27/05/2026
እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
Ethiopian National Accreditation Office
EAS was established as an autonomous federal government office having its own legal personality.
EAS was established as an autonomous federal gov’t office having its own legal personality will offer accreditation services on a national & Intern' basis for conformity assessment bodies.. The mandate of EAS is to accredit, by formal third-party recognition, the competence of Conformity Assessment Bodies (CABs) to perform specific activities, such as test, calibrations, certifications or inspecti
27/05/2026
እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
26/05/2026
በኢትዮጵያ የ118 ዓመታት የንግድ ሚኒስቴር ታሪክ የመጀመሪያው የንግድ ፖሊሲ
(አዲስ አበባ ፡ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወጥ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ በይፋ አፅድቃለች። ይህ የላቀ ስኬት ሀገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ከተቋቋመበት የ118 ዓመታት ረጅም ታሪኳ ውስጥ ራሱን የቻለና የነፃ ገበያ ሥርዓቱን የሚመራ ወጥ የፖሊሲ ሰነድ ያገኘችበት የመጀመሪያው ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።
ቀደም ሲል ወጥ የሆነ የንግድ ፖሊሲ አለመኖሩና የንግድ ሕጎች በተለያዩ አዋጆችና መመሪያዎች ውስጥ ተበታትነው መገኘታቸው በገቢና ወጪ ንግድ መካከል ቅንጅት እንዳይኖር ከማድረጉም በላይ፣ በንግድ ሥርዓቱ ላይ ፍትሃዊ ውድድር እንዲጠፋ፣ ሕገ-ወጥነት እንዲስፋፋና ሸማቾች ለከፍተኛ ምሬት እንዲዳረጉ በምክንያትነት ይጠቀሳል።
በአሁኑ ወቅት የጸደቀው ፖሊሲ እነዚህን መዋቅራዊ ክፍተቶች በመሙላት የሀገር ውስጥና የውጭ ንግድ አስተዳደርን በሳይንሳዊ መንገድ ለመምራት፣ የወጪ ንግድን በማዘመን ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በታሪፍና ማበረታቻዎች ለመደገፍ እንዲሁም የሸማቾችን መብትና ደህንነት ለመጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ አዲስ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ በዋናነት በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ፣ በትብብርና ቅንጅት፣ በግልፅነትና ተገማችነት እንዲሁም በፍትሃዊ ውድድር መርሆዎች ላይ የተገነባ ነው። የሰነዱ አጠቃላይ ይዘትም የሀገር ውስጥ የግብይት ሥርዓትን ማዘመን፣ የገቢና ወጪ ንግድ አስተዳደር ማዕቀፍን ማጠናከር፣ ፍትሃዊ ንግድን ማስፈንና የዲጂታል ንግድ (E-commerce) ሥርዓትን መገንባት ላይ ያተኩራል።
በአጠቃላይ ፖሊሲው በንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ከፍተኛ መተማመንን በመፍጠር፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብና የሀገሪቱን የንግድ ምህዳር ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የተጣለ ትልቅ መሠረት ነው።
23/05/2026
21/05/2026
21/05/2026
The AFRAC Mutual Recognition Arrangement (MRA) Council meeting has concluded during the AFRAC Mid-Year Virtual Meetings.
The Council is responsible for managing membership within the AFRAC MRA, helping to strengthen trust in accreditation results and supporting the recognition of conformity assessment across Africa.
The meeting reaffirmed the importance of collaboration in building a strong, credible, and trusted accreditation system that supports trade and development across the continent.
19/05/2026
The African Accreditation Cooperation (AFRAC) Mutual Recognition Arrangement (MRA) Committee convened today to deliberate on matters aimed at strengthening the AFRAC MRA framework and enhancing confidence in accreditation across the continent.
The Committee plays a critical role in safeguarding the integrity, harmonisation, and international recognition of accreditation systems among AFRAC members.
Through such engagements, AFRAC continues to promote cooperation, competence, and trust in accredited conformity assessment services in Africa.
18/05/2026
ለላብራቶሪ አክሬዲቴሽን የትርፍ ሰዓት እጩ ባለሙያዎች (Potential Technical Assessors) የተዘጋጀ ሥልጠና ዛሬ በይፋ ተጀመረ!
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት (EAS) ለእጩ የላብራቶሪ አክሬዲቴሽን ምዘና (Potential Technical Assessors) ባለሙያዎች 3ኛውን ዙር ሥልጠና ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ይህ ሥልጠና በዋናነት ያተኮረው በላብራቶሪ የፍተሻ ዘዴዎች ማረጋገጫ፣ ትክክለኛነት ፍተሻ እና ልኬት (Method Validation, Verification, and Measurement Uncertainity) ጽንሰ-ሀሳቦች ላይ ነው።
ይህንን እጅግ አስፈላጊ የዕውቀትና ክህሎት ማሳደጊያ መድረክ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም እና የላብራቶሪ አክሬዲቴሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌቴ ብርሃኑ በመክፈቻ ንግግራቸው በይፋ ከፍተውታል። በንግግራቸውም የምዘና ባለሙያዎች አቅም ማደግ ሀገራዊ የጥራት መሠረተ-ልማትን ለማጠናከር ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል።
ለሚቀጥሉት አምስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ ከዘርፉ የተወጣጡ 27 የተለያዩ የላብራቶሪ ምዘና ባለሙያዎች (Potential Technical Assessors) እየተሳተፉ ይገኛሉ። ሥልጠናው ባለሙያዎቹ በዘርፉ ያላቸውን እውቀት በማሳደግ፣ በሀገራችን የሚገኙ የላብራቶሪዎችን የብቃት ደረጃ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ግምገማ ለማድረግ እና የፍተሻ ውጤቶችን ይበልጥ ተዓማኒነት እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማስቻል የጎላ ሚና ይጫወታል።
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |