31/08/2026
"ኮቢ ማይኖ አይንሽን ጨፍነሽ የሚታይ አይነት ተሰጥኦ ያለው ነው።"
[ አላዛር አስገዶም ]
ይህ ፔጅ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ የሚወጡ መረጃዎችን ባማረ መልኩ የሚቀርብበት ቻናል ነው።
31/08/2026
"ኮቢ ማይኖ አይንሽን ጨፍነሽ የሚታይ አይነት ተሰጥኦ ያለው ነው።"
[ አላዛር አስገዶም ]
31/08/2026
ማን ዩናይትድ ተጨማሪ ተጫዋች ላያስፈርም እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል።
አመራሮቹ ትክክለኛ እድል ከተገኘ ወዲያው እንደሚጠቀሙበት ሲገለፅ ካልሆነ ግን እስከቀጣዩ ክረምት ይጠብቃሉ ተብሏል።
[Daily Mail, Talk Sport]
31/08/2026
ዚርኪዜ ወደ አሮጊቷ ጁቬንቱስ የሚያደርገው ዝውውር ያበቃለት ነገር ይመስላል ።
ቮልትማድን አስፈርመዋል ።
31/08/2026
ከማን ዩናይትድ ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው ወጣቱ አማካይ ሉዊስ ፔጅ በትላንትናው የኦልትራፎርድ ጨዋታ ታድሞ ነበር።
31/08/2026
ጆሽዋ ዚርክዚ የፊዮሬንቲናን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል !
ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር አጥቂ ጆሽዋ ዚርክዚ ከጣሊያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።
ፊዮሬንቲና ለዚርክዚ ዝውውር ባለፈው ረዕቡ ዕለት ለዩናይትድ በቋሚነት በ30 ሚሊዮን ዩሮ ማስፈረም የሚያስችላቸውን ውል ያካተተ የ5 ሚሊዮን ዩሮ የውስት ውል ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።
ሆኖም ተጫዋቹ በግል የዝውውር ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል ፤ ከፊዮሬንቲና ባሻገር ሌላኛው የጣሊያን ክለብ ጁቬንቱስ ለሊቱን ለተጫዋቹ ዝውውር ይፋዊ ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል።
ጁቬንቱሶች ለተጫዋቹ የውሰት ውል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ለውሰት ውሉ 2.5 ሚሊዮን ዩሮ እና ወደፊት በቋሚነት ተጫዋቹን በ30 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም የሚያስችላቸውን ጥያቄ ማቅረባቸው ተዘግቧል።
ዩናይትድ ከተጫዋቹ ዝውውር ከውሰት ውሉ ገንዘብ ጋር ተደምሮ አጠቃላይ የ 35 ሚሊዮን ዩሮ ጥያቄ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።
ተጫዋቹ ስለ ወደፊት ቆይታው ገና ያልወሰነበት ሲሆን ጁቬንቱሶች ከዚርክዚ ባሻገር ከኒውካስል ቮልትማዳን በተመለከተ ንግግሮች ማድረጋቸው ተነግሯል።
ዘገባው የፋብሪዚዮ ሮማኖ እና ዲማርዚዮ ነው።
31/08/2026
ማትያስ ኩኛ በኢንስታግራም ገፁ ፦
"We miss you ❤️🔥🔱 »
ደህና አደራችሁ የማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ ቤተሰቦች ?
30/08/2026
ሉክ ሾ ፦
"ከልምዴ አንፃር የመጀመርያው ጎል እንዳይቆጠርብን የተሻለ ነገር ማድረግ ነበረብኝ።
ለሰራሁትም ነገር በራሴ ላይ በጣም ተናድጄ ነበር፤ ለዚህም ኃላፊነቱን እወስዳለሁ።"
30/08/2026
ካሪክ ስለዝውውር ገበያው:-
"ቡድኑን ስለማጠናከር በተመለከተ ምንጊዜም ክፍት ነን። እኔም ለእድሎች በሬን አልዘጋም።"
30/08/2026
ዩሪ ቴልማንስ በዛሬው ጨዋታ 11.9 ኪሎ ሜትሮችን ያካለለ ሲሆን ሜዳ ውስጥ ከነበሩት ሁሉም ተጫዋቾች የተሻለም ነው።
ከዚህ በተጨማሪ 4 የጎል እድሎችን በመፍጠር ረገድ እንዲሁ ቀዳሚው ተጫዋች ነው።
አሁንም ቢሆን ከኳስ ውጭ ያለውን እንቅስቃሴ ማሻሻል አለበት። ያኔ ሰዎች ስለ እሱ ብቃት ማውራት ይጀምራሉ!!
30/08/2026
ሀሪ ማጓየር፦
"በባለፈው ጨዋታ ላይ በደረሰብን ሽንፈት ሁላችንም አዝነን ነበር፤
ምክኒያቱም በፕሪ ሲዝን ወቅት ለሀል ሲቲ ጨዋታ ስንዘጋጅ ነበር።
ዛሬ ግን ጨዋታውን ተቆጣጥረን 3 ነጥብ ማግኘት ችለናል።
ገና ሲዝኑ ጅማሮ ላይ ቢሆንም እንኳን ለቀጣዩ ጨዋታ በደንብ መዘጋጀት አለብን።"