31/05/2026
ፍጻሜውን ባገኘው ሻምፒዮንስ ሊግ ክለቦች የሚያገኙት የገንዘብ መጠን
👉 ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ 127 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 አርሰናል 124.7 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ባየር ሙኒክ 110.8 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ሊቨርፑል 95.3 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 አትሌቲኮ ማድሪድ 90.7 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ሪያል ማድሪድ 90.1 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ባርሴሎና 86.5 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ማንችስተር ሲቲ 84.4 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ቼልስ 80.2 ሚሊዮን ፓውንድ
👉 ቶተንሀም ሆትስፐር 74.3 ሚሊዮን ፓውንድ
30/05/2026
የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂን አርሰናልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
ፒኤስጂ አርሰናልን በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍ የዋንጫው አሸናፊ ሆኗል።
ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነበር ያጠናቀቁት።
የአርሰናልን ግብ ካይ ሀቨርትዝ የፒኤስጂን ደግሞ ኡስማን ዴምቤሌ ማስቆጠር ችለዋልተ
በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ የሻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፈዋል።
ፒኤስጂ በሁለት ተከታታይ አመት ዋንጫውን በማሸነፍ ከሪያል ማድሪድ ቀጥሎ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።
30/05/2026
ባርሰሎና አንቶኒ ጎርደንን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ
ባርሴሎና ለተጫዋቹ ዝውውር 69.3 ሚሊዮን ፓውንድ ወጭ አድርጓል፡፡ የ25 ዓመቱ እንግሊዛዊ ከባርሴሎና ጋር እስከ 2031 የሚቆየውን ውል ፈርሟል፡፡
በኒውካስትል ዩናይትድ የ3 ዓት ተኩል ቆይታው ራሱን በሚገባ ያሳየው ጎርደን አሁን ወደ ሌላ ትልቅ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡
የቀድሞው የኤቨርተን የመስመር አጥቂ ይሄንን ትልቅ ክለብ በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡
29/05/2026
ሀገሬ ቴሌቪዥን የዓለም ዋንጫን የቀጥታ ስርጭት እንዳያስተላልፍ ለምን ተፈለገ?
የእግዱ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር የተገናኘ ነው።
የኢትዮጵያ ቴሌቪን ከዚሁ ጋር በተገናኘ ቴሌቪዥን ጣቢያው ስርጭቱን እንዳያስተላልፍ የሚጠይቀው ደብዳቤ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ተልኳል።
ጉዳዩ ከጥቅም ግጭት ጋር የተያያዘ መሆኑን የአንዳፍታ ሚዲያ ምንጮች ገልጸዋል።
ሀገሬ ቴሌቪዥንን በቅርቡ በስራ አስኪያጅነት የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ነዋይ ይመር ሀገሬ ቴሌቪዥን የዓለም ዋንጫን በቀጥታ ስርጭ ለማስተላለፍ የሚያስችለውን ስምምነት መፈረሙን ከተናገረ በኋላ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝቷል።
ጋዜጠኛ ነዋይ ላለፉት 12 ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የስፖርት ክፍል ሀላፊነት ያገለገለ ሲሆን በቅርቡ ወደ ሀገሬ ቴሌቪዥን በዋና ስራ አስኪያጅነት መቀጠሩ ይታወቃል።
በዚህ ስዓት ሀገሬ ቴለቪዥን የጨዋታ የቀጥታ ስርጭቶችንና የስፖርት ተንታኝ ጋዜጠኞችን እያስተዋወቀ ይገኛል።
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ምንም አይነት ማስታወቂያ እንዳያስነግሩ መመሪያ መተላለፉም ታውቋል።
28/05/2026
አርባ ምንጭ ከተማ በሊጉ ስድስተኛ ድሉን አስመዘገበ
ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉት አርባ ምንጭ ከተማዎች ለዋንጫ ክብር ከሚጫወተው መቻል ጋር ባደረጉት የምሽቱ ጨዋታ ግብ በማስቆጠሩ ረገድ ቀዳሚ መሆን ችለዋል።
በ32ኛው ደቂቃ ላይ በፈጠሩት ፈጣን መልሶ ማጥቃት ኤፍሬም ታምራት በጥሩ ቅብብል ያመቻቸውን ኳስ አሸናፊ ተገኝ በጥሩ አጨራረስ ወደ ግብነት ቀይሮ አርባምንጭን መሪ አድርጓል።
ከዚህ ግብ በኋላ መቻሎች የአቻነት ግብ ለማግኘት በቁጥር በዝተው ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም የሚያደርጉትን ጫና የአርባምንጭ ተከላካዮች በመቋቋማቸው የመጀመሪያው አጋማሽ በአዞዎቹ 1ለ0 መሪነት ተጠናቋል።
ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ መቻሎች በፍጥነት ወደ ጨዋታው የመለሳቸውን ግብ ማስቆጠር ችለዋል::
ከማዕዘን ምት ተሻግሮ በተጫዋቾች የተጨራረፈውን ኳስ ቻርለስ ሙሴጌ አግኝቶ ወደ ግብነት በመቀየር መቻልን አቻ ማድረግ ችሏል።
ይሁን እንጂ አርባ ምንጭ ከተማዎች ሳይደናገጡ ወዲያውኑ ምላሽ ሰጥተዋል።
በ60ኛው ደቂቃ ላይ መነሻውን ከቀኝ መስመር ያደረገውን ኳስ ጄሮም ፍሊፕ በጥሩ ቅልጥፍና ተጫዋቾችን አልፎ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ቴዎድሮስ በንቲ መረብ ላይ በማሳረፍ አዞዎቹን በድጋሚ መሪ አድርጓል።
ከግቧ መቆጠር በኋላ መቻሎች የአቻነት ግብ ፍለጋ በቁጥር በዝተው ወደፊት በመጠጋት ተከታታይ ጥረቶችን ሲያደርጉ በአንፃሩ የአርባምንጭ ከተማ ተጫዋቾች በራሳቸው የግብ ክልል በጥንቃቄ አፈግፍገውና ተጠቅጥቀው በመከላከል የመቻሎችን ሀሳብ ማክሸፍ ችለዋል።
ጨዋታውም በአርባ ምንጭ 2ለ1 አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ አርባ ምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት የሚያግዘውን ወሳኝ ሶስት ነጥብ ሲያገኝ መቻሎች በበኩላቸው ከሊጉ መሪ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት የሚያጠቡበትን ወርቃማ ዕድል ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።
28/05/2026
የእንግሊዝ ክለቦች በአውሮፓ መድረኮች አልተቻሉም
አስቶንቪላ✅
ክርስታል ፓላስ✅
አርሰናል ?
28/05/2026
በ34ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አርባምንጭ ከተማ ከመቻል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች እና ከቦታ ለውጥ በኋላ ሲመለስ አርባ ምንጭ ከተማ በአዳማ ሳ/ቴ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ከመቻል ጋር ይገናኛል፡፡
በሊጉ ላለመውረድ እየታገለ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ በቀሩት ጨዋታዎች ውጤት ይዞ መውጣት የህልውናው ጉዳይ በመሆኑ ከጨዋው ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት ይፋለማል፡፡
መቻል በአንፃሩ በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ለመቆየት በጨዋታው ድልን ለመቀዳጀት ይፋለማል፡፡
አዞዎቹ ለጨዋታው የሚያደርጉትን ዝግጅት በአዲስ አበባ ሱሉልታ ሜዳ ያከናወኑ ሲሆን የፊታችን ሀሙስ ግንቦት 20 /2018 ዓ.ም ከመቻል ጋር ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡
አርባ ምንጭ ከተማ በሊጉ ካደረጋቸው 33 ጨዋታዎች 29 ነጥቦችን በመሰብሰብ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኝ ሲሆን መቻል በበኩሉ 33 ጨዋታዎችን አድርጎ 58 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በአምስት ነጥቦች ርቆ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ሃዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና፤ድሬዳዋ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእለተ ሀሙስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን አርብ ዎላይታ ዲቻ ከነገሌ አርሲ፤ምድረገነት ሽሬ ከሃዲያ ሆሳዕና፤ፋሲል ከነማ ከሸገር ከተማ ይገናኛሉ፡፡
በእለተ ቅዳሜ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ፤መቀለ ሰባአንደርታ ከባህርዳር ከተማ እንድሁም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵ መድን ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
28/05/2026
የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ 16 የስታዲየሞች ]
ለ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ 14 ቀናት ብቻ ሲቀሩት፣ በታሪክ ትልቁ ለሆነው የቅድመ-ውድድር ዝግጅት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል።
በዚህ ታላቅ ውድድር ላይ 48 ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በሜክሲኮ በሚገኙ 16 ስታዲየሞች ውስጥ 104 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
እንደ ኤስታዲዮ አዝቴካ (Estadio Azteca) ያሉ ታሪካዊ ስታዲየሞች፣ ለዓለም ዋንጫው ተስማሚ ሆነው ከተዘጋጁት ግዙፍ የኤን.ኤፍ.ኤል (NFL) ስታዲየሞች ጋር በመሆን ትኩረትን ይስባሉ፤ ከእነዚህም መካከል በዳላስ የሚገኘው ኤቲ ኤንድ ቲ ስታዲየም (AT&T Stadium) እና የፋይናል ጨዋታው የሚስተናገድበት በኒው ዮርክ አቅራቢያ የሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም (MetLife Stadium) ይገኙበታል።
በርካታ ስታዲየሞች የተፈጥሮ ሳር ከመትከል ጀምሮ የመቀመጫ ዝግጅታቸውን ከፊፋ መመዘኛዎች ጋር እስከማስተካከል ድረስ ትልቅ ቅድመ-ዝግጅት አድርገዋል።
28/05/2026
ክሪስታል ፓላስ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ ለዩሮፓ ሊግ ማለፉን አረጋግጧል።
ይህንንም ተከትሎ በሚቀጥለው አመት በአውሮፓ መድረክ የሚሳተፉ የእንግሊዝ ክለቦች ቁጥር 9️⃣ ደርሷል።
ከፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ግማሽ ያህል የሚጠጉት ክለቦች በአውሮፓ መድረክ የሚጫወቱ ይሆናል።
በአውሮፓ መድረክ ማን ይሳተፋል ?
⏩ ሻምፒየንስ ሊግ :- አርሰናል ፤ ማንችስተር ሲቲ ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ፤ አስቶን ቪላ ፤ ሊቨርፑል
⏩ ዩሮፓ ሊግ :- በርንማውዝ ፤ ሰንደርላንድ ፤ ክሪስታል ፓላስ
⏩ ኮንፈረንስ ሊግ :- ብራይተን