Dilla Sport ዲላ ስፖርት

Dilla Sport ዲላ ስፖርት

Share

ስፖርትን በቅርበት

15/08/2026

ላሊጋው ተመልሷል!

ተወዳጁ የስፔን ላሊጋ ​የ2026/27 አዲስ የውድድር ዘመን ዛሬ በይፋ ይጀምራል። 🇪🇸

​አዲስ የውድድር ዘመን። አዲስ ትግልና ፈተና።🏆❤️

Photos from Dilla Sport ዲላ ስፖርት's post 14/08/2026

ሻክታር ዶኔትስክ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የቻምፒየንስ ሊግ የቤት ጨዋታዎቹን በቼልሲው የመጫወቻ ሜዳ ስታምፎርድ ብሪጅ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለውና ክለቡን በይፋ ለማስመዝገብ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
​—
ምንጭ፦

14/08/2026

ትላንት ⏩️ ዛሬ

​የእግር ኳስ ዓለም ሕያው ታሪክ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የእግር ኳስ ዘመኑ 25ኛ Season (የውድድር ዘመኑን) ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል! 🤯👏

​ከስፖርቲንግ ሊዝበን የልጅነት አጀማመር እስከ አል ናስር እና የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን መሪነት... የ25 ዓመታት የማይበገር የጽናት፣ የፍላጎት እና የላቀ ብቃት ጉዞ! 👑⚽

14/08/2026

ጊዜው አብቅቷል 🔵🇦🇷

​ቼልሲ ለአርጀንቲናዊው የክለቡ አማካይ ኤንዞ ፌርናንዴዝ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ አሁን አበቃ! ⏰

​እስከተቀመጠው ጊዜ ገደብ ድረስ ከማንቸስተር ሲቲም ሆነ ከሌላ ማንኛውም ክለብ የቀረበ ምንም አይነት ይፋዊ የፅሁፍ የዝውውር ጥያቄ ለብሉዞቹ አልደረሰም።

​በዚህም ምክንያት፡
ቼልሲ ተጫዋቹን ለመልቀቅ ያስቀመጠው የ120 ሚሊዮን ፓውንድ መስፈርት አሁን ዋጋ አጥቷል። ይህ መስፈርት በግንቦት ወር ለኤንዞ ወኪሎች በቃል ደረጃ ተነግሯቸው የነበረ ሲሆን፣ ፍላጎት ላላቸው ክለቦች እንዲያቀርቡት ተፈቅዶላቸው ነበረ።

ማንቸስተር ሲቲ ከጊዜ ገደቡ ማለፍ በኋላም ቢሆን ተጨማሪ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ ይሞክር አይሞክር ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

ቼልሲዎች በአሁኑ ወቅት ኤንዞ ፌርናንዴዝ ለ2026/27 የውድድር ዘመን በስታምፎርድ ብሪጅ እንደሚቆይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች ሆነዋል። 🔵✍️

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

Photos from Dilla Sport ዲላ ስፖርት's post 14/08/2026

🔔 ዳራ ቀባዶ የ2018 “ጀግኒት ሰመር ካፕ” ዘውድን ተቀዳጀ!

​ላለፉት ስድስት ሳምንታት በዲላ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ሲካሄድ የሰነበተውና በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የ2018 “ጀግኒት ሰመር ካፕ” የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በታላቅ ድምቀት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በአሰልጣኝ ያብስራ ሀብታሙ አስተባባሪነት የተዘጋጀው እና በሀገራችን በተለያዩ የሊግ እርከኖች የሚጫወቱ ተስፋ ያላቸውን ሴት ስፖርተኞችን ያሳተፈው ይህ ውድድር፣ ከሲዳማ ክልል የመጣውን ዳራ ቀባዶን ባለድል በማድረግ ተጠናቋል።

​ዛሬ በዲላ ስታድየም (ትንሿ ሜዳ) በተካሄደው ውጥረት የበዛበት የመጨረሻ ጨዋታ፣ የዋንጫ ተስፋ የነበራቸው ዲላ ኤግልስ ከ አለታ ጩኮው ዴ ፕሪስ እግር ኳስ አካዳሚ ጋር ተገናኝተዋል።

ዴ ፕሪስ አካዳሚ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸናፊ ቢሆንም፣ በነጥብ እና በጎል ብልጫ የበላይነቱን የያዘው ዳራ የውድድሩ አጠቃላይ ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

​በአዘጋጇ ዲላ ከተማ አስተናጋጅነት 5 የተለያዩ የእግር ኳስ ቡድኖችን አሳትፎ ሲካሄድ የቆየው የጀግኒት ሰመር ካፕ የዳራ የበላይነት ሲያጠናቅቅ ​ዳራ ከ 5 ጨዋታ አራቱን በማሸነፍ በአንዱ ተሸንፎ ​በዚህ አስደናቂ ማጠቃለያ የታሪካዊው ጀግኒት ሰመር ካፕ 2018 ዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል።

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

14/08/2026

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቀው የእግር ኳስ የዳታና ስታቲስቲክስ ተቋም ኦፕታ (OPTA) አዲስ ትንበያ መሠረት፤ አርሰናል የ2026/27 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ለማንሳት የላቀ ቅድመ-ግምት (Clear Favourites) አግኝቷል! 🔥🔴⚪️

በOPTA ትንበያ መሰረት መድፈኞቹ 38% ዋንጫውን የማንሳት ግምት ሲሰጠው ማንቸስተር ሲቲ በ20.5% ሁለተኛ ሊቨርፑል በ 9.2% ሶስተኛ ደረጃ ሰጥቷቸዋል

እርሶስ ምን ይላሉ የOPTA ትንበያ የሚሆን ይመስሎታል? ሀሳቦን ያጋሩን

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

14/08/2026

ማንቸስተር ሲቲ የፔፕ ጓርዲዮላን ተፅዕኖ አቅልሎ ተመልክቶት ይሆን?

​ፔፕ ጓርዲዮላ ከክለቡ መልቀቃቸውን ተከተሎ ስድስት የዋናው ቡድን ተጫዋቾች ማንቸስተር ሲቲን የለቀቁ ሲሆን፣ ተጨማሪ ተጫዋቾችም በሩን አንኳክተው ለመውጣት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

​🚪 ክለቡን የለቀቁ ተጫዋቾች፦
​🇳🇱 ቲጃኒ ሬይንደርስ ➡️ አል-ቃድሲያ (£52M)
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 ጄምስ ትራፎርድ ➡️ ሊድስ ዩናይትድ (£40M)
​🇨🇭 ማኑኤል አካንጂ ➡️ ኢንተር ሚላን (£12M)
​🇳🇱 ናታን አኬ ➡️ ፈነርባቼ (£6M)
​🇵🇹 በርናርዶ ሲልቫ ➡️ ሪል ማድሪድ (በነፃ)
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 ጆን ስቶንስ ➡️ ኢንተር ሚላን (በነፃ)

​⏳ ክለቡን ይለቃሉ ተብለው የሚጠበቁ፦
​🇪🇸 ሮድሪ ሄርናንዴዝ
​🇧🇷 ሳቪንሆ

​🗣️ እርሶስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አለዎት? ከስር በኮመንት ያካፍሉን! 👇💬

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

14/08/2026

ኮዲ ጋክፖ ወደ ቶተንሃም? 😲🤝

​የሆላንዱ ታዋቂ የስፖርት መገናኛ ብዙሃን VI (Voetbal International) እንደዘገበው ከሆነ፤ ቶተንሃም ሆትስፐር እና የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጫዋች ኮዲ ጋክፖ በግል ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ስምምነት ላይ ደርሰዋል!

​የዴ ዜርቢ ፍላጎት፡ የሞሪስዮ ፖቼቲኖን ተኪ ሁነው ስፐርስን እየመሩ የሚገኙት ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ የሆላንዳዊውን አጥቂ በስፐርስ ማሊያ ማየት እንደሚፈልጉ የገለጹ ሲሆን፣ ክለቡም ከሊቨርፑል ጋር ኦፊሴላዊ ንግግር ጀምሯል። 📞

​የዝውውሩ ሁኔታ፡ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ዝውውሩ ስኬታማ ሆኖ የመጠናቀቅ ትልቅ ተስፋ እና መተማመን እየጨመረ ይገኛል። 👀

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

14/08/2026

ማንቼስተር ሲቲ ለአርጀንቲናው የአማካይ ስፍራ ኮከብ ኤንዞ ፈርናንዴዝ (Enzo Fernández) 120 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጣ የዝውውር ጥያቄ አዘጋጅቷል! 💰🔥

​የፕሪምየር ሊጉ ኃያል ክለብ ይህንን አርጀንቲናዊ አማካይ ወደ ኢቲሃድ ለማምጣት እና የዝውውር ጥያቄውን ይፋ ለማድረግ በሙሉ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

​ምንጭ DiMarzio

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

14/08/2026

አርሰናል የቪክቶር ኦሲሜንን ዝውውር ጠየቀ! 💣

​አርሰናሎች የ27 ዓመቱን ናይጄሪያዊ አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜንን ማስፈርም ስለሚችሉበት ሁኔታ የቱርኩን ክለብ ጋላታሳራይን ጠይቀዋል!

​በተቃራኒው ደግሞ የቱርኩ ክለብ በዚህ የዝውውር መስኮት የሰሜን ለንደኑን ክለብ መስመር ተጫዋቾች የሆኑትን ገብርኤል ማርቲኔሊን እና ወጣቱን ኤታን ኑዋኔሪን በቋሚነት ወይም በውሰት የራሱ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

​ይህ ጉዳይ አጥቂው በአሁኑ ወቅት በበርካታ የአውሮፓ ትላልቅ ክለቦች አይን ውስጥ የገባ በመሆኑ፣ በዝውውር መስኮቱ መጨረሻ ላይ ትልቅ ትኩረት የሚስብ እና ሁኔታው በፍጥነት ሊቀያየር የሚችል ጉዳይ ነው! 🔜📝✅

ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/gidfc

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Dilla?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Dilla