03/08/2025
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ከባህርዳር ቴብል ቴኒስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር በ ቴብል ቴኒስ ስፖርት ጎበዝ እና ልምድ ባላቸዉ አሰልጣኞች እድሜአቸዉ ከ 13 እስከ 17 አመት የሆኑ ታዳጊ ወጣቶችን በሁለቱም ጾታ በፕሮጀክት አቅፎ ማሰልጠን ይፈልጋል ስለዚህ ፍላጎቱ ያላችሁ በሙሉ በሚቀጥለዉ ሳምንት ማክሰኞ በ29/11/2017 , ሀሙስ በ 01/12/2017 እና ቅዳሜ በ03/12/2017በሹም አቦ አዳራሽ መመዝገብ ይቻላል ወይም በከተማዉ ስፖርት ጽ/ቤት ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ እና መሰልጠን የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን
ማሳሰቢያ
ስልጠናዉ የሚሰጠዉ በነጻ ነዉ
የስልጠና ቦታ ፖሊ ፊትለፊት ሹም አቦ አዳራሽ
22/05/2025
ሀይሌ ለ 14ኛ ጊዜ ሻምፒዮን በመሆኑ ከራሱ ልጆች፣ ከ ዳርት እና ቦክስ ስፖርተኞች ሰርፕራይዝ ተደርጓል እንዲሁም ከ ህይወት ምግብ ቤት ለቴብል ቴኒስ እና ዳርት ስፖርተኞች ላመጡት ዉጤት እና ላሳለፉት መልካም ጊዜ ሽኝት ተደርጓላቸዋል ስፖርተኞችም ለተደረገላቸዉ ነገር ህይወትን በማመስገን ተሰነባብተዋል ።
20/05/2025
ደሴ ላይ በተካሄደዉ የመላዉ አማራ ጨዋታዎች የባህርዳር ቴብል ቴኒስ ቡድን 1ኛ ሆኖ ዉድድሩን ጨርሷር
ሀይሌ በነጠላ ሻምፒዮና ዉድድር ለ 14 ኛ ጊዜ የክልሉ ሻምፒዮን በመሆን ማንም ሊደርስበት እማይችል ሪከርድ በማስመዝገብ አሸንፋል
ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ አሰልጣኝ በመሆንም ተመርጧል
የባህርዳር ቴብል ቴኒስ ቡድን እንኳን ደስ አላችሁ ።
21/05/2023
የባህር ዳር ከተማ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የጠረጴዛ ቴኒስ ዉድድር ዛሬ ፍጻሜዉን አገኘ
1ኛ-🥇አማራ ሚዲያ ኮርፖሬት(አሚኮ) 👉ወርቅ
2ኛ-🥈ባ/ዳር ዩኒቨርስቲ ፔዳ 👉ብር
3ኛ-🥉ባ/ዳር ኢትዮ ቴሌኮም 👉ነሀስ
በመሆን ዉድድራቸዉን ጨርሰዋል
28/03/2023
የባህርዳር ቴብል ቴኒስ በጎንደር ከተማ በተካሄደዉ 8ኛዉ የመላዉ አማራ ዉድድር በጥሩ ዉጤት 3 ወርቅ 2 ብር 1ነሀስ በማምጣት ዉድድራቸዉን ጨርሰዋል
በነጠላ ሻምፒዮና በተደረገዉ ዉድድር ሀይለሚካኤል አወቀ ሁሉንም በማሸነፍ ለ 13ኛ ጊዜ የክልልሉ ሻምፒዮን ሆኗል በዚህም ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል ቡድኑ ዛሬን አርፎ ነገ ወደ ባህርዳር ይንቀሳቀሳል ።
27/03/2023
ዛሬ ፍጻሜዉን ባገኘዉ የነጠላ ሻምፒዮና ዉድድር ሀይሌ ሁሉንም ተጫዋቾች በማሸነፍ የአማራ ክልል ሻምፒዮን በመሆን ወርቁን በመዉሰድ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል
ሀይሌ ከዚህ በፊት 12 ጊዜ ሻምፒዮን የነበረ ሲሆን ከዛሬዉ ጋር ለ13ኛ ጊዜ የክልሉ ሻምፒዮን እና ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል ።
🥇🏆🥇🏆🥇🏆🥇🏆🥇🏆🥇🏆🥇
19/03/2023
የባህርዳር ቴብል ቴኒስ ልኡካን ቡድን በጎንደር ከተማ
19/08/2022
የ 2014 8ኛዉ የአማራ ክልል የታዳጊዎች የጠ/ቴኒስ ዉድድር ኮከብ አሰልጣኝ
ኢንስትራክተር ሀይለሚካኤል አወቀ
12/02/2022
ከተማችንን ለረጅም አመታት በዉጤታማነት ያስቀጠሉ እና ያስተዋዎቁ የከተማችን የቴብል ቴኒስ አምባሳደሮቻችን ።