Gamo tv

Gamo tv

Share

ይህ የጋሞ ተለቪዥን ትክክለኛ የፈስቡክ ገጽ ነው።ገጹን
ላክ፣ሸርና ኮሜንት በማድረግ፣ወቅታዊና እውነተኛ መረጃዎችን በየዕሌቱ ይከታተሉ።

13/04/2026

ጋሞ ጨንቻ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አደገ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ "ሀ" እየተሳተፈ የሚገኘው ጋሞ ጨንቻ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

‎ዛሬ በጅማ ስታዲየም ጨዋታውን ያደረገው ጋሞ ጨንቻ ቡራዩ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን 41 ያደረሰው ጋሞ ጨንቻ የምድቡ መሪ በመሆን ወደ 2019 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

Gamo tv

Photos from Gamo tv's post 08/04/2026

ጋሞ ጨንቻ ፕሪሚየርሊጉን ለመቀላቀል ከጫፍ የደረሰበትን ውጤት አስመዝግቧል

‎​አርባ ምንጭ ፦ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን )

በ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 17ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ጋሞ ጨንቻ ነቀምት ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀሪ አንድ ጨዋታ እየቀረው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፕሪሚየርሊጉ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል፡፡

በጨዋታው የጋሞ ጨንቻ ሁለት የማሸነፊያ ግቦችን ፎሳ በፍፁም ቅጣት ምትና ማቴዎስ ኤሊስ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡

ድሉን ተከትሎ ጋሞ ጨንቻ ነጥቡን ወደ 38 በማድረስ ከተከታዮቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 ከፍ አድርጓል፡፡

ነቀምት ከተማ በአንፃሩ ቀሪ አንድ ጨዋታ እየቀረው ወደታችኛው ሊግ የወረደ የመጀመሪያ ክለብ ሆኗል፡፡

በነገው እለት የካ ክ/ከተማ ንብ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ከሆነ አፕሎቹ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀሪ አንድ ጨዋታ እየቀራቸው ወደ ፕሪሚየርሊጉ መቀላቀላቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

ጋሞ ጨንቻ እስከአሁን በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ካደረጋቸው 17 ጨዋታዎች 2 ግቦች ብቻ የተቆጠሩበት ሲሆን ከእነዚህም ግቦች መካከል አንዷ ግብም በፍፁም ቅጣት ምት የተቆጠረች ነች፡፡

ይህም የሚሆን ከሆነ በ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚርሊግ ጋሞ ዞን በሁለት ክለቦችም ለመጀመሪያ ጊዜ ይወከላል፡፡

✍️በዮሐንስ ባይሳ

Photos from Gamo tv's post 13/03/2026

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጨፎ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ ተገኝተው በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦችን አፅናኑ

#ዱቡሻ ~መጋቢት 04/2018 ዓ.ም

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጨፎ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ ተገኝተው በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦችን አፅናንተዋል።

በክልሉ ጋሞ ዞን መጋቢት 01/2018 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ በተለይ ደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የመሬት መንሸራት አደጋ እስከ ትላንት ቀን 8 ሰዓት ድረስ የ70 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

አደጋው በደረሰበት አከባቢ አስከሬን የማፈለለጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።.

በደረሰው አደጋ የሰው ህይወት ከማለፉና ንብረት ከመውደሙ ባሻገር 3 ሺህ 480 የቤተሰብ ዓባላት ያሉዋቸው 575 አባወራና እማወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖችን አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ከደቡቡ ኢትዮጵያ ክ/መ/ኮ

Photos from Gamo tv's post 12/03/2026

በመጀመሪያው ናዳ የተዋጡ ሰዎችን ለማውጣት የመጣውን ሕዝብ የሚያሳይ ምስል - (ሁለተኛው ናዳ ሳይከሰት በፊት)

ሁለተኛውና ከፍተኛ አደጋ ያደረሰው ናዳ እነዚህንም ጭምር ነው የዋጠው።🥺😭

Photos from Gamo tv's post 07/12/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ለሁሉም ክልሎች እና ለአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የመልካም ምኞት መግለጫ ስጦታ አበርክተዋል።

አርባምንጭ፤ ህዳር 28/2017 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

በመድረኩ ላይ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ወደ እንግዳ ተቀባይዋና ውቧ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ከተማዋን ለነዋሪዎች ሳቢና ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማትና ሌሎችም የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ምሽቱ በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተለያዩ ሙዚቃዎች የደመቀ ሲሆን የእራት ፕሮግራምና የሙዚቃ ዝግጅቱ እንደቀጠለ ነው።

Photos from Gamo tv's post 26/11/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ በተገኙበት የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአርባምንጭ ማዕከል በመከበር ላይ ይገኛል።

አርባምንጭ ፣ኅዳር 17 I 2017 ዓ.ም (ጋሞ ቴቪ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ በተገኙበት የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል "በህብር ወደ ኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ ማዕከል በመከበር ላይ ይገኛል።

በመረሀ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ በዓሉን ስናከብር ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክረን ለማስቀጠልና ጉድለቶችን ለማረም አመራሩ እና አባሉ ቃል በመግባት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

ፓርቲው ዋልታ ረገጥነትን በማስወገድ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማስፈን በመደመር መንገድ የጀመረውን ጉዞ አጠናክሮ ሀገሪቱን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማድረስ እየተጋ እንደሚገኝም ወ/ሮ ፀሐይ ገልጸዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በበኩላቸው ፓርቲው በሀገሪቱ ታሪክ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አካሂዶ በአብላጫ ድምጽ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በመጨረስ የተለያዩ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

አቶ አባይነህ አክለውም ፓርቲው እንደዞናችንም በቀደሙት ጊዜያት ያልተመለሱ የተለያዩ የህዝብ ጥያቄዎችን በመመለስ ህዝባዊነቱን ማሳየቱን ገልጸዋል።

በመድረኩ የፓርቲውን የአምስት ዓመት ጉዞ የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ታዉቋል።

መርሃ ግብሩ በተለያዩ ሁነቶች ታጅቦ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ፣ የክልል፣ የዞንና ከሁሉም መዋቅር የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎች፣ ደጋፊዎች፣ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

Photos from Gamo tv's post 23/11/2024

አርባምንጭ ከተማ ከሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ ድል ቀንቶታል

ዛሬ በ10፡00 ሰዓት ከወልዋሎ አድግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር የተገናኙት አዞዎች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

የአርባምንጭ ከተማን የማሸነፊያ ግቦችን በፍቅር ግዛው በ 22'ኛው'ደቂቃ እንድሁም አህመድ ሁሴን 49ኛው ደቂቃ ኳስን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

Photos from Gamo tv's post 22/11/2024

ወጣቶች አሉታዊ ተፅዕኖ ያላቸዉ መጤ ልማዶችን በመተዉ ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸው ተጠቆመ።

አርባ ምንጭ ፤ ህዳር 13/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን )

የጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አሉታዊ ተፅዕኖ ያላቸዉ መጤ ልማዶችን ለመከላከል ዓላማ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጀ ጳውሎስ መድረኩ አሉታዊ ተፅዕኖ ያላቸዉ መጤ ልማዶችን ለመከላከል ዓላማ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል።

ወጣቱን ወደ ጥፋት የሚመሩ አደንዛዥ እፆችን ማምረት ፣ መነገድ ይሁን መጠቀም በወንጀል እንደሚያስጠይቅ ተጠቁሟል ።

ለሀገር እድገትና ብልጽግና የወጣቱ ሚና በተመለከተ በመድረኩ ተብራርቷል ።

Photos from Gamo tv's post 21/11/2024

በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አገአሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አርባምንጭ ከተማ ገባ።

አርባምንጭ፤ ህዳር 12/03/2017 ዓ.ም(ጋሞ ቴለቪዥን )

የልዑክ ቡድኑ አባላት አርባምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጋሞ ዞንና በአርባምንጭ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አባይነህ አበራን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና በጋሞ አባቶች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

እንግዶቹ በአርባምንጭ ቆይታቸውም ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ብሎም እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ይቃኛሉ።

ከአብይ ኮሚቴዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የስራ ውይይትና ግምገማ እንደሚያደርጉና የልማት ስራዎችንና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።

Photos from Gamo tv's post 19/11/2024

በክልሉ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለፀ።

አርባምንጭ፥ ህዳር 10/2017ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን )

"ኮንትሮባንድና ህገ- ወጥ ንግድን ለመከላከል እና የኤክስፖርት ምርት ማነቆዎችን ለመፍታት በጋራ እንረባረባለን!!" በሚል መሪ ሃሳብ የንቅናቄ መድረክ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ጤናማ የገበያ ስርዓት ለሀገር ሉዓላዊነት ቁልፍ መሆኑን አመላክተዋል።

ህገ - ወጥ የነዳጅ ግብይት የኑሮ ውድነትን እያባባሰ ነው ያሉት አቶ ገብረመስቀል ግብረ-ሀይሉ ለጉዳዮ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኮንትሮባንድ የንግድ ስርዓትን የሚያዛባና የውጪ ምንዛሪን የሚያሳጣ በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ክልሉ ዘርፈ ብዙ አምራች መሆኑን ጠቁመው የሀገር ውስጥ ምርትን ማበረታት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በ2016 በጀት ከክልሉ ከተላኩ ምርቶች ከ53 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን ጠቅሰዉ ይህንን ይበልጥ ለማሳደግ ኮንትሮባንድ ተግዳሮት መሆኑንም ገልፀዋል።

በክልሉ ከፍተኛ የወጪና የገቢ ኮንትሮባንድ ዝውውር መስተዋሉን የገለፁት አቶ ገለቦ ከ972 ሚሊዮን 770 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው እቃዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል ።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬዘር ኦርካይዶ የኮንትሮባንድ ንግድ ከኢኮኖሚ ችግር ባሻገር በክልሉ እና በሀገር ደረጃ የሚያስከትለው ስጋት ከፍተኛ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ መርሃ-ግብሩ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን መከላከል እና ወደ ውጪ በሚላኩ ምርቶች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

በመርሃ-ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ጫላን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የፀጥታ ዘርፍና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Photos from Gamo tv's post 19/11/2024

Dugeha Tophphiya kilile payyateththa biiron HIV Eedisenne hepitaytese harge teqonne naago mac'aray 2016 bajete laytha ootho polonne oyqettida bajete laytha heedzdzu aginata halcho polo mixxi xeelo duulata Arba Minc'e kataman oothettishe dees.

Gaammo Arba Minc'e :Balbala 9/2017M.L( Gaammo Telebizhine)

Dugeha Tophphiya kilile payyateththa biiro kaalo kaappo Daanna Gaashsha Maatoosay duulatan beettidi hashshu saro yideta kiita aaththida gidishin, Eedise hargey salo sa'a deththan benippe doommidi haysa gaththo dereteththa kifileta shempo dhaysishe dizaysa yootida.

Tophphiyanka hargezi mala, zereththanne qoommo shaakkenna dalga gidida muruutancha gadaaddeta worshe dizaysi qasse ikkonoome , polettikaninne dereteththa bolla wolqama naaqo gaththishe dees gida.

Dugeha Tophphiya kililen ubba zonetankka qeeri naytaninne mac'c'ata bolla hargey dalga qoha gaththishe dizaysa yootidi, issi laytha giddon undena gidiza gadaaddeti hargen oyqettizaysanne delga asay qasse hargezan hayqizayasa malatida.

Duulatazan kililenne zoone dhoqqa kaappoti, payyateththa mac'ara kaappotinne oothanchati beettida.

Photos from Gamo tv's post 16/11/2024

በክልሉ አሪ ዞን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወነ የሚገኘው የልማት ተግባር የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚዲያ ቱር እያደረገ የሚገኘው ልዑክ በኦሪ ዞን በጥላ ማኑፋክቸሪንግ አክስዮን ማህበር የበቆሎ ምርጥ ማባዣ ጣቢያንና የኮሪደር ልማትን ጎብኝቷል።

አርባምንጭ፥ ህዳር 06/2017 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)፦

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ አዜብ ዘውዴ የበርካታ ብሄረሰቦች መኖሪያ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘርፈ ብዙ የልማት ስራ የሚሆን አመቺ ስነምህዳርና አየር ንብርት መታደሉን ገልፀዋል።

በክልሉ በሁሉም የልማት ዘርፎች የወጣቶችን ተሣትፎ በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወነው ተግባር አበረታች ለውጥ መታየቱንም አብራርተዋል።

በክልል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ በተሰጠው ትኩረት አመርቂ ውጤት እየታየ መገኘቱን ያስታወቁት ወ/ሮ አዜብ፤ የኣሪ ዞኑ መልካም ተሞክሮን ለአብነት አንስተዋል።

ክልሉ ለጠለቀ ማህበራዊ መስተጋብር መሠረት የሆኑ ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት መሆኑን ያስገነዘቡት ወ/ሮ አዜብ፤ የክልሉን እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ በማልማት የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል ብለዋል።

የኣሪ ዞን የሚታወቀው በኮረሪማ ምርት እና ምርጥ ዘር አቅርቦት መሆኑን ያስታወቁት ወ/ሮ አዜብ፤ በየአካባቢው የሌማት ትሩፋትን በማጎለበት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የገበያ ተኮር ግብርና ምርትን ማሣደግ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

የኣሪ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አጣ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል በብዝሀ ባህልና ማህበራዊ እሴት የደመቀውን የዞኑን ህዝብ ያልተዳሰሰውን የተፈጥሮ ፀጋና ማህበራዊ ሀብት ለተቀረው ህዝብ ለማስተዋወቅ ሚናው የላቀ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በተለይም ከሀገራዊ ለውጥ ወዲህ የዞኑ ህዝብ የልማት ተሣትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው፤ በገጠሪቱ ዞኑ በስፋት የሚታወቀውን የቡናና ኮረሪማ ምርት ማሣደግና ከክልሉ ብዝሃ ማዕከላት መካከል አንዷ የሆነችውን የጅንካ ከተማን በህብረተሰብ ተሣትፎ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ማስዋብ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የኣሪ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ የባካ ዳውላ ምርጥ ዘር አቅርቦት ማህበር በ15 ሄ/ር የእርሻ መሬት ምርጥ ዘር ብዜት በማከናወን ለአርሶ አደሩ እያሰራጨ መገኘቱ በዞኑ የግብርና ልማትን ከማጠናከር ረገድ የጎላ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

አቶ አውግቸው ዘውዴ የባካ ዳውላ ምርጥ ዘር ብዜት ማህበር ሰብሳቢ ሲሆኑ፤ መንግስት ያመቻቸውን የ15 ሄ/ር የእርሻ መሬት በመጠቀም በህብረተሰቡ ፍላጎት መሠረት ምርጥ ዘር እያባዙ እንደሚያሰራጩ ተናግረዋል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Gamo
Arba Minch'