Ethiotenama Consultancy & training

Ethiotenama Consultancy & training

Share

አጠቃላይ የጤና መረጃዎች፣ ጤና ተቋማት እና ከጤና ጋር የተያያዙ ስራዎች
Information about health, health institutions and healt

http://www.ethiotenama.com

አጠቃላይ የጤና መረጃዎች፣ ጤና ተቋማት እና ከጤና ጋር የተያያዙ ስራዎች

Information about health, health institutions and health related jobs

Photos from HagereTube's post 15/11/2025
15/11/2025

ማርበርግ ቫይረስ

1) በሽታው ምንድን ነው?

#የቫይረሱ አይነት: ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው።

#ክብደት: በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል)።
#ታሪክ: በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል።

2) ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?)
+++ ዋናው #ምንጭ: የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው።

+++ ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው #ስርጭት: ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው።
3) #ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ።

የሚከተሉትን እንመልከት
#የመጀመሪያ ደረጃ ላይ : ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት።
#ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ): ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም።
#የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)።

4)የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች
#ፈውስ: ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም።
#ህክምና: የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው።
#ፈሳሽ መተካት (IV fluids): በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው።
#የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም።
#የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት።

በጣም #አስፈላጊው ነጥብ
-) የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው።
_) ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ
1) የዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization - WHO): Marburg Virus Disease (MVD)

2) የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention - CDC : Marburg Hemorrhagic Fever (Marburg HF)

ባምላኩ አበባው
ፕሮፌሽናል ነርስ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል

Photos from Ethiotenama Consultancy & training's post 08/06/2023

#እናመሰግናለን| 346,000 ብር
#እህታችን ፍሬህይወት ተስፋዩ የልብ ቫልብ መጥበብ በህፃንነቷ ገጥሟት በሙሉወንጌል ኮምፓሽን ድጋፍ ህንድ አገር አርተፊሻል/ሰውሰራሽ ቫልቭ ተገጥሞላት ነበር። ከአስር አመት በኋላ የተገጠመው ቫልቭ በቂ ደም ማስተላለፍ ካለመቻሉ የተነሳ አንዱ ቫልቭ አቁሞ ሁለተኛው ብቻ በደም ማቅጠኛ እንክብል በመታገዝ ህይወቷን ለማቆየት እየተሰራ ነው።
ነገር ግን በቂ ደም ለሰውነቷ የመሰራጨት አቅም በማነሱ በከፍተኛ ድካም/ የአካል መዛል
የእጅና እግር እንቅስቃሴ መጓደል ገጥሟት በከፍተኛ ህመም ላይ ትገኛለች። ቤተሰቧ ለማሳከም ባላቸው አቅም ቢሯሯጡም በመጨረሻ ህይወቷን ለማዳን የቫልቭ ቅየራ ቀዶ ጥገና በአስቸኳይ ካላደረገች ህይወቷ አደጋውስጥ እንደሆነ ተገልፆላቸው በጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። ህክምናው በጥቁር አንበሳ ያለ ቢሆንም 600 ታካሚ ወረፋ መያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ደግሞ አመታት ሊወስድ የሚችል በመሆኑ የፍሬ ህይወት አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም። ሃኪሞች አቅም ካለ ወደ ግል ህክምና ተቋም ወስደው ህይወቷን መታደግ እንዳለባቸው መከሩ።
ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የሚገፉት ወላጅ ቤተሰብ በአዲስ አበባ በሚገኝ የልብ ቀዶ ጥገና ማዕከል በመሔድ ሂሳብ አስተመኑ። ጥገናውን ለማድረግ 560000/ አምስት መቶ ስልሳ ሺህ እንደሚያስፈልግ በደብዳቤ ገለፁላቸው። ወላጅ ተጨነቀ። ባለ ተስፋዋ ፍሬህይወት በህመሙ ምክንያት ትምህርት አቋርጣ ቤት ከተሰበሰበች ቆየች። ተስፋዋ ወደመመንመን ተቃረበ። መኖር ፈልጋለው ትላለች ለመተንፈስ በሚታገል ለሆሳስ ንግግር።
በኋላም የሐዋሳ ትዝታ ወደ ቤታቸው በመሔድ ሁኔታውን ካጣራ በኋላ ለናንተ ደግ እና አዛኝ ወገኖቻችን አሳወቅን። የምንኮራባችሁ ሁሌም ከመልካምነት ጎን የምትሰለፉ እናንተም አላሳፈራችሁንም። በአጭር ቀን ውስጥ ከ 100 ብር እሰከ 230,000 ብር ድጋፍ በማድረግ ወገንተኝነታችሁን አሳያችሁን። በአጠቃላይ እስከ ትላንት ብቻ 346,000 ብር ለገሳችሁ። ይህ ርብርባችሁ የፍሬን ተስፋ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቿንም ተስፋ ከጨለማ ወደ ብርሐን አሸጋገረ። ነገር ግን አሁንም 214,000 ብር ይቀራልና አነሰ በዛ ሳንል የበኩላችንን በመለገስ፣ ደውሎ አይዞሽ አለንልሽ በማለት የወጣቷን ባለብዙ ተስፋና ህልም ወጣት እንታደጋት።
ውድ ቤተሰብ የባንክ አካውንት ያስቀመጥነው የእናቷንና የአባቷን ሲሆን አጠቃላይ ስቴትመንት እንዲሁም የለጋሾችን ሁኔታ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። አዎ ፍሬ ታክማ እንደእኩዮቿ በፈገግታ ለማመስገን ትመጣለች! ፈጣሪ ይረዳታል።
መልካምነት ይከፍላል።

17/07/2022

It's not often you see a finish like this in the 10,000m!

Letesenbet Gidey held off Hellen Obiri and Margaret Chelimo Kipkemboi to take the title!

13/07/2022

አማኑኤል ሆስፒታል ታካሚ የሰራው የግርግዳ ቅብ

📷 ዶ/ር ዮናስ ላቀው ፤ የአእምሮ ህክምና ሀኪም

08/07/2022

ማንሳት የማልፈልገው ርዕስ ነበር ። ነገር ግን ብዙ አካባቢዬ ላይ ያሉ ሰዎች በዚህ ነገር ተከፍተው ስላየሁና ሰዉም እንደ እውነት እየተቀበለው ስለሆነ ትንሽ ልበልበት።

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው የተመረኩት ሀኪም ነኝ ብሎ በተገነጣጠለ እንግሊዘኛ የሆነ ፌዝ ይሁን ምር ያለየለት ቪዲዮ የሰራው ልጅ ማነው? ምን ቻናል ላይ ነው ኢንተርቪው የሰጠው? ማይክ ወይ ሪከርደር ያጣ የትኛው ሚዲያ ነው በስልክ ቃለመጠይቅ ያደረገለት? የትኛው ሀኪም ነው "graduation" ለማለት "congratulation" የሚለው?

ምን እንግሊዘኛ ባይችል "patient" የሚልን ቃል ጠፍቶበት በስድ አማርኛ ታካሚን "በሽተኛ" ብሎ የሚጠራ ሀኪም ከየት ተገኘ? ምን ቃል ቢጠፋበት በህክምናው አለም በቀን "50" ጊዜ ሳይጠራ የማይውል ቃል "patient" አይደለም እንዴ?

ህክምና እንደሌላ ትምህርት ቲዮሬቲካል አይደለም። ለስድስት ሰባት አመታት በየቀኑ seminar, morning, bedside, round እየተባለ በፈረንጂኛው ስንተካተክ አይደለም እንዴ እድሜያችንን የጨረስነው?

በየቀኑ በእንግሊዘኛ presentation ሳያቀርብ… በዚሁ ቋንቋ መልስ ሳይሰጣጥ … ሳይጨቃጨቅ የተመረቀ የትኛው ሀኪም ነው? "eachother … together" እያለ በግድ እንግሊዘኛ ለመስበር መታገልስ አላማው ምንድነው ?

በነገራችን ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ ሀኪም ያስመረቀው ያለፈው ዐመት ሚያዚያ ላይ ነው። በዚህ ዙር አዲስ የተመረቀ ሀኪም የለም።

ይሄን አይነት የሀኪምን ስም የሚያጎድፍ ስራ መስራት አላማው ምንድነው? ህዝቡስ በሀኪሙ ላይ ያለው አመኔታ እንዲሸረሸር ማድረግ ማንን ይጠቅማል። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲስ ይሄን ልጅ በስም ማጥፋት ወንጀል ሊጠይቅ አይችልም ወይ? አስቸኳይ ይቅርታ ለባለሞያውም ለተቋሙም ማድረስ ግዴታው ነው ባይ ነኝ ።

Dr. YosephWorkneh
ቴሌግራማችን: t.me/HakimEthio

Photos from Ethiotenama Consultancy & training's post 02/07/2022

ዛሬ አንድ እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ ላካፍላችሁ።ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ግለሰቦች እየሮጡ እንዲሁም እየጨው ትንሽ ልጅ አቅፈው በስራ ገበታ ይመጣሉ።ምንድ ነው ብለን ህፃኑን ከለበሰው ልብስ ስናወጣው በህይወት እና በሞት መሃል ሆኖ ያጣጥራል እራሱንም ስቷል።ወድያው እኛም የድንገተኛ እርዳታ እስትንፋስ (CPR) መስጠት ጀመርን ይሁን እና የህፃኑ እስትንፋስ እና የልብ ምት እንደቆመ ተራዳን። እኛም ክስተቱን ለማወቅ ስንሞክር አንድ አብራ የመጣች የልጁ ተንከባካቢ ውሃ የያዘ ባልዲ ውስጥ ሰጥሞ ነው አለችኝ።ምግብ ማብሰያ ገብቼ ስወጣ የህፃኑ ጭንቅላት ከባልዲው ውሃ ውስጥ ነው አለችኝ።ማመን አልቻልኩም በድንጋጤ መጨው ጀመርኩኝ አለችኝ።ጎረቤት ተሰበሰበ ህፃኑን ይዘን እየሮጥን መጣን አለችኝ ።እኔም እንባዬ መጣ ።አዛው እንዳለው የህቴን ልጅ ሞት ትዝ አለኝ።ቀጥላም ባልዲ ወስጥ ያለው ውሃ ጥልቀት ስላልነበረው ይሰጥማል ብዬ ፈፃሞ አላሰብኩም አለችኝ።እኔም እንደው ትንሽ ጀባ ልበላችሁ ።
መስጠም በእንግሊዘኛ drowning ምንድነው ??
መስጠም ውሃ ወደ ሳንባችን እንዲገባ እና የመተንፈስ ችግር እንዲከሰት ያደርጋል ። ውሃ ወደ ሳንባ ሲገባ የኦክስጅንና የካርቦንዳይኦክሳይድ ልውውጥን ያስተጓጉላል። በዚህም ምክንያት መስጠም የገጠመው ልጅ የመስጠም ምልክቶች ያሳያል ።መተንፈስ መቸገር፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ፣የፊት የከንፈር መጥቆር ።የልብ ምት መጨመር እና የምት መዛባት ።ውሃ ከአፍ ውስጥ መውጣት እንዲሁም የሆድ መነፋት ያስከትላል ።
እንደዚ አደጋ ሲያጋጥሞት ብቻዎትን ከሆኑ እርዳታን ይጥሩ።ተጎጂውን ከውሃ ውስጥ ያውጡት።ከውሃ ውስጥ ካወጡት በኃላ ተጎጅው የሚተነፍስ ከሆነ በማገገሚያ አቀማመጥ ያስተኙት ።የአንገት አጥንቶች ተሰብረው ሊሆን ስለሚችል እንዳይነቃነቅ ጥንቃቄ ያድርጉ ።ብርድ ልብስ ወይም ጃኬት ይደርቡለት።
ተጎጅው የማይተነፍስ ከሆነ ወደ ድንገተኛ መርጃ ስልክ ይደውሉ ።እንዲሁም ተጨማሪ እርዳታን ጮኸው ይጣሩ ።ተጎጅውን በጀርባው ያስተኙት አፍ ወስጥ መተንፈስ ሚከለክል ነገር ካለ በጥንቃቄ ይመልከቱ ። ባህድ ነገር ካገኙ በጣትዎ እስከደረሰበት ያስወግዱ ።እስትንፋስ (CPR ) መስጠት ይጀምሩ ።
በደቡብ አፍሪካ በየዓመቱ 600 ህጻናት ሰጥመው እንደሚሞቱ ይገመታል። ሜይ 15 ዓለም አቀፍ የውሃ ደህንነት ቀን ነው እናም በዚህ አመት ለመስጠም ተጋላጭ ለሆኑት - ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ትኩረት መስጠት እንፈልጋለን ። ታዳጊዎች በውሃ ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚያጋጥሟቸው ቦታዎች እና በቤታቸው አቅራቢያ ናቸው።
ወላጆች እና ተንከባካቢዎች - እባክዎን በቤትዎ ውስጥ ወይም በአቅራቢያዎ ያለ ማንኛውም የተከማቸ ውሃ ለልጆች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጡ። ባልዲዎች፣ ታንከሮች እና ገንዳዎች በአስተማማኝ ሁኔታ የተዘጉ ወይም ለህጻናት የማይደርሱ መሆን አለባቸው።
የአለም ጤና ድርጅት ህጻናትን ከመስጠም የሚከላከሉ አራት እርምጃዎችን ይጠቁማል፡- የውሃ አቅርቦትን የሚቆጣጠሩ እንቅፋቶችን መትከል; ለቅድመ ትምህርት ቤት ህጻናት ከውሃ ርቀው አስተማማኝ ቦታዎችን መስጠት፣ ብቃት ባለው የልጅ እንክብካቤ፣ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት የውሃ ደህንነት እና የመዋኛ ክህሎትን ያስተምሩ እና በአስተማማኝ ማዳን እና ማነቃቂያ ውስጥ ያሉ ተመልካቾችን ማሰልጠን።
ልጆች በጥቂት ሴንቲሜትር ውሃ ውስጥ ሊሰምጡ ይችላሉ። እባክዎን ቤትዎ ከውሃ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጡ።አብዛኛው የጨቅላ ህፃናት ሞት በመታጠቢያ ገንዳዎች እና በትላልቅ ባልዲዎች ውስጥ ይከሰታል።ህጻናት በውሃ ውስጥ እና በአካባቢው ሲሆኑ እንዲሁም በልጆች እና ጎልማሶች መካከል የህይወት ጃኬቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ ቅርብ ፣ የማያቋርጥ ፣ በትኩረት እና ችሎታ ያለው የአዋቂዎች ቁጥጥር።
ክትትል የማይደረግበት መዳረሻን ለመከላከል፡ ባለ አራት ጎን ገንዳ አጥር ቢያንስ 4 ጫማ ቁመት ያለው በራሱ የሚዘጋ እና የሚዘጋ በሮች ገንዳውን ከቤት እና ከጓሮው ሙሉ በሙሉ የሚለይ።
በቤት ውስጥ፣ የሕፃናት መታጠቢያ ወንበሮች ወደላይ ሊጠጉ እንደሚችሉ ይወቁ፣ እና ልጆች ከነሱ ሾልከው ወጥተው በመታጠቢያ ገንዳ ውስጥ በጥቂት ኢንች ውሃ ውስጥ ሊሰምጡ ይችላሉ። ጨቅላ ሕፃናት በመታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ብቻቸውን መተው የለባቸውም፣ ለአንድ ደቂቃም ቢሆን።
ወላጆች እና ተንከባካቢዎች ቁጥጥር ካልተደረገበት ወደ መዋኛ ገንዳ ፣ ክፍት ውሃ ወይም መታጠቢያ ገንዳ እንዳይገቡ መከላከል አለባቸው።
በመጸዳጃ ቤት ውስጥ መስጠምን ለመከላከል ትናንሽ ልጆች በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ብቻቸውን መተው የለባቸውም, እና የመጸዳጃ ቤት መቆለፊያዎች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ.
ከተጠቀሙ በኋላ ወዲያውኑ ውሃ ከኮንቴይነሮች ለምሳሌ ከፓል እና ባልዲዎች መወገድ አለበት.
ዶክተር መሐመድ በሽር የህፃናት እስፔሻሊስት ሐኪም ።አንብበው ሲጨርሱ በቀናነት ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ።

Photos from DireTube's post 06/05/2022
Photos from Hakim's post 03/03/2022
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa
58967