31/08/2026
ማስታወቂያ !
This is the official social media page of the Ethiopian Athletics Federation, bringing you the latest news, updates, and achievements. Her Excellence Mrs.
Although the exact roots of Ethiopian Athletics cannot be retraced back accurately, it is widely believed that the sport was widely practiced in schools and military camps before 1897. The sport was limited to these parts of society only because others did not have access to equipment used for competitions or was not organized in a manner that motivated progress. But after signs that the sport was
31/08/2026
ማስታወቂያ !
31/08/2026
በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የማራቶንና የመም ውድድሮች አስደናቂ ውጤት አስመዝግበዋል።
ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው የሲድኒ ማራቶን፣አትሌት አዲሱ ጎበና 2:04:42 በመሮጥ ድል ተቀዳጅቷል።
በዚህም ባለፈው ዓመት በአትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ የተያዘውን የውድድሩ ክብረወሰን ከሁለት ደቂቃ በላይ አሻሽሏል።
አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ 2:04:46 በመግባት ሁለተኛ ሲሆን፣ አትሌት ጀማል መኮንን 2:04:59 አምስተኛ ወጥቷል።
የ2025 አሸናፊው አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ ደግሞ 2:05:16 ስድስተኛ ሆኗል።
በሴቶች ውድድር አትሌት ሹሬ ደምሴ 2:22:32 ሶስተኛ፣አትሌት ሄቨን ሀይሉ 2:22:56 አራተኛ እና አትሌት መሰረት አበባየሁ 2:23:40 አምስተኛ ሆነዋል።
በሜክሲኮ ማራቶን ደግሞ አትሌት አለምፀሀይ አሰፋ የሴቶችን ውድድር ስታሸንፍ፣አትሌት ተስፋየ ሌንጮ እና አትሌት ባለው ይሁኔ በወንዶች 2ኛና 3ኛ ወጥተዋል።
በህንድ ሀይደራባድ ማራቶን አትሌት ሰቦቃ ንጉሴ የወንዶችን ውድድር ሲያሸንፍ፣አትሌት ኢማና ሰይፉ እና አትሌት ፀጋ ደስታ በሴቶች 1ኛና 2ኛ ሆነዋል።
በናይጄሪያ እንጉ ማራቶንም አትሌት አበሩ መኩሪያ በሴቶች አሸናፊ ስትሆን፣አትሌት ሀብታሙ ግርማ እና አትሌት ሽፈራው ዳልቲማዮ በወንዶች 2ኛና 3ኛ ወጥተዋል።
በጀርመን አትሌት ንግስት ጌታቸው የ800 ሜትር ውድድርን 1:58.04 በሆነ ጊዜ አሸንፋለች።
በስዊዘርላንድ ቤሊንዞና ደግሞ አትሌት አስቴር አሬሪ በ1500 ሜትር 3:59.54 በመሮጥ ሶስተኛ ሆናለች፤ ይህም ከ4 ደቂቃ በታች የገባችበት አዲስ የግል ምርጥ ሰዓቷ ነው።
30/08/2026
አትሌት አዲሱ ጎበና የሲድኒ ማራቶንን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ
ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 24ኛው የሲድኒ ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊው አትሌት አዲሱ ጎበና ድል ተጠናቋል።
ውድድሩ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተሰጠው ሲሆን፣አትሌት አዲሱ ጎበና ድሉን ያገኘው የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል ነው።
አትሌት አዲሱ ጎበና 2:04:42 በመግባት የሲድኒ ማራቶንን በማሸነፍ የውድድሩን ክብረወሰን አሻሽሏል።
አትሌቱ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ውድድር 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
በወንዶች ውድድር ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ጥሩ ውጤት አስመዝግበዋል።
አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ 2:04:46 በሆነ ጊዜ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣አትሌት ጀማል መኮንን 2:04:59 በመግባት 5ኛ ወጥቷል። የባለፈው ዓመት የሲድኒ ማራቶን አሸናፊ የነበረው አትሌት ሀይለማርያም ኪሮስ ደግሞ 2:05:16 በሆነ ጊዜ 6ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።
በሴቶች ውድድር የኦሎምፒክ አሸናፊዋ ኬንያዊቷ ፒርስ ጅፕችርችር አሸናፊ ሆናለች።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም በሴቶች ውድድር ጥሩ ውጤት አስመዝግበዋል።
አትሌት ሹሬ ደምሴ 2:22:32፣ አትሌት ሄቨን ሀይሉ 2:22:56 እና አትሌት መሰረት አበባየሁ 2:23:40 በሆነ ጊዜ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
28/08/2026
በ2ኛው የአፍሪካ ዞን 5 ሀገራት ወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 6 ሜዳሊያዎችን አግኝታ አጠናቀቀች
ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም
በኬንያ ላለፋት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ዞን 5 ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ትናንት ምሽት ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ በውድድረ ካስመዘገበቻቸው 12 ሜዳልያዎችን ውስጥ 4 የወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎች በአትሌቲክስ ተመዝግቧል ።
የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያዎች በሴቶች 800 ሜትር፣ በሴቶች 3000 ሜትር እና በሴቶች 5000 ሜትር የእርምጃ ውድድር የተገኙ ሲሆን፣ ሌላው የወርቅ ሜዳሊያ በሴቶች 1500 ሜትር ተገኝቷል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በወንዶች 1500 ሜትር እና በወንዶች 3000 ሜትር ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
27/08/2026
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ
ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም
በክልሉ የሚገኙ የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶችን ውጤታማነት ለማሳደግና እና ተተኪ ስፖርተኞችን በሳይንሳዊ መንገድ ለማፍራት የሚያስችል የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ የአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና በወራቤ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
ስልጠናውን የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የክልሉ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብለቱ እንደገለጹት፣ ክልሉ በአትሌቲክስ ዘርፍ እጅግ ምቹና ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ፀጋ እና እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ውጤት ለመቀየር ፕሮፌሽናል አሰልጣኞች ያስፈልጋሉ ብለዋል።
እንደ ማሳያም በ2017 እና 2018 ዓ.ም ብቻ ከክልሉ የተገኙ ከ30 በላይ አትሌቶች በተለያዩ ክለቦች ታቅፈው በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን ከማወዳደር ባለፈ በሰው ሃይል ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረጉን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ "ያለንን አቅም ወደ ውጤት ለመቀየር ፕሮፌሽናል አሰልጣኞች መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር እንደሆነም አስረድተዋል።
ክልሉ በኦሊምፒክ እና በአፍሪካ ሻምፒዮናዎች ውጤት ያስመዘገቡ መሰል ታዋቂ አትሌቶች የወጡበትና የአትሌት ቤተሰቦች መገኛ መሆኑን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህን ትልቅ አቅምና መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ክልሉን የአትሌቲክስ ማዕከል ለማድረግ በስፋት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚደገፉ በክልሉ ሶስት የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፣ በአልቾ ውሪሮ፣ በጉመራ እና በሚሻ አካባቢዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን በማንሳት፣ እነዚህ ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በቅርበት መከታታልና መደገፍ ይገባል ብለዋል።
በቀጣይም በ2019 ዓ.ም በሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንዳንድ ፕሮጀክቶች ለማቋቋም ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ያስታወቁት ፕሬዚዳንቱ፣ በእያንዳንዱ መዋቅር 25 አትሌቶችን በማቀፍ በአጠቃላይ 250 አዲስ ተተኪ አትሌቶችን ወደ ስልጠና ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ አብራርተዋል።
ስልጠናው ይህንን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ሰልጣኞች በከፍተኛ ዲሲፕሊን ስልጠናውን እንዲከታተሉ፣ ከስልጠናው ከሚያገኙት እውቀት በተጨማሪ በራሳቸው ንባብ እና ዘመናዊ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል።
አክለውም፣ስልጠናው የተዘጋጀው በጀት ተርፎ ሳይሆን፣ ለዘርፉ እድገት ስልጠናው መሰረታዊና አስፈላጊ በመሆኑ ካለ ውስን በጀት ላይ ተቀንሶ ዘርፉን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
የእንኳን ደህና መጣቹሁ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳኒ ሳሎ በበኩላቸው፣ ከተማዋ ሰላማዊ እና እንግዳ ተቀባይ መሆኗን አስታውቀዋል።
ስልጤ ዞን የበርካታ አትሌቶች መገኛ አካባቢ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከነዚህም መካከል እንደ ሙክታር እድሪስ፣ በይቱላ ፣አጃይባ አሊዬ እና አሊ አብዱልመና ያሉ አለም አቀፍ ዝና ያተረፉ አትሌቶችን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
ስልጠናው በተለይም በአልቾ ውሪሮ ወረዳ የተገነባው የአትሌቲክስ ስልጠና ማዕከል በተጠናቀቀበትና በተመረቀበት ወቅት ላይ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ያሉት አቶ ሳኒ፣ ለአትሌቲክስ እድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ አብራርተዋል።
ሰልጣኞች በከተማዋ በሚቆዩባቸው ቀናትም ወራቤ ሰላማዊና እንግዳ ተቀባይ ከተማ መሆኗን ገልጸው፣ ትኩረታቸውን በስልጠናው ላይ በማድረግ ለነገው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስኬት የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ባሶሬ እንደገለጹት፤ ይህ ሥልጠና በክልሉ በ7 ዞኖች እና በ3 ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ የአትሌቲክስ ፕሮጀክት አሰልጣኞች የተዘጋጀ መሆኑ ገልጸዋል።
ሥልጠናው ቀደም ሲል ከነበሩት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ አዳዲስ የአሰልጣኞች ምልመላና ዝግጅት ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመው፣
በክልሉ ያሉ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎችን በመለየትና በማሰልጠን ቀጣይነት ያለው የማይደርቅ የተተኪ አትሌት ምንጭ መፍጠር ነው ያሉት አቶ ማርቆስ፣ አሰልጣኞች ዘመናዊና ሳይንሳዊ የሥልጠና ዘዴዎችን ተጠቅመው አትሌቶችን እንዲያዘጋጁ ብቃታቸውን ማሳደግ ብለዋል።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከክልሉ የተውጣጡ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሥልጠና ልምድ በካበቱ ኢንስትራክተሮች የንድፈ-ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
ይህም ሰልጣኞች ጥራት ያለውና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እውቀት እንዲቀስሙ ዕድል ይፈጥራል ያሉት አቶ ማርቆስ፣ ሥልጠናው ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ መሆኑን ገልጸዋል።
"ብቁ አሰልጣኝ ከሌለ ብቁ አትሌት ሊኖር አይችልም" ያሉት አቶ ማርቆስ፣ ስልጠናው አሰልጣኞች እራሳቸውን በዘመናዊ ስፖርታዊ ሳይንስ እና ስነ-ልቦና እንዲያበቁ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በስልጠናው የመክፈቻ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ቡላድ ናሙዝን ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ እና ሌሎች የፌዴሬሽኑ የስራ ሃላፊዎችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል።
ለዚህ ስልጠና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ልምድና ዕውቀት ያላቸውን አራት የአትሌቲክስ ኢንስትራክተሮችን በመመደብ ስልጠናው በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጥ እያደረገ ይገኛል።
ይህም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ በተግባር እንዲውል ከሚያደርጉ ተግባራት አንዱ ሲሆን፣ የአትሌቲክስ ስፖርት በክልሉ እንዲያድግና የሰው ኃይል አቅሙ እንዲጠናከር የሚያበረክት ነው።
መረጃው የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው
26/08/2026
ደማቅ አቀባበል ለጀግኖች አትሌቶች ዮሚፍ እና ፎቴን!
ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም
በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበው ጀግናው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሴቶች የውድድሩን አዲስ የቦታ ክብረወሰን በማስመዝገብ ያሸነፈችው ጀግናዋ አትሌት ፎቴን ተስፋይ ዛሬ ማታ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዚህም ከፍተኛ የስፖርት ድል ይዘው ወደ አገራቸው ለተመለሱት ሁለቱ ጀግኖች አትሌቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ 56:51 በሆነ ጊዜ በመግባት፣ በዩጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ የነበረውን 57:20 የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል አዲሱን የዓለም ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል።
በሴቶች ውድድር ደግሞ አትሌት ፎቴን ተስፋይ 1:03:57 በሆነ ጊዜ በመግባት የውድድሩን የቦታ ክብረወሰን በማሻሻል በአንደኝነት አሸንፋለች።
ሁለቱ ጀግኖች አትሌቶቻችን አዲስ አበባ ሲገቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፣ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት የማነ ፀጋይ፣ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አመንሲሳ ከበደ፣ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎን ጨምሮ አሰልጣኞች፣ የአትሌቶቹ ቤተሰቦችና ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት፣ በፌዴራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ አጃቢነት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
እንኳን ደህና መጣችሁ፤ የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ በማድረጋችሁ እንኮራባችኋለ !!
24/08/2026
በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጁ
ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል ።
በሰሜን አየርላንድ ላርን ከተማ በተካሄደው Antrim Coast Road Race ውድድር፣ በዚህ ዓመት አዲስ በተጨመረው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን የበላይነታቸውን አሳይተዋል።
በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት አይናዲስ መብራቱ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በማጠናቀቅ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።
በወንዶች 5 ኪሎ ሜትር ደግሞ አትሌት ኤርሚያስ ግርማ በ13 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ደረጃ በመያዝ አሸንፏል ።
በዚሁ ውድድር የሴቶች 21 ኪሎ ሜትር ግማሽ ማራቶን ላይ አትሌት ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በ1 ሰዓት 6 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ሆናለች።
አትሌት ውዴ ከፍያለው ደግሞ 1 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዛለች።
በወንዶች ግማሽ ማራቶን አትሌት ይስማው ድሉ 1 ሰዓት 1 ደቂቃ ከ5 ሰከንድ በማስመዝገብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በፓላንድ ሲሊሲያ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል አትሌት ገመቹ ጎዳና ርቀቱን በ8 ደቂቃ ከ2 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ደረጃን ይዞ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።
በሴቶች 1,500 ሜትር አትሌት ፅጌ ዱጉማ 3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በሆነ ውጤት በአስደናቂ አጨራረስ የውድድሩን ድል ተቀዳጅታለች።
በሴቶች 5,000 ሜትር ደግሞ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
23/08/2026
ፎቴን ተስፋይ የ2026 ቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶንን አሸነፈች
ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የ2026 የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን የሴቶች ውድድር አትሌት ፎቴን ተስፋይ አሸናፊ ሆናለች።
አትሌቷ 21 ኪሎ ሜትሩን 1:03:57 በሆነ ጊዜ በመጨረስ የውድድሩን የቦታ ክብረ ወሰን በማሻሻል በአንደኝነት አሸንፋለች ።
በዚሁ ውድድር በወንዶች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓለም አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል።
23/08/2026
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በግማሽ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበ
ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ከደቂቃዎች በፊት በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
አትሌቱ 21 ኪሎ ሜትሩን 56:51 በሆነ ጊዜ በመጨረስ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።
በዚህም በዩጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ የነበረውን 57:20 የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል አዲሱን የዓለም ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል።
ይህ የዮሚፍ ቀጄልቻ አስደናቂ ውጤት በኢትዮጵያ የርቀት ሩጫ ታሪክ ላይ ሌላ ታላቅ ምዕራፍ ሆኗል።
በተያያዘ በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፎቲዬን ተስፋይ 1:03:57 በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆኗለች ።
23/08/2026
BACK WITH KEJELCHA 🫨
Former world record-holder Yomif Kejelcha reclaims the half marathon world record* from Jacob Kiplimo, clocking 56:51* in Buenos Aires 💪
That’s 29 seconds off the previous
mark 💥
World Athletics
World record flash 🔗 bit.ly/4xiWcNZ
*Pending ratification procedures