Addis Ababa City Cycling Federation

Addis Ababa City Cycling Federation

Share

To promote and encourage cycling throughout Addis Ababa and around. Make Cycle tourism as a sustainable development means to Ethiopia.

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 11/07/2024

🏆🏆🏆 𝑯𝒂𝒕 𝒕𝒓𝒊𝒄𝒌 🏆🏆🏆

ይህ ድል ለቢንያም ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን ክብርና ሞገስ ያሰጠ ድል በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ብስክሌት ማህበረሰብ ልናመሰግነው ይገባል! ትጋቱና ጀግንነቱ አሁን ላለነው የብስክሌት ስፖርተኞች ምሳሌና ብርታት ይሁነን።

ቢንያም እናመሰግናለን !!!

11/07/2024

🇪🇷 Biniam Girmay! 🇪🇷

🏆 It's already the 3rd, but victory always tastes exquisite for Biniam Girmay! 🏆

| Continental

06/07/2024

A second victory for 🇪🇷 Biniam Girmay!
🇪🇷 Biniam Girmay is looking for his 2nd win at the !

l Continental

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 30/06/2024

የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ።

ብርቱ ፉክክር በታየበት እና በርካታ ተመልካቾች የተመለከቱትን የ140 ኪሎ ሜትር የኤሊት ወንዶች ውድድር ነጋሲ ኃይሉ በድንቅ ብቃት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳልያ ሲያገኝ ሙሉ ክንፉ ብር የጉና ስፖርት ክለቡ አማን ተክለሃይማኖት የነሐስ ሜዳልያ አግኝቷል::

በኤሊት ሴቶች፣ በሁለቱም ጾታ በግል ክሮኖሜትር፣ በጁኒየር በጎዳና ላይ ውድድር የሁለቱም ጾታ አሸናፊ የሆኑ ስፓርተኞች ከዕለት የክብር እንግዶች እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል::

ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው ሻምፒዮና አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሲዳማና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 170 ሳይክሊስቶች መሳተፋቸው ይታወሳል

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 29/06/2024

በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር አሰተናጋጅነት ለ4ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ነገ ፍፃሜውን ያገኛል።

በኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወርቅ እና የነሐስ ሜዳልያ አስመዘገበ

100 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የጁኒየሮች የብስክሌት ውድድር አዲስ አበባን በመወከል የተወዳደሩት የአዲስ አበባ ፓሊስ ክለቦች አዕምሮ መንግስቱ እና በሀይሉ ፍቅሬ አንደኛና ሶስተኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል

በጉጉት የሚጠበቀው የ140 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የኤሊቶች ውድድር ነገ ከ8:30 ጀምሮ መነሻውን አድዋ ድል መታሰቢያ መድሻውን ሜክሲኮ በማድረግ እንደሚካሄድ ተመልክቷል

ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው ሻምፒዮና አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሲዳማና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 170 ሳይክሊስቶች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 27/06/2024

የኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር 2ኛ ቀኑን ይዟል

በኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር እንደቀጠለ ነው

ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው ሻምፒዮና አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሲዳማና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 170 ሳይክሊስቶች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ተመልክቷል

በዩሲአይ ዩኒየን ሳይክል ኢንተርናሽናል እየተመዘገበ ያለው አመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በሁለቱም ፆታ የሚካሄድ ሲሆን በሴቶች ኤሊትና ጁኔር እንዲሁም በወንዶች ጁኔርና ኤሊት ስፖርተኞች እየተወዳደሩ ሲሆን አሸናፊዎች የብሔራዊ ቡድን እጩ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

ሻምፒዮና ውድድሩ ከሰኔ 18 እስከ 23 2016 ድረስ እንደሚካሄድ ተገለጸ ሲሆን ከኩዬ ፈጬ እስከ ቦሌ ቡልቡላ በሸፈነው ርቀት የተለያዩ የግል ሰዓት ሙከራ ውጤት እየተመዘገቡ እንደሚገኝ ተገልጽዋል።

መረጃውን የጋራን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ነው።

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 24/06/2024

ስምንት ክልሎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ነገ ይጀምራል

በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌድሬሽን የ2016 የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር 170 ሳይክሊስቶች እና 8 ክልሎችን በማሳተፍ ከሰኔ 18 እስከ 23 2016 ድረስ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ዛሬ በጁፒተር ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ተወዳዳሪዎች ወደ ከተማችሁ እንኳን በደህና መጣችሁ ብለው ውድድሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ቢሮው ከጎናችሁ በመሆን አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ደስ ብሏችሁ እንድትመለሱ ለማድረግ አበክሮ ይሰራል ብለዋል
ተወዳጅ እና ተናፋቂ የሆነው የብስክሌት ስፖርት የኮሪደር ልማት እየተካሄደ ባለበት ጊዜ መከናውኑ መልካም እድል ነው ያሉት አቶ ዳዊት የከተማችን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ለስፓርተኞች ትልቅ እድል እንዳለው በመረዳት ውድድሩ በአዳዲስ መንገዶች ጭምር እንዲደረግ ከስምምነት መደረሱ ለስፓርቱ የተሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ አስረድተዋል
የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌድሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ወንድሙ ኃይሌ በበኩላቸው በውድድሩ ከ220 የስፓርት ልዑካን እንደሚሳተፉብት ገልጸው በሦስት ቦታዎች የሚደረገው ውድድር ከቦሌ ቡልቡባ ኮዬ ፈጬ፣ ከእንጦጦ ጽዮን ሆቴል እና በአድዋ ኮሪደር ልማት ዙሪያ እንደሚካሄድ ገልጸዋል::

አቶ ወንድሙ አያይዘውም ፌድሬሽኑ ብስክሌትን ትልቅ ደረጃ ለማድረስ ስፓርቱን የሚያጠናክር ውድድሮችን ከዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የጊዜ ሰሌዳ በመናበብ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል
በውድድሩ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳዳሮች ክለቦችና የግል ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ በመግለጫው የተመላከተ ሲሆን አሸናፊዎች የብሔራዊ ተወዳዳሪ እጩ እንደሚሆኑ በውድድሩ ደንብ ላይ ተጠቅሷል::

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 18/06/2024

የአዲስ አበባ ከተማ ብስክሌት ፌዴሬሽን በ2016ዓ/ም የተከናወኑ ውድድሮችን ገመገመ ።

ፌዴሬሽነ በየደረጃው ከሚገኙ ከአመራሮች ጀምሮ ከስራ አስፈሚ አካላት፣ ቡድን መሪዎች፣ከክለብ አሰልጣኞች፣ስፖርተኞች እና ባለሙያዎች ጋር በተደረጉት ውድድሮች ላይ እና በ2016ዓ/ም አዲስ አበባ በምታዘጋጀው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውይይት ተካሂዷል።

በውድድሮች ላይ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት በጥንካሬ እና በክፍት ተነስተዋል።

ፌዴሬሽኑም በቀጣይ የሚስተካከሉት ጉዳዮች ወስዶ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንደሚያደረግ በመግለጽ ከሁሉም የስፖርቱ ቤተሰብ በጋ ለመስራ በቁርጠኝነት የገለጸ ሲሆን በጥንካሬ የተነሱ ሀሳቦች ሁሉም የስፖርቱ ቤተሰብ ተረባርቦ ያሳካቸው ሲሆን በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጠሉ ገልጠዋል።

የ2016ዓ/ም ኢትዬጵያ ሻምፒዮና ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኔ 17-23/2016ዓም በተመረጡ የውድድር ቦታዎች እንደሚደረግ እና እንደ ከተማ ጥሩ መስተንግዶ ለማድረግ እና ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን ውይይቶችን አደረገ።

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 24/12/2023

የታዳጊዎች ምዘና እና የክለቦች ያቋም መለኪያ የብስክሌት ውድድር ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የታዳጊ ወጣቶች ምዘና እና የክለቦች የአቋም መለኪያ የብስክሌት ውድድር ዛሬ ተጀምሯል።

በታዳጊ ሴቶች 13.6 ኪሎ ሜትር በሸፈነው ማውቴን ውድድር ትዕግስት ካሳሁን ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ማለፊያ ሽፈራው እና ሉሌ ሁንዶ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በተመሳሳይ በታዳጊ ወንዶች 17 ኪሎ ሜትር የማውቴን ውድድር የኮልፌ ክፍለ ከተማ ተወዳዳሪ የሆኑት ሀቢብ ሀይደር እና ሀይለ እየሱስ ደምስ ተከታትለው በመገግባት አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ውድድራቸውን ሲያጠናቅቁ የግል ተወዳዳሪ የሆነው ሙአዝ ሰይድ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቆል።

ብርቱ ፉክክር በታየበት እና የተመልካችን ቀልብ በገዛው 61.2 ኪሎ ሜትር የክለቦች የኮርስ ውድድር የኢትዮ ኤሌክትሪክ ተወዳዳሪው አዲሱ መኮነን ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ሰለሞን አለሙ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ሁለተኛ ገዛሀኝ በድሉ ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።ዛሬ የተጀመረው የብስክሌት ውድድር እስከ ጥር 19/2016 ዓ.ም የመሚካሄድ ይሆናል።

ለተጠናቀረው መረጃ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮን እናመሰግናለን።

Photos from Addis Ababa City Cycling Federation's post 23/12/2023

የተወደዳችሁ የአዲስ አበባ የብስክሌት እስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ
ነገ በ13/4/2016 የክለቦች የአቋም መለኪያ ውድድር የሚጀምር ሲሆን መርሀ ግብሩ ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ በ 3 የውድድር ካታጎሪዎች የሚደረግ ሲሆን መላው የከተማችን ብስክሌት ውድድር አድናቂዎች በስፍራው በመገኘት ውድድሩን እንድትመለከቱ ስንል እንጋብዛለን።
የመርሀግብሩን ዝርዝርና የተወዳዳሪዎችን ህግጋት በውድድር ሰንጠረዥ ላይ ይመልከቱ።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa
67457