18/10/2022
Woldia sport degafi Mahiber
sapport our team
18/10/2022
18/10/2022
Sport
04/02/2020
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ውሎ
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ስምንተኛ ሳምንት 16 ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ተካሂደዋል። ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይደረጋሉ። የሳምንቱን ውሎም እንዲህ ተመልክተነዋል።
ምድብ ሀ
ቅዳሜ ዕለት ቢሾፍቱ ላይ በተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ገላን ከተማን የገጠመው ወሎ ኮምቦልቻ 1-0 በማሸነፍ በጥሩ ግስጋሴው ቀጥሎበታል። በመጨረሻው ደቂቃ ሀብታሙ ደሙ ያስቆጠራት ጎል ኮምቦልቻ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ለገጣፎ ለገዳዲን እግር በእግር እንዲከተል አስችሎታል።
ለገጣፎ ላይ የምድቡ መሪ ለገጣፎ ለገዳዲ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ በባለሜዳው 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። በ59ኛው ደቂቃ ዳዊት ቀለመወርቅ ለገጣፎን ቀዳሚ ሲያደርግ ኤሌክትሪክ ከ76ኛው ደቂቃ የአቻነት ግብ አስቆጥረው የነበረ ቢሆንም የጨዋታው ፊሽካ በሚጠበቅበት ወቅት ዘካርያስ ከበደ ጣፎዎችን ጮቤ ያስረገጠች የማሸነፍያ ጎል አስቆጥሯል።
አክሱም ከተማ በሜዳው አቃቂ ቃሊቲን አስተናግዶ 2-0 አሸንፏል። ሠላማዊ ገብረሥላሴ በ13ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ በመምራት ጨዋታውን ያጋመሱት አክሱሞች በ58ኛው ደቂቃ ዘካርያስ ፍቅሬ ተጨማሪ ግብ አሸንፈው ወጥቸዋል።
ደብረ ብርሃን ላይ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ከፌዴራል ፖሊስ ያደረጉት ጨዋታ በባለሜዳው 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለደብረብርሃን ሙሉቀን ወንድሙ በ10ኛው ደቂቃ ነው ያስቆጠረው።
ወልዲያ ከተማ ላይ በግዙፋ አለማቀፍ እና ኢተናሽናል በ ሸህ ሙሀመድ ሁሴን አል-አሙዲን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ወልዲያ ስፖርት ክለብ ከደደቢት በ1 አቻ ውጤት ተለያይተዋል። ደደቢቶች በ55ኛው ደቂቃ በ መድሃኔ ታደሰ ባስቆጠረው ጎል እንግዶቹ መሪ ቢሆኑም አንዱዓለም ንጉሴ 75ኛው ደቂቃ የአቻነቱን ግብ አስቆጥረው 1-1 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።
ደሴ ከተማ ከ ሶሎዳ ዓድዋ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል።
06/01/2020
ከፍተኛ ሊግ ሀ | ለገጣፎ መሪነቱን ሲረከብ ደሴ ከተማ እና ደደቢት አሸንፈዋል
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት ተካሂደዋል። ለገጣፎ ወደ አንደኝነቱ ሲመለስ ደደቢት ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል። ደሴ ከተማም ወደ ድል ተመልሷል።
በሳምንቱ ከተጠበቁ ጠንካራ ጨዋታዎች መካከል የነበረው የደሴ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ደሴ ላይ ተከናውኖ ባለሜዳው 1-0 አሸንፏል። የጦሳ ፈርጦቹን ብቸኛ የማሸነፍያ ጎል በግምባሩ በመግጨት ያስቆጠረው በ89ኛው ደቂቃ ላይ በድሩ ኑርሁሴን ነው።
ለገጣፎ ለገዳዲ በሜዳው ወልዲያን አስተናግዶ 3-0 በማሸነፍ ወደ ሰንጠረዡ አናት ከፍ ብሏል። ቡድቹ ያለ ጎል ወደ ዕረፍት ያመሩ ሲሆን ልደቱ ለማ 48ኛው እና አብዲሳ ጀማል በ51ኛውደቂቃ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ጎሎች መምራት ችለዋል። የሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት እየመራ የሚገኘው ልደቱ 82ኛው ደቂቃ ለራሱ ሁለተኛ፣ ለቡድኑ ሦስተኛ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው ተጠናቋል።
ወደ ደብረብርሃን ያመራው ደደቢት የከፍተኛ ሊግ የመጀመርያ ድሉን አሳክቷል። ከእረፍት መልስ አፍቅሮት ሰለሞን ያስቆጠራት ብቸኛ ጎል ለደደቢት ሦስት ነጥቦችን አስገኝታለች።
አክሱም ላይ አክሱም ከተማ ከገላን ከተማ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። አክሱሞች ዘካርያስ ፍቅሬ በ33ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ ቢሆኑም ከሁለት ደቂቃ በኋላ ብሩክ እንዳለ ለገላኖች ግብ አስቆጥሮ አቻ ማድረግ ችሏል።
ሶሎዳ ዓድዋ እና ወሎ ኮምቦልቻ እንዲሁም ፌዴራል ፖሊስ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ያደረጓቸው ጨዋታዎች ያለ ግብ የተጠናቀቁ መርሐ ግብሮች ናቸው።
08/12/2019
የ2012 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዓመታዊ ስብሰባ እና የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ተከናወነ
የ2011 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዓመታዊ ስብሰባና የ2012 የውድድር ዘመን የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ ረፋድ በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል።
ዝግጅቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በንግግራቸው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከነበረበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው ገልፀው ስፖርቱን ለሰላማዊ ግንኙነት መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል። ባለፈው ዓመት በአንዳንድ ቦታዎች የተከሰቱት ችግሮች በዘንድሮ ውድድር ዓመት እንዳይከሰቱ ጠንክሮ መስራት እነሰደሚገባም ገልፀዋል። “ሁላችሁም ወደ ምትሄዱበት ቦታ የሰላም አምባሳደር መሆን አለባችሁ።” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመቀጠል ከከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አቶ ስንታየው ወልደማርያም የ2011 የውድድር ዘመን አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም አቶ ፍቃዱ ጥላሁን ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የ2011 ውድድር ዓመት የዳኝነት አፈፃፀም ሪፖርት ለተሰብሳቢዎች ቀርቧል።
መርሃግብሩ ከሻይ እረፍት መልስ በማስከትል የ2012 የውድድር ደንብ የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አባል አቶ ኃይሉ ምህረትአብ አማካይነት ቀርቧል ፤ የ2012 የምድብ ድልድል እንዴት በምን መልክ ተመደቡ የሚለውን በኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ በሆኑት ሻምበል ሀለፎም ቀርቧል። በመቀጠል ከተሳታፊዎች በቀሩቡት ሪፖርቶችና በቀጣይ ውድድሩ በምን መልክ መካሄድ አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ በርካታ ሀሳቦች ተሰጥተዋል። በሊጉ የሚዲያ ትኩረት ማጣት፣ መውጣት መውረድ ጉዳይ ፤ የውድድሩ የቅርፅ ለውጥ፣ የምድብ ድልድል አወጣጥና ሌሎች በርካታ ጉዳዩች የተነሱ ሲሆን የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ከመካሄዱ በፊት ፌዴሬሽኑ ባወጣው ምድብ ድልድል እንቀጥል፤ በፊት በነበረው ድልድል የወረዱት እና ወደላይ የወጡት ብቻ በየምድቡ ይግቡ እና እንዳአዲስ እጣ ይውጣ የሚል የሀሳብ ክርክር ተደርጦ በድጋሚ እጣ ይውጣ የሚለው ውድቅ ሆኞ በስተመጨረሻ ፌዴሬሽኑ አስቀድሞ ባወጣው ምድብ ድልድል እንቀጥል ወይም በፊት በነበረው ድልድል የወረዱት እና ወደላይ የወጡት ብቻ በየምድቡ ይግቡ የሚለው ሀሳቦች ለቤቱ ድምፅ እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን በድምፅ አሰጣጡ ወቅት የነበረው ስርአት አልባ እንቅስቃሴ ስብሰባውን ሲያውክ ተስተውሎል። በስተመጨረሻም በድምፅ ብልጫ 27 ለ9 በሆነ ውጤት ፌዴሬሽኑ ባወጣው ምድብ ድልድል እንቀጥል የሚለው ሀሳብ ፀድቋል።
በዚህም መሠረት የኢትዮጽያ ከፍተኛ ሊግ ምድቦች የሚከተሉት ሆነዋል፡-
ምድብ ሀ
ደደቢት
ሶሎዳ ዓድዋ
ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን
አክሱም ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ደሴ ከተማ
ፌዴራል ፖሊስ
ገላን ከተማ
አቃቂ ቃሊቲ
ወልዲያ
ወሎ ኮምቦልቻ
የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች
ለገጣፎ ከ ደሴ ከተማ
አክሱም ከተማ ከ ደብር ብርሃን
ገላን ከተማ ከ ሶሎዳ አድዎ
ወልዲያ ከ ፌዴራል ፖሊስ
ደደቢት ከ ኤሌክትሪክ
ወሎ ኮምበልቻ ከ አቃቂ ቃሊቲ
ምድብ ለ
መከላከያ
ሻሸመኔ ከተማ
ኢኮስኮ
ሀላባ ከተማ
ቤንች ማጅ ቡና
ጅማ አባቡና
ነቀምት ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ
ጋሞ ጨንቻ
ካፋ ቡና
ወላይታ ሶዶ
ሀምበርቾ
የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች
ወላይታ ሶዶ ከ አምበሪቾ
ከፋ ቡና ከ ቤንች ማጂ ቡና
ሻሸመኔ ከ ጋሞ ጨንቻ
አዲስ አበባ ከ መከላካያ
ነቀምት ከ ሀላባ ከተማ
ኢኮስኮ ከ ጅማ አባቡና
ምድብ ሐ
ደቡብ ፖሊስ
ኢትዮጵያ መድን
ባቱ ከተማ
ጌዴኦ ዲላ
አርባምንጭ ከተማ
ስልጤ ወራቤ
ከምባታ ሺንሺቾ
ቡታጅራ ከተማ
የካ ክፍለ ከተማ
አር
19/11/2019
እንኳን ደስ አላችሁ እኳን ደስ አለን
የ ኢትዮጲያ ውቧ ዕና ፅዱ ከተማ ባህር ዳር የተደረገውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው
ኢትዮጲያ - ከ - አይቬሪኮስት
ያገናኘው ጨዋታ
በ 15 ደቂቃ ሱራፌል ዳኛቸው በግምት 23 ሜትር አካባቢ በተገኘው ቅጣት ምት የመጀመሪያዋን ጎል ሲያስቆጥር
በ 25 ደቂቃ ደግሞ ለግብፁ ክለብ የሚጫወተው ኘሮፌሽናሉ እና የቁርጥ ቀና ልጇ ሽመልስ በቀለ ሁለተኛዋን ጎል አክሏል ። ኳሱ እደተጀመረ በ 3 ተኛው ደቂቃ አይቬሪኮስቶቹም ካለ ምንም ጎል እዳይወጡ ያረገቻቸውን ጎል አስቆጥረው ነበር ። ዋሊያወቹ በሜዳቸውና ከ 60.000 ሽ በላይ አረጓዴ ቢጫ ቀይ ሰደቃላማ ይዞ በገባው ደጋፊዋ ፊት የ አለማችንን ከዋክብት ያፈራችው ዕና ያቀፈችው የ አፍሪካዋን በኳስ ታላቅ ሀገር 2-1 አሸንፋ ወታለች ።
ዛሬ ዋሊያወቹ ወደ ሜዳ ሲገቡ ታላቅ መነሳሳት ዕና የማሸነፍ ወኔ ይዘው መግባታቸውን አስተውለናል።
እኛም ይበል ይበጂ ብለናል ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን ብለናል
25/10/2019
የምስጋና ዜና
ከዚህ ቀደም የወልድያ እስቴዲዬምን በካፍ ለማስመዝገብ ስራ መጀመራችንን ነግረናችሁ እንደነበርና የከተማው ባለሀብቶች በሙሉ ፈቃደኝነት በመነሳሳት እዛ አካባቢ የነበረውን የማይፈለግ አፈር በማንሳት እና የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ካሳ በመክፈል መሬቱን በማዘጋት ስራ መጀመሩ ይታወቃል።
ታዲያ የዚሁ ቀጣይ ስራ ለሆነው የአስፓልትና የኮብልስቶን ስራ የሚሆን የሀብት ማፈላለግ ስራ ለማከናወን
♥ከወልድያ አማራ ወጣቶች ማህበር
♥ከከተማ ነገዴወች
♥ከሀይማኖት አባቶች
♥ከሴቶች የተዋቀረ 14 አባል ያለው ኮሚቴ ለሁለት በመከፈል በአዲስ አበባና በባህርዳር እንቅስቃሴ በማድረግ
1ኛ。 Era አንድ ኪ·ሜ በ30 ሜትር የሆነና ሚድያ ያለው ከሸህ አላሞዲ አደባባይ እስከ እስቴዲየሙ ድረስ የአስፓልት መንገድ ሙሉ ወጭውን በመቻል ባስቸኳይ ሰርቶ ለማስረከብ ተስማምቶ የአማራ መንገድ ስራወች ኢንተር ኘራይዝ ከወልድያ ፍላቂት ከሚገነባው መንገድ አካል እንዲሆን ተደርጓል ።
2ኛ。የአማራ ገጠር መንገድ ኤጀንሲ በድሮው እንጨት ተራ ተገንጥሎ በአዲሱ እንጨት ተራ እስቴድዬም የሚወስደውን 1ከ·ሜ በ 20 ሜትር መንገድ የአፈር ቆረጣ እና ሙሊት አከናውኖ ለኮብልስቶን ስራ ዝግጅ በማድረግ በፍጥነት ለማስረከብ ተስማምቷል።
3ኛ。የአማራ መንገድና ህንፃ ቁጥጥርና ዲዛይን ኢንተር ኘራይዝ የዲዛይን ሙሉ ወጭ በመሸፈን በፍጥነት ለመስራት ተስማምቷል።
4ኛ。ዳ/ር አረጋ ይርዳው በተለመደ ተቆርቆሪነት የውስጥ የስታዲዬም ስራ ማለትም የሜዳውን ሳር መቀየር፣ የተጫዋቾች መግቢያ ታነል፣ ሁለት የልምምድ ሜዳ ከነ ሻወሩ እና ሌሎች ካያያዝ ጉድለት የተበላሹ ስራወችን የማረም ስራ አስጀምረውልናል።
5ኛ。የአማራ ቢሄራዊ ክልላዊ መንግስት እርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እስቴድዬሙን እንደሚያስመዘግብ ቃል በመግባት ለቀረው የድልድይና የኮብልስቶን ስራ የሚሆን ገንዘብ ከእስፓርት ኮምሽን ጋር በመነጋገር የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ መሆኑን በመቆጨትና በተቆርቋሪነት መንፈስ ነግረውን በቀጣይ ለሰሜን ወሎ ወጣት የስራ እድል እንዲያገኝና አጠቃላይ ህብረተሰብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ልማቶች ላይ ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
ይህን እንቅስቃሴ በምናደርግበት ጊዜ ከፍተኛ አስተዋፀኦ በማድረግ ታሪክ የማይረሳው ተግባር ያከናወኑ ግለሰቦች
1ኛ。አቶ ደመቀ መኮንን
2ኛ。አቶ ተመስገን ጥሩነህ
3ኛ。ዳ/ር አረጋ ይርዳው
4ኛ。አቶ ደሳለኝ ወዳጃ
5ኛ。አቶ መብት አድማሴ
6ኛ。አቶ አስማማው አድማስ
7ኛ。አቶ ጥላየ ቢተው
8ኛ。ኢንጅነር ሀብታሙ
9ኛ。ሌሎች የክልል ቢሮ ሀላፊወችና ምክትል ቢሮ ሀላፊወች ላሳያችሁን አክብሮት፣ ለነበራችሁ ቀና አስተሳሰብ፣ ሀሳባችንን ተረድታችሁ ድጋፍ በማድረግ፣ ገንቢ የሆኑ ሀሳቦችን በመስጠትና ባሳያችሁን የመቆርቆር ስሜት እጅግ የላቀ ምስጋና እያቀረብን በቀጣይ ባሉ የህብረተሰብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ የመልማት ጥያቄወች ላይ ባሳያችሁን ቆራጥነትና ተቆርቋሪነት ልክ እንድትሰሩ አደራ እያልን እኛም የወልድያ አማራ ወጣቶች ብሎም የሰሜን ወሎ አማራ ወጣቶች በምታከናውኗቸው የልማት ተግባራት ሁሉ እንደሁል ጊዜውም አብረን በመሆን እነደምናግዝ ከወዲሁ እናረጋግጥላችኀለን።
13/08/2019
ሆን ተብሎ እውቅና የተነፈገው ፤ የወልዲያ አለማቀፍ ስታዲየም አጠቃላይ መረጃ!!!
በ19 ሺ ሄክታር መሬት ስፋት ላይ ያረፈ ነው፣ -የዓለም አቀፉን እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ደረጃ የሚያሟላ 105 ሜትር ርዝመት፣ 68 ሜትር የእግርኳስ ሜዳ እና ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ደረጃን የጠበቀ የመሮጫ ትራክ አሉት፣ -ርዝመቱ 47 ሜትር፣ የጎኑ ስፋት 26 ሜትር የሆነ የተሟላ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የቅጫት ኳስ ሜዳዎችን በአንድ ላይ የያዘ ሁለገብ ሜዳ እና እያንዳንዱ 24 ሜትር በ11 ሜትር የሆኑ ሁለት የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ሜዳዎችን እንዲሁም የኦሎምፒክ ደረጃን የጠበቀ ስፋቱ 25 ሜትር በ50 ሜትር፣ ጥልቀቱ ከ2 እስከ 5 ሜትር የሚደርስ የመዋኛ ገንዳም አካቷል፡፡
-ስታዲየሙ በአንድ ጊዜ 25 ሺ ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችሉ የፕላስቲክ ወንበሮች ተገጥመውለታል፡፡ ከእነዚህ መካከል 100 ደረጃቸውን የጠበቁ ወንበሮች ለክብር እንግዶች (ቪአይፒ)፣ 50 ወንበሮች ደግሞ ለአሰልጣኞች፣ ለተቀያሪ ተጫዋቾች እና ለአራተኛው ዳኛ አገልግሎት የሚውሉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለወንዶችና ለሴቶች ተለይተው የተዘጋጁ የልብስ መቀየሪያ ክፍሎችን ይዟል፣ -ስታዲየሙ ለተመልካቾች ምቾት ሲባል ዙሪያውን ጥላ (canopy) ያለው ሲሆን በምሽት ወቅት አገልግሎት ለመስጠት 156 ዘመናዊ መብራቶች ተገጥመውለታል፡፡ የሜዳው ብርሃን በተጨዋቾች ዕይታ ላይ ተጽዕኖ ሳያሳድር ለሜዳው በቂ ብርሃን እንዲሰጥ ተደርጎ ተሰርቷል፣ -ስታዲየሙ ዙሪያውን 7 በሮች፣ በአደጋ ጊዜ ወደሜዳው ሊያስገባ የሚችል የአምቡላንስ ተሽከርካሪ መተላለፊያ በር አለው፣ ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አካቷል፡፡
ስታዲየሙ በሶስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ 32 መኝታ ክፍሎች እና ባለአንድ ፎቅ የእንግዳ ማረፊያ ያለው ሲሆን በተጨማሪም የገላ መታጠቢያ ክፍሎች፣ መጸዳጃ ቤቶች (በተለያዩ ቦታዎች ከ238 በላይ)፣ ቢሮዎች፣ የተጎዱ ተጨዋቾች ማረፊያ ክፍሎች፣ የሕክምና መስጫ ክፍሎች፣ የእንግዳ ማረፊያ አሉት፣ -የክብር ትሪብዩኑ ሕንጻ ባለሶስት ፎቅ ሆኖ በውስጡ በአንድ ጊዜ አራት ቡድኖችን ሊያስተናግዱ የሚችሉ ክፍሎች አሉት፡፡ የልብስ መቀየሪያ ክፍሎች፣ ሻወር፣ መጸዳጃ፣ የስብሰባ፣ የህክምና ወዘተ ክፍሎችም አሉት፡፡
በተጨማሪም ሕንጻው የክብር እንግዶች ማረፊያና ማስተናገጃ፣ ጨዋታዎችን በራዲዮ ወይንም በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ስምንት ቻናሎች እና የድምጽ መከላከያ (Sound proof) የተገጠሙለት የጋዜጠኞች ክፍል እንዲሁም ለተመልካቾች ምግብ ማዘጋጃ ክፍሎች አሉት፡፡
-ለስታዲየሙ በዝናብ ጊዜ መጫወት እንዲያስችል የሰረገን ውሃ ወደውጭ የሚያስተላልፍ ደረጃውን የተበቀ የተፋሰሰ ቦይ (Drange system) አለው፡፡ በተመረጡ ሥፍራዎች የድምጽ ማጉያዎች ሲስተም ተገጥመውለታል፣ የውድድር ውጤቶችን ጎላ ባለ ሁኔታ ለማስታወቅ የሚያስችል የነጥብ ማሳያ ሰሌዳ አካቷል፣ -ስታዲየሙ በአንድ ጊዜ እስከ 270 ሜትር ኪዩብ ወይም 270 ሺ ሊትር ውሃ ለማጠራቀም የሚያስችሉ 36 ታንከሮች ተገጥመውለታል፣ ድንገተኛ የእሳት አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ሶስት የውሃ የእሳት ማጥፊያዎች እንዲሁም በቁጥር 14 የሆኑ በካርቦንዳይኦክሳይድ እሳት ማጥፊያ ሲሊንደሮች በተመረጡ ቦታዎች እንዲቀመጡ ተደርገዋል፡፡
-ስታዲየሙ ከወልዲያ ከተማ በስተምዕራብ ቀደም ሲል መቻሬ እየተባለ በሚጠራና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በቅርበት የሚገኝ ሲሆን የአካባቢው መልክዐምድር ማራኪ መሆኑ ተጨማሪ ውበትን አላብሶታል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Bole
Addis Ababa