Manchester United Ethiopian Fans

Manchester United Ethiopian Fans

Share

News Update of Manchester United!

19/10/2025

05/01/2025

FT

ሊቨርፑል 2-2 ዩናይትድ

05/01/2025

የጨዋታው አሰላለፍ

24/12/2024

የማንቼስተር ዩናይትድ ስታዲየም ኦልድትራፎርድ የአይጥ መንጋ አስቸግሮታል ተባለ

የማንችስተር ዩናይትድ ሜዳ የሆነው ኦልድትራፎርድ በአይጥ መንጋ መቸገሩ ተሰምቷል፡፡

የንጽህና ተቆጣጣሪዎች በቅርቡ ባደረጉት ምልከታ÷ስታዲየሙ አይጥ በብዛት እንደመሸገበት መረዳታቸውንና ለቡድኑ የምግብ ንጽህና የሁለት ኮከብ ምዘና (ሬቲንግ) እንደሰጡት ተገልጿል።

በዚህም ለቡድኑ የምግብ ንጽህና ከአራት ኮከብ ወደ ሁለት ዝቅ ያለ ነጥብ እንደተሰጠውና የተፈጠረውን የጥራት መጓደል እንዲያሻሽል ምክረ ሃሳብ መቀበሉን ሜይል ኦንላይን ዘግቧል።

ተቆጣጣሪዎች ባደረጉት ፍተሻ በስታዲየሙ ምድር ላይ ባሉ ሱት በተባሉ ልዩ መዝናኛዎችና ኪዮስኮች ጭምር አይጥ እንደሚርመሰመስባቸው አረጋግጠዋል ተብሏል።

እግር ኳስ ቡድኑ አይጥንና ሌሎች ነፍሳትን ለመቆጣጠር ከጸረ-ተባይ ተቆጣጣሪ ድርጅቶች እና ከአካባቢው አስተዳደር ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ለዚህ ችግር የተጋለጠው ኦልድትራፎርድ በባቡር ሃዲድና በቦይ መካከል የተገነባ በመሆኑ ሳቢያ እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል።

የማንቼስተር ዩናይትድ ቃል አቀባይ እንዳለው÷ በስታዲየሙ ሁሉም ክፍል ጠንከር ያለ የአይጥና ተባይ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንና ምግብ በሚከማችበትና በሚዘጋጅበት ቦታ ሁሉ ከፍተኛ የንጽህና ጥንቃቄ ይወሰዳል።

ቡድኑ የተሰጠውን ደረጃ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ማንኛውንም አስፈላጊ የማሻሻያ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ያረጋገጠው፡

በርካታዎቹ የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ቡድኖች የ5 ኮከብ የምግብ ንጽህና ደረጃ እንዳላቸው የጠቀሰው ዘገባው÷ አዲሱ የቡድኑ ባለቤቶች ስታዲየሙን ለማደስ ካልሆነም እንደ አዲስ ለመስራት እያሰቡ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

በፈረንጆቹ 1910 የተገነባው ኦልድትራፎርድ እርጅናው ጸንቶበት ጣራው በተደጋጋሚ ሲያፈስ መታየቱ የተጠቆመ ሲሆን÷ ትናንት በቦርንማውዝ ከተሸነፈ በኋላ የቡድኑ አሰልጣኝ ለድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ጣሪያው በማፍሰሱ ጋዜጠኞች ሲቸገሩ ታይተዋል።

22/12/2024

FT
.
ዩናይትድ 0-3 ቦርንማውዝ

22/12/2024

30'
ዩናይትድ 0-1 ቦርንማውዝ

Photos from Manchester United's post 22/12/2024
22/12/2024

የ ጨዋታው አሰላለፍ

21/12/2024

ሩበን አሞሪም

" በተቃራኒ ሳጥን ውስጥ የምናደርገው እንቅስቃሴ ተሻሽሏል አንዳንድ ጨዋታዎች ነበሩ በተቃራኒ ሳጥን አከባቢ ተገኝተን ነገር ግን ምንም ስጋት መፍጠር ያልቻልንባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ አሁን ቡድናችን ፈጣን እንደሆነ የበለጠ ተጭኖ እንደሚጫወት አካላዊ ብቃታችን እያደገ እንዳለና ጨዋታዎችን እየተረዳን እንዳለ ይሰማኛል

ሩበን አሞሪም በልምምድ ወቅት ስለሚሰራቸው ተጨማሪ ስራዎች

" ልምምድ .... ቀላል ነው ምክንያቱም ተጨዋቾችን እያቀያየርክ መሞከር ነው ነገር ግን በእያንዳንዱ ተጨዋቾች መሃል ግኑኝነት መፍጠር ትንሽ ፈታኝ ነው ከተለያዩ ተጨዋቾች ጋር በአንድ ቦታ ላይ የምትሰራ ከሆነ ያንን የግኑኝነት መስመር መዘርጋት ይፈትናል በውድድር አመቱ አጋማሽ ነው አብረን የሆነው ይሄ ይታወቃል እናም ተጨማሪ ጊዜ ስላለን ከቡድኑ ጋር በደምብ እንለማመድበታለን ይሄ ነው

ሩበን አሞሪም ስለ ኦልድትራፎርድ

" በኖቲንግሃም በዛ መንገድ የተሸነፍንበት ሁኔታ በጣም ይከብድ ነበር ስለዚህ ለደጋፊዎቻችን በመጫወት በቀጣይ ዝማሬያቸውን መስማትና ውስጣቸው ላይ ደስታን ማስቀመጥ እንፈልጋለን

ሩበን አሞሪም ስለ ማርከስ ራሽፎርድ

"በሚገባ ለእሁዱ ጨዋታ የሚኖር ይመስለኛል የፀባይ ችግር አለ ? የለም ተመሳሳይ ነገር ነው አሁንም

ሩበን አሞሪም ስለ አንቶኒ

" የበለጠ በራስ መተማመን ያስፈልገዋል በአያክስ የነበረውን አንቶኒ ካስታወሳቹ አንድ ለአንድ ለመጋፈጥ በራስ መተማመኑ ያነሰ ነበር ነገር ግን ይሻሻላል ይሄንን ማድረግ አለበት ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል እኔም የተሻለ ተጨዋች እንዲሆን እረዳዋለሁ

አሞሪም ስለ ማውንት ጉዳት

" ማውንትን እንዴት እንደሚጫወት በማስተማር ነው ላግዘው የምችለው በማገገሚያ ጊዜው ስለተለያዩ ነገሮች እንዲረዳ ለማድረግ እንሞክራለን መጥፎው ነገር ግን ከብዙ ጉዳቶች እያገገምክ ከመጣ መለማመድ ባለብን ልክ ላንለማመድ እንችላለን "

አሞሪም ስለ ቶፕ 4

" የሚቻል አይደለም ብልህ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን አይመጥንም ትላለህ ነገር ግን ለደጋፊዎቹ መናገር የምፈልገው እውነቱን ነው መጀመሪያ ስለ ውጤቱ ትተን አቋማችን ላይ እናተኩር ከዛ በመጨረሻ የሚፈጠረውን እናያለን ይሄንን ብዙ ጊዜ ተናግሪያለሁ በምንጨርስበት ደረጃ ብዙ ልወቀስ እችላለሁ ይሄንን አውቃለሁ እኛ ግን ስለ ቀጣይ ጨዋታ እያሰብን አቋማችንን ነው መመልከት ያለብን ብሏል.

20/12/2024

እርግጥ ነው ሽንፈት ሽንፈት ነው በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ያናዳል በተለይ እንዲህ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሲሆን ነገር ግን ከጨዋታው ዩናይትድ ወደጨዋታው ለመግባት ያደረገውን ተጋድሎ አለማድነቅ አይቻልም

አሞሪም ከቴን ሀግ የሚለየው አንዱ ነገሩ ቅያሪዎችን ለማድረግ አይዘገይም ምንም እንኳን በፎስተር ስህተት ቢገኙም እነዛ ጎሎች ተቀይረው የገቡት አማድ እና ዚርክዜ ለጎሎቹ መቆጠር ጥረት አድርገዋል ደሞም ጨዋታው የተቀየረው ቅያሪውን ካደረገ በኃላ ነበር ። በተመሳሳይ በብዙ ጨዋታዎች በቅያሪዎቹ የተነሳ ዩናይትድ ነጥብ ይዞ የወጣባቸው ጨዋታዎች በርካታ ነበሩ ።

ማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ ስም ያላቸውን ተጨዋቾች ይዟል እንጂ በስኳድ በጥራት ደረጃ ገና እንደሚቀረው የዛሬው ጨዋታ ከበቂ በላይ ማሳያ ነው !!

18/12/2024

#ቀጣይ ጨዋታ

ካራባኦ ካፕ
#ቶትንሃም ከ #ዩናይትድ
ሐሙስ ማታ 4:00

18/12/2024

" ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ " ራሽፎርድ

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በቀጣይ ለአዲስ ፈተና ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል።

ስለ ማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት ቆይታው የተጠየቀው ማርከስ ራሽፎርድ " ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብዬ አስባለሁ " በማለት ተናግሯል።

“ ማንችስተር ዩናይትድን የምለቅ ከሆነ ከእኔ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ መጥፎ ነገር አይሰማም ሁልጊዜም በዩናይትድነቴ እቀጥላለሁ።“ሲል ራሽፎርድ ተናግሯል።

“ ሌሎች ተጨዋቾች ክለቡን እንዴት እንደለቀቁ አውቃለሁ እኔ እንደነሱ መሆን አልፈልግም የምለቅ ከሆነ በራሴ በይፋ የማሳውቅ ይሆናል።“ ራሽፎርድ

“ ከማንችስተር ደርቢ ውጪ መሆኔ ያበሳጫል ነገርግን ተከስቷል ጨዋታውን አሸንፈናል ወደፊት እንቀጥላለን " ያለው ራሽፎርድ " ምርጡ አቋሜ ገና አልመጣም " ሲል ተደምጧል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa