Elmedin Mohammed page

Elmedin Mohammed  page

Share

writing about football

05/11/2022

መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እንድትነግርዋቸው የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው። እነርሱ የሚያስቡትን ካላወራችሁ እናንተ ስህተተኞች ናችሁ። እነርሱ አረንጓዴና ቀይ ቀለም ከወደዱ እናንተ ቢጫ የመውደድ መብት የላችሁም፤ እንደውም ቢጫ የሚባል ቀለም የለም ሁሉ ሊልዋችሁ ይችላሉ። እናንተ እንጂ እነሱ ምንም የማለት መብት አላቸው። እነርሱ ያሰቡትን፥ እነርሱ የሚፈልጉትን ካላላችሁ እናንተ ልክ ብትሆኑም እንኳ ልክ አይደላችሁም። እንደ አህያ መልክ አንድ አይነት በሚዘመርበት "እኔን" ሆኖ መቆም በኛ ሀገር ኃጢአት ነውና።

ኤፍሬም ስዩም
የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች
ገጽ:-72

03/11/2022

greham Potter vs Quique setien

እነዚህ ሁለት አሰልጣኞች በአነስተኛ በጀት ተፎካካሪ ቡድን መገንባት እንደሚቻል በነበሩባቸው ክለቦች፤
ፖተር በብራይተን ሰቴን በሪያል ቤትስ ያሳዪ ባለሙያዎች ናቸው።

ትልልቅ ቡድኖች ከምትከተለው የእግር ኳስ ዕሳቤ ውጪ በቶሎ ውጤት የሚፈልጉ በመሆናቸው እራሳቸውን በመካከለኛ ቡድን ውስጥ በሚገባ አሳይተው ለሚመጡ አሰልጣኞች ፈታኝ እየሆኑ ነው።

ኬኬ ሴቴን ዕድገቱን እየጨረሰ የነበረውን ባርሴሎናን ተረክበው ውጤታቸው የክለቡን ሃላፊዎችና ደጋፊዎች ማስደሰት ባለመቻሉ ከባርሴሎና ተሰናብተዋል።

ግራሃም ፖተር ከአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች ውጪ እምብዛም የማይታወቀውን ብራይተንን የራሱ የሆነ የጨወታ መንገድ ያለው ቡድን አድርገው ጥሩ እግር ኳስን ከውጤት ጋር አሳይተው ለትልቁ ኅላፊነት ለመረከብ መንደርደሪያ ሆኖታል።

ግራሃም ፖተር የሴቴን ዕጣ ይደርሰው ይሆን? ወይስ በብራይተን ያሳየውን ማራኪ ቡድን በቼልሲም ከውጤት ጋር የሳያናል??

26/10/2022

"ዕድሜና እግር ኳሳችን"

በቀድሞ ስሙ መከላከያ በአሁኑ አጠራር መቻል ተጫዋች በነበርኩበት ጊዜ ክለቡ አጠቃላይ ምርምራ ሊያደርግልን የኛን አድራሻ እና ዕድሜ በሆነ ፎርም ላይ ሊሞላ መረጃ ከኛ እየወሰደ ነው።

የኔ ተራ ደርሶ አድራሻዬን ካስሞላሁ በኋላ ዕድሜ ስባል 26 ስል ከኔ ቀጥሎ የነበረው ጓደኛዬ😂 27ትን ከፈራሀው 28 አትልም እንዴ😂ሲለኝ ይመዘግብ የነበረው ሰውዬ😂😂😂😂😂

የኢትዮጵያን እግር ኳስ የዕድሜ ችግር ለመፍታት ፊፋ እና ካፍ ያስቀመጧቸውን መሰፍርቶች በሟሟላት ከዕድሜ ጋር በተደጋጋሚ የሚነሱ ሃሜቶችን ፌዴሬሽኑ ለመቅረፍ እየሞከረ እንደሆነ ይሰማኛል።

በእኔ ዕድሜና ከኔ በፊት በነበሩት አመታት ከነበሩት ወጣት እና ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኖች አንፃር ስናየው "የአበቡከር"(ይህ ትውልድ)በብዙ ርቀት የተሻለ ሆኖ ይታያል።

በዕርግጥ አስገዳጁ የ MRI ምራመራ ሁሉም ሀገራት የዕድሜ ጉዳይ ላይ ጠንከር እንዲሉ አድርጓቸዋል።

እኛ ሀገር ከዕድሜ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በሂደት እየቀረፍን መሆኑን ማነፃፀር ያለብን ከራሳችን፣ ከዚህ በፊት ስንጓዝበት ከነበረው መንገድ ጋር ነው መሆን ያለበት። በአውሮፓውያን መለኪያ ከሄድን መቼም ችግሮቻችንን ላይ ለውጥ ማምጣት አንችልም።

ዕድሉ ደረጀ ምን ሆነህ ነው 99% ትክክለኛ ዕድሜ ነው የመረጥኩት የምትለን???100% ምርጫው ትክክል ነው።

23/10/2022

ሮናልዶ ጨወታው ሳያልቅ ሄደ!!
ዳንኤል ታደለስ?

1996 ወንጂ ስኳር በሜዳው ሃረር ቢራን ይገጥማል ሀረርን ከመግጠማችን በፊት በነበረው ጨወታ ላይ የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የነበረው ዳንኤል በዚህ ጨወታ ላይ ግን ተጠባባቂ ሆኖ ወደጨዋታው ይሄዳል

በጨዋታው ላይ ፍፁም የበላይነት የነበረው ወንጂ ስኳር
6ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ያሸንፋል። እናማ ዳኒሻ ሆዬ የቡድኑ ማሸነፍ እሷ ተጠባባቂ በመሆኗ የተገኛ ድል ስለመሰላት ጨወታው ሲያልቅ ሻንጣዋን ሸከፋ ወደ መኪና ተራ😂 አብሮ አደግ ጓደኛው ኤርሚያስ ታደሰ(ለበጎ ነው ጩሀታችን የቡና መዝሙር የዘፈነው) ተው እንጂ ቡድናችን አሸንፎ እንዲህ መሆን አይገባህም ልጆቹ ያዝኑብሃል ብላ ለማባባል መሞከር😂ዳኒሻ ሆዬ አትከተለኝ ተመለስ ብሎ ዲንጋይ ማንሳት 😂ቢለመን ተው ቢባል አሻፈረኝ ብሎ ሻንጣውን ለኤርሚ ወረውሮ ሄደ። በወቅቱ አሰልጣኛችን ኢንስትራክተር አብረሃም ለተጫዋቾች ቅርብ ስሜታችንን የሚረዳ ኮች ስለነበረ ይቅርታ ጠይቆ ወደ ቡድኑ ተመልሶ በአሸማጋዬች ጓዳዩ አለቀ።

አመቱ ሲያልቅ ዳንኤል ታደለ ከወንጂ ጋር ተለያየ ማቆም በማይገባው ሰአት በባህሪው ምክንያት ኳስ አቆመ።

ሮናልዶስ??? ድንገት በቃኝ ሊለን ይሆን??

በነገራችን ላይ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች በእግር ኳስ ያጋጥማሉ እኔ ሮናልዶ ጨወታው ሳያልቅ መሄዱ አልገረመኝም በእግር ኳስ ያገኛቸው ክብሮች እና አሁን ያለበት ሁኔታ ሊጣጣሙለት አልቻሉም እግር ኳስ ደግሞ በትላንት የምትኖርበት ሙያ አይደለም ዛሬ ዛሬ ዛሬና ዛሬ ብቻ በምታሳየው ፐርፎርማንስ ነው የምትዳኘው!!

ተጫዋቾች ከአሰልጣኞቻችሁ ጋር እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲገጥሟችሁ ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ከክለቡ እና ከአሰልጣኙ ጋር ለመለያየት ሞክሩ!!

"ዳኒዬ በኛ ይብቃ ትውልድ ይዳን ለማለት ነው"

20/10/2022

ሊጉ ላይ ጎሎች እየተቆጠሩ ነው እስከ አሁን በግሌ አሰልቺ የምለው ጨወታ አላየሁም ዳኞች ብቻ! ቀጥታ ቀይ ካርድ እና ፔናሊቲ ለመሰጠት አይፍሩ!!

17/10/2022

ከአዲስ አበባ ክለቦች አንዱ ውስጥ የአንድ ክለብ ቦርድ አባል አለ! ቅልጥ ያለ የቡና ደጋፊ ነው የሱ ክለብ ከቡና ጋር ሲጫወት ማንን የሚደግፍ ይመስላችኋል?
የክለብ ቦርዶች ዝውውር ሲጀመር ይህ ሰው በነፃ😂

14/10/2022

ቀጣዪ የሊግ ካምፓኒው ሰብሳቢ ማን ይሁን?

በህዳር ወር ክለቦች የሚወክሏቸውን ሰዎች በሚመርጡበት ምርጫ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያገኘውን ወርቃማ ዕድል አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል ለውጥ አስፈላጊ ይመስላል።
ሊጉን እየመሩ ያሉ አካላት በሚፈለገው መልኩ መምራትና የኢትዮጵያን እግር ኳስ ማሳደግ እንዳልቻሉ የሊግ ካምፓኒው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ዛሬ በሰጡት ቃለምምልሰ የተረዳን ይመስለኛል።

በውስጡ ከክለቦቻቸው ከስራ የለቀቁ የክለብ አመራሮችን የያዘው ሊግ ካምፓኒ እንደገና ፈርሶ ሊጉ ላይ ያሉ ሁሉንም ክለቦች በሚያስማማ መልኩ እንደገና መዋቀር ያለበት ይመስለኛል።
ከነዚህ ሰዎች አንዳቸው ሰብሳቢ ቢሆኑ ምን ትላላችሁ?

1-አቶ አብነት ገብረመስቀል(ቅዱስ ጊዮርጊስ)

2-አቶ መላኩ ፈንታ (ፋሲል ከነማ)

አቶ መላኩ የፋሲል ከነማ ፕረዚዳንት ስላልሆኑ ህጉ አይፈቅድም ካላችሁ ህጉን አሻሽሉት

3-አቶ አበባው ሰለሞን( ወልቂጤ ከተማ)

10/10/2022

LA MASIA Principle...
"pass it, pass it and pass it again. Pass precisely, move well, pass again, pass, pass and pass.
We want every move to be smart, every pass accurate. That's how we make the difference from the rest of the teams."

Photos from Elmedin Mohammed  page's post 04/10/2022

የአውሮፓ ክለቦች አሰልጣኝ ሲቀጥሩ የሚያወጡትን ማስታወቂያ ማግኘት የሚችል ካለ ቢተባበረኝ? ሰሞኑን ቼልሲ እና ብራይተን አሰልጣኞቻቸውን ሲቀጥሩ ስንት ገፅ የፈጀ ማስታወቂያ በክለባቸው ፅ/ቤት ለጥፈው ይሆን😂

03/10/2022
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Arba Mintch?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Arba Mintch