Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Awash
  • Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት Alhamdulillah

29/09/2026
23/09/2026

ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ከውልደት እስከ እርጅናው፣ ከደደቢት በረሃ እሰከ አራት ኪሎ ሽፍትነትና የህዝቦች እልቂት የማይለየው የህወሓት አዛውንቶች ክበብ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በአፋር ህዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጦርነት ከፍተው አድረዋል።

ህወሓት ለግማሽ ክፍለ-ዘመን በጦርነትና በትውልድ ደም አፍሳሽነት አድጎና ተመንድጎ፣ በምድር ላይ ያለ-ምንም ለውጥ በደም ቁማር ጃጅቶ መኖር የሚፈልግ የቀጠናው ጠንቅ የሆነ ወሮበላ ቡድን ነው።

የኢትዮጵያን መፍረስ ከሚፈልጉ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የክህደት ሽርክና የገባው የህወሓት ተላላኪ ቡድን ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን በአብአላ፣ በመጋሌ፣ በወሰማና በሌሎች አካባቢዎች ላይ ሀገር ሰላም ብሎ በተኙት ንጹሐን ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል።

የቡድኑ እኩይ ዓላማው በመጀመሪያ ትግራይን ትውልድ አልባ ማድረግ ስሆን፣ ቀጥሎም ጎረቤት ክልሎችን በመውረር ለዘላለሙ በህዝቦች መካከል የማያበራ ቁርሾና ቅራኔ መፍጠር ነው። ፍላጎቱም በኢትዮጵያ ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት እንዳይኖር በማድረግ፣ ሀገራችን ሁሌም ለጠላቶቿ የተንበርካኪነት ሚናን የምትወጣ ሀገር ሁና ማየት ነው።

ከትናንት ጥፋቱ የማይማር ለጥፋትና ለእልቂት የተደራጀው የህወሓት ተላላኪ ቡድን ለፈጸመው ወረራ መራር ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል።

ይህ ዘራፊና ነቀርሳ ቡድን የትግራይን ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት ነው። ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋነኛ ተግባሩ የህዝቦቹን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ ስለሆነ፣ ከሌሎች ወዳጅ ሀይሎች ጋር በመሆን አጸፋዊው ራስን የመከላከል እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።

23/09/2026

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ይካሄዳል - አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፡፡

አፈ ጉባዔ ታገሰ ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ÷7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተሳትፈው በስኬት መጠናቀቁን አስታውሰዋል፡፡

ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መከናወኑንም ነው የገለጹት፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቁመዋል፡፡

በዚህ መሰረትም መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

አፈ ጉባዔው ለመርሐ ግብሩ አስፈላጊ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቀዋል ማለታቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

22/09/2026
ሳምንታዊ መልዕክትየመጀመሪያው እና ትልቁ ልማት ሰላም ነው!ሰላም ጦርነት በመቆሙ ብቻ የሚረጋገጥ ሁኔታ አይደለም። እውነተኛና ዘላቂ ሰላም የሚገነባው ሰዎች በክብር ሲኖሩ፣ ልዩነቶች በግጭት ሳ...
21/09/2026

ሳምንታዊ መልዕክት
የመጀመሪያው እና ትልቁ ልማት ሰላም ነው!

ሰላም ጦርነት በመቆሙ ብቻ የሚረጋገጥ ሁኔታ አይደለም። እውነተኛና ዘላቂ ሰላም የሚገነባው ሰዎች በክብር ሲኖሩ፣ ልዩነቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት ሲታዩ፣ ፍትሕና እርቅ ለማህበረሰቡ መሠረት ሲሆኑ ነው።

በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ለዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላም ግንባታ ፅኑ አቋም አለው። ይህ አቋማችን በንግግር ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን፤ በዕለት ተዕለት ተግባራችን፣ በምንመርጣቸው ቃላት እና ለወደፊት ትውልድ በምናስቀምጠው መሰረት የሚመዘን ነው።

በሀገራችን የሰላም ጉዳይን ከፖለቲካዊ ውይይት፣ ከብሔራዊ መግባባትና ከልማት ጋር ማያያዝ አስፈላጊ ነው። የመደመር ፍልስፍናም በኢትዮጵያ እውነታ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካዊ አስተሳሰብን፣ የተነጣጠሉ አቅሞችን በመደመር የጋራ አቅም መፍጠርን እና ለጋራ እጣ ፈንታ በትብብር መሥራትን ያበረታታል።

በመደመር የቀረበው አንድ ጠንካራ ሀሳብ “የመጀመሪያው እና ትልቁ ልማት ሰላም ነው” የሚለው ነው። ይህ አተያይ ሰላምን እንደ የልማት ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ልማት የሚቻልበት መሠረታዊ ሁኔታ እንደሆነ ያቀርበዋል።

ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ለማምጣት በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማደራጀት ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተሳታፊዎች በጠረጴዛ ዙሪያ የሚነጋገሩበትን እድል ፈጥሯል።

ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የጦር መሣሪያ መጠቀም ብቻ መፍትሔ አይሆንም። የተፈጠሩ ልዩነቶችን ለመፍታት ውይይት፣ ምክክር፣ መደማመጥ ፣ እርቅ እና የጋራ መግባባት ያስፈልጋሉ። የተለያዩ አስተሳሰቦች መኖራቸው በራሱ ችግር አይደለም፤ ዋናው ጉዳይ ልዩነቶችን ወደ ግጭት ሳይሆን ወደ ውይይት የሚወስድ የፖለቲካ ባህል መገንባት ነው።

ይህም የብሔራዊ ምክክር ሂደት ዋና የፖለቲካ ጥያቄ እንዲሆን ያደርገዋል። የተለያዩ የማህበረሰብና የፖለቲካ አካላት በአንድ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠው ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ ውይይት ማስተናገድ ሲችሉ፣ የፖለቲካ ምህዳር ከግጭት ወደ ሀሳብ ውድድር ይሸጋገራል። በዚህ አተያይ፣ ሰላም የአንድ ተቋም፣ የአንድ ፓርቲ ወይም የአንድ ቡድን ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ዜጎችና ባለድርሻዎች የጋራ ኃላፊነት ነው።

የዛሬ የሰላም ምርጫ የነገውን ትውልድ ዕጣ ፈንታ ይወስናል። ልዩነትን እንደ ጠላትነት ከማየት ይልቅ እንደ ውይይት እድል ማየት፤ ግጭትን በኃይል ከማስቀጠል ይልቅ በምክክር መፍታት፤ እና የተከፋፈሉ አቅሞችን ወደ የጋራ ዓላማ ማሰባሰብ የዘላቂ ሰላም መሠረቶች ናቸው።

በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የህዝብን መሻት የመንግስትንም ቁርጠኝነት በመገንዘብ ሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እያስመዘገበች ያለችው ስኬቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና ሰላሟም እንዲፀና መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ብልፅግና ፓርቲ
11/1/2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ

20/09/2026
Qafar Ledda Missoyna uddih kutbeh buxal fayyale mihratleela taceeh tan 2 ayroh sugeh yan oyti gexsoh aynabaabad aydakaak...
13/09/2026

Qafar Ledda Missoyna uddih kutbeh buxal fayyale mihratleela taceeh tan 2 ayroh sugeh yan oyti gexsoh aynabaabad aydakaakan yumurruqe.
Tama Aydakaakanal daqorti Magaalah Xiinissoh Saqolti Gebi Resu Zoon Fanteena mirocti Edde Tengelem Kinnuuk, Gifta Saaqid Kee Gifta Esse Yeceh Yan Aydakaakan Esseroora Gacsa Luk maqar lee gural meqe Gabah Assagolla Abak kataatene.
* 19 daga takke gabbaaqi cibtitte mexxat le kibneh cogda
* oyti rakiiboh oytih cibta asta luk
* massoynah maysaxxagah matbaqat baarluk kusaaqime meklah caaloota kee fantaaxaw le ammuntitte.
2019 taama daffeyteh tan waktih addat gaba kaltam faxximtaamih afkanitte kee duddale edde radaanam xiqsisse.
በአፉር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ከፍተኛ የባለሙያ ቡድን ለሁለት ቀን ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ስልጠናው በገቢ ረሱ ዞን ማእከል እና አጠቃላይ ወረዳዎች የከተማ ከንቲባ አመራሮች ያሳተፈ ሲሆን አንድ እቅድ አንድ ሪፓርት በአቶ ሰኢድ በአቶ ኢሴ የተሰጠው ስልጠና በንቃት በጥያቄና መልስ አሳታፊ ነበረ፡፡
* ከ19 በላይ ሪፓርቲንግ ወጥ ፎርማት በጥራት አሞላል ዘዴ
* በዳታ ቤዝ መረጃ አገባብ ጥንቃቄዎች ዙሪያ
* የፓርቲ መታዉቂያ ህትመት የክፍያ ሁኔታዎች አፈፃፀም እና ተያያዥ ርእሶችን በሰፊው ዳስሷል፡፡
የ2019 ስራዎች በተቀመጠላቸው ግዜ ሰሌዳ መጠናቀቅ እንዳለባቸው አቅጣጫዎች እና በቂ ግንዛቤ እንዲጨበጥ አስችአል፡፡ 03/01/2019 አዋሽ7ከተማ

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ክቡር ሀጂ አወል አርባ ለ2019 አዲስ ዓመት ያበሰሩት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት------------------------የተከበራችሁ የአፋር ብሔ...
11/09/2026

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ክቡር ሀጂ አወል አርባ ለ2019 አዲስ ዓመት ያበሰሩት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
------------------------

የተከበራችሁ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝቦች እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ መላው ኢትዮጵያውያን፤ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና በሰላም አደረሳችሁ።

አዲሱ ዓመት የሕዝባችን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጥበት፣ ሰላምና ወንድማማችነት በሀገራችን ምድር ይበልጥ የሚጸናበት ታሪካዊ የዕድገት ዘመን እንዲሆንልን በራሴና በክልላዊ መንግሥቱ ስም መልካም ምኞቴን አስተላልፋለሁ።

ያለፈው የ2018 በጀት ዓመት ያጋጠሙንን ፈተናዎች በፅናት በመጋፈጥ በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዘርፎች የላቁ ስኬቶችን ያስመዘገብንበት ነበር። አስተማማኝ ሰላምን በማረጋገጣችን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍሰቱ ከማደጉ ባሻገር በጤና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ፣ በትምህርት፣ በዘመናዊ ግብርና እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሮች የተገኙ ውጤቶች የሕዝባችንን የዕለት ተዕለት ሕይወት በበጎ መልኩ ቀይረዋል።

በአዲሱ ዓመት በሕዝባችን ነፃ ድምፅ በሚመሠረተው አዲሱ መንግሥታችን አማካኝነት የተጀመሩ ግዙፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ የታጀበ አሰራርና ሙሉ አቅም እናስቀጥላለን። የያዝናቸውን ስትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካትም የስራ ባህላችንን ወደ ላቀ ተቋማዊ ጥራት በማሳደግ፣ ጊዜን በቁጠባ በመጠቀምና «በጊዜ የለኝም» ከፍተኛ የሕዝባዊ አገልግሎት ስሜት በመመራት የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በሙሉ እንወጣለን።

ስለሆነም መላው የአፋር ሕዝብ፣ አመራሩ፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በጠንካራ ወንድማማችነትና በላቀ የሥራ መንፈስ ተጋግዘን ክልላችንንና ሀገራችንን ወደ ተሻለ ከፍታ እንድናሸጋግር ጥሪዬን አቀርባለሁ።

2019 የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እና የታላላቅ ድሎች ዓመት ይሁንልን!

Address

Awash
7240

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share