04/09/2025
ክለባችን ሀዋሳ ከተማ አጥቂው ጌታነህ ከበደን ዛሬ አስፈረመ
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው እና በተለያዩ ክለቦች የተጫወተው ጌታነህ ከበደ ከሁለት አመታት የፋሲል ከነማ ቆይታ በኃላ ቀጣይ ማሪፍያው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ መሆኑ ታውቋል።
እንኳን በሰላም ወደ ክለባችን መጣህ !
This is the official page of Hawassa City Sport Club. Get exclusive behind scenes,news and engage wi Awassa Kenema is a football club established in 1968 e.c.
It is one of the most strongest and efficient club in Ethiopia and also it is the only regional club to lift the Ethiopian premier league. Its home stadium is called Awassa kenema stadium. Home kit: Blue and white shirt &
white shorts
04/09/2025
ክለባችን ሀዋሳ ከተማ አጥቂው ጌታነህ ከበደን ዛሬ አስፈረመ
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው እና በተለያዩ ክለቦች የተጫወተው ጌታነህ ከበደ ከሁለት አመታት የፋሲል ከነማ ቆይታ በኃላ ቀጣይ ማሪፍያው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ መሆኑ ታውቋል።
እንኳን በሰላም ወደ ክለባችን መጣህ !
30/08/2025
23/08/2025
አሰልጣኝ ተመስገንን ዳና ዋና አሰልጣኝ ያደረገው ሀዋሳ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር በይፋ አጠናቀቀ
#ሽመልስ በቀለ ከረጅም አመት በኋላ የልጅነት ክለቡ ተመልሷል። ለሁለት ተከታይ አመቶች ከግብፅ መልስ በመቻል የነበረው እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመቻል መለያ ለኮከብ ጎል አስቆጣሪነት ሲፎካከር የቆየ ሲሆን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና መቻል በኋላ በቅርቡ ከብሔራዊ ቡድን ራሱን ያገለለው አማካዩ ለሀዋሳችን ፈርሟል።
#በተመሳሳይ በኦሜድላ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ የተጫወተው ቁመተ መለሎው የተከላካይ አማካይ አብነት ደምሴንም ምርጫውን ሀዋሳ አድርጓል።
08/08/2025
ሀዋሳ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ከምስረታው አንስቶ እየተካፈሉ ከሚገኙ ሁለት ቡድኖች መሐል አንዱ የሆነው ሀዋሳ ከተማ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሦስት አሰልጣኞት ሲመራ የቆየ ሲሆን በተለይ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረትን የኋላ ኋላ ከቀጠረ በኋላ ከወራጅ ቅርቃር ተላቆ በአስደናቂ ጉዞ በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጡ ይታወሳል። ለቀጣዩ የ2018 የውድድር ዘመን በሙሉጌታ ምሕረት እየተመራ እንደሚቀጥል ሲጠበቅ የነበረው ቡድኑ በትናንትናው ዕለት አሰልጣኙ ወደ መቻል ማምራቱን ተከትሎ የክለቡ ቦርድ በዛሬው ዕለት ማምሻውን ባደረገው ፈጣን ስብሰባው አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን ምርጫውን ማድረጉን በተለይ ሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችላለች።
የሀዋሳን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖችን በማሰልጠን የክለብ ህይወትን የጀመረው አሰልጣኝ ተመስገን በተለያዩ ጊዜያቶችም የኢትዮጵያን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖችን ጭምር በማሰልጠን ጥሩ ጊዜያቶችን ማሳለፍም ችሏል። 2011 የሀዋሳ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ በመቀጠል በከፍተኛ ሊጉ ደቡብ ፓሊስን በፕሪምየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡናን ያሰለጠነው አሰልጣኙ በአሁኑ ሰዓት የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ረዳት በመሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ሲያገለግል ቆይቶ በመጨረሻም ወደ ቀደመው ቤቱ በአንድ ዓመት ውል በይፋ ተቀላቅሏል።
Soccer Ethiopia
07/07/2025
የአቦል ቤት የፌስቡክ ገፅን አሁኑኑ ይቀላቀላሉ 👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61574420481124
AVIATOR በመጫወት ቀኖን ያሳምሩ!!
https://abolbet.com/games
ድልን በአቦል ቤት ያጣጥሙ!!!
ሁሉንም በአንድ ቦታ አቦል ጋር ያግኙ
Telegram | Facebook | Instagram
26/06/2025
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሲጠናቀቅ ክለባችን ሀዋሳ ከተማ አራተኛ ደረጃን ይዞ ሲፈፅም አጥቂው አሊ ሱለይማን ደግሞ በ21 ጎል የአመቱ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመባል የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።
25/06/2025
"እኔ በህይወት እያለው ሀዋሳ ከነማ አይወርድም" ሀቁንም አገኘ
በልጅነት ዕድሜው ጎበዝ እግር ኳስ ተጫዋች ቢሆንም የተመኘውን የሀዋሳ ከተማን የዋናውን ቡድን መለያ ለብሶ ግን መጫወት አልቻለም ፣ እያየ ያደገውን ክለብ ከልቡ እየደገፈ በውስጡ ፍቅሩን ያስቀረው የያኔው ታዳጊ ወደ ትምህርቱ በማድላት በስኬት ካጠናቀቀ በኋላ ከተሰማራበት የንግድ ዘርፍ ጎን ለጎን ክለቡን ለዘመናት ደግፏል በልቡ ውስጥ አትሞ አስቀምጧል። በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ካሉ ወጣት ባለሀብቶች አንዱ የሆነው ይድነቃቸው አስፋው ያኔ በልቡ ያስቀመጠው ክለብ አዘቅጥ ውስጥ ሲገባ ዝም ብሎ ሊቀመጥ አልቻለም "እኔ በህይወት እያለው ሀዋሳ ከተማ አይወርድም" በሚል በነበረው ተነሳሽነት ዋጋዎችን ጭምር በመክፈል ስሙን በክለቡ የታሪክ ማህደር ውስጥ ማስቀመጥ ችሏል።
አንጋፋው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወደ ከፍተኛ ሊጉ የመውረድ አዝማሚያ ላይ በነበረበት ወቅት ክለቡን ለማዳን በተግባር ከተገኙ ጥቂቶች መሐል አንዱ መሆን የቻለው ይድነቃቸው አዳማ ከተማ ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር በሚካድበት ወቅት ከአስር በላይ መኪኖችን እያዘጋጀ ፣ ለደጋፊዎቹም ወጪያቸው እያቸለ ቡድኑ ውጤታማ መሆን እንዲችል አዳማም ሆነ ውድድሩ ወደ ሀዋሳ በመጣበትም ወቅት ለተጫዋቾች ከኪሱ ገንዘብን በማውጣት የማበረታቸ ገንዘብን በማርከት እስከ መጨረሻው ድረስ ከቡድኑ ጎን ሆኖ አይዟችሁ አለው በማለት የክለቡ ታሪክ እንዳይበላሽ በማድረጉ ብዙሀኑ የክለቡ ወዳጆች ሲያመሰግኑት ይኖራሉ። ይድኔ ለክለባችን ስላደረከው ትልቅ አበርክቶ ስለ በጎነትህ ሁሉ ፈጣሪ ይክፈልህ በቀጣይም ከክለቡ ጎን ሆነህ በድል ጎዳና እንደምንጓዝ ጥርጥር የለንም !
25/06/2025
ከክለቡ ጎን ያልራቀው ሰው !
ሀዋሳ ከተማ ከነበረበት የወራጅነት ቦታ መውጣት እንዲችል የክለቡ የቦርድ አመራሮች አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን በመቅጠር ቁርጠኛ ውሳኔን ማስተላለፍ ቢችሉም ዓመቱን ሙሉ ከክለቡ ጎን በተለይ ከአሰልጣኙ እና ተጫዋቾቹ ጎን በመሆን አይዟችሁ ምንስ ጎደለ ምንስ ይሟላ በማለት በየጊዜው ከዋናው የመንግሥት ስራው ጎን ለጎን በጠንካራ የአመራርነት ውሳኔው ክለባችን በሊጉ እንዲቆይ በ2018 የተሻለ ሆኖ መገኘች ይችል ዘንድ የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣናት ዋና ሀላፊ እና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መልኩ ማርቆስ የነበራቸው ድርሻ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ለክለባችን ለከፈሉት ወደር የማይተካለት ስራ ከልብ ከልብ ምስጋናችን ይድረስህ ፈጣሪ ያክብርልን እንላለን ፣ በተረፈ ግን ሌሎች የቦርድ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አመራሮችም ይህ ምስጋና ለእናንተም ነውና ውሰዱ ለማለት እንወዳለን።
25/06/2025
ሳይሰስቱ ዋጋ የከፈሉ የክለቡ የቁርጥ ቀን ልጆች !
አመቱን በጥሩ ጅምር በሚደት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤት እያጣ በመጣው ቡድን ውስጥ እነሱ ነበሩ። በአሰልጣኞች የቡድን አጠቃቀም እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተስፋ ወደ ሚያስቆርጥ ደረጃ የደረሰው የታሪክ ማህደሩ ቡድናችን አንጋፋው ሀዋሳ ከተማ በሁለት አሰልጣኞች ቢመራም ውጤት እያጣ ደካማም ውጤት እያስመዘገበ በመጓዙ በመጨረሻም ለማሰናበት በተከታታይ ከተገደደ በኋላ የክለቡን ባለ ታሪክ የቀድሞው ተጫዋቹን አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን በመቅጠር አሰልጣኙ ተጫዋቾቹን ቡድኑን ማትረፍ እንዲችሉ ከልቡ ባስተላለፈው የማንቂያ ደውል እና በሰራው ትልቅ ስራ መነሻነት እነዛ በውጤት ተከፍተው የነበሩ ተስፋም ቆርጠው የታዩት ተጫዋቾቻችን በእልህ ፣ በወኔ እና ባልሸነፍ ባይነት ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል 15 ነጥቦችን ብቻ ይዞ 17ኛ ደረጃ ላይ ለነበረው ቡድናችን ካደረጉት ተጋድሎ በኋላ 38 ነጥቦችን በመሰብሰብ 53 ነጥቦችን ይዞ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ እንዲችል እኚህ የቁርጥ ቀን ተጫዋቾቻችን አድርገዋል። እናንተ ውድ የክለባችን ተጫዋቾች ለከፈላችሁት ዋጋ ሳትሰስቱ ለሰጣችውን አልሸነፍ ባይነት እና ስኬት ሁሌም በክለቡ የታሪክ አካል ሆናችኋል እና ስላደረጋችሁት ስለከፈላችሁት የድል ጉዞ ከልብ እናመሰግናለን ፈጣሪ ባከበራችሁት ክለባችን ልክ ክብሩ !
24/06/2025
ይሄ ነው ሀዋሳ ከተማ 💪💪💪
በማህበራዊ ሚዲያ ሲወራ የነበረውን ሀሜት ሁሉ ሰጥ ያደረገ ውጤት ጀግናው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ አዳማ ከተማን በሜዳው 2ለ1 በማሸነፍ አመቱን በድል አሸብርቆ ጨርሷል። ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ክብሩን ይውሰድ 🙏🙏🙏 በነገራችን ላይ 2005 አዳማ የወረደው በሀዋሳ ተሸንፎ ነበር ከ11 አመት በኋላም በተመሳሳይ የወረደው በክለባችን ተሸንፎ መውረዱን አረጋግጧል።
ውጤት
ሀዋሳ ከተማ 2-1 አዳማ ከተማ
45+1' አቤኔዘር ዮሐንስ | 21' ቢኒያም አይተን
65' በረከት ሳሙኤል (ፍ.ቅ.ም)
እኛ ነን ሐይቆቹ 💪💪💪
16/06/2025
ከእርሱ የተሻለ ማንም አልነበረም ፣ ሆኖም ደግሞ የልጅነት ቡድኑ ቀና እንዲል አድርጎታል 💪💪💪
በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ የተመሠረተው አንጋፋው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ ከየትኛውም የክልል ቡድን የቀደመ የታሪክ ስኬት ያለው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ ሀገሪቷ ላይ የገነነ ስምን የያዘ እጅግ ታሪካዊ ክለብ ነው። በ1990ዎቹ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲመሠረት ከመሠረቱ ክለቦች መካከል በአሁኑ ሰአት የቀሩት ቡድኖች ይህው የህልውናችን ባለቤት ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ብቻ ናቸው። በርካታ ጠርተን የማንጨርሳቸውን ተጫዋቾች ከታች በማሳደግ ለራሱም ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ሆነ ለሌሎች ክለቦች የመገበው ሀዋሳ ዘንድሮ በ2017 ክፉኛ ጉዞን ያደረገ ቢሆንም ዕድሜ ለሙሉጌታ ምህረት ይግባው እና ታሪኩ እንዳይበላሽ ታሪኩን ጠብቆለታል።
በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ በኋላም በጊዜያዊ አሰልጣኙ ወንድማገኝ ተሾመ ሲመራ በደረጃ ሰንጠረዡ 17ኛ ላይ በ15 ነጥቦች ተቀምጦ የነበረውን ቡድኑን በመረከብ በ14 ጨዋታዎች አስራ አንዱን በማሸነፍ በሁለቱ አቻ በመውጣት በአንድ ሽንፈት ብቻ 35 ነጥብን በመሰብሰብ ያ ወረደ አበቃለት የተባለውን አንጋፋ ክለብ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነው ከልጅነቱ ጀምሮ በክለቡ ተጫውቶ ላቩን አፍሶ በአምበልነት እስከ መምራት በደረሰው በቀድሞው የተከላካይ አማካዩ ተጫዋቹ ሙሉጌታ ምህረት ያልሳሱ በረከቶች በሊጉ መቆየት ብቻም ሳይሆን አሁን አራተኛ ላይ በመጨረሻ ጨዋታ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ መጨረስ እንዲችል መንገዱን ጠርጎለታል።
ከእርሱ የተሻለ ማንም አልነበረም ፣ ሆኖም ደግሞ የልጅነት ቡድኑ እንዲከበር አስችሏል ፣ ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ፣ አንድ ጊዜ የጥሎ ማለፍ አሸናፊ ፣ የ1996 የሊጉ ምርጥ ተጫዋች ለሆንክለት ክለብህ አመለሸጋው ሙሉጌታ ምህረት ለሰራህው ስራ ክብር ይገባሀል እና ሁሉም የክለቡ ወዳጅ እና ደጋፊ ከልብ የማይጠፋ ታሪክን ሰርተሀል እና ስለሆነው ሁሉ እናመሰግንሀለን እግዚአብሔር ይመስገን !
🙌
16/06/2025
ሀዋሳ ከተማ በተከታታይ ያለ መሸነፍ ጉዞውን ባህርዳር ከተማን አሸንፎ አስመዝግቧል 💪💪💪
በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው አንጋፋው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ 3ለ0 በሆነ ውጤት ባህርዳር ከተማን በማሸነፍ በድል መገስገሳቸውን ቀጥለዋል። አስራ ሰባተኛ ደረጃ ላይ የነበረው ቡድናችን አሁን አራተኛ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ከተጫወተው ባህርዳር ከተማ ጋር ነጥቡን በአንድ ዝግ በማድረጉ በቀጣይ የመጨረሻ የአዳማ ጨዋታ ነጥብ ካገኘ ሦስተኛ ሆኖ መፈፀምም ይችላል።
ባህር ዳር ከተማ 0-3 ሀዋሳ ከተማ
03' ማይክል ኦቱሉ
48' ዓሊ ሱሌይማን
82' ዓሊ ሱሌይማን
እኛ ነን ሐይቆቹ እንኳን ደስ አላችሁ 💪💪💪💪