Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association

Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association

Share

ይህ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የእግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ሙያ ማህበር ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው። Our game Is Fair Play

24/07/2026

💥በየዓመቱ ክረምት ላይ የሚካሄደው የባህር ዳር ከተማ ፉትሳል ውድድር በዚህ ዓመት የስያሜ ለውጥ በማድረግ "የፌደራል ዳኛ ደረጀ አመራ ፉትሳል ውድድር" በሚል እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ይህ የፉትሳል ውድድር ቅዳሜ ሀምሌ 18/2018 ዓ/ም የሚጀምር ሲሆን ማህበራችን ከባህርዳር የቀድሞ ተጨዋቾች ጋር የመክፈቻ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

ጨዋታውም ውድድሩ በሚደረግበት ሚሊኒየም ሜዳ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን ዋና ዓላማውም የማህበራችንን አባል ፌደራል ዳኛ ደረጀ አመራን ለማስታወስ ይሆናል።

ይህንን ፕሮግራም ላዛጋጁ አካላት ታላቅ ክብርና ምስጋና እናቀርባለን።

Photos from Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association's post 19/07/2026

💥ማህበራችን ሻምፒዮን ሆኗል

"በራስ አቅም የመልማት ምልክት" በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የአልማ ሳምንት ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ የነበረው ማህበራችን የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታድየም ሰው ሰራሽ ፉትሳል ሜዳ ከአማራ ልማት ማህበር ጋር የዋንጫ ጨዋታ ያከናወነው ማህበራችን 7 ለ 5 በማሸነፍ የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

17/07/2026

💥የመምሪያ 2 የእግር ኳስ ዳኝነት ስልጠናን ይመለከታል

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር ተተኪ የእግር ኳስ ዳኞችን ለማሰልጠን በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ በዚሁ የማህበሩ ገፅ መረጃ ማድረሳችን ይታወሳል።

በመሆኑም ተገቢውን መስፈርት አሟልታችሁ የተመዘገባችሁ በሙሉ ስልጠናው በቅርቡ የሚሰጥ ስለሆነ ተገቢውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

በተለያየ ምክንያት ምዝገባ ያለፋችሁ ነገር ግን በስልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው አድራሻ በመደወል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

0918338978

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ይደረግ

30/06/2026

💥በባህር ዳር ከተማ በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ የሚካሄደው የፉትሳል ውድድር ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ በሚሊኒየም ሜዳ በቅርቡ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በመሆኑም የዚህን ክረምት የውድድር ስያሜ ላለፉት 6 ዓመታት በፉትሳል ዘርፍ በዳኝነት ከማገልገልም ባለፈ በተደጋጋሚ የውድድሩ ምስጉን ዳኛ በመሆን ተሸላሚ ለነበረውና በቅርቡ በድንገተኛ ሞት ላጣናው የማህበራችን አባል ስም "የፌደራል ዳኛ ደረጀ አመራ ፉትሳል ውድድር" በሚል እንዲጠራ የውድድር አዘጋጆች አሳውቀዋል።

ማህበራችንም እንደዚህ አይነት በጎ እሳቤ ላይ ለተሳተፉ የፉትሳል አዘጋጅ ወንድሞቻችንን ምስጋናውን ያቀርባል።

Photos from Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association's post 27/06/2026

💥የማህበራችን አባላት በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን የአማራ ሊግ የፍፃሜ ውድድር በብቃት መርተዋል።

ከፍፃሜው በኋላም ከአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ተቀባ ተባባል እጅ የወርቅ ሜዳሊያቸውን ተረክበዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ።

Photos from Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association's post 20/06/2026

💥የማህበራችን አባላት በአማራ ሊግ ውድድር ላይ በዳኝነት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መልካም የውድድር ጊዜ

07/06/2026

💥የአማራ ሊግ ውድድር ወደ ከተማችን ሊመጣ ነው።

የአማራ ሊግ የምዕራብ ቀጠና በባህር ዳር ከተማ ከሰኔ 7/2018 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል።

27/05/2026

💥ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል - አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ !

ኢድ ሙባረክ !

Photos from Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association's post 08/05/2026

💥የማህበራችን ፕሬዘዳንት ፌደራል ዋና ዳኛ አማረ ካሳሁን ትላንት በጋሞ ጨንቻ እና ሀላባ ከተማ መካከል የተካሄደውን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማጠቃለያ የፍፃሜ ውድድር ከሌሎች የሙያ ባለደረቦቹ ጋር በመሆን በብቃት መርቷል።

እንኳን ደስ አለህ አኩርተኸናል 👏👏👏

Photos from Bahirdar City Foot Ball Referees & Commissioners Association's post 01/05/2026

💥የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር የምድብ ሀ እና ምድብ ለ ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ በአፄ ቴዎድሮስ ስታድየም ይካሄዳሉ።

ሙሉ ፕሮግራሙን 👇👇👇 ይመልከቱ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Bahir Dar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Bahir Dar