07/11/2025
ሩበን አሞሪም - የጥቅምት ወር የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ አሰልጣኝ
ብሪያን ኢምቡሞ - የጥቅምት ወር የፕሪምየርሊጉ ኮከብ ተጨዋች
👍👍
Transfer news and all related news about our club GGMU 🛑🛑🛑
MANCHESTER UNITED🛑🛑🛑
07/11/2025
ሩበን አሞሪም - የጥቅምት ወር የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ አሰልጣኝ
ብሪያን ኢምቡሞ - የጥቅምት ወር የፕሪምየርሊጉ ኮከብ ተጨዋች
👍👍
01/11/2025
በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ መተናል።
Come on United 💪💪💪
01/11/2025
... የመጀመሪያውን አጋማሽ ዮናይትድ ጎል ቢያስቆጥርም ለካውንተር አታክ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ሲጠቁ ነበር... የዮናይትድ የተከላካይ መስመሩ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ መለወጡን የሚያሳይ የሶስቱ የመሀል ተከላካይ የሚያሳዩት እጅግ ድንቅ የሆነ መከላከል ዮናይትድን እየመራ እንዲወጣ አድርጎቷል። የሉክ ሾው አቋም እጅግ ድንቅ ነው። መረጋጋት ብቻ ነው የሚያስፈልገን በምናገኘው አጋጣሚ ጎል ለማስቆጠርም እጅግ ቅርብ ነን...➠ሼር
UNITED 🔴💪
30/10/2025
ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕርሚየር ሊጉ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ ሊመረጥ ይችላል!...
• ሶስት ጨዋታዎች
• ሶስት ድሎች
• 8 ጎሎች አስቆጠረ
• 3 ጎሎች ተቆጠረበት
• 1 ክሊን ሺት
30/10/2025
🚨🎙️የስካይ ስፖርት እና የቢቢሲ ተንታኝ ስቴፈን ዋርኖክ ማቲየስ ኩንሃን ከኤሪክ ካንቶና ጋር አነፅሯል፡-
“ማቲየስ ኩንሃ በዚህ የውድድር ዘመን ልዩ ነው። በእኔ አስተያየት የማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር መስኮት ምርጥ ፈራሚ ነው። በአንፊልድ በተደረገው የሊቨርፑል እና የዩናይትድ ጨዋታ ላይ ነበርኩ፣ እና በሜዳው ውስጥ በአንድ ማይል ርቀት ምርጡ ተጫዋች እሱ እንደሆነ አስቤ ነበር።”
“ኤሪክ ካንቶናን የሚያስታውሰኝ ትዕቢት አለው - ለማንቸስተር ዩናይትድ መጫወትን እንደወደደው ማየት ትችላላችሁ። የዩናይትድ ማልያ ለብሶ ወደ ሜዳ ሲገባ ለክለቡ ለምን እንደፈረመ ለሰዎች እያሳየ ነው።”
“በአሁኑ ገበያ፣ ለእሱ 62.5 ሚሊዮን ፓውንድ ማግኘት በጣም ጥሩ ስምምነት ነው፣ እና እሱ ቀድሞውኑ ከዩናይትድ ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ ነው። ጥፋቶችን ያስገኛል፣ ፈጣን እግሮች አሉት፣ እና በግልጽ የጎል ስጋት ነው።
“ዩናይትድን ከመቀላቀሉ በፊት ያሳሰበኝ አንድ ነገር የሥራ ፍጥነቱ እና ፕረሲንጉ ነበር፣ ነገር ግን ያንን ማድረግ እንደሚችል ማሳየት ጀምሯል። እስካሁን ድረስ በጣም ጥሩ ፈራሚ ነው።”
ገፁን ፎሎው በማድረግ በየቀኑ መረጃ ያግኙ🙏🙏🙏
29/10/2025
" ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድን ናፍቆ ነበር "
የኖቲንግሀም ፎረስት ተጨዋች ሞርጋን ጊብስ ኋይት ፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ናፍቆ ነበር ሲል ተናግሯል ።
" ባለፉት አራት እና አምስት ጨዋታዎች ዩናይትድ መጫወት በሚገባው መንገድ እየተጫወተ እንደሆነ ማስተዋል እንችላለን ተጨዋቾቹ የዚህን ክለብ አርማ ለብሶ መጫወት ምን ያክል ክብር እንደሆነ እንደተረዱ ባለፉት ጨዋታዎች እያሳዩ ነው ።"
" ይሄንን ማለትም ከሰሞኑ እያየነው የምንገኘውን ዩናይትድ ፕሪሚየር ሊጉ ጭምር ናፍቆት ነበር ።" ሲል ተናግሯል