ ኃጢአታቸውም ይሰረይላቸዋል።
 የንስሐ ጥምቀት፡ የንስሐ ጥምቀት ልጅነትን ላገኙ ሰዎች ሕይወት ፈተና ለሚደርስባቸው ድካምና ጉስቁልና ፈውስ እንዲሆን የሚሰጥ ሊደጋገምም የሚችል የጥምቀት ዓይነት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያጠምቀው የነበረ ጥምቀት የንስሐ ጥምቀት ማሳያ ነው፡፡ ምንም እንኳን ዮሐንስ ጥምቀትን ያጠምቅ የነበረ ቢሆንም የዮሐንስ ጥምቀት ልጅነትን የሚያሰጥ ጥምቀት አልነበረም:: የዮሐንስ ጥምቀት የንስሐ ጥምቀት ነበር:: ራሱም አንዲህ ሲል መስክሯል “እኔ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ …ከኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ግን በእሳት ያጠምቃችኋል..” (ማር 1፡4-8 ማቴ 3፡11 ሉቃ 3፡16 ሐዋ 19፡4)፡፡ በነቢዩ ሕዝቅኤልም ‹‹ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝብም ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ›› (ሕዝ 36፡25-28) ተብሎ የተtነገረውም የንስሐ ጥምቀትን የሚያመለክት ነው፡፡
እንደአጠቃላይ ምስጢረ ጥምቀት ከሥጋ የተወለደ ሰው ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዶ የእግዚአብሔርን የጸጋ ልጅነት የሚያገኝበት ታላቅ ምስጢር ነው፡፡ ይህም ምስጢር ከሌሎች ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ቀዳሚ ነው ፡፡ በሥላሴ ስም የተጠመቀ ሰውም አምላኩ ክርስቶስ፣ እምነቱ ክርስትና፣ ማንነቱ ክርስቲያን፣ እናቱ ቤተክርስቲያን ይሆናሉ፡፡
ይህም የጥምቀት ቀን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢረ ጥምቀትን ራሱ ተጠምቆ አርአያ በመሆን፣ ጥምቀት ለመዳን አስፈላጊ መሆኑን በማስተማር፣ በሠላሳ (፴) ዓ.ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የምናስታውስበት ደማቅ ዓመታዊ በዓላችን እና እሱን የመንመስልበት መታሰቢያችን ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! ይቆየን
መጋቤ ሐዲስ እንጅነር በቃሉ ቢምረው

06/01/2024

ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት።
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። (ሉቃስ ፪፣፲፩)
አዳዲስ ኹነት የተከናወነበት እንደ ክርስቶስ ልደት ያለ ክስተት ዓለም አስተናግዳ አታውቅም። እንኳንስ ከዛሬ 2016 ዓመታት በፊት ለነበሩ ሰዎች ይቅርና ዛሬ ላይ ብዙ መረጃ እና ማስረጃ ብሎም ጠለቅ ያለ ሳይንሳዊ አመክንዮ ማግኘት በሚቻልበት ዘመን ላይ እንኳን ሆነን ለማመን የሚከብዱ ታላላቅ ክስተቶች ተከናውነዋል። ለምሳሌ ያህል፦
 መላእክት ከሰዎች ጋር አብረው አመስግነዋል።
 እንስሣት ተፈጥሮአዊ ባልሆነ መልኩ እስትንፋሳቸውን ገብረዋል ምስጋናም አቅርበዋል።
 ጨለማ በሚያስደንቅ እና ታይቶ በማይታወቅ ብርሃን ተሞልቷል።
 ድንግል በድንግልና ልጅ ወልዳለች።
 የወደታች ዘመናት አቆጣጠር ፍጻሜ አግኝቶ ወደላይ መቁጠር ተጀምሯል።
 ብዙ የሰማይ ሰራዊት በምድር ታይተዋል።
 ሁለት የማይጣመሩ ማንነቶች አንድ ሆነዋል... መለኮት እና ትስብዕት...
 ታላላቅ ነገስታት በፍርሃት ውስጥ ወድቀዋል።
 በጽንሰቱ ወቅት የስድስት ወር ሕጻን ሳይቀር ሀሴት አድርጓል።
 ሌላም ብዙ እጅግ ብዙ ተአምራት ተከናውኗል።
ይህ ሁሉ የሆነው ከዛሬ 2016 ዓመታት በፊት በዳዊት ከተማ በቤተልሄም ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት የተወለደው በዚህ ጊዜ ነበር። ልደቱም በተመቻቸ ቦታ፣ ቤት ውስጥ ወይም ሆስፒታል አልነበረም። ይልቁንም በእንስሣት ማደሪያ ውስጥ በበረት ነው የተወለደው።
ይህም የሆነው በወቅቱ የሕዝብ ቆጠራ ስለነበረ ከተማዋ በሰዎች ስለተሞላች ማደሪያም ሆነ ማረፊያ ማግኘት ቀላል አልሆነምና ድንግል ማርያም የመውለጃ ጊዜዋ ሲደርስ በበረት ውስጥ በከብቶች ማደሪያ የበኵር ልጇን ወለደችው። አውራ ጣቱንም ካሰረች በኋላ በጨርቅ ጠቅልላ ግርግም ላይ አስተኛችው።
ወቅቱም የብርድ ጊዜ ነበርና በማደሪያቸው ለተወለደው ህጻን የበረቱ ውስጥ እንስሣት በትንፋሻቸው ሙቀት ሰጡት።
የልደት በዓል በስጦታዎች የተሞላ ነው። ከእንስሣት እስትንፋስ እስከ ሰብዐ ሰገል (የምሥራቅ ጠቢባን) የወርቅ፣ የእጣን እና የከርቤ ስጦታዎች ተበርክተዋል።
ዛሬም እኛ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ስናከብር ከጎናችን ያሉ እና የኛን ድጋፍ የሚፈልጉ እኅት ወንድሞችን እያሰብን እና “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” የሚለውን አምላካዊ ቃል በተግባር የምንገልጽበት ዕለት በመሆኑ እርስ በርስ በመጠያየቅ አብሮነታችንን እናረጋግጥ።
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።
ይቆየን!!!
መልካም በዓል!!!

Bekalu Bimrew in የዮቶር ቤተሰቦች የመንፈሳዊ ትምህርት መመማሪያ 05/03/2023

ውድ ጓደኞቼ!!!
ይህ ወቅት የቤተክርስቲያንን እና የሀገራችንን ጉዳይ እንደራሳችን ጉዳይ የምናይበት ነው።
ቀና ልብ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቻችን እኩል ከኛው ጋር እየተፈተኑ ነው። ከኃይማኖት እና ከሀገር በላይ የምንሳሳለትም ሆነ የምናስብለት ምንም ነገር ስለሌለ ስለምናየው ችግር ሁሉ በድፍረት ትክክል ነው የምንለውን የመፍትሔ ሃሳብ እናስቀምጥ።
እራሳችንን የመፍትሔው አካል አድርገን በየአንዳንዱ የእለት ከእለት እንቅስቃሴአችን ለቤተክርስቲያናችን ብሎም ለሀገራችን የሚበጅ ተግባር እንፈጽም።

Bekalu Bimrew in የዮቶር ቤተሰቦች የመንፈሳዊ ትምህርት መመማሪያ ይህ ወቅት የቤተክርስቲያንን እና የሀገራችንን ጉዳይ እንደራሳችን ጉዳይ የምናይበት ነው። ሁሉም የዚህ ግሩፕ አባላት ቀና ልብ ያላቸውን ኦርቶዶክሳውያን አባል ያድርግ። ስለምናየው ችግ...

09/02/2023

ዓለም ከኦርቶዶክስ ምእመናንን ታዛዠነት ሊማር ይገባል።
ሰው እንዴት እስከ ሞት ይታመናል?
ይህ ወቅት ተዘግቶ ለቆየው ስንክሳር ብዙ ምዕራፎችን የሚጨምር ነው።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa