Zemen sport

Zemen sport

Share

Sport/ስፖርት :- የሁሉም አይነት የሀገር ውስጥና የውጪ ስፖርት ዘገባዎች፣ ጣፋጭና አስደናቂ የስፖርት ታሪኮች መናኻሪያ! https://www.facebook.com/profile.php?id=100068953226327
https://t.me/zemensport

02/09/2026

"የተከበሩ የአርጀንቲና አምባሳደር"!

🇦🇷️👑 በአርጀንቲና እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የሊዮኔል ሜሲ ያህል የሀገሪቱን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ አድርጎ ያነሳ ተጫዋች ማግኘት ይከብዳል። ሜሲ ሜዳ ውስጥ በሚያሳየው አስደናቂ ጥበብ እና ከሜዳ ውጭ በሚታወቅበት ትህትና የአርጀንቲናን እሴት፣ ማንነት እና በጎ ምስል ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ የዘመናችን ትልቅ ስፖርተኛ ነው።

ይህን ታላቅ አስተዋጽኦ ለመዘከርም የአርጀንቲና ኮንግረስ ለኮከቡ ልዩ እውቅና ለመስጠት ተዘጋጅቷል። በዚህም መሰረት ሊዮኔል ሜሲ "የተከበሩ የአርጀንቲና አምባሳደር" የሚል የክብር ማዕረግ የሚሰጠው ይሆናል።

የሜሲ ስም በሀገሩ አርጀንቲና ሲነሳ ሁልጊዜም ድንቅ ታሪኮችን ያስታውሰናል። ከዓመታት በፊት በሜሲ የትውልድ ከተማ ሮሳሪዮ፣ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚል የመጀመሪያ ስም እንዳያወጡ በሕግ መከልከሉ ይታወሳል። የአካባቢው ባለስልጣናት ይህንን ውሳኔ አስተላልፈው የነበረው፣ አብዛኛው ወላጅ ልጁን "ሜሲ" ብሎ መጥራት በመጀመሩ ምክንያት በትምህርት ቤቶችና በመንግስት መዝገቦች ላይ የሚፈጠረውን ከፍተኛ የስም መደናገር ለመከላከል ነበር።

በአንድ ወቅት በገዛ ትውልድ ከተማው ስሙ ለህፃናት እንዳይሰጥ እስከ መከልከል ደርሶ የነበረው የሜሲ ስም፣ ዛሬ ግን የሀገሪቱ የክብርና የማንነት ምልክት ሆኖ በመላው አርጀንቲና ኮንግረስ የከበረ "የሀገር አምባሳደር" የሚል ማዕረግን ለመቀናጀት በቅቷል።👑⚽

01/09/2026

የ477 ቀናት "ጨለማ" ሲበራ!

🚑🤩 የቶተንሃም እና የስዊድን ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ትልቅ የደስታ ዜና ሰምተዋል! የ26 ዓመቱ ኮከብ ዴጃን ኩሉሴቭስኪ ከባድ የጉልበት ቀዶ ሕክምና አድርጎ ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር ገደማ (477 ቀናት) ከሜዳ ከተራቀቀ በኋላ፣ በመጨረሻ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ የመጀመሪያ ቡድን ልምምድ ተመልሷል!

ይህንን በልዩ ሁኔታ ያከበረው ኩሉሴቭስኪ፣ “477” ቁጥር ሻማ የተቀመጠበትን ኬክ ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ በመቁረስ በደስታ ፎቶ ተነሥቷል። ቤተሰቦቹ የጻፉለት ደብዳቤም የብዙዎችን ስሜት ኮርኩሯል፣ ደብዳቤው እንዲህ ይነበባል፦

🗣️ "ከእንግዲህ ዳግም ኳስ ሊጫወት አይችልም ብለውን ነበር... ነገር ግን አንተ ማን እንደሆንክ አያውቁም ነበር! ላለፉት 477 ቀናት ከህመም፣ ከጥርጣሬ፣ ከቀዶ ሕክምናዎች እና ከማያልቁ የህክምና ልምምዶች ጋር ታግለሃል። ዛሬ ወደሚገባህ ትክክለኛው ቦታህ ተመልሰሃል። ባንተ ከሚገባው በላይ እንኮራብሃለን፤ ይህ ወደ ሜዳ ከመመለስህ በላይ የፅናትህ፣ የአልሸነፍ ባይነትህና የማንነትህ ማረጋገጫ ነው!" 🥹 🙏✨

01/09/2026

«ኬሮድ» ለ6ኛ ጊዜ በወልቂጤ ሰማይ ስር!

: በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ስፖርትን፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤንና ማህበራዊ ሁነቶችን ለማስፋፋት በሚል አያሌ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች ሲበራከቱ ይታያሉ። አብዛኞቹ ትልቅ አላማና ህልም ሰንቀው ቢጀምሩም፣ እንደጀመሩት ሳይቀጥሉ የአንድ ሰሞን መነጋገሪያ ብቻ ሆነው መቅረታቸው ግን የዘወትር እውነታ ነው።

ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ካስቆጠረውና መሰረቱን በጠንካራ ሁኔታ ከተከለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስተቀር አብዛኞቹ የጎዳና ላይ ውድድሮች በሂደት ብዙ ሳይዘልቁ ተረስተው ይቀራሉ።

ይህንን በመስበር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሳይቆራረጥ ተከታታይነቱን ያስጠበቀው በጉራጌ ዞን የሚካሄደው «ኬሮድ» የጎዳና ላይ ሩጫ ነው። ስሙ ከጉራጊኛ ቋንቋ «ሰላም» ወይም «ሰላምን ተናገር» የሚል ጥልቅ ትርጉም የያዘው ይህ ውድድር ለ6ኛ ጊዜ የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫውን የፊታችን መስከረም 10/2019 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ስፖርታዊ አቅምን ከመገንባት ባሻገር ማህበራዊ ትስስር ሲፈጥር የቆየው «ኬሮድ» የሩጫ ውድር በቀጣይ ወልቂጤ ላይ ሲካሄድ ከ20ሺ በላይ አጠቃላይ ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል። ከእነዚህም መካከል ከ25 የአትሌቲክስ ክለቦች የተወከሉ 2000 ፕሮፌሽናል አትሌቶች (1300 ወንዶች እና 700 ሴቶች) የሚሳተፉ ሲሆን፣ የዊልቸር ተወዳዳሪዎችም የዚህ አካታች ሁነት አካል እንደሚሆኑ የውድድሩ አዘጋጆች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።

የውድድሩ መስራችና ፕሬዝዳንት የቀድሞ አትሌትና አሁን አሰልጣኝ የሆነው ተሰማ አብሽሮ፣ "ለዘንድሮው አሸናፊዎች ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሽልማት በጀት ተዘጋጅቷል። የውድድሩ ዋነኛ ዓላማም በክልሉ ያሉ ተስፈኛ ወጣት አትሌቶችን ማበረታታትና በቀጣይ ለኢትዮጵያ የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ማፍራት ነው፤ ውድድሩ በወልቂጤ ብቻ ተወሰኖ አይቀርም፣ በቀጣይ ወደ ሌሎች ከተሞችም ለማካሄድ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።" ብሏል።

በሌላ በኩል በአካባቢው የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የመጣውን ነባራዊ ለውጥ አስመልካቶ የውድድሩ አዘጋጅና የክልሉ ተወላጅ የሆነው የ2020 ኦሊምፒክ የ10ሺ ሜትር አሸናፊው ኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ ከዚህ በፊት በአካባቢው የነበረው የሩጫ እንቅስቃሴ በአብዛኛው በትምህርት ቤቶች የተወሰነ እንደነበር ገልፆ፣ ኬሮድ ሩጫ ከተጀመረ በኋላ ግን በርካታ ወጣቶች ወደ አትሌቲክስ እንዲመጡና በስፖርቱ እንዲነቃቁ ማድረግ መቻሉን ተናግሯል። "አሁንም በክልሉ በርካታ አትሌቶችን ለማፍራት በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራን እንገኛለን።" በማለትም አክሏል።

በዚህ ደማቅ ስፖርታዊና ሁነት ላይ ታዋቂ ከዋክብትን ጨምሮ በርካታ ወጣትና ተስፈኛ አትሌቶች የሚካፈሉ ሲሆን፣ መስከረም 10 ወልቂጤ ከተማ የሰላምና የስፖርት አምባ በመሆን እንግዶቿን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቷን አጠናቃለች ተብሏል።

31/08/2026

👏✨ የአያክስ አምስተርዳም አካዳሚ የወደፊት ተስፋ የሆነው የ11 ዓመት በታች ቡድን ተጫዋች ሲብ ዜልደንቱይስ፣ ድንቅ የእግር ኳስ ጥበቡን ለበጎ አድራጎት በማዋል የበርካቶችን ትኩረት መሳብ ችሏል። ታዳጊው ለአያክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ገንዘብ ለማሰባሰብ ኳስ በማንጠባጠብ እያንዳንዱ ኳስ ባንጠባጠበ ቁጥር አንድ ዩሮ ሰብስቧል!

ታዳጊው ስታዲየም መሀል ቆሞ ሳይታክት እና ኳሷ መሬት ሳትነካ 3085 ጊዜ በማንጠባጠብ የተመልካቹን አፍ አስከፍቷል! በዚህ ድንቅ ብቃቱም 3085 ዩሮ ለበጎ አድራጎት ማሰባሰብ ችሏል። ይህን ያህል አንጠባጥቦ ያቋረጠውም እግሩ ደክሞት ወይም ኳስ አምልጣው ሳይሆን በአያክስ እና በሲዮን መካከል የሚደረገው የኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ ሊጀምር ጥቂት ደቂቃዎች በመቅረታቸው ብቻ ነበር!

የታዳጊውን ኳስ የማንጠባጠብ ችሎታ በስሜት ሲከታተል የነበረው መላው የሲዮንና የአያክስ ደጋፊ፣ ለታዳጊው ቆሞ በታላቅ ጭብጨባ ድጋፍና አድናቆቱን ሰጥቶታል። አጀበው። ❌❌❌

31/08/2026

🌟🇲🇱ከትናንት ጀምሮ የእግር ኳሱ ዓለም ትኩረት የማሊው ወጣት አማካይ ማሊክ ያልኩዬ ላይ አርፏል። የብራይተኑ ኮከብ ትናንት በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ ላይ ግብ ካስቆጠረ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።

ያልኩዬ ሜዳ ላይ ካለው አስደናቂ ብቃት በላይ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ግን ሌላ ነገር ነበር! ብዙዎች የፊቱን ገጽታ በማየት "ይህ ልጅ በምንም ተአምር የ20 ዓመት ወጣት ሊሆን አይችልም!" በሚል አላስፈላጊ የዕድሜ ክርክር ውስጥ ገብተዋል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ የተለየ ነው። ማሊክ ገና በሕፃንነቱ ጀምሮ የፀጉር መርገፍን በሚያስከትለው 'አሎፔሺያ' በተባለ ተፈጥሯዊ ችግርን አልፎ የመጣ ብርቱ ወጣት ነው።

በአይቮሪኮስት የሚገኘው የልጅነት አካዳሚው 'ASEC Mimosas' ይህን ያልተገባ አሉባልታዎችና ክርክሮች ለመግታት፣ የማሊክን ከ2018 እስከ 2026 የነበሩ የታሪክ ፎቶግራፎችን ይፋ አድርጓል። አካዳሚው አላስፈላጊ ጥርጣሬዎችን ለማስወገድ የዕድገት ሂደቱን በምስል በማስደገፍ የልጁን ማንነትና ዕድሜ በግልጽ አስመስክሯል።

የአንድ ተጫዋች ትልቁ መለኪያ ውጫዊ ገጽታው ሳይሆን በሜዳ ላይ የሚያሳየው ተጋድሎና ጥበብ ነው። ማሊክ ያልኩዬ በገጠመው የተፈጥሮ ሁኔታ ሳይበገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙን ማስጠራት የጀመረ የነገው ኮከብ ነው፤ ሰንደቅ አላማውን እና ተሰጥኦውን በሜዳ ላይ በሚያሳየው አስደናቂ ብቃት ብቻ መመዘን ይገባል! 🇲🇱💫

30/08/2026

⚪️"ለውጥማ አለ!"🔥

ፖርቹጋላዊው አወዛጋቢ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ ወደ ኃያሉ ክለብ ሪያል ማድሪድ ከተመለሱ በኋላ በሳንቲያጎ በርናቤው አዲስ አየር እየነፈሰ ነው! በሪያል ማድሪድ ቤት የሆነ አዲስ ነገር እየተቀየረ ነው!

በነጩ መልበሻ ቤት ከተለመደው የልምምድ ፕሮግራም በኋላ፣ የቡድኑ ሙሉ ተጫዋቾች አብረው ምሳ ተመግበዋል—በሳቅ፣ በጨዋታ እና ከቀን ወደ ቀን በሚጎለብት የወንድማማችነት ፍቅር የተሞላ ድንቅ ቆይታ እያደረጉ ነው። ሞሪንሆ በሜዳ ላይ ጠንካራ ቡድን ብቻ ሳይሆን፣ ከሜዳ ውጭም የማይበገር ቤተሰብ እየገነቡ ይገኛሉ። 🫂🤍

ይህች ትንሽ የምትመስል ግን ትልቅ ትርጉም ያላት ዝርዝር ነገር በሜዳ ላይ የሚታየውን አንድነት የምትወስን ሚስጥር ናት። ከሜዳ ውጭ በፍቅርና በወንድማማችነት የተሳሰረ ቡድን፣ በሜዳ ላይ ማንም የማይሰብረው ብረት ይሆናል!
👑 "ቤተሰቡ" በድጋሚ በደማቅ ሁኔታ እየተመለሰ ነው! "ማድሪዲስታስ..." የዚህን አዲስ ሪያል ማድሪድ ለውጥና ለየት ያለ የደስታ መንፈስ እያስተዋላችሁት ነው? 👀🔥⚪️🤍

30/08/2026

⚽️🇮🇹 የቀድሞው የሪያል ማድሪድ፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ኤሲ ሚላን የክንፍ መስመር ተጫዋች የነበረው ብራዚላዊ ኮከብ ሮቢንሆ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈርዶበት በብራዚል እስር ቤት በጽኑ እስራት ላይ ይገኛል። ሮቢኒሆ የእግር ኳስ ተጫዋችነት ታሪኩ በአሳዛኝ ሁኔታ ቢቋጭም፣ የሥሙ መጠሪያ የሆነው የ18 ዓመት ልጁ ሮቢንሆ ጁኒየር የአባቱን ፈለግ ተከትሎ ሜዳው ላይ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ተነሥቷል። የአባቱ የህይወት ጠባሳ ሳይበግረው በሴሪ ኤው መድረክ የራሱን ስም የሚያስጠራበትን አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ተዘጋጅቷል!

ወጣቱ አጥቂ የራሱን መንገድ ለመቀደድ ከሳንቶስ ወደ ጣሊያኑ ክለብ ጄኖዋ በውሰት ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ደርሷል። ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት ወደ ጣሊያን የተጓዘው ወጣት ተስፈኛ 8 ሚሊዮን ዩሮ የግዥ አማራጭ ተቆርጦለታል። ሳንቶስም ወደፊት ከሚሸጥበት ዋጋ 10% ያገኛል። ወጣቱ አጥቂ የህክምና ምርመራውን አጠናቆ ዝውውሩን ይፋ ለማድረግ ቀደም ብሎ ጣሊያን ደርሷል። 👏✨

29/08/2026

በሲድኒ ማራቶን አዲሱ ጎበና የቦታዉን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ::

🥇 🇪🇹 Addisu Gobena 2:04:42 CRPB
🥈 🇪🇹 Chimdessa Debele 2:04:46 SB
🥉 🇱🇸 Tebello Ramakong 2:04:57 NR
4, 🇹🇿 Alponce Sinbu 2:04.57
5, 🇪🇹 Jemal Yimer 2:04.59
6, 🇪🇹 H/Mariyam Kiros 2:05.16
8, 🇪🇹 Dawit Wolde 2:06.41
12, 🇪🇹 Seifu Tura 2:08.26
14, 🇪🇹 Sisay Lema 2:08.47
15, 🇪🇹 Degefa Tolla 2:09.57
17, 🇪🇹 Hagos G/Hiwot 2:10.56 PB
19, 🇪🇹 Challa Ketema 2:12.14

C@- china abdi

Photos from Zemen sport's post 29/08/2026

«ገደብ የለሽ ሕልም እና የጽናት ውጤት!»

በማራቶን እጅግ ስኬታማ መሆን ከቻሉ የዘመናችን አትሌቶች ግንባር ቀደም የሆነው ኬንያዊ ኮከብ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ፣ በቪየና ማራቶን የሰውን ልጅ የሩጫ ገደብ በመስበር ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች (በ1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ) በመሮጥ ዓለምን ያስደመመበትን ገድል ለማሰብ የተዘጋጀው ልዩ የአይሱዙ ተሽከርካሪ (Kipchoge 1:59 Limited Edition D-Max) የመጨረሻውና 159ኛው መኪና በስጦታ ተበርክቶለታል።

የጃፓኑ ግዙፍ የመኪና አምራች አይሱዙ የምስራቅ አፍሪካ ቤተሰቦች በልዩ ትኩረት ያዘጋጇቸው እነዚህ 159 ተሽከርካሪዎች፣ እያንዳንዳቸው የኪፕቾጌን ስም፣ የክብር ፊርማ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ «ገደብን ማለፍ» የሚለውን የጽናት ታሪኩን በኩራት የተሸከሙ ናቸው።

ኪፕቾጌ ይህ ታሪካዊ ስጦታ በተረከበበት ወቅት በደስታና በክብር በተሞላ ስሜት «ከዚያች የማትረሳ የቪየና ማለዳ ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ቀን በኬንያ ጎዳናዎች ላይ እስከሚንከባለሉት 159 ተሽከርካሪዎች ድረስ ያለው ጉዞ፣ በእውነትም በጽናትና በሂደት በሚያምኑ 159 ባለቤቶች የተጻፈ የጋራ ድል ነው!» በማለት ተናግሯል። ይህ ተራ የመኪና ሽልማት ሳይሆን፣ በቁርጠኝነትና በጠንካራ ስራ የማይቻል የሚመስልን ግብ ማሳካት እንደሚቻል ለዓለም ያወጀ የጽናትና የህልም ማረጋገጫ ማህተም ነው ተብሏል።

29/08/2026

🇪🇹 የታሪክ አሻራ ዳግም የሚታደስበት የሲድኒ ማራቶን!

: ለኢትዮጵያውያን የአትሌቲክስ ቤተሰቦች “ሲድኒ” ስትጠራ የደስታ ትዝታ፣ የታሪክ አሻራ እና የጀግንነት ወግ አብሮ ትዝ ይላል። ከ26 ዓመታት በፊት በ2000 የሲድኒ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በታሪኳ ያልተደገመ ድንቅ ውጤት ስታስመዘግብ፣ ጀግናው አትሌት ገዛኸኝ አበራ ከ32 ዓመታት በኋላ የማራቶን የወርቅ ዘውድን ወደ ሀገሩ የመለሰበት ታሪካዊ ስፍራ ነበረች።

የዚያ ኦሊምፒክ የመዝጊያ መርኃግብር የሆነውን የማራቶን ውድድርን ምክንያት በማድረግ ሲድኒ በየዓመቱ ታላቅ የማራቶን ውድድር ማዘጋጀቷን ቀጥላለች። ዛሬ ደግሞ ያ የታሪክ መድረክ ከሰባቱ የዓለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች አንዱ ለመሆን በበቃው የፕላቲኒየም ደረጃ በያዘው የሲድኒ ማራቶን ምሽት 5:00 ሰዐት ጀምሮ የርቀቱን ከዋክብት ሊያፋልም ተዘጋጅቷል!

በወንዶቹ ውድድር የቦታው ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ኃይለማሪያም ኪሮስ በ2:06:06 በሆነ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበውን ያለፈው ዓመት ድል ለመድገም ወደ ፍልሚያው ይገባል። ነገር ግን መንገዱ አልጋ በአልጋ አይሆንም! በቅርቡ በቶኪዮ የዓለም ቻምፒዮን መሆን የቻለው ታንዛኒያዊው አልፎንስ ሲምቡን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ኮከቦች ለኃይለማሪያም ከባድ ፈተና ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቦስተን ማራቶን አሸናፊውና የ2:01:48 አስደናቂ ሰዓት ያለው አትሌት ሲሳይ ለማ የአሸናፊነት ቅድመ ግምቱን በመምራት የሚሰለፍ ሲሆን፣ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ኮከብ ልኡል ገብረስላሴ፣ ዳዊት ወልዴ፣ ሰይፉ ቱራ እና አዲሱ ጎበና ቀላል ግምት የሚሰጣቸው አትሌቶች አይደሉም። በ5 እና 10 ሺህ ሜትር እንዲሁም በሀገር አቋራጭ ስሙ የገነነው ሀጎስ ገብረሕይወት ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን ብቅ ብሎ የመጀመሪያ አሻራውን ለማስቀመጥ ይህን ታሪካዊ መድረክ መርጧል። ሀጎስ ምናልባትም ባለፉት በርካታ ዓመታት የትራክ ቀንደኛ ተቀናቃኙ ዮሚፍ ቀጄልቻ በመጀመሪያ ማራቶኑ ለንደን ላይ የፈፀመውን ገድል ሳይታሰብ ሊደግም የሚችልበት እድልም ዝግ አይደለም።

በሴቶቹ ውድድርም የኢትዮጵያውያን የማራቶን ንግስና ምሽቱን ሲድኒ ላይ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል። ሹሬ ደሚሴ፣ ሄቨን ኃይሉ፣ ሩቲ አጋ፣ መሠረት አበባየሁ እና አበሩ አያና በዚህ ታላቅ መድረክ ለማንፀባረቅ በውድድሩ የሚሰለፉ ኢትዮጵያውያን ኮከቦች ሲሆኑ፣ የኦሊምፒክ እና የዓለም ቻምፒዮኗ ኬንያዊት ፔሬስ ጄፕቺርቺር ዋና ተፎካካሪያቸው ትሆናለች። የሲድኒ ጎዳናዎችም አዲስ ታሪክ ሊጽፉ ጥቂት ሰዓታት ቀርተዋቸዋል—የቀደመው የታሪክ አሻራ በወርቃማ እግሮች ዳግም የሚታደስበት የሲድኒ ማራቶን! 🇪🇹🏃‍♀

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa