30/08/2026
🔴በተጠባቂው የሲዲኒ ማራቶን አዲሱ ጎበና የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር አሸነፈ
🔴በሴቶች ሹሬ ደምሴ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች
🔴አዲሱ ጎበና የውድድሩ አሸናፊ በመሆኑና ሪከርድ በመስበሩ 125,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
በ2025 የሲድኒ ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያዊው አዲሱ ጎበና የ2026 የሲዲኒ ማራቶን አሸናፊ በመሆን አዲስ ታሪክ አፅፏል፤አዲሱ ጎበና ተጠባቂውን የሲድኒ ማራቶን 2:04:42 በሆነ ሠዓት በመጨረስ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን አዲስ የውድድሩን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ነው አሸናፊ የሆነው።
አዲሱ ጎበና በመጨረሻው ግማሽ ማይል ከሀገሩ ልጅ እና ተፎካካሪው ቺምዴሳ ደበሌ ጋር የነበረውን ርቀት በማስፋት በሶስት ሰከንዶች ልዩነት አሸናፊ ሆኗል።
የ21 ዓመቱ አዲሱ ጎበና እና የ22 ዓመቱ ደበሌ፣ ወደፊትም በርካታ ፍልሚያዎች እንደሚኖሯቸው የሲዲኒው ማራቶን አሳይቷል።
የሌሶቶው ቴቤሎ ራማኮንጎአና 2:04:57 በሆነ ሠዓቶ በመጨረስ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፤ ይህ ውጤት ባለፈው ዓመት ሶስተኛ ከወጣበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በሁለት ደቂቃ ያህል የተሻለ ነው።
ራማኮንጎአና፣ ባለፈው ዓመት በሁለተኛነት ያጠናቀቀ ሲሆን ወጥቶ በዚህ ውድድርም እንዲሁ 2:04:57 በመግባት አራተኛ የሆነውን የኬንያውን አልፎንስ ሲምቡን በመጨረሻው የሩጫ ክፍል በፈጣን ፍጥነት (ስፕሪንት) በመቅደም ነበር ያሸነፈው።
አዲሱ ጎበና ውድድሩን ካጠናቀቀ በኋላ በሠጠው አስተያየት “በጣም ደስተኛ ነኝ፤ባለፈው ዓመት ሁለተኛ ወጥቼ ነበር፤ ከስህተቴ ተምሬ ጠንክሬ ሠርቼና ስህተቴን አርሜ ጥሩ ብቃት አሳይቼ ክብረ ወሰኑን በመስበር ማሸነፍ ችያለሁ።”ብሏል
አዲሱ ጎበና የውድድሩ አሸናፊ በመሆኑ 139,000 የአውስትራሊያ ዶላር ወይም 100,000 የአሜሪካ ዶላር ጋር ሽልማት አግኝቷል።
በተጨማሪም፣ የውድድሩን ክብረ ወሰን በመስበሩ ተጨማሪ 35,000 የአውስትራሊያ ዶላር ወይም 25,000 የአሜሪካ ዶላር) ጉርሻም አግኝቷል።
ቀደም ሲል የነበረው ክብረ ወሰን - ሲድኒ የአለም የማራቶን ሜጀርስ (World Marathon Majors) ውድድሮች አካል በሆነችበት የመጀመሪያ ዓመት (እ.ኤ.አ. 2025) የተመዘገበው - 2:06:06 ነበር።
🔴የወንዶች ምርጥ 10
1.አዲሱ ጎበና 🇪🇹— 2:04:42
2.ጨምዴሳ ደበሌ ጉደታ 🇪🇹— 2:04:46
3.ቲቤሎ ራማኮንጎና 🇱🇸— 2:04:57
4.አልፎንሶ ሲምቡ 🇹🇿— 2:04:57
5.ጀማል መኮንን 🇪🇹— 2:04:59
6.ኃይለማሪያም ኪሮስ ከበደው 🇪🇹 — 2:05:16
7.ቪንሰንት ኒጊቲች 🇰🇪— 2:05:28
8.ዳዊት ወልዴ አረጋ 🇪🇹 — 2:06:41
9.ኬኔዲ ኩሙታይ 🇰🇪— 2:06:50
10.ጊልበርት ኪቤት 🇰🇪— 2:07
በሲዲኒ ማራቶን በሴቶች ድል ወደ ኬንያ አምርቷል፤የኦሎምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮኗ፣ፕሬስ ጂፕቺርቺርን 2፡18፡31 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኝነት አጠናቀቀች። የሀገሯ ልጅ ቼፕታይ በ2፡22፡11 ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ፣ ኢትዮጵያዊቷ ሹሬ ደሚሴ በ2፡22፡33 ሰዓት ሶስተኛ ሆና አጠናቀቀች።ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን ሄቨን ሀይሉ ደሴ 2:22:57 በሆነ ሠዓት አራተኛ እንዲሁም መሠረት አበባየሁ በ2:23:40 አምስተኛ በመሆን አጠናቃለች
🔴በሴቶች Top 10
1 ፔሬስ ጂፕቺርቺር🇰🇪2:18:31
2 ኢሪን ቼፕታይ🇰🇪2:22:11
3 ሹሬ ደምሴ🇪🇹2:22:33
4 ሄቨን ኃይሉ🇪🇹2:22:57
5 መሠረት አበባየሁ🇪🇹2:23:40
6 ፕሪስካህ ቼሬኖ🇰🇪2:23:49
7 ስቴላ ቼሳንግ🇺🇬2:23:52
8 ፍቅርተ ወረታ🇪🇹2:25:18
9 ኤሊይ ፓሽሊ 🇦🇺2:28:28
10 አበሩ አያና🇪🇹2:28:30