ገሬ ሞባይል ጥገና

ገሬ ሞባይል ጥገና

Share

in our page you will get latest technology technology news, troubleshooting for various cellphones. tips on different cellph0922003151one uses.

31/10/2025

ጥንቃቄ ያድርጉ አንድሮይድ አፕልኬሽን ሲያወርዱ

📌አዲስ የአንድሮይድ ተጋላጭነት የባለ ሁለት እርከን መለያ ቁጥሮችን (2FA ኮዶችን) ያለፍቃድ ሊሰርቅ ይችላል ተባለ

| የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የተገኘ አዲስ እና አደገኛ የደህንነት ጉድለት ይፋ አድርገዋል።

ይህ ግኝት፣ ጠላፊዎች የባለ ሁለት እርከን የማረጋገጫ (2FA - Two-Factor Authentication) ኮዶችን ጨምሮ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ያለተጠቃሚው እውቅና እና ያለምንም ልዩ ፍቃድ እንዲሰርቁ ያስችላል።

"Pixnapping" ወይም "Pixel Stealing" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የጥቃት ዘዴ፣ አንድሮይድ አፕሊኬሽኖች ምስሎችን በስክሪኑ ላይ እንዴት እንደሚያሳዩ ያለውን ሂደት ይጠቀማል።

ተንኮል አዘል አፕሊኬሽን (Malicious App) በማይታይ ሁኔታ የስክሪን ላይ መረጃን "በመለካት" እና ቀለሞችን "በማወዳደር" መረጃውን ያወጣል።

ይህ አዲስ ጥቃት ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተለየ የሚያደርገው፣ እንደ ስክሪን ሾት ማንሳት ወይም ልዩ የስርዓት ፍቃድ (Special Permissions) በፍጹም አያስፈልገውም። በቀላሉ አፕሊኬሽኑ በስልኩ ላይ ተጭኖ መገኘቱ ብቻውን በቂ ነው ተብሏል።

በሙከራዎች ይህን ዘዴ በመጠቀም እንደ Google Authenticator ባሉ አፕሊኬሽኖች የሚፈጠሩትን ባለአንድ ጊዜ የይለፍ ቁጥሮች (OTP) በአጭር ጊዜ ውስጥ መውሰድ እንደሚቻል ተረጋግጧል።

የሳይበር ደህንነት ቡድኖች ይህን ከባድ ተጋላጭነት ለጉግል ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፣ ኩባንያው ለፒክሰል (Pixel) እና ለሌሎች የአንድሮይድ ስልኮች የደህንነት ማሻሻያዎችን (Security Patches) እየለቀቀ ነው።

ሁሉም የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች የደህንነት ስጋት ውስጥ እንዳይገቡ የስልካቸውን ሲስተም ሶፍትዌር በአፋጣኝ ወደ የቅርብ ጊዜው ስሪት እንዲያሳድጉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

እንደ መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ ተጠቃሚዎች ከታመነበት Google Play Store ውጪ ከሌሎች ምንጮች አፕሊኬሽን ከመጫን እንዲቆጠቡ ተመክሯል።

11/10/2025

የገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎች (AirPods) የጤና ስጋት

በገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎች ደህንነት ላይ በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት፣ የብሉቱዝ ጨረር በሰው አካል ላይ ስለሚያስከትለው ውጤት ክርክሩን እንደገና ቀስቅሷል። ጥናቱ እንዳመለከተው፣ እንደ ኤርፖድስ (AirPods) ያሉ ገመድ አልባ ማዳመጫዎች ከባህላዊ ባለገመድ የጆሮ ማዳመጫዎች እስከ 150 እጥፍ የሚበልጥ የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረር (electromagnetic radiation) ያመነጫሉ — ይህ በተለይ በየቀኑ ለሰዓታት ለሚጠቀሙ ሰዎች አሳሳቢ ነው። እያንዳንዱ መሳሪያ በራሱ ዝቅተኛ መጠን ያለው ጨረር ቢያመነጭም፣ ከጭንቅላትና ከአንጎል ጋር ያለው የማያቋርጥ ቅርበት ስለሚያስከትለው የረጅም ጊዜ ተጋላጭነት ጥያቄዎችን ያስነሳል።

የብሉቱዝ ቴክኖሎጂ የሚሰራው የድምፅ ሞገዶችን በሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ኤሌክትሮማግኔቲክ ፊልድስ (RF-EMFs) በማስተላለፍ ነው። እነዚህ ምልክቶች በጆሮና በጭንቅላት አካባቢ በሚገኙ ስስ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ያልፋሉ፤ እነዚህም ለሙቀት-አማቂና ሙቀት-አልባ የጨረር ውጤቶች በቀላሉ ተጋላጭ ናቸው። ምንም እንኳን አሁን ያሉት የደህንነት ገደቦች በሰውነት ክፍሎች ላይ ሙቀት እንዳይፈጠር ለመከላከል ላይ የተመሰረቱ ቢሆኑም፣ አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለረጅም ጊዜ ለዝቅተኛ ጨረር መጋለጥ በነርቭ ሥርዓትና በሴሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። በአንፃሩ፣ ባለገመድ የጆሮ ማዳመጫዎች ድምፅን የሚያስተላልፉት በኤሌክትሮማግኔቲክ ሳይሆን በሜካኒካል መንገድ በመሆኑ ከጨረር ነፃ ናቸው።

የጤና ባለሙያዎች ምቾትን ሳይሰዉ ለጨረር መጋለጥን ለመቀነስ ቀላልና ተግባራዊ እርምጃዎችን ይመክራሉ። እነዚህም፦

* ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ ማዳመጥን መገደብ፣

* ጥቅም ላይ በማይውሉበት ጊዜ የጆሮ ማዳመጫዎችን አውጥቶ ማስቀመጥ፣

* ለረጅም ሰዓት በሚሰሩበት ጊዜ ወደ ባለገመድ ወይም ከጆሮ በላይ የሚደረጉ ማዳመጫዎችን መቀየር፣ እንዲሁም

* ለስልክ ጥሪዎች የስፒከር ሁነታን (speaker mode) መጠቀምን ያካትታሉ።

የገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ከዕለት ተዕለት ህይወታችን ጋር የማይነጣጠል እየሆነ ሲመጣ፣ ዋናው መፍትሔው ልክን ማወቅና ጥንቃቄ ማድረግ ነው — ይህም ፈጠራን እየተቀበሉ የሰውነትን ወሳኝ አካል ሊደርሱ ከሚችሉ ተደራራቢ ውጤቶች መጠበቅ ነው።

እወዳችኋለሁ
(30/01/2018 ዓ.ም )
#ተዋነይ

ተዋነይ - Tewanay

ቴሌግራም : https://t.me/TewanayTMC
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100050145534341

Telegram: Contact @TewanayTMC

Photos from ገሬ ሞባይል ጥገና's post 28/06/2025

!!
📢 ( መ/ር ፍፁም ድኖ ለቤቱ በቅቷል !!!)
👉 እርሱ የአለማቱ,,, የፍጥረት ሁሉ ጌታ አንድዬ ፈጣሪ የጠራች ምስጋና ይግባው ። ከአዛኙና ሩህሩሁ,,, እዝነትና ርህራሄ (ማዳን) በመቀጠል ፀሎታችሁና ድጋፋችሁ እንዲሁ ከንቱ አልቀረችም ። መ/ር #ፍፁም የተሳካ ህክምና አድርጎ በጤንነት ወደ ቤቱ ተመልሷል ። ከልጆቹም ተቀላቅሏል ። ውዶቼ እንኳን ደስ አላችሁ ።

ከመጀመርያው ጀምሮ በገንዘብ ፥ በፀሎት እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ከመ/ሩ ጎን በመሆን ችግራችንን ለተካፈላችሁ ፤ የማይነጥፍ ፍቅራችሁንም ላጋራችሁን ,,,,,,, " ከልብ እናመሠግናለን!!" ልንል ፈልገን #ቃላቶቹ ,,, የናንተን መልካምነትና ቅንነት ለመግለፅ አነሳቸው ። አይገልጿችሁምም ።

👉 ,,,, እውነት እናንተን ለማመስገን ቃላቶች አጥረውናል !!! !! የመምህሩን ህይወት ለመታደግና ከልጆቹም በጤና እንዲቀላቀል,,,, ቤቱም በሣቅና ደስታ እንዲሞላ ከፈጣሪ በታች ምክንያት ስለሆናችሁን ,,,, #አንድዬ ዘረ-ማንዘራችሁን ከክፉ ይጠብቅልን !!! በቤት በደጃችሁ ሣቅና ደስታ ይሙላ ። አትጉደሉ,,,,አይጉደልባችሁም ። በረካ ሁኑ/ተባረኩልን ። በጣም ,,,, በጣምምምም,,, በጣም እንወዳችኋለን ። ሠላማችሁም ብዝትዝት ይበልልን ።❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
Tatek Dache

24/03/2025

ወላጅ ለሆናቹና ለሞግዚቶች

26/02/2025

የህዝብ ልጅ ልበ ቅን ክቡር ዶ/ር ቴድሮስ ካሣሁን 🙏🙏🙏🙏

1,457,000.00
አንድ ሚልየን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ብር

በለንደን ከተማ በተካሄደው የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ላይ ከታዳሚዎች እና ከአስተባባሪዎች የተገኘውን 8,300 ፓውንድ (1,457,000.00 ብር) አዘጋጆቹ ወደ መቄዶንያ አካውንት ገቢ አድርገዋል።

እናመሰግናለን!!

23/02/2025

በምትወደው ቀን መጠራት መታደል ነው ኪዳነምህረት በምልጃዋ ከፃድቃኖች መደር ነብስህን ታሣርፈው RIP

18/02/2025

ወደብ አልባነትና የአለፉት 33 ዓመታት አገራዊ ሸክሞች
ከወንድማገኝ አሸብር
🔴በኢትዮጵያና በዐማፅያን መካከል የነበረው የ17 ዓመታቱ ጦርነት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያን ለዘመናት ትገለገልበት ከነበረው የቀይ ባሕር ይዞታዋ ተነቀለች። ወደብ አልባ አገርም ሆነች።

🔴ባለፉት 33 ዓመታትም ወደብ አልባ አገር ሆና እና ከአክሱም ዘመነ መንገሥት ጀምሮ ይዞታዋ ከነበረው ከቀይ ባሕር ተገልላ ኖራለች። በዚህም ወደብ አልባ አገሮች የሚያጋጥማቸውን ፈተና ለመጋፈጥ ተገዳለች። ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ፈተናዎች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው።

🔵የመጀመርያው ኢኮኖሚያዊ ጫና ነው። ዶክተር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም ‹‹አሰብ የማን ናት?›› በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ እንደአሰፈሩት፤ እንደ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ የሆኑ አገሮች ከዋና ዋና የገበያ ማዕከሎች የተገለሉና ከገበያ ማዕከል የራቁ ሲሆኑ ወደብ አልባነት ለኢኮኖሚ ዕድገታቸው ከፍተኛ ማነቆ ሆኖባቸዋል።

ዶክተር ያዕቆብ፤ ቻውድሪና ኤርዳነቢልግ የተባሉ ምሁር የአደረጉትን ጥናት ጠቅሰው እንደጻፉት፤ ወደብ አልባና ወደብ ያለው በሁሉም ነገር ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት አገሮች በኢኮኖሚ ዕድገታቸው ሲነጻጸሩ፤ ወደብ አልባው አገር 1 በመቶ በኢኮኖሚ ዕድገቱ ወደ ኋላ ይቀራል። ይህም ማለት:-
🔵 ወደብ ያለው አገር ኢኮኖሚውን በእጥፍ ለማሳደግ 24 ዓመታትን ሲፈጅበት፤ ወደብ አልባው አገር ኢኮኖሚውን በእጥፍ ለማሳደግ 36 ዓመታት ይፈጅበታል።
🔵በሌላም በኩል ወደብ አልባ መሆን ብቻ የአንድ አገር የውጭ ንግድ መጠንን ከ33 በመቶ እስከ 43 በመቶ ሊቀንሰው ይችላል።

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪም ሆነ የእርሻ ውጤቶች የሚመረቱት ከወደብ በራቀ አካባቢ በአብዛኛው በመሐሉና በምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ስለሆነ እነዚህን ምርቶች ወደ ወደቡ ለማዝለቅ ብዙ ወጪ ይጠይቃል። ስለሆነም ከባድ ዕቃ ለማምረት ለሚፈልግ ኢንቬስተር ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የመጀመርያ ምርጫ ልትሆን አትችልም።

በዓለም የበለጸጉ ጥቂት ወደብ አልባ ሀገሮች እንዳሉ ይታወቃል። በእነዚህ አካባቢ ያሉ ሰፋፊ ገበያና የዳበረ ኢኮኖሚን በመጠቀም የወደብ አገልገሎት አለመኖር የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ ችለዋል። ሆኖም ወደብ አልባ ሆኖ በዓለም ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለ አንድም አገር እንደሌለ ዶክተር ያዕቆብ ገልጸዋል።

በአገር ደረጃ ከላይ የተገለጸው እንዳለ ሆኖ ወደብ አልባነት ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የቀን ተቀን ኑሮ ጋር ቁርኝት አለው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ለተከሠተውና በየቀኑ እንደ ሮኬት ለሚወነጨፈው የኑሮ ውድነት አንዱ ምክንያት የወደብ አለመኖር ነው። በየጊዜው በወደብ ላይ የሚጣለው ታሪፍና ቀረጥ መናር ወደ አገር ውስጥ የሚገባውንና የሚወጣውን ሸቀጥ ዋጋ እንዲንር እያደረገው ይገኛል። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ በምትጠቀምበት የታጁራ ወደብ ላይ በአንድ ቅጽበት እስከ 25 በመቶ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።

ፖል ኮሊየር የተባሉ ምሁር እንዳሉትም፤ ወደብ አልባ አገሮች ወደ ውጭ የሚልኳቸው ምርቶች በአብዛኛው በአንድና ሁለት ምርቶች ላይ ብቻ የተወሰኑ ናቸው። ስለሆነም ከድህነት የመላቀቅ ዕድላቸው በጣም የመነመነ ነው። የውጭ ባለሃብቶችም አይመርጧቸውም። በወደብ ኪራይ እና በትራንስፖርት ምልልስ ለተጨማሪ ወጪ ስለሚዳረጉም ለሸቀጦች ዋጋ መናርና ለኑሮ ውድነት የተጋለጡ ናቸው።

የባሕር በር ያለው አገር ከዓለም ጋር ይገበያያል። ወደብ የሌለው አገር ግብይቱ ከጎረቤቱ ጋር ብቻ ነው፤ ሲሉም ፖል ኮሊየር ይገልጻሉ። ስለዚህም ወደብ አልባ አገሮች የጎረቤቶቻቸው እስረኞች ናቸው፤ ሲሉም ጽፈዋል።

🔵በአጠቃላይ የባሕር በር አለመኖር ለኢኮኖሚና ለል

15/02/2025

ቀደምቶቹ ለአሁኑ የአፍሪካ ህብረት መሠረቶች

Photos from ገሬ ሞባይል ጥገና's post 18/07/2024

CONGRAJULATION!!! Atoti

ጉባ ከተማ ለፍፃሜ ማለፉን አረጋገጠ
========================

በመለያ ምት ጉባ ከተማ 4ለ1 መንጌ ቤላሻንጉልን በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።
በቀጣይ በዋንጫ እንገናኛለን!!!!!!

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Alaba K'ulito?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Zobechame Sub City
Alaba K'ulito
ገሬሞባይል

Opening Hours

Monday 08:30 - 19:00
Tuesday 08:30 - 19:00
Wednesday 08:30 - 19:00
Thursday 08:30 - 19:00
Friday 08:30 - 19:00
Saturday 08:30 - 19:00
Sunday 08:30 - 19:00