ቤጉ ስፖርት - Begu Sport

ቤጉ ስፖርት - Begu Sport በዚህ ገጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ
ወቅታዊ እና ትኩስ የስፖርት መረጃዎች ይቀርቡበታል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካዉንስል የክረምት በጎ ፍቃድ አካል የሆነው የእግር ኳስ ዉድድር ሊጀመር ነው።**********************ውድድሩ በአሶሳ ከተማ በሚገኙ በተመዘ...
26/08/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካዉንስል የክረምት በጎ ፍቃድ አካል የሆነው የእግር ኳስ ዉድድር ሊጀመር ነው።
**********************
ውድድሩ በአሶሳ ከተማ በሚገኙ በተመዘገቡ አስር መስጂዶች መካከል የሚደረግ ሲሆን የዕጣ ማዉጣት ሥነ ሥረዓቱ በዛሬው ዕለት ተካሂደዋል።

ይህ የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የክረምት በጎ ፈቃድ አካል የሆነው የእግር ኳስ ዉድድር ቅዳሜ ነሃሴ 23/2018 በአሶሳ መለስተኛ ትምህርት ቤት ሜዳ ይጀምራል።

በመክፈቻውም አቡበከር መስጂድ vs ሀሊድ ብን ወሊድ መስጂድ መካካል ከቀኑ 7 ሰአት የሚጀምር ይሆናል።

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን አሳወቀችሀገራችን የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ጥያቄዋን ያቀረበችበት ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ...
24/08/2026

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን አሳወቀች

ሀገራችን የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ጥያቄዋን ያቀረበችበት ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ማስገባቷን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ዶክመንቶችን ያካተተ ሰነድ (BID HAND BOOK) ለካፍ በማስገባት ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሽነር ኢብራሂም ሃጂ መንሱር ኬንያ ገብተዋልኮሚሽነሩ ወደ ኬንያ የተጓዙት የአፍሪካ ሀገራት ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (ANOCA) ዞን 5 ጨዋታ ለ...
24/08/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሽነር ኢብራሂም ሃጂ መንሱር ኬንያ ገብተዋል

ኮሚሽነሩ ወደ ኬንያ የተጓዙት የአፍሪካ ሀገራት ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (ANOCA) ዞን 5 ጨዋታ ለመሳተፍ ሲሆን ከኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ጋር ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኬንያ ተጉዘዋል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ወሃ ዋና፣ ውሹ እና ቴኳንዶ ስፖርቶች ትካፈላለች።

ነብሮ ቮሊቦል ክለብ የፀባይ ዋንጫን ይዞ ወደ አሶሳ ገባ!!‎‎አሶሳ፣ ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም. — በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና የቮሊቦል ውድድር ከክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ...
24/08/2026

ነብሮ ቮሊቦል ክለብ የፀባይ ዋንጫን ይዞ ወደ አሶሳ ገባ!!

‎አሶሳ፣ ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም. — በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና የቮሊቦል ውድድር ከክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ቤኒሻንጉል ጉሙዝን ወክሎ የተሳተፈው የወረዳ ሁለት ነብሮ ቮሊቦል ክለብ የፀባይ ዋንጫን ጨምሮ 3 የቮሊቦል ኳሶችና 1 የቮሊቦል መረብ ተሸልሞ ዛሬ ወደ አሶሳ ከተማ ገብቷል።

‎በኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ወክሎ የተሳተፈው ነብሮ ቮሊቦል ክለብ ከክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባደረገው ውድድር ያሳየውን ተሳትፎና መልካም ባህሪ ተከትሎ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

‎ክለቡ ከውድድሩ የተገኘውን ልምድና ሽልማት ይዞ አሶሳ ሲደርስ በወረዳ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችና በክለቡ ደጋፊዎች አቀባበል የተደረገለት ሲሆን የክለቡ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የልዑካን ቡድኑ በውድድሩ ያሳዩት ተሳትፎ ለቀጣይ የሥልጠናና የዝግጅት ሥራዎች ጠቃሚ ልምድ እንደሆነ ተገልጿል።

‎ለክለቡ ተጫዋቾችና አሰልጠኞች የወረዳ ሁለት ወ/ስ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አንዱዓለም መኮነንና የወረዳው ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ለሜሳ በቀለ ለክለቡ ያላቸውን አድናቆትና አክብሮት ለመግለፅ አበባ ይዘው የተቀበሏቸው ሲሆን ለልዑካን ቡድኑ ማምሻውን የእራት ግብዣ መርሃ ግብርም ተደርጎላቸዋል።

ነብሮ ቮሊቦል ክለብ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ አሸናፊ ሆነከነሃሴ 10/2018 እስከ ነሃሴ 17/2018 ድረስ በአድስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የቮሊቦል ክለቦች ውድድር ዛሬ ሲጠናቀቅ የቤኒሻንጉል...
23/08/2026

ነብሮ ቮሊቦል ክለብ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

ከነሃሴ 10/2018 እስከ ነሃሴ 17/2018 ድረስ በአድስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የቮሊቦል ክለቦች ውድድር ዛሬ ሲጠናቀቅ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የወከለው ነብሮ ቮሊቦል ክለብ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ አሸንፏል።

ክለቡ ከዋንጫ በተጨማሪ ሶስት ኳስ እና መረብ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

በቀጣይም በክልሉ ያለውን እምቅ አቅም መጠቀም እንዲያስችል ለክለቡ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረጉለት ተገልጿል።

ነብሮ ቮሊቦል ክለብ በወረዳ ሁለት ስር የሚገኝ ሲሆን በወረዳው እና በክልሉ ድጋፍ እየተደረገለት የሚገኝ ክለብ ነው።

በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ከ15 አመት እና ከ17 አመት በታች እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ።*******************************************ነሀሴ 17/2018 አ.ም ፤...
23/08/2026

በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ከ15 አመት እና ከ17 አመት በታች እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ።
*******************************************

ነሀሴ 17/2018 አ.ም ፤ በአሶሳ ከተማ አስተዳደር መ/ኮ/ባ/ቱ ስፓርት መምሪያ አዘጋጅነት የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብርን አስመልክቶ ሲካሄድ የቆየው ከ15 አመት በታች እና ከ17 አመት በታች የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር በ15 አመት ኮሞሻ ተስፍ ቡድን በ17 አመት በታች አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አሸኛፊነት ተጠናቋል።

በውድድሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት የአሶሳ ከተማ አስ/ር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አቢዮት ማተቡ መንግስት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ውስጥ የበጎ ስራዎችን ተጠናክረው የማህበረሰቡ ባህል እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን እየሰረ ይገኛል።

ይህ የታዳጊዎች የእግርኳስ ውድድር አንዱ የማህበራዊ ዘርፍ የበጎ ፍቃድ ስራ ላይ ተካቶ እንዲሰራ መደረጉ የሚበረታታና ሊቀጥል የሚገባ የትውልድ ማስተሳሰሪያ ነው በማለት በቀጣይ የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብር ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ንቅናቄ ተጠናክሮ ስለሚቀጥል የስፓርቱ ማህበረሰብና የከተማዋ ነዎሪዎች በንቃት እንዲሳተፋ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአሶሳ ከተማ አስ/ር መ/ኮ/ባ/ቱ/ስ መምሪያ ሀላፊ አቶ በድሉ አበራ ስፖርትና በጎ ስራ የማይነጣጠሉ የጤናማ ትውልድ ማበልፀጊያ ዘርፎች በመሆናቸው ይህ የታዳጊ ቡድኖች የእግር ኳስ ውድድር ጤናማ ተተኪ ስፓርተኞችን እና በበጎ ስራ የሚሳተፉ ዜጎችን ለማፍራት ተቀናጅቶ የተዘጋጀው መርሀ ግብር በስኬት ተጠናቋል ብለዋል።

በመጨረሻም በውድድሩ ሂደት ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ፤ ዳኞችና ለተሳተፉ ቡድኖች ፤ ለኮከብ ስፓርተኞችና አሸናፊ ቡድኖች የምስጋና ሰርተፍኬት ፣ ልዩ ልዩ ሽልማትና የዋንጫ ሽልማት ተሰጥቶ መርሀ ግብሩ ተጠናቋል።

መንጌ ቤላሻንጉል B የ2018 ዓ/ም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲቲ ካፕ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነዛሬ በተደረገው የማጠቃለያ ውድድር መንጌ ቤላሻንጉል B  ነስር ክለብን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸ...
22/08/2026

መንጌ ቤላሻንጉል B የ2018 ዓ/ም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲቲ ካፕ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ

ዛሬ በተደረገው የማጠቃለያ ውድድር መንጌ ቤላሻንጉል B ነስር ክለብን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሲቲ ካፕ ሻምፒዮን ሆኗል።

21/08/2026

የተወዳጁ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ የውድድር ዘመን በሻምፒዮኑ አርሰናል እና ኮቨንተሪ ሲቲ ጨዋታ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ጅማሮውን ያደርጋል።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ አርሰናል ከኮቨንተሪ ሲቲ ጋር በኤምሬትስ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።

አርሰናል የወቅቱ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ነው። ተጋጣሚው ኮቨንተሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል።

ሁለቱ ቡድኖች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲገናኙ የአሁኑ ለ19ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 18 ጨዋታዎች አርሰናል 10ሩን በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ኮቨንተሪ ሲቲ ሦስት ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪ አምስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

አርሰናል በ18ቱ ጨዋታዎች ላይ 25 ጎሎችን ሲያስቆጥር ኮቨንተሪ ሲቲ 13 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ በ2001 ነበር።

በወቅቱ ባደረጉት ጨዋታ አርሰናል በዴኒስ ቤርካምፕ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል። ኮቨንተሪ ሲቲ በዛው ዓመት ከሊጉ ወርዷል።

ኮቨንተሪ በፍራንክ ላምፓርድ እየተመራ በሻምፒዮንሺፑ በ95 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሷል።

በማይክል አርቴታ የሚመራው አርሰናል የሻምፒዮንነት ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን ከአዲስ አዳጊው ክለብ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይጀምራል።

ኮቨንተሪ ሲቲ በመጀመሪያው የሊግ ጨዋታው ከሊጉ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።

የ36 ዓመቱ ቶም ብራሞል የመክፈቻውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራሉ።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

⚽ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ርክክብ ተደረገየካማሺ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት ለካማሺ ከተማ ታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።ነሐሴ 14/2018ዓ/ም ...
20/08/2026

⚽ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ርክክብ ተደረገ

የካማሺ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት ለካማሺ ከተማ ታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።

ነሐሴ 14/2018ዓ/ም ( ካማሺ )

የካማሺ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ለካማሺ ከተማ ታዳጊ እግር ኳስ ፕሮጀክቶች የስፖርት ትጥቅና የእግር ኳስ መሳሪያዎችን ርክክብ አድርጓል።

የድጋፉ ተጠቃሚዎችም፦
⚽ የ“U-15 የማሄሻ” ታዳጊ እግር ኳስ ፕሮጀክት
⚽ መጦይላ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ
⚽ የካማሺ ከተማ ካናማ እግር ኳስ ፕሮጀክት ናቸው።

በርክክቡም የስፖርት መለያዎች፣ የእግር ኳስ ኳሶች እና የእግር ኳስ ጎል መረቦች ጨምሮ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች ድጋፍ ተደርጓል።

የካማሺ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢና የካማሺ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ግሽላይ ድንባሻ በመልዕክታቸው፣ ካማሺ ከተማን በእግር ኳስ የሚያስጠሩ ብቁ ስፖርተኞች መፍለቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

“እዚህ የምትገኙ የእግር ኳስ ፕሮጀክት ታዳጊዎች ጠንክራችሁ በመለማመድና በትጋት ከሠራችሁ ወደ ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ትችላላችሁ፤ የካማሺ ከተማንም ስም በትልቅ ድል ማስጠራት እንደምትችሉ ተስፋ አለኝ” ብለዋል።

አክለውም፣ “ስፖርት ተግባርን፣ ትጋትንና ተከታታይ ልምምድን የሚጠይቅ ነው፤ ያለ ልምምድና ትጋት ውጤት ማምጣት አይቻልም” ሲሉ አስገንዝበዋል።

የዛሬው ድጋፍ ታዳጊ ስፖርተኞች በተሻለ ሁኔታ እንዲለማመዱ፣ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና ወደ ከፍተኛ የስፖርት ደረጃ እንዲደርሱ የሚያግዝ ነው።

ካማሺ በስፖርት ይበልጣል! ⚽🏆
ታዳጊዎቻችን የነገ የካማሺ ተስፋዎች ናቸው!

#ካማሺ #ስፖርት #እግርኳስ

ኤርምያስ ትግሬ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ጋሞ ጨንቻ አምርቷልከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ተጫዋች አዲስ አዳጊዎችን ተቀላቅሏል በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በሚሳተፉበት ፕ...
20/08/2026

ኤርምያስ ትግሬ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ጋሞ ጨንቻ አምርቷል

ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ተጫዋች አዲስ አዳጊዎችን ተቀላቅሏል

በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በሚሳተፉበት ፕሪምየር ሊግ ስብስባቸውን ለማጠናከር በእንቅስቃሴ ላይ ያሉት እና በዝውውር መስኮቱ በአመዛኙ በከፍተኛ ሊጉ ላይ ጥሩ ጊዜ ያሳለፉ ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ የሚገኙት በአሰልጣኝ ማትዮስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች አሁን ደግሞ በመንጌ ቤንሻንጉል ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ተጫዋች ኤርሚያስ ትግሬ አስፈርመዋል።

በሶጌ ከነማ እግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ኤርሚያስ በመሐል ተከላካይነት እና አማካይ ተከላካይ ሆኖ መጫወት የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ቆይታ አድርጎ አሁን ማረፊያውን አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ አድርጓል።

ethiopia

Address

Asosa

Telephone

+251920437021

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤጉ ስፖርት - Begu Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቤጉ ስፖርት - Begu Sport:

Shortcuts

Share

Category