The gunners fans in ethiopia

The gunners fans in ethiopia

Share

ስለ እግርኳስ በፍቅር እናወራለን በየሰዓቱ አዳዲስ መረጃን እናሳውቃለን: በጥልቅ ትንታኔ ስለ ክለቦች እናወራለን ኳስ እና ኳስን መሰረት አድርገን እንወያያለን።

12/09/2023

እንኳን ለ አዲስ ዓመት 2016 በሰላም አደረሰን ። በአዲስ ዓመት አይረሴውን 49 ጨዋታ ያልተሸነፈውን ቡድን ሀይላይት ልጋብዛችሁ።

12/09/2023

OFFICIAL

እንግሊዛዊው ተጫዋች ዴክላን ራይስ የአርሰናል የነሀሴ ወር ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል ።

06/09/2023

ኦዴጋርድ የባሎንዶር የመጨረሻ 30 እጩ ውስጥ ተካቷል።

03/09/2023

ጄሱስ ዳሎትን አስተኝቶ ምርጥ አጨራረስ ፋቢዮ ቬራ አሲስት

Photos from The gunners fans in ethiopia's post 03/09/2023

ዛሬ ልዩ ነበርን ።

03/09/2023

Arsenal

03/09/2023

Arsenal vs Man united .......ቤተሰቦች እስቲ ግምታችሁን አስቀምጡ

03/09/2023

➥ መድፈኞቹ ከ ቀያይ ሰይጣኞቹ!

አርሰናል ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

◦በሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ብዙ ደጋፊዎች ያሉዋቸው ክለቦች ዛሬ በፕሪምየር ሊጉ ይፋለማሉ ፤ የዲኤስቲቪ ቤቶች ቀድመው ጥቅጥቅ ብለው ይሞላሉ ፤ ደጋፊዎች ክለቦቸውን እየወገኑ ሲነቋቆሩ ይውላሉ ፤ በዚህ ጨዋታ መሸነፍን አምርረው ይጠላሉ።

📅 ዛሬ ነሐሴ 28/2015 ዓ/ም
🏟️ ኤምሬትስ ስታድየም
👀 አንቶኒ ቴይለር

ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ

- እውነታዎች
- አሰልጣኞች ምን አሉ
- የውጤት ግምቶች
- የቡድን ዜና እና
- ግምታዊ አሰላለፍን እንዳስሳለን...

▪|| እውነታዎች!

◍ አርሰናል ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት 8 የኤምሬትስ ስታድየም ላይ ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

◍ የዚህ ጨዋታ በከፍተኛ ጎሎች መጠን የተጠናቀቀው ውጤት የተመዘገበው በ2011 ሲሆን በጨዋታው ማን ዩናይትድ 8-2 አርሰናልን አሸንፎ ነበረ።

◍ ማን ዩናይትድ አርሰናልን 8-2 ያሸነፈው በዚሁ ወር ነሐሴ ላይ ነበረ።

◍ የዚህ ጨዋታ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ዋይን ሩኒ በ12 ጎሎች ሲሆን ከፍተኛ ጨዋታ ያደረገው ደግሞ ሪያን ጊግስ በ50 ጨዋታዎች ነው።

◍ አርሰናል እና ማን ዩናይትድ እስከዛሬ እርስ በእርስ ባደረጓቸው ጨዋታዎች አርሰናል 87 ጊዜ ሲያሸንፍ ማን ዩናይትድ 98 ጊዜ አሸንፏል 55 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል።

▪|| አሰልጣኞች ምን አሉ?

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ:

"በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለውን ታሪክ እና ያለፉትን ጨዋታዎች እናውቃለን ፤ ስለዚህ በ
እሁድ ትልቅ ፉክክር እና ትልቅ ፍልሚያ የሚጠብቀን ይሆናል ፤ በሦስት ነጥብን አሳክተን መውጣት እንደምንፈልግ ግልጽ ነው።"

የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ:

“በፕሪምየር ሊግ ውስጥ ካሉት ትልልቅ ጨዋታዎች አንዱ ነው ፤ ያንን ፍልሚያ እየጠበቅን ነው ፤ ሁልጊዜም አጓጊ ጨዋታዎች ጠንከር ያሉ ጨዋታዎች ናቸው ፤ ለደጋፊ ሁልጊዜ ይሄ ጨዋታ ትልቅ ድል ነው ሚሆነው ስለዚህ ጨዋታውን በጉጉት እንጠብቃለን።"

◍ || የውጤት ግምቶች!

90 Mins : አርሰናል 3-2 ማንቸስተር ዩናይትድ

ላውሮ ከ BBC SPORT : አርሰናል 3-2 ማንቸስተር ዩናይትድ

ጆን ኖውስ ከ Sky sport : አርሰናል 3-1 ማንቸስተር ዩናይትድ

◍ || የቡድን ዜና

➥ አርሰናል:

በአርሰናል በኩል ጁሪየን ቲምበር ከጨዋታው ውጭ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ቶማስ ፓርቴም ጉዳት እንዳስተናገደ ተነግሯል።

ጋቢ ጄሱስ ከጉዳቱ በማገገም ሙሉ ለሙሉ ለጨዋታው ብዙ ነው።

➥ ማንቸስተር ዩናይትድ:

ከአዲሱ ፈራሚ ሶፊያን አምራባት ውጪ ማን ዩናይትድ ሆይሉንድን እና ሬጉሊዮንን በጨዋታ የሚያገኝ መሆኑን ኤሪክ ቴን ሀግ ተናግረዋል።

በተጨማሪ ማን ዩናይትድ ሉክ ሻው ፣ ቫራንን ፣ ማይኖን እና አማድ ዲያሎን በጨዋታው አያገኝም።

◍ || ግምታዊ አሰላለፍ!

አርሰናል : በ 4-3-3 አሰላለፍ

ራምስዴል ፣ ዋይት ፣ ሳሊባ ፣ ማጋሀሌሽ ፣ ዚንቼንኮ ፣ ኦዴጋርድ ፣ ራይስ ፣ ቪዬራ ፣ ሳካ ፣ ኒኬቲያህ እና ማርቲኔሊ

ማንቸስተር ዩናይትድ : በ 4-2-3-1 አሰላለፍ

ኦናና ፣ ቢሳካ ፣ ሊንድሎፍ ፣ ማርቲኔዝ ፣ ዳሎት ፣ ካስሜሮ ፣ ኤሪክሰን ፣ አንቶኒ ፣ ፈርናዴዝ ፣ ራሽፎርድ እና ማርሲያል

-

31/08/2023

የአመታት በዋላ በምንሳተፍበት የቻንፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ለይ ስንት ነጥብ ይዘን ምናጠናቅቅ ይመስላቹዋል ?

31/08/2023

ድልድል

31/08/2023

ሴቪያ ጋር አርሰናል

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa