Bizu Dani መድፈኛው

Bizu Dani መድፈኛው

Share

ስለ አርሰናል

Photos from Bizu Dani መድፈኛው's post 22/06/2026

አርጀንቲና በሜሲ ግቦች ታግዛ ወደ ጥሎ ማለፍ ተሸጋገረች
**************

በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ምድብ አስር 2ኛ ጨዋታዋን ያደረገችው አርጀንቲና፤ ኦሰትሪያን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

ቴክሳስ ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና አግኝታው የነበረውን የፍፁም ቅጣት ምት ቢያመክንም፤ የማሸነፊያዎቹን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል።

እነዚህ ግቦች ለሊዮኔል ሜሲ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ 5ኛ፣ አጠቃላይ በውድድሩ ተሳትፎ ታሪኩ ደግሞ 18ኛ ሆነው ተመዝግበዋል።

በዚህም ሜሲ በጀርመናዊው ሚሮስላቭ ክሎዘ ተይዞ የነበረውን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን በእጁ ሲያስገባ፣ በሁለቱ ጨዋታ እርሱ ባስቆጠራቸው አምስት ግቦች 6 ነጥብ የሰበሰበችው አርጀንቲና ወደ ጥሎ ማለፉ መሸጋገሯን አረጋግጣለች።

ወደ አራተኛ የዓለም ሻምፒዮንነት የምታደርገውን ጉዞም አስምራለች።

Photos from Bizu Dani መድፈኛው's post 11/06/2026

በእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው የ2026ቱ ሃገራት ዓለም ዋንጫ ዛሬ ማታ ጅማሮውን ያደርጋል:: በ3 ሀገራት አዘጋጅነት 48 ሀገራት በ12 ምድብ ተከፋፍለው የምፋለሙት ጨዋታ ጅማሮውን ያደርጋል:: በሰሜን አሜርካዊቷ መክሲኮ ውስጥ በአንጋፋው Mexico City Stadium በደማቅ ሁኔታ መክፈቻውን አዘጋጇ ሀገር መክሲኮ ከ ደቡብ አፍርካ ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ ይጀምራል::

መልካም ቆይታ
ሀገሬ ቲቪ ጨዋታን በቀጥታ የሚያስተላልፍ ይሆናል::

Photos from Bizu Dani መድፈኛው's post 31/05/2026

በእንግሊዝ ታሪክ አስደናቂ ከሚባሉ የዋንጫ አከባበር ስነስርአቶች (ፐሬይድ ) መካከል የዛሬው የአርሰናል አንዱ ሆኗል ። ዋው !!
ደማቅ በነበረው የመድፈኞቹ የዋንጫ አከባበር ላይ ከአንድ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ታድሟል::
North London forever whatever the weather💪🔴⚪

31/05/2026

ስፔን ያለዉንም እንግሊዝ ያለዉንም እኛ ሀገር ያለዉንም ሁሉንም የሚያመሳስላቸዉ ለአርስናል ያላቸዉ ጥላቻ ነዉ። አርስናል ከ22 አመታት ጥበቃ በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሲያነሳ አንድም "Congratulations" ያለዉ ክለብ የለም ሲሸነፍ ግን ሙድ ለመያዝ የቀደማቸዉ የለም።

ኤርሊንግ ሃላንድ ደስታዉን እንኳን መቆጣጠር አቅቶት ጨዋታዉ ሳያልቅ ነዉ የፖሰተዉ። ሪቻርልሰን የሚጫወትበትን ክለብ ረስቶ አርስናል ላይ ለማሾፍ ሞክሯል። ቸልሲ የዛሬ 5 አመት የበላዉን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ "ኑ እና ጎብኙልኝ" ብሎ ከትላንቱ ጨዋታ በኋላ ለጥፏል። ኖቲንግሃም እንኳን በአቅሟ በአፄ ድምድም ጊዜ የበላችዉን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ፖስታለች። እኛ ሀገር ስላሉት ባናወራ ይመረጣል።

የአርስናል ደጋፊ ግን በዚህ ሁሉ ዉስጥ የሀብታም ለቅሶ ነዉ እያለቀሰ ያለዉ። የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ባለቤት ስለሆነ ከፍቶታል😂

ለማንኛዉም በአርስናል ሽንፈት የተደሰታችሁ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ወዳለሁ። አሁን እንደ ወንድ ልጅ ዘንድሮ ወይ በቅርብ አመታት ያሸነፋችሁን ዋንጫችሁን እና ሜዳሊያችሁን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጡና ኑ እንወያይ እስቲ😁

Photos from Bizu Dani መድፈኛው's post 30/05/2026

ሞስክዌራን መቀየር እያለብህ አለመቀየርህ ዋጋ አስከፈለን ይብረዠ

ዛሬ በፒዬዤ ማሸነፍ የተደሰተዉ አብዛኛዉ ደጋፊ ክለቡ ባሳለፍኩት ብሎ የሚመኘዉን አመት ነዉ አርስናል ያሳለፈዉ። ሽንፈቱ ቢያስቆጭም ግን ደግሞ የአለም ማብቂያ አይደለም። በአጋጣሚ ወይ በእድል እዚህ አልደረስንም ቀጣይ አመትም ደግመን እንመጣለን ስንመጣም በብዙ ነገር ተምረን በብዙ ነገር ራሳችንን አሻሽለን ይሆናል።

በዚሁ አጋጣሚ በዚህ ጨዋታ ዙሪያ ቲክቶክ ገፃችን ላይ የተወሰነ ሀሳብ አንስተናል። እየገባችሁ ሀሳብ እንለዋወጥ ወዳጅ ያልሆናችሁ ታች ባስቀመጥኩት ሊንክ እየገባችሁ ተወዳጁ።

ለአርስናል እና ለአርስናላዊያን መጪዎቹ አመታት የሚያሩ በብርሃን የተሞሉ እንጂ አንገት የሚያስደፉ አይደሉም። የዚህ ክለብ መሰረት በአሸዋ ላይ አልተገነባም።

30/05/2026

ፕሪምየር ሊጉ የሚኮራበት ቡድን ነው። የፍጹም ቅጣት ምት መለያ የእግር ኳስ አስቀያሚው ክፍል ነው።

አርቴታ እና ልጆቹ እልህ አስጨራጭ በነበረው የውድድር ዘመን በሶስተኛ ቡድን ምርጫው የውስጥ ሊግ ውድድርን ሲያደርግ የነበረውን ቡድን የተፋለማችሁቡት መንገድ የሚያስደንቅ ነው።

የ7ሺ ደቂቃ ልዩነት በሁለቱ ቡድኖች መካከል ዴምበል ቪትኒሀ ማርኩዊኖስ የውስጥ ሊግ ውድድር ጨዋታዎችን የሚያደርጉት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከፊታቸው ባልነበሩባቸው የሳምንቱ መጨረሻ ነበር።

አርሰናል በሀገር ውስጥ ሊግ የተፋለመው የኮንፍረንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያሳኩትን ጨምሮ ዘጠኝ ክለቦች በቀጣይ አመት በአውሮፓ መድረክ መሳተፋቸውን ባረጋገጡበት ነው።

ካይ ሀቨርትዝ በርንሌይ ያስቆጠራት ጎል የሊጉን ዋንጫ መዳረሻ በመወሰን ትልቅ ሚና ነበራት። ዛሬም በፍጻሜው እንደተመለከትነው ነው።በውድድር ዘመኑ ግን ከአርባ ብዙ ያላነሰ ጨዋታ እሱ እና አምበሉ ኦዲጋርድ አምልጧቸዋል።

የአምናው የቡድኑ ከፍተኛ አስቆጣሪ ሚኬል ሜሬኖ በብዙ መንገድ በቡድን ማጥቃት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያለው ለወራት አልነበረም። ቲምበር ሳካ ካላፊዮሪ በሙሉ ብቃታቸው መጫወት አልቻሉም።

BRAVO ARTETA !!

29/05/2026

ዲያጎ ስሞኔ:-

አርሰናልን በጋዜጦችና በቴሌቭዥን ሲታይ በቀላሉ እሚሸነፍ ቲም ይመስላል ግን ሜዳ ላይ ሲጫወቱ ስታያቸው በጣም ይገርማል እንድውም 11 ተጨዋቾች ናቸው ብዬ የቆጠርኩነትም ጊዜ አለ ብሏል !

26/05/2026

እንኳን ደስ አላችሁ/ እንኳን ደስ አለን🔥❤

ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ መድንን በማሸነፍ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጠዋል።

❤️

25/05/2026

ሸላሚው ማነው❓

ትናንት የተጫዋቾቹ አንገት ላይ ሜዳሊያ ያጠለቀው፥ ለ22 አመታት በናፍቆት የጠበቁትን ዋንጫ ለአምበሉ ኦዲጋርድ ያቀበለው፥ አብሯቸው ሲፈነድቅ ያመሸው የክብር እንግዳው፥ ሸላሚው ማን ነው?

ስሙ ኢማኑኤል ነሚቻ ይባላል፤ አርሴናል ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫ ሲወስድ 5 አመቱ ነበር፤ አሁን 27 ደፍኗል፤ ከኤምሬትስ ስታዲየም በ10 ደቂቃ ርቀት በኢስልተን ይኖራል፤ የሰሜን ለንደን ዩናይትድ ተጫዋችና አምባሳደርም ነው

ሰሜን ለንደን ዩናይትድ ከ13 አመት በፊት የተቋቋመ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ተጫዋቾች ቡድን ነው፤ መስራቹና ዋና አሰልጣኙ ሀሮልድ ቤኔት እድሜያቸው ከ5-30 አመት የሆናቸውን ታዳጊና ወጣቶችን በእግር ኳስ ጥላ ስር አቅፎ ያሰለጥናል፤ ሴት ልጁም የቡድኑ አካል ናት፤ አርሴናልም ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ይህንን ተቋም ይደግፋል

ከተመሰረተ ጀምሮ የቡድኑ አባል የሆነው ኢማኑኤል ደግሞ ለሻምፒዮኖቹ ቅርብ የሆነ፥ አርቴታን ጨምሮ ተጫዋቾችን ቃለመጠይቅ ያደረገ፥ በልምምድ ቦታ በተደጋጋሚ እየተገኘ ከቡድኑ ጋር ያሳለፈ የመድፈኞቹ ተወዳጅ ቤተሰብ ነው

የአርሴናል አመራሮች ታድያ ከሱፍ ለባሽ ባለስልጣናትና ከዝነኛ ሰዎች ይልቅ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለበትን ኢማኑኤል ነሚቻን አስቀድመው፥ ለታላቅ ሃላፊነት መርጠውት፥ የሊጉ ሹሞችም በሃሳቡ ተስማምተው፥ በታሪካዊ ቀን በአለም ፊት ደማቅ ታሪክ ፅፈዋል፤ ኢማኑኤልም የተጣለበትን አደራ በሚገባ ተወጥቶ ራሱንና የወከለውን አላማ ለአለም አስተዋውቋል

ይህ ውሳኔ በአለም ላይ ለሚገኙ ከስድስት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለስፖርቱ አለም ትልቅ ክብር ሆኖ ተመዝግቧል፤ እግር ኳስ ከውጤቱ ባለፈ ይህን መሰል ሰብአዊ ውበት እንዳለውም አሳይቷል

(ታምሩ ዓለሙ)

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Bensa Daye
Awassa