30/08/2026
391
2 ቀናቶች ብቻ ..
የፊዮረንቲና 100ኛ አመት በዓል
ዕለተ እሁድ ነሀሴ 24/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ ይከታተሉ።
የዝውውር መስኮቱ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል።ታላላቅ ክለቦችም ክፍተቶቻቸውን ለመሸፈን የመጨረሻ አማራጮቻቸው እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
በነዚህ ሁለት ቀናት ሌሎች ታላላቅ ዝውውሮች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።
እነማን ወዴት?
የጣሊያኑ የቀድሞ ሀያል ፊዮረንቲና 100ኛ አመቱን እያከበረ ይገኛል።
ቢሆንም አንጋፋው ክለብ በቀድሞ መንገዱ ላይ አይገኝም።
በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ቆይታ እናደርጋለን።
የአውሮፓ የሊግ ጨዋታዎች ቀጥለዋል
👉 ሻምፕዮኑ ኮቨንትሪ ከሁለት ጨዋታ ሁለት ሽንፈት
በፕሌይኦፍ የተቀላቀለው ሀል ሲቲ ከ ሁለት ጨዋታ ሁለት ድል
👉 የዲዘርቢ እና ስፐርስ ደካማ ጅማሮ ቀጥሏል።በሰንጠረዡ መጨረሻ ተቀምጠዋል።
👉 ሊቨርፑል ረጅሙን የውድድር ወራቶች እንዴት ይወጣው ይሆን?በሜዳው ከሽንፈት ተርፏል።
👉 ሩበን አሞሪም በሚላን 6 ነጥብ አሳክተዋል
ዛሬ
ቼልሲ ከ ብራይተን
ማን ዩናይትድ ከ ኤፕስዊች
በነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
23/08/2026
390
ጆሴ እና ሪያል
ዌስትሀም ?
ዕለተ እሁድ ነሀሴ 17/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ ይከታተሉ።
ከ 13 አመት በኋላ ከሪያል ማድሪድ ጋር ዳግም የተወዳጁት ጆሴ ሞሪንሆ የመጀመሪያ ድላቸውን ትናንት አሳክተዋል።
አዲስ ፈራሚያቸው ባለቀ ሰአት አሸናፊ አድርጓቸዋል።ጆሴ በባርሴሎና የተያዘባቸው የበላይነት ቀልብሰው ሪያልን ያነግሱት ይሆን?
ዌስትሀም ችግር ውስጥ የገባ ይመስላል።በውቡ ስታድየሙ የለንደን ደርቢ ጨዋታ ካሸነፈ 10 ጨዋታዎች ተቆጥረዋል።
በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ቆይታ እናደርጋለን።
የአውሮፓ የሊግ ጨዋታዎች በይፋ ተጀምረዋል
👉 ኮቨንትሪ ትንሽ ቡድን መስሎ 3 ጎል ብቻ አስተናግዶ በአርሰናል ተሸንፏል።
👉 አዲስ አዳጊው ሀል ሲቲ ማን ዩናይትድን 2-0 በማሸነፍ አስደናቂ ጅማሮ አድርጓል።
👉 ረብጣ ዶላሮች ያፈሰሰው ቶተንሀም በብሬንትፎርድ 3-0 ተቀጥቷል።
👉 ማድሪድ ባለቀ ሰአት ባስቆጠረው ጎል 2-1 አሸንፏል።
ዛሬ
ኒውካስትል ከ ሊቨርፑል
ሲቲ ከ ቦርንማውዝ
በነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
16/08/2026
389
በፕሪምየርሊጉ አርሰናልን የሚፎካከር ይኖራል?
የቻዊንጋ እህትማማቾች
ዕለተ እሁድ ነሀሴ 10/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ ይጠብቁን።
የአውሮፓ የሊግ ውድድሮች እየተጀመሩ ነው።በላሊጋው የመጀመሪያዎቹ ሁለት የመክፈቻ ጨዋታዎች ሁለት ቀይ ካርዶች የታዩበት ነበር።
የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግን ጨምሮ ሌሎች ሊጎች በቀጣዮቹ ሳምንታት ይጀመራሉ።
በፕሪምየርሊጉ ሻምፕዮኑ አርሰናል ዋንጫውን ደግሞ የማግኘት እድል እንዳለው በስፋት እየተደመጠ ይገኛል።
ከዋንጫ አሸናፊነት የሚያቆመው ቡድን ይኖራል?ከሆነ እነማን?
የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ በሞሮኮ ይከናወናል።
ካሜሮን እና ማላዊ ይፋጠጣሉ
የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጎትተው ለፍፃሜ ያበቁት ደግሞ የቻዊንጋ እህትማማቾች ናቸው።
ክለቦች የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ
👉 ማን ዩናይትድ 2-4 ኤሲሚላን
👉 ቼልሲ 3-1 ሶሴዳድ
🔥 ሞርጋን ሮጀርስ ጎል አስቆጥሯል
በነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
09/08/2026
388
አራሆ ወደ ሊቨርፑል
ምርጥ ዝውውር ወይስ ስጋት?
ዕለተ እሁድ ነሀሴ 03/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ ይጠብቁን።
ሊቨርፑል በዝውውር መስኮቱ ላይ እስከ አሁን ድረስ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ አይገኝም።
ታላቁ ተጨዋቻቸው ሞ ሳላህ ከለቀቀ በኋላ ቦታው በጠንካራ ተጨዋች አልተተካም።
በሌሎች ቦታዎችም እንዲሁ ክፍተቶች ቢኖሩም የስካሁኑ ዝውውር ቡድኑን ከፍ ያደረጉ አይመስሉም።
አሁን ደግሞ አራሆ ወደ ክለቡ በውሰት ውል መቀላቀሉ ተሰምቷል።ተጨዋቹ ወደ ሊቨርፑል መዛወሩ ጥሩ ዝውውር ወይስ ስጋት?
የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ ጥቂት ቀናቶች ቀርተውታል።ክለቦችም የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ
👉 ማን ዩናይትድ 1-1 ፒ ኤስ ጂ
የአዳዲስ የማን ዩናይትድ ፈራሚዎች ጅማሮ እንዴት አያችሁት?
👉 ቼልሲ 3-0 ኤሲ ሚላን
ጂዮቫኒ ኩዌንዳ በቀኝ መስመር ላይ ዊሊያን እስቲቫኦን መፎካካር አይችልም?
ዛሬ
አርሰናል ከ ዶርትሙንድ
ሲቲ ከ አትሌቲኮ
ሊቨርፑል ከ ሞናኮ
በነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
07/08/2026
387
የተረሱት መሠረት ጣዮች
The Underrated Pioneers
ኢትዮ-አዲስ ስፖርት የነሐሴ 1/2018 የዕለተ-አርብ የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።
እግር ኳስ በየዘመናቱ ቀጥሎ ሊመጣ ላለው ነገር ፈር የቀደዱ አልያም መሠረት የጣሉ ኃያሌ ባለሙያዎችን አሳይታናለች። እነዚህ ፈር ቀዳጆች በተለያየ ኃላፊነት ላይ ሆነው ማገልገል የቻሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል አሰልጣኞችም ይገኙበታል። ሆኖም እነዚህ ታሪክ ሰሪዎች በተገቢው መጠን አድናቆትና ምስጋና ሲሰጣቸው የማንመለከትበት ጊዜ ይኖራል። የዚህ ሰለባ ከሆኑ ታላላቅ አሰልጣኞች መካከል ሁለቱን በዛሬው መሰናዶአችን እንዳስሳለን።
ታላላቆቹ የአውሮፓ ሊጎች ሊመለሱ እጅጉን ተቃርበዋል። ይህንን ተከትሎ ክለቦች የመጨረሻ ደረጃ ዝግጅታቸውን በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ እያደረጉ ይገኛሉ። በሜዳ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ከሜዳ ውጪ ደግሞ ዝውውሮች!
ነገ በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች
✅ማንችስተር ዩናይትድ ከፒ ኤስ ጂ
✅ቼልሲ ከኤሲ ሚላን
✅ኢንተር ሚላን ከጁቬንቱስ ሲጫወቱ
እሑድ ደግሞ
✅አርሰናል ከዶርትሙንድ
✅ሲቲ ከአትሌቲኮ
✅ሊቨርፑል ከሞናኮ ይፋለማሉ።
የዝውውር መስኮቱም ያልጠበቅናቸውን ዝውውሮች ጨምሮ አስደምሞናል። ሮድሪ ወደባርሳ የማቅናቱን ነገር እንዴት አያችሁት?
በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳባችሁን አጋሩን።
-የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
02/08/2026
386
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ!
የአካል ብቃት፣ጤናማ አመጋገብ፣በቂ እረፍት ..
ዕለተ እሁድ ሀምሌ 26/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።
የዛሬ ቆይታችን ከተጋባዥ እንግዶች ጋር ይሆናል።ልምዳቸውን ያካፍሉናል።
ስለ ጤናማ የኑሮ ልምምዶች፣አመጋገብ እና የአካል ብቃትን ጨምሮ በሌሎች ሀሳቦች ላይ ቆይታ ይኖረናል።
የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ ጥቂት ሳምንታት ቀርተውታል።ክለቦችም የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
👉 ቶተንሀም 2-1 ቼልሲ
👉 አርሰናል 4-1 ጂሮና
👉 ማን ዩናይትድ 2-1 አትሌቲኮ ማድሪድ
👉 ኖርጋርድ ወደ ኤቨርተን ለመዘዋወር ተስማምቷል።ይህም የጉማሬሽ ወደ አርሰናል የሚያደርገው ዝውውር ይበልጥ መቃረቡን የሚያመለክት አይሆንም?
የዛሬ ጭምጭምታዎች
👉 ማን ዩናይትድ ማይልስ ልዊስ ስኬሊን ለማዘዋወር ሁኔታዎችን እያጤነ ነው።
👉 ሲቲ ፔድሮ ኔቶ ላይ አይኑን ጥሏል።
በነዚህ እና በሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
31/07/2026
385
Delap's Dramatic Drop (3D)
ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ ሐምሌ 24/2018 የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ትውላለች።
በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ካሉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አንዱ ቼልሲ ነው። ሰማያዊዎቹ በተለያዩ ስፍራዎች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲገኙ የአጥቂ መስመራቸውም ከተጠናከሩ ቦታዎቻቸው መካከል ይጠቀሳል። አንጋፋው ዳኒ ዌልቤክ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ሲሆን ኒኮላስ ጃክሰንን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾችም በዚሁ ስፍራ የሚገኙ አማራጮች ናቸው። በዚህ ሁሉ መካከል ሊያም ዴላፕ ተረስቷል። ከአንድ አመት በፊት እንደእንግሊዝ እግር ኳስ ተስፋ ይታይ የነበረው ዴላፕ አሁን የሚገኝበት ሁኔታና የነገሮች መገላበጥ አሳዛኝ ነው። በዛሬው መሰናዶአችን በዋናነት በዚህ ዙሪያ እናደርጋለን።
✅የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ የወቅቱ ትልቅ ርዕስ ነው።ሆኖም ሰሞኑን ገበያው ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ይመስላል። ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል?
✅ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርና ፊፋ ተፋጥጠዋል። ምክንያቱ ደግሞ "የዓለም ዋንጫ ለገበያ የሚቀርብ ሸቀጥ አይደለም!" የሚል ነው። የUEFA ሀሳብ ትክክል አይመስላችሁም?
✅የሊግ ውድድሮች ለመጀመር ተቃርበዋል።ምን ያህል ጉጉት አድሮባችኋል?
በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሀሳባችሁን እያጋራችሁ ጠብቁን።
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
26/07/2026
384
የዝውውር ዝምታ በሊቨርፑል
ዕለተ እሁድ ሀምሌ 19/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።
የአውሮፓ የ 2026/2027 የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ አንድ ወር ብቻ ቀርቶታል።
ክለቦችም የቅድመ ውድድር ጊዜያቸውን በልምምድ፣በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እንዲሁም ክፍተቶቻቸውን ለመድፈን በዝውውሩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የእንግሊዙ ሊቨርፑል ግን እስከ አሁን ድረስ በንቃት ተሳትፎ እያደረገ አይገኝም።
ምንም እንኳን የዝውውር መስኮቱ ክፍት ቢሆንም የሊጉ ጅማሮ መቃረብ ተከትሎ ክለቡ በዝውውር ላይ መቀዛቀዙ ደጋፊዎችን አሳስቧል።
ሊቨርፑል ለምን ዝምታን መረጠ?
👉 ፔዤ ተጠባባቂ ተጨዋቾቹን ለሌሎች ክለቦች ማከፋፈሉን ቀጥሏል።ጎንካሎ ራሞስ ወደ ሚላን፣ ካንግ ኢን ሊ ወደ አትሌቲኮ ተቀላቅለዋል።
👉 ቪኒ፣አልቫሬዝ እና ጉማሬሽ ከ አርሰናል ጋር ስማቸው የተነሱ ተጨዋቾች ናቸው።መድፈኞቹ ማንን ማስፈረም ይችላሉ?
👉 ፓልመር፣ጇ ፔድሮ፣ሞርጋን ሮጀርስ፣ስቲቫኦ፣ፔድሮ ኔቶ እና ሌሎች።ቼልሲ ጠንካራ የአጥቂ ስብስብ ያለው ቡድን ነው ማለት እንችላለን?
በነዚህ እና በሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
24/07/2026
383
የርገን ክሎፕ- አዲሱ የጀርመን አለቃ
ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ ሐምሌ 17/2018 የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ትውላለች።
በዓለም ዋንጫው አሳፋሪ ቆይታ የነበራት ታላቋ የእግር ኳስ ሀገር ጀርመን ከገባችበት የውጤት ማጣት አዘቅት ያወጣኛል ብላ ያሰበችውን ባለግርማ ሞገስ የርገን ክሎፕ ዛሬ በይፋ ቀጥራለች። በሊቨርፑልና በዶርትሙንድ በሰሩት ተአምር ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ክሎፕም ስራውን ለመቀበል ሳያንገራግሩ ለ 2030 የዓለም ዋንጫ የታለመውን ፕሮጀክት ተቀብለዋል። በዛሬው መሰናዶአችን በዋናነት በዚህ ዙሪያ እናደርጋለን።
ከአለም ዋንጫው መጠናቀቅ መልስ የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ ተፋፍሟል።
✅ አርሰናል ብሩኖ ጊማሬሽን ማስፈረሙ የሚቀር አይመስልም።
✅ቼልሲ ላክሮአን ከፓላስ መንትፏል።
✅ሲቲ ወጣቱ አዩብ ቡአዲ ላይ አይኑን ጥሏል።
✅የዘንድሮው ዩናይትድ ድምፁን አጥፍቶ እየሰራ ነው።
✅ሊቨርፑል እስካሁን ሳላህን አልተካም።
የዝውውር ገበያውን እንዴት እያያችሁት ነው? በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሀሳባችሁን እያጋራችሁ ጠብቁን።
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
19/07/2026
382
ቆይታ ከ ተጋባዥ እንግዳ ጋር
ዕለተ እሁድ ሀምሌ 12/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።
የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ዛሬ ምሽት ይከናወናል።አርጀንቲና እና ስፔን ለሌላ ክብር ፊትለፊት ይፋጠጣሉ።
የልዊስ ዴላ ፎንቴ እንደ ቡድን የሚንቀሳቀሰው ስፔን ጠንካራ አልሸነፍ ባይነትን መገለጫው ካደረገው አርጀንቲና
የሮድሪ እና ጓደኞቹ የኳስ ፍሰት ከ ፓራዴዝ እና ጓደኞቹ የሜዳ ላይ ተጋዳይነት
አይን ውስጥ የሚገቡት ሜሲ እና ያማል?
ከወር በላይ ቆይታ በነበረው የ 48 ሀገራት ውድድር ዛሬ ከሁለቱ አንዱ በአሸናፊነት ይሞሸራሉ።አርጀንቲና ወይስ ስፔን?
እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በጋራ 10 ጎሎችን አስቆጥረው ደረጃቸውን ለይተው ወጥተዋል።
ኪሊያን ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ ከሜሲ ፊት ተቀምጧል።አሁን የምንግዜው የአለም ዋንጫው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እርሱ ነው።
ዛሬ ቆይታ የምናደርገው ከእንግዳ ጋር ይሆናል።
ማን አሸናፊ ይሆናል?
ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት