Football Referees Association of North Shawa Zone

Football Referees  Association of North Shawa Zone

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Football Referees Association of North Shawa Zone, Sports Team, Debre Birhan.

06/02/2026

🔴 #ማስታወቂያ ለሁሉም እንዲደርስ #ሼር ይደረግ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የጨዋታ ታዛቢዎች/አሴሰሮች ስልጠና በመስጠት የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡትን በየሊጐች መድቦ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዳኛ የነበራችሁ እና ከዚህ ጋር የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቻ በተቀመጠው ሊንክ እየገባችሁ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡

💥 #መስፈርት

➊- ፌደራል ዳኛ የነበረ
➋- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያወዳድራቸውን ሊጎች በዳኝነት የሰራ
➌- እንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ያለው
➍- የሚሰጠውን የጤና ምርመራ የሚያልፍ
➎- ጥሩ ስነ ምግባር ያለው
➏- በማናቸውም የእግር ኳስ ክለብ እና የክልልና ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች አባል እና አመራር ያልሆነ
➐- የኮምፒውተር አጠቃቀም ክህሎት ያለው
➑- ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ እና ከዚያ በላይ
➒- ከደባል ሱስ የፀዳ
➓- በስነ ምግባር ጥሰት ተቀጥቶ ያልታገደ

እዚህ ይመዝገቡ 👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfmAWpJXe8xOKHB3xTIUXFMv6Z2SiyPiQC3vKbCm0txXgq80A/viewform?usp=publish-editor

የጤና ምርመራ፤ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት እና ስልጠናው የሚጀመርበት ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡

🌀

Photos from  Football Referees  Association of North Shawa Zone's post 19/12/2025

12ኛዉ የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ሰራተኞች ዉድድር በትናንትናዉ እለት(09/04/2018 ) በደ/ብርሃን ከተማ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በዚህ ዉድድር ላይ 11 ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ ሲሆን ዉድድሩም እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

Telegram https://t.me/ensrf

✅ page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090656254922

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

19/12/2025

ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር የ2026 ኢንተርናሽናል ዳኞችን ዝርዝር አሳውቋል።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ከወራት በፊት የ22 እጩዎች ዝርዝር አሳውቆ የነበረ ሲሆን ሁሉም የጨዋታ አመራሮች በፊፋ ፀድቀዋል። በተጨማሪም ለ5 ዓመታት ተቀንሶ የቆየው የአንድ የረዳት ዳኛ ኮታ እንዲመለስ ፌዴሬሽናችን ለፊፋ ያቀረበው ተደጋጋሚ ጥያቄ እና የማሳመን ሥራ ተቀባይነት አግኝቶ ከ2026 ጀምሮ የወንድ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞቻችን ቁጥር ወደ 7 መመለስ ችሏል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዳኞች ልማት ላይ ለውጥ ለማምጣት እያከናወነ ባለው ስራ አዳዲስ ብቁ ዳኞችን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ለማምጣት ባደረገው ጥረት በዘንድሮው የፊፋ ዳኞች ዝርዝር 43% የጨዋታ አመራሮች በአዲስ ተተክተዋል። በፊፋ በፀደቀው አዲሱ የኢንተርናሽናል ዳኞች ዝርዝር በወንዶች አራት ዳኞች (ዳንኤል ይታገሱ፣ ሄኖክ አበበ፣ ሃይማኖት አዳነ እና ባህሩ ተካ) በሴት አንድ ዳኛ (ዮርዳኖስ ሙሉጌታ) ፣ በወንድ ረዳት ዳኛ አራት (ሲራጅ ኑርበገን፣ ዘመኑ ሲሳይነው፣ አማን ሞላ እና ኤልያስ መኮንን) እንዲሁም በሴት ረዳት አንድ (መቅደስ ብርሃኑ) በአጠቃላይ 10 የጨዋታ አመራሮች በአዲስ መልክ ተካተዋል።
ለነባሮችም ሆነ በአዲስ ለተካተታችሁ ዳኞች እንኳን ደስ አላችሁ ።

Telegram https://t.me/ensrf

✅ page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090656254922

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

06/12/2025

የመስሪያ ቤቶች ስፖርት ዉድድር በዞን ደረጃ ታህሳስ 8/4/2018 ጀምሮ እንደሚመራ ዞኑ ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሳወቀ በመሆኑ ዳኞችም ይህንን አዉቃችሁ አስፈላጊዉን የቅድመ ዝግጅት ስራ እንድትሰሩ እናሳዉቃለን።

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ ፔጁን እና ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ።

Telegram https://t.me/ensrf

✅ page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090656254922

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

05/12/2025

ለU20 ሊግ የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

የU20 ሊግ የጨዋታ አመራሮች በ02/04/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 1፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ.የተሻሻሉ ሕጎች ትምህርት እና የውድድር ዝግጅት ገለፃ ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ
በ2017 የውድድር ዓመት ሁለት ጊዜ ፈተና የወደቃችሁ እና በአመቱ ምንም ጨዋታ ያልመራችሁ ለፈተናው መምጣት የማትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የሚመጡትን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”
ኢእፌ

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ ፔጁን እና ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ።

Telegram https://t.me/ensrf

✅ page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090656254922

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

Telegram: Contact @ensrf

05/12/2025

🔴
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️

ከሁለት ዓመታት በላይ ተቋርጦ የቆየው የአማራ ሊግ ውድድር ለመጀመር ዝግጅት ላይ እንዳለ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዞኖች በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
ይህ ለክልሉ ማህበረሰብ ወጣቶችና ነጋዴዎች ማህበራዊም ኢኮኖሚያዊም መነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታልና መልካም ተግባር መነሳሳት ነው።

መወዳደር የምትፈልጉ በየዞኑ ያላችሁ ክለቦችም መመዝገብ ትችላላችሁ

✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ ፔጁን እና ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ።

Telegram https://t.me/ensrf

✅ page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090656254922

💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow

02/12/2025

🔴 ኢትዮጵያዊው ዳኛ የፍጻሜውን ጨዋታ ይመራል

የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የፍጻሜ ጨዋታውን ኢትዮጵያዊው ዳኛ ይመራዋል።

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በከፍተኛ ድምቀት ያለፉት ቀናት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ህዳር 23/2018 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚደረጉ የፍጻሜ እና የደረጃ ጨዋታዎች መዝጊያውን ያገኛል።

ኢትዮጵያ ከኬንያ ከሚያደርጉት የደረጃ ጨዋታ በመቀጠል የሚካሄደውን ተጠባቂውን የታንዘኒያ እና የዩጋንዳን የፍጻሜ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ይመራዋል። አብረውት በረዳትነት የጅቡቲ እና የሩዋንዳ ዳኞች የተመረጡ ሲሆን በአራተኛ ዳኝነት ከሱማሌ መመደባቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Photos from  Football Referees  Association of North Shawa Zone's post 18/11/2025

በማህበራችን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፌደራል ዳኛ አብዱራህማን ይማም አማካኝነት ለተከታታይ 5ቀን ሲሰጥ የነበረው መሠረታዊ የአቅም ማጓልባቻ የዳኞች ስልጠና መጠናቀቁን ወጣቶችና ስፖርት ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤትገለፀ።
ህዳር 08 ቀን 2018
አጣዬ

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ትብብር እና በፌደራል የእግር ኳስ ዳኛ አብዱራማን ይማም አሰልጣኝነት ሲሰጥ የነበረው መሠረታዊ የአቅም ማጓልባቻ የዳኞች ስልጠና መጠናቀቁን የገለፁልን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ እንግዳሠው ታፈሰ ሲሆኑ ስልጠናው ለሰልጣኞች ትልቅ መነቃቃት ፍጥሯል በማለት ተናግረዎል።

መሠረታዊ የአቅም ማጓልበቻ ለነባር እና ለአዲስ ዳኞች ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 28 ወጣቶች ስልጠናውን አጠናቀዋል።

በእግር ኳስ ሲሰጥ በቆየው ስልጠና ማጠቃልያ ላይ ተገኝተው አስተያየት የሰጡት የፌደራል የእግርኳስ ዳኛ አብድራህማን ይማም እንደተናገሩት ስልጠናው በከፍተኛ ዳኝነት የሚሰጥ በመሆኑ እናተ ያለምንም ወጭ እና ድካም በማግኛታችሁ እድለኛ መሆናቸውን ተናግረው በቀጣይ በእግር ኳስ ሜዳላይ ብቃት ያለው ዳኛ በመሆን ሀገራችሁን እንድትወጡ የሚል መልእክት አስተላልፈው እኔ ግዴታዬ እየተውጣው ነዉ በማለት ተናግረዋል።

በመቀጠል ለተከታታይ ይሰጥ በነበረው የዳኝነት ስልጠና ላይ እውቀት በጨበጡት መሰረት መመዘኛ ጥያቄ ወይም ፈተና ጥሩ ውጤት በማምጣት 1ኛ_3ኛ ለመጡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥተዋል በዚሁ መሰረት ተከታትለው አንደኛ የውጡት ሁለቱ ሰልጣኛች የሆኑት የአጣዬ ሁለተኛ ደረጃ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ብሩክ ምንዳ እና ኢማን ወንደሰን ሲሆኑ በ3ኛነት የወጣችሁ የአጣዬ ሁለተኛ ደረጃ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሴት ሰልጣኝ ዳኛ ወጣት ሃና ምንዳሁን በእለቱ ተሸልመዋል።

በመቀጠል የተናገሩት የፌደራል የእግርኳስ ዳኛ አብድራህማን ይማም በትናትናው እለት የንድፍ ሀሳብ ስልጠና አጠናቀው ወደ ዛሬ ወደ ተግባር መሠረታዊ የዳኝነት ስልጠና መቀጠሉን ተናግረው ለመጀመርያ ጊዜ የሴቶች እና የወንዶች የዳኞች ስልጠና መቀጠሉን ተናግረው

በቀጣይ በአጣዬ ከተማ የእግር ኳስ አጨዋች እጥረት እንዳይፈጠር ጠንክራችሁ አቅማችሁን እንድታጠናክሩ የሚል መልክት ፌደራል ዳኛ አብዱራህማን ተናግረዋል።

በመጨረሻም እግር ኳስ ዳኝነትስልጠናዉ መጠናቀቁን አስመልክቶ መልእክት ያስተላለፋት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ እንግዳሠው ታፈሰ ለተከታታይ 5ቀን ሲሰጥ ለነባር እና አዲስ የዳኞች የእግር ኳስ መሠረታዊ የዳኝነት እና የአቅም ማጓልበቻ ስልጠና መጠናቀቁን አስመልክቶ እንደተናገሩት የነበረን ቆይታ በጣም ጥሩ እንደነበረ እና እውቀት የጨበጣችሁበት በማለት የተናገሩት ኃላፊው ይሄንን ስልጠና ለማግኛት እያዳዳችሁ ከ30ሺህ ብር በላይ የምትጠየቁበት ስልጠና በነፃ ያለ አንድ ክፍያ ላሰለጠናችሁ አሰልጣኝ
የፌደራል የእግርኳስ ዳኛ አብድራህማን ይማም አመስግነዋል በማለት ተናግረው በቀጣይ የከተማችን ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን እና ክልላችን ስም በበጎ አስጠርታችሁ እንደምንኮራባችሁ መልእክት አስተላልፈው ተጠናቋል።
መረጃዉ የአጣዬ ከተማ ኮምኒኬሽን ነዉ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Debre Birhan?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Debre Birhan