Amhara Football Referees

Call Directions

Amhara Football Referees It describes new releases of football Laws of the Game and over all Football and Referees Info. page. Our Game is Fair Play

😭😭  #የሀዘን 😭😭  #መግለጫ !😭😭የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ብርሃኑ ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ብርሃኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮ...
03/10/2026

😭😭 #የሀዘን 😭😭 #መግለጫ !😭😭

የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ብርሃኑ ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኮሚሽነር ብርሃኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም ጊዜያት በማገልገል አሳልፈዋል። የኮሚሽነር ብርሃኑ ሥርዓተ ቀብር በነገው ዕለት መስከረም 24 ቤተል ኮልፌ ክ/ክፍለ ከተማ አጠገብ ባለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6፡00 ይፈጸማል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኮሚሸነር ብርሃኑ ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ይመኛል።

Ethiopian Football Federation

Amhara Football Referees

💥 ነፍስ ይማር

🔴 ለፕሪሚየር ሊግ ኮሚሽነሮች     የስልጠና ጥሪን ይመለከታል⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️ለ2019 ዓ/ም የውድድር ዘመን በተሻሻሉ ሕጎች ዙሪያ እና የጨዋታ አመራሮችን በተሻለ መ...
03/10/2026

🔴 ለፕሪሚየር ሊግ ኮሚሽነሮች
የስልጠና ጥሪን ይመለከታል
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

ለ2019 ዓ/ም የውድድር ዘመን በተሻሻሉ ሕጎች ዙሪያ እና የጨዋታ አመራሮችን በተሻለ መንገድ መገምገም የሚቻልበትን ሁኔታዎች ለመሰልጠን ረቡዕ 27/01/2019 ዓ/ም አትላስ አካባቢ በሚገኘው አዝማን ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በ2018 ዓ/ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሚሽነርነት ተመድባችሁ ስትሰሩ የነበራችሁ ብቻ እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እያስተላለፍን ስልጠናውን ያልወሰደ ኮሚሽነር በውድድር አመቱ የማይመደብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#ማሳሰቢያ፦ በቅርቡ በFIFA MA Instructors course ስልጠና የወሰዳችሁ የፕሪሚየር ሊግ ኮሚሽነሮች የስልጠና ጥሪው እናንተን አይመለከትም።

Amhara Football Referees

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

🔴 የራሱ ሜዳ ያለው የእግር ኳስ አካዳሚ በባህር ዳር ከተማ ተከፈተ።መስከረም 22/2019. ባህር ዳርስሙን አየሁ ስፖርት አካዳሚ በማለት ምቹ የእግር ኳስ ሜዳን በራስ አቅም እና ሙሉ ወጭ በ...
02/10/2026

🔴 የራሱ ሜዳ ያለው የእግር ኳስ አካዳሚ በባህር ዳር ከተማ ተከፈተ።

መስከረም 22/2019. ባህር ዳር

ስሙን አየሁ ስፖርት አካዳሚ በማለት ምቹ የእግር ኳስ ሜዳን በራስ አቅም እና ሙሉ ወጭ በመስራት በእግር ኳሱ መስክ በትልልቅ ክለቦች ተጫውተው ያለፉ ተጭዋቾች ዛሬ ትናንት ያለፉበትን በትምህርትም የጨበጡትን የስፖርት ዕውቀት ለታዳጊወች ለማጋራት የነገ ተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራን በውብ ሜዳ ትልቅ ራእይን የሰነቀ አካዳሚ ከፍተው ብቅ ብለዋል።

ይህ አካዳሚ ለታዳጊዎች ስልጠናን ከመስጠት ባለፈ የሜዳ ኪራይ ግልጋሎትን በመስጠት ለስፖርት ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን ለእግር ኳስ አፍቃሪዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል።

በአካዳሚው ልጆቻችሁ እንዲሰለጥኑ የምትፈልጉ ወላጆች ሜዳውን በኪራይ መገልገል የምትሹ እግር ኳስ አፍቃሪዎች ከስር በተቀመጠ ቁጥር ደውላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።

Amsalu Esmelealem እና ሄኖክ አቻም የለህ መልካም የስራ ጊዜ ይሁንላችሁ።

የመመዝገቢያ ስልክ ቁጥሮች
0953257363
091 870 2229
0948689784

አድራሻ ቀበሌ 03 በሙሉአለም የባህር ማህከል እና በማዘጋጃ መሀል ነው።

Amhara Football Referees

🌀Setu Birhn

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

🔴 ለወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ አመራሮች     ⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከመስከረም 29/2019 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚጀምር መገለፁ ይታወቃል። በመሆኑ...
30/09/2026

🔴 ለወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከመስከረም 29/2019 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚጀምር መገለፁ ይታወቃል። በመሆኑም ሰኞ በ25/01/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 1፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ሙሉ ቀን ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ ስለተሻሻሉ የጨዋታ ሕጎች እና ቅድመ የውድድር ዝግጅት ገለፃ ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ:- ጥሪዉ የሚመለከታችሁ ብቻ እንድትገኙ እናሳስባለን።

🌀EFF Refereeing Departement

Amhara Football Referees

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

🔴 የአንደኛ ደረጃ አካል ብቃት አሰልጣኝነት ሥልጠና ተጠናቀቀ።ባህር ዳር / 2019 ዓ.ምየባህር ዳር ከተማ የአካል ብቃት አሰልጣኞች ማህበር ከአማራ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ፣ ከባ/ዳር ከተ...
28/09/2026

🔴 የአንደኛ ደረጃ አካል ብቃት አሰልጣኝነት ሥልጠና ተጠናቀቀ።

ባህር ዳር / 2019 ዓ.ም

የባህር ዳር ከተማ የአካል ብቃት አሰልጣኞች ማህበር ከአማራ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ፣ ከባ/ዳር ከተማ ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ እንዲሁም ከባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአንደኛ ደረጃ የአካል ብቃት አሰልጣኞች ስልጠና ከመስከረም 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ በባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ሲሰጥ የቆየው የአንደኛ ደረጃ የአካል ብቃት አሰልጣኝነት ስልጠና መስከረም 16/2019 ተጠናቋል።

ስልጠናው የንድፈ ሀሳብ እና የሜዳ ላይ ተግባር ስልጠና ያካተተ ነው።

የክፍል ውስጥ ስልጠናው በደጀኔ ብዙነህ (መ/ር) እና በሹመት አጎናፍር (ዶ/ር) እንዲሁም የተግባር ስልጠናው በአሰልጣኝ ጥበቡ ወረት ፣ በማስተር አንተነህ ጥሩዓየሁ፣ በአሰልጣኝ ይልቃል እና በሰአልጣኝ ዳኝነት እንዲሁም በአሰልጣኝ ውብሸይ አማካኝነት ሲሰጥ ቆይቶ ተጠናቋል።

በምርቃት መርሃ ግብሩም የአብክመ ባ/ቱ/ስፖርት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ አዱኛ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አቶ ደሳለኝ በመገኘት በቀጣይ ለሚሰጠው 2ኛ ደረጃ የአካል ብቃት አሰልጣኝነት ስልጠና ሁለት ዓመት ሳይጠብቁ በቀጥታ እንዲሳተፉ ለተፈቀደላቸው ከ1 እስከ 3 ለወጡት ሰልጣኞች ሰርተፊኬት ሽልማት አበርክተዋል።

ይህን ሥልጠና እንዲሰጥ ላመቻቻችሁ የባ/ዳር ከተማ የአካል ብቃት አሰልጣኞች ማህበር፣ የአብክመ ባ/ቱ/ስ/ቢሮ፣ ባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ እንዲሁም መምህራንና አሰልጣኞች ለሰጣችሁት ስልጠና ምስጋናችን የላቀ ነው።

ተከታታይነት ያለው ስልጠና በማሰጠት አሰልጣኞችን ማፍራትና ማብቃት ተገቢ ነው እንላለን።

Amhara Football Referees

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

🔴 ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።💥 የአማራ እግር ኳስ ዳኞች መልካም በዓል ይመኛል።Amhara Football Referees ✍️ ፈጣ...
27/09/2026

🔴 ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

💥 የአማራ እግር ኳስ ዳኞች መልካም በዓል ይመኛል።

Amhara Football Referees

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

🔴 የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት ባሉበት ሆነው በኦንላይን ይቁረጡ !ማክሰኞ መስከረም 19 ከቀኑ 10፡00 የሚካሄደው ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት  eff-ticke...
25/09/2026

🔴 የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት ባሉበት ሆነው በኦንላይን ይቁረጡ !

ማክሰኞ መስከረም 19 ከቀኑ 10፡00 የሚካሄደው ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት eff-tickets.com ላይ በመግባት በገፁ ላይ በቅደም ተከተል የተቀመጡትን መመርያዎች በማሟላት መግዛት ይችላሉ።

🟣 የቲኬት ዋጋ

✳️ ፕሪምየም ደረጃ 500 ብር
✳️ ካቴጎሪ 2 ደረጃ 200 ብር
✳️ ካቴጎሪ 3 ደረጃ 100 ብር

Ethiopian Football Federation
Amhara Football Referees

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

🔴 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በ2027 ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የሚወክሉ ዳኞችን መርጦ ለፊፋ መላኩን አሳውቋል። በምስሉ ላይ የተዘረዘሩት የጨዋታ አመራሮች❶...
23/09/2026

🔴 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በ2027 ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የሚወክሉ ዳኞችን መርጦ ለፊፋ መላኩን አሳውቋል።

በምስሉ ላይ የተዘረዘሩት የጨዋታ አመራሮች

❶ በ2018 ዓ/ም በነበራቸው የጨዋታ አፈፃፀም ብቃት

❷ የወደፊት ተስፋ ሰጭነታቸው

❸ በዓለም አቀፍ ኮርሶች ተሳትፎ ላይ በተደረገላቸው ምዘና ያመጡትን ውጤት እና ይህንን ተከትሎ በፊፋ ኢንስትራክተሮች ጥቆማ

❹ ኢንተርናሽናል ዳኞች የነበሩ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ግምት ውስጥ በማስገባት በዝርዝሩ ላይ በሚታየው መልኩ የጨዋታ አመራሮችን ለፊፋ መላኩን አሳውቋል።

በቀጣይ በፊፋ ፀድቆላቸው የሚመጡ የጨዋታ አመራሮች ሀገራችንን በ2027 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ የሚወክሉ ይሆናል።

Ethiopian Football Federation
Amhara Football Referees

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

21/09/2026

Level One Fitness Course

21/09/2026

🔴 የአንደኛ ደረጃ አካል ብቃት አሰልጣኝነት ሥልጠና ቀጥሏል።

ባህር ዳር / 2019 ዓ.ም

የባህር ዳር ከተማ የአካል ብቃት አሰልጣኞች ማህበር ከአማራ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ፣ ከባ/ዳር ከተማ ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ እንዲሁም ከባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአንደኛ ደረጃ የአካል ብቃት አሰልጣኞች ስልጠና ከመስከረም 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ በባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው የንድፈ ሀሳብ እና የሜዳ ላይ ተግባር ስልጠና ያካተተ ነው።

የክፍል ውስጥ ስልጠናው በደጀኔ ብዙነህ (መ/ር) እና በሹመት አጎናፍር (ዶ/ር) እንዲሁም የተግባር ስልጠናው በአሰልጣኝ ጥበቡ ወረት ፣ በማስተር አንተነህ ጥሩዓየሁ፣ በአሰልጣኝ ይልቃል እና በሰአልጣኝ ዳኝነት አማካኝነት ለተከታታይ 10 ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።


Amhara Football Referees

💥

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።

✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees

✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

Address

Bahir Dar

Telephone

251918005743

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Football Referees posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category