20/08/2026
ብሩክ ሙሉጌታ በይፋ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል ...
________________________
ስም:- ብሩክ ሙሉጌታ
የሚጫወትበት ቦታ:- የመስመር አጥቂ
የነበረበት ክለብ :- ኢትዮጵያ መድን
ኮልፌ ቀራንዮ፣ በመቐለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን የተጫወተው የመስመር አጥቂው ብሩክ ሙሉጌታ በይፋ ዛሬ የጣና ሞገዶቹን ተጠናቋል ።
እንኳን ደህና መጣህ
መልካም የወድድር ዘመን ።
17/08/2026
ቤልሔም ሽመልስ የግዮን ንግስቶችን ተቀላለቀለች ....
_________________________
ስም:- ቤተልሔም ሽመልስ
የምትጫወትቀት ቦታ:- አማካይ
የነበረችበት ክለብ :- ሲዳማ
አማካይ ተጫዋቿ የቀድሞዋ የፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች ቤተልሔም ሽመልስ የግዮን ንግስቶችን ተቀላቅላለች።
እንኳን ደህና መጣሽ
መልካም የውድድር ጊዜ
17/08/2026
የግዮን ንግስቶቹ በረኛ ወደ ባህር ዳር ተመልሳለች ....
_________________________
ስም:- ባንችአየሁ ደመላሽ
የምትጫወትበት ቦታ :- ግብ ጠባቂ
የነበረችበት ክለብ:- ሲዳማ ቡና
ባለፈው የውድድር ዓመት በሲዳማ መለያ በተደጋጋሚ የጨዋታ ኮከብ ተብላ የተሸለመች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂዋ ባንቹ ወደ ፕሪምየር ሊግ ወዳሳደገችው ባሕር ዳር ከነማ ተመልሳ ለመጫወት ተስማምታለች ።
ድል ለግዮን ንግስቶቹ
መልካም የውድድር ዘመን
#ባህርዳር
16/08/2026
የኛ ባሕር ዳር ....
የኛ ባሕር ዳር በመጨረሻም የብሔራዊ ቡድኑ ከስደት ነፃ አውጭ ሆና ተገኝታለች ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሐገሩ ላይ ይጫወታል ።
15/08/2026
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።
በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል። ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።
የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ለአሚኮ እንደገለጹት ለበርካታ ዓመታት የዓለም አቀፍ ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያ እና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መኾኑ ተረጋግጧል ብለዋል።
ይህ ትልቅ የስፖርት ስኬት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦች አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ውድድሮችን በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት እንዲያደርጉ ያስችላል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል ብለዋል። ይህ ስኬት በመገኘቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንዲያደርግ ፈቃድ ማግኘቱ የአማራ ክልል እና የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በታሪካዊ ፣ በተፈጥሯዊ እና በባሕላዊ የቱሪዝም ሃብቶች ለታደለው የአማራ ክልል ተጨማሪ ሃብት ነው።የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።
በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል። ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።
የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ለአሚኮ እንደገለጹት ለበርካታ ዓመታት የዓለም አቀፍ ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያ እና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መኾኑ ተረጋግጧል ብለዋል።
ይህ ትልቅ የስፖርት ስኬት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦች አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ውድድሮችን በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት እንዲያደርጉ ያስችላል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል ብለዋል። ይህ ስኬት በመገኘቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንዲያደርግ ፈቃድ ማግኘቱ የአማራ ክልል እና የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በታሪካዊ ፣ በተፈጥሯዊ እና በባሕላዊ የቱሪዝም ሃብቶች ለታደለው የአማራ ክልል ተጨማሪ ሃብት ነው።
መረጃው :- የባሕር ዳር ከተማ ኮምንኪኬሽን
15/08/2026
ማንያዘዋል ካሳ በጣና ሞገዶቹ ቤት ውሉን አራዝሟል ....
_________________________
ስም :- ማንያዘዋል ካሳ
የሚጫወትበት ቦታ :- ተከላካይ
ከከፍተኛ ሊግ ተገኝቶ ያሳለፍነው ዓመት በጣናሞገዶቹ መለያ ድንቅ የውድድር ዓመት ማሳለፍ የቻለው ወጣቱ ተከላካይ ማንያዘዋል በባህር ዳር ከነማ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል ።
መልካም የውድድር ጊዜ
14/08/2026
አንተህ ተፈራ ውሉን አድሷል ....
________________
ስም :- አንተነህ ተፈራ
የሚጫወትበት ቦታ :- አጥቂ
በጥር የዝውውር መስኮት የጣና ሞገዶቹን የተቀላቀለውና ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገው በዓመቱ 7 ጎሎች ማስቆጠር የቻለው አንተነህ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በክለቡ የሚያቆየውን ውል አራዝሟል ።
መልካም የውድድር ጊዜ
13/08/2026
ቻርለስ ሙሴንጌ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል ....
ስም :- ቻርለስ ሙሴንጌ
የሚጫወትበት ቦታ :- አጥቂ
የነበረበት ክለብ :- መቻል