Dire Dawa Football Federation

Dire Dawa Football Federation

Share

This is Official page of DDFF

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 01/03/2026

የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት

​ክቡራን የድሬዳዋና የመላው ሀገራችን ስፖርት ቤተሰቦች፤
​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) የዓለም አቀፍ ጨዋታዎቹን በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም እንዲያደርግ ዕውቅናና ፈቃድ በማግኘታችን የተሰማኝን ከፍተኛ ደስታ በራሴና በድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስም ለመግለጽ እወዳለሁ።

​ይህ ታሪካዊ ስኬት ዝም ብሎ የተገኘ ሳይሆን፣ በከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነት የመጣ ውጤት ነው። በተለይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ላደረጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ፣ ለሰጡት የቅርብ ክትትልና ላሳዩት የስፖርት መሪነት ጥበብ በፌዴሬሽኑ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። የእሳቸው ቁርጠኝነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ ይህንን የምስራች ለመስማት ባልታደልን ነበር።

​ይህ ስታዲየም መፈቀዱ ለከተማችን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚዋና ለገጽታ ግንባታውም ትልቅ ትርጉም አለው። የድሬዳዋ ስፖርት አፍቃሪም እንደ ሁልጊዜው እንግዳ ተቀባይነቱንና ለብሔራዊ ቡድኑ ያለውን ፍቅር በተግባር እንደሚያሳይ እምነቴ ፅኑ ነው።

​በመጨረሻም፣ ይህ ስኬት እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የፌዴሬሽን አባላት፣ የሥራ ኃላፊዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።
​ድሬዳዋ የሰላም፣ የፍቅርና የእግርኳስ ከተማ መሆኗን በዓለም አቀፍ መድረክ በድጋሚ የምታረጋግጥበት ጊዜ አሁን ነው!

​ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ስፖርታችንን ይባርክ!

ኮሚሽነር አለሙ መግራ
የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

01/03/2026

ለተግባራዊ አመራርና ለስፖርቱ ዕድገት ለቆሙት ከንቲባችን ምስጋና ይሁን!

​የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ደረጃውን ጠብቆ ለዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ብቁ እንዲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ያሳዩት ቁርጠኝነት ዛሬ ፍሬ አፍርቷል። ስታዲየሙ የሀገር ገጽታን በሚገነባ መልኩ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ያልተቆጠበ ጥረት በድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የስፖርት ቤተሰቡም ይህንን ትልቅ ዕድል በመጠቀም የከተማችንን ስም እና እንግዳ ተቀባይነት ለዓለም ለማሳየት ዝግጁ እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 19/02/2026

በድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ2018 ዓ/ም ከፍተኛ የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ሀምሳ አራት ጨዋታ ክንውኖች ተገመገመ።

ይኸው የግምገማ ሂደትም በዳኞች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በውድድር ላይ የታዩ ከፍተቶችን ለማረም እና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እያለመ እንደሆነም ተገልጿል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ እና የድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ በመድረኩ ላይ በመገኘት እንደተናገሩት የድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ ተዋቅሮ ስራ ከጀመረ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ የእግርኳስ እንቅስቃሴን ማነቃቃት የተቻለ ሲሆን አሁን ላይ በፊት ከነበረው እጅግ የተሻለ ለመድረስ ደሞ ካሰብነው ብዙ የሚቀረን መሆኑን በመረዳት እንደ ሀገር በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ምሳሌ አድርጎ ለማስቀጠል በተለይ ዳኞች ለሙያው ትልቅ ትኩረት በመስጠትና የተጣለባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት እግር ኳሱን የተሻለ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።

የአልቢተር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው የሚታዩ የዳኝነት ክፍተቶችን በቅርበት በመከታተል ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ገለፀዋል ።

በድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ኃይሉ በ 2018 ዓ/ም የከፍተኛ ዲቪዚዬን ተወዳዳሪ ቡድኖች መካከል በተደረገ 54 ጨዋታዎች መካከል 286 ቢጫ ካርዶች 19 ቀይ ካርዶች 126 ጎሎች የተመዘገቡ ሲሆን በነዚህም ጎሎች ውስጥ 74 ተጫዋቾች የጎል ባለቤት መሆናቸውን በጹፋቸው ገልፀው በዳኝነትና በጨዋታ ኮሚሽነሪዎች መካከል የታዩ ክፍተቶችና ጠንካራ ጎችንም ለቤቱ በስፋት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የውይይት መድረክ ላይ የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እና የድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ያህዬ አባድር የአልቢተር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጀማል አህመድ የውድድር እና ስነ ስርአት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ኃይሉ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ የማነ ዘገየ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች የጨዋታ ኮሚሽነር እና ዳኞች በተገኙበት ሰፊ ውይይት በማድረግ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም እና ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል።

Photos from Dire VIP football Club's post 16/02/2026
Photos from Dire Tv - አማርኛ's post 15/02/2026
14/02/2026

የደረጃ ሰንጠረዥ

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 12/02/2026

#ዜና /የድሬዳዋን እግር ኳስ ለማሳደግ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ

በድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአልቢተር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጀማል አህመድ አማካኝነት የድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ለሚያጫውቱ ከ28 በላይ ለሚሆኑ ዳኞች የትጥቅ ድጋፍ ተበርክቷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮሚሽነር አለሙ መግራ ለእግር ኳሱ ዘርፍ እያበረከቱት በሚገኙት ከፍተኛ አስተዋፆ "ኳሱ የኛ ነዉ" በሚል እየተሰሩት በሚገኙት ስራዎች ድሬዳዋ ላይ በአሁኑ ሰዓት እግር ኳሱ በከፍተኛ መነቃቃት ላይ እንደሚገኝ አቶ ጀማል ገልፀዋል።

አቶ ጀማል አያይዘውም ዳኞች የእግር ኳስ ጨዋታዎች በሰላም እንዲጠናቀቁ የጎላ ሚና እንዳላቸው አመላክተው፤የድሬዳዋን እግር ኳስ ለማሳደግ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽን ም/ፕሬዝዳንት ወጣት ያሀዬ አባድር በበኩላቸው በየጊዜው በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የወጣቱን የእርስ በእርስ ትስስርና ቅርበት እያጠናከሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የድሬዳዋን የእግር ኳስ ታሪክ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ደግሞ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽን የውድድርና ስነ-ስርአት ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ወጣት ኤርሚያስ ሀይሉ ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት በየአካባቢው የተጀመሩት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ምቹ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የትጥቅ ድጋፍ የተበረከተላቸው ዳኞች በበኩላቸው ለተበረከተው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

DDGC

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 07/02/2026

#ዜና | የድሬዳዋ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከስፖርቱ ባሻገር በፅዳት ዘመቻ መሳተፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱ መወጣት እንደጀመረ ተገለፀ ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 09 የአስተዳደሩ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ና ተጫዋቾች እንዲሁም የፀጥታ ሀይሎችና ነዋሪዎችን ያሳተፈ የፅዳት ዘመቻ ተከናውኗል ።

በፅዳት ዘመቻው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ የእግር ኳስ
ፌዴረሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ያህያ አባድር እንደገለፁት የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ
ከስፖርቱ ባሻገር ከተማውን ከህብረተሰቡ እንዲሁም ከፀጥታ ሀይሎችና የእግርኳስ ተጫዋች ቡድኖችን በጋራ በመሆን በፅዳት ዘመቻው በመሳተፍ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን በመወጣት ዘመቻውን ማከናወናቸውን ገልጸዋል ።

ምክትል ምክትልፕሬዚዳንቱ አክለውም የፅዳት ዘመቻውን በቀጣይ በሳምንት አንድ ጊዜ በማፅዳት የፅዳት ዘመቻው ባህል አድርገው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የወረዳ 09 የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ
የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ኤርሚያስ
ሄኖክ እንደገለፁት የፀጥታ ሀይሉ የአካባቢውን ፀጥታ ከማስጠበቅ ባሻገር ህብረተሰቡ በሚያከናውነው የልማት ተግባራት ከማህበረሰቡ እንዲሁም ከፌዴሬሽኑ ጎን በመቆም ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በፅዳት ዘመቻው የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ አባሎችና አመራሮች እንደገለፁት ከእግርኳስ ጨዋታዎች ባሻገርም የሚኖሩበት አካባቢ ና ወረዳ በማፅዳት ሌሎችንም ወጣቶችም ለማነሳሳት መሆኑንም ገልፀዋል።

በፅዳት ዘመቻው የወረዳው አመራሮች
ዘየእግር ኳስ የፌደሬሽኑ አመራሮች፣ቡድን መሪዎች፣ ተጫዋቾች፣የፀጥታ ሀይሎችና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል ።

06/02/2026

#ውጤት

⏰ FULL-TIME

🏟 ሳቢያን ሜዳ

06/02/2026

⏰ FULL-TIME

🏟 ሳቢያን ሜዳ

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 03/02/2026

የድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Dire Dawa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Dire Dawa