Global Sport ግሎባል ስፖርት

Global Sport ግሎባል ስፖርት

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Global Sport ግሎባል ስፖርት, Sports Event, NA, Addis Ababa.

16/08/2024

ልእለ ሀያሏና እጅግ ሀብታሟ አሜሪካ በፓሪሱ ኦሊምፒክ ወርቅ ላገኙ አትሌቶቿ $37,500 ዶላር ስትሸልም፣ ብር ላገኙ ደግሞ $22,500 ዶላር እና ነሐስ ላመጡ 15,000 ዶላር ሰጥታለች።

በዕለቱ የባንክ ምንዛሬ አንድ የአሜሪካን ዶላር ወደ 102 የኢትዮጵያ ብር እየተመነዘረ ነው። ይህን መሰረት በማድረግም እንደገመትኩት ከሆነ አሜሪካ ወርቅ ላገኙ አትሌቶቿ 3.9 ሚሊዮን ብር ሸልማለች ማለት ሲሆን፣ ብር ሜዳሊያ ላገኙ 2.4 ሚሊዮን ብር፣ ነሐስ ላመጡት ደግሞ 1.6 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ሸልማለች እንደማለት ነው።

ከአለም እጅግ ደሀ ሀገራት ተርታ ያቆምናት ኢትዮጵያ ግን ከአሜሪካ አንጻር ቸርነት ያልጎደላት ሆና አግኝቻታለሁ። አገራችን ኢትዮጵያ ለብቸኛው ባለ ወርቅ አትሌት 7 ሚሊዮን ብር ስትሸልም፣ ለባለ ብር ሜዳሊያ አትሌቶቿ 4 ሚሊዮን ብር ሸልማለች። ኢትዮጵያ አሠልጣኞቹን ጭምር ሸልማለች።

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ 2 ሚሊዮን ብር ቢሸለምም ነገር ግን ለኔ ስድብ ነው አይመጥነኝም ብሎ ሽልማቱን መመለሱ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል። አሜሪካ ከአለም በሜዳሊያ ብዛት አንደኛ እንድትሆን ያደረጓትን አትሌቶቿን ብቻ እንጂ አሰልጣኞችን አልሸለመችም። ለአሠልጣኝ ስባሪ ሳንቲም የማይሰጡት አሜሪካውያን ታዲያ የ 2 ሚሊየን ብር ሽልማት አይመጥነኝም የሚል አሰልጣኝ በኢትዮጵያ መኖሩን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን።

ደሀዋ አገራችን ባይኖራትም ቸር ናት።

Alemayehu Mamo
‐----------

How much do Team USA athletes get paid for winning an Olympic medal?

The payments offered through what the USOPC calls "Operation Gold" are unchanged for 2024.

Athletes will earn $37,500 for every gold medal in Paris, $22,500 for every silver and $15,000 for each bronze.

14/08/2024

The question remains: how did they succeed in colonizing Africa?

14/08/2024
14/08/2024

2002 ⏩ 2024

Cristiano Ronaldo has now scored in 𝟮𝟯 consecutive club seasons ⚽️♾

12/08/2024

ለንፅፅር

ጎረቤታችን ኬንያ ወደ ፓሪስ ኦሎምፒክ የላከችው 160 ልዑካን ቡድን ነበር ።

ከነዚህ ውስጥ ፦

- 81 አትሌቶች
- 43 አሰልጣኞች ፣ ቡድን መሪዎች እና የህክምና ባለሙያዎች
- 3 ዳኛ
- 5 የአትሌቶች ቤተሰብ
- 26 የማናጅመንት ቡድን እና
- 3 የመንግስት ተወካዮች

ሀገራችን ኢትዮጵያ በበኩሏ 275+ ልዑካን ቡድን ነበር የላከችው ።

ከነዚህ ውስጥ ፦

- 39 አትሌቶች

- 28 አሰልጣኞች እና የህክምና ባለሙያዎች

- 70 ኮሚቴዎች

ከነሱ በተጨማሪ ደግሞ በቅርቡ ሀትሪክ ስፖርት በዘገበው መሠረት

- 138 የክልል ኮሚሽነሮችና የመንግስት ዋናና ምክትል ኃላፊዎች

- ቁጥራቸው በእውን ያልታወቁ የአመራሮች ቤተሰቦች ፣ ጋዜጠኞች እና አጫፋሪዎች ተልከዋል።

✍ ሳባ

10/08/2024

በተጠባባቂው እና መጨረሻ በተካተተው አትሌት ድል አድርገናል።

ኦሎምፐመክ ሬከርድ!!

ጀግና።

Photos from Global Sport ግሎባል ስፖርት's post 10/08/2024

በፓሪስ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን የመጀመሪያው ወርቅ ለኢትዮጵያ በታምራት ሞላ! እንኳን ደስ ያለን!

in - Men's Marathon

Tamirat Tola 🇪🇹 (2:06:26) wins 's first🥇

(📷: Getty Images)

10/08/2024

Congra Ethiopia 🏅🏅🏅🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ በታምራት ቶላ አግኝታለች እንኩዋን ደስ ያለን

2:06:26
New Olympics record 😲

10/08/2024

Phenomenon (ክስተት) እየተባለ የሚሞካሸው ሮናልዶ በኢንተር ሚላን 10 ቁጥር ለብሷል። ኢንተር ጣሊያናዊውን ሌጀንድ ሮቤርቶ ባጆን ሲያስፈርም ሮናልዶ በእግር ኳስ ውስጥ ያልተለመደ ነገር አድርጓል፡ በአክብሮት እና በአድናቆት ለባጆዮ 10 ቁጥርን ተወ።

በዚያን ጊዜ ዛሞራኖ ለኢንተር እየተጫወተ ነበር እና ቁጥር 9 ለብሶ ነበር ሮናልዶ ለባጆዮ ያለውን ክብር ሲመለከት 9 ቁጥርንም በመተው ሊሸልመው ወሰነ።

እናም ዛሞራኖ በእግር ኳስ ታሪክ ያልተለመደውን ማሊያ ለብሶ ነበር፨ 1+8 ማሊያ።

በህይወት ውስጥ የተከበረ ሰው ለመሆን የመጀመሪያው እርምጃ ሌሎች ሰዎችን ማክበር ነው.

10/08/2024

ዛሬ የሚካሔዱ የኢትዮጵያውያን አትሌቲክስ ውድድር

⏰ ጠዋት 03:00

የወንዶች ማራቶን ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች - አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣ አትሌት ታምራት ቶላ እና አትሌት ደሬሳ ገለታ

⏰ ማታ 03:00

የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች - አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት ፣ አትሌት ቢኒያም መሀሪ እና አትሌት አዲሱ ይሁኔ

⏰ ማታ 03:25

የሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች - ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ

መልካም እድል 🇪🇹❤️

10/08/2024

Chelsea Team Bus for the upcoming season
😅

10/08/2024

"ኦሎምፒክ ተሳትፎ ነው እንጂ ሽልማት ግዴታ አይደለም፣ እነ ሀይሌ እና ቀነኒሳ አስለምደውን ነው እንጂ " ዶክተር አሸብር

መጀመርያውኑም እኛ ነን ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ የወጣነው እንጂ እሱ እኮ ለተሳትፎ( ለቫኬሽን) ዘመድ አዝማዱን ይዞ ፓሪስ እንደሄደ ያውቅ ነበር:: ቀድሞም ነግሮናል:: ደፋር ነው ግን በፈጣሪ!!

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


NA
Addis Ababa