Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት

Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት

Share

welcome to the OFFICIAL Mesrak Sport Media

12/05/2026

የዓለም አትሌቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጆን ረጂዮን አዲስ አበባ ገቡ

የዓለም አትሌቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆን ረጂዮን እና የጨረታዎች፣ ውድድሮች እና ሁነቶች ዳይሬክተ ማርክ ሀስት ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ አመራሮች ኢትዮጵያ መምጣት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዓለም አትሌቲክስ ጋር የጀመረውን የስፖርት ዲፕሎማሲ የበለጠ የሚያጠናክር ይሆናል።

አመራሮቹ በመገባደድ ላይ የሚገኘውን የ አደይ አበባ ዓለምአቀፍ ስቴዲየምን ጨምሮ ሌሎች የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ጨምሮ 2028 አልቲሜት ሻምፒዮን ሺፕ ለማዘጋጀት ለዓለም አትሌቲክስ ጥሪ ማቅረቧን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

( AMN )

ግንቦት 4/2018 ዓ.ም

Photos from Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት's post 12/05/2026

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአራት አዳዲስ ተጨዋቾችን ፊርማ ይፋ አደረገ

በሜዳም ከሜዳም ውጭ ሲቸገር የቆየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች እንዳያስፈርም በፊፋ መታገዱ ይታወሳል፡፡

ክለቡ ከከሰሱት የቀድሞ ተጨዋቾች ጋር የነበረውን አለመግባባት በመፍታቱ ከቀናት በፊት ነበር የተጣለበት የዝውውር እገዳ የተነሳው፡፡

አንጋፋው ክለብ ዛሬ አመሻሽ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ አራት የውጭ ሐገር ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾችን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

የ23 ዓመቱ ጋናዊ ተከላካይ ኬልቪን ኤዶ ዶሴህ ቀዳሚው ነው፡፡ አይቮሪኮስታዊ አማካይ ካርተር አሂሮ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጓዊ አጥቂ ክሪስ ቶሉንጋ እንዲሁም ጋናዊ አጥቂ አልፍሬድ ሜንሳህ ፈረሰኞቹን መቀላቀላቸውን ይፋ ተደርጓል፡፡

አዲስ የፈረሙት ተጨዋቾች በአፍሪካና በአውሮፓ የተለያዩ ሐገራት ተጫውተው ያሳለፉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ተጨዋቾቹ ክለቡን ከመውረድ የሚታደጉና በቀሪ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ቡድኑን የሚያነሳሱ እንደሚሆኑ የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ አሰልጣኝና ተጨዋቾቹን ወደ ክለቡ ያመጡት ሚቾ ተናግረዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ 14 ተጨዋቾች እንደለቀቁበት የገለጹት ደግሞ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ናቸው፡፡

ክለቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ በሊጉ ለመቆየት አራት ተጨዋቾችን ማስፈረሙ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አሰልጣኙ ገልጸዋል፡፡

ፈረሰኞቹ በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጪው ሐሙስ ከወላይታ ድቻ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በሊጉ ካደረጓቸው 31 ጨዋታዎች 39 ነጥቦችን ሰብስበው 12ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው ይታወቃል፡፡ ( AMN )

ግንቦት 4/2018 ዓ.ም

12/05/2026

ኢትዮጵያ እና ግብፅ ነገ ይጫወታሉ

ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ ወደ አፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የተመለሰችው ኢትዮጵያ፣ ነገ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ከግብፅ አቻዋ ጋር የምድብ መክፈቻ ጨዋታዋን ታደርጋለች። በአሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ይኸው ብሔራዊ ቡድን በጠንካራው ምድብ አንድ ከሞሮኮ እና ቱኒዚያ ጋር የተደለደለ ሲሆን፣ በዚህ ውድድር ላይ ግማሽ ፍፃሜውን ጨምሮ እስከ 10ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ሀገራት በኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የማለፍ ታሪካዊ ዕድል ያገኛሉ።

AdissAdmas

12/05/2026

የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
2025/26 CBE Ethiopian Premier League

የጨዋታ ቀን/31ኛ ሳምንት
ግንቦት 03/2018

አዳማ ሳ/ቴ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም
10:00

አሰላለፍ
ነገሌ አርሲ - ድሬዳዋ ከተማ

12/05/2026
Photos from Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት's post 12/05/2026

ኢትዮጵያ በባህልና ቋንቋ፣ በጥበባትና ስፖርት ዘርፍ ያላትን ተሞክሮ ለናይጄሪያ ልዑክ ቡድን አጋራች።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ለሚገኙት የናይጄሪያ ብሔራዊ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ጥናት ተቋም (NIPSS) ከፍተኛ አመራሮች የአገሪቱን የባህል፣ የቋንቋ፣ የኪነጥበብ እና የስፖርት ፖሊሲዎችና አፈጻጸሞች የሚዳስስ ገለጻ ተደርጓል።

የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ አቶ አለማየሁ አርጋው የዘርፉን የፖሊሲ ማዕቀፎች፣ አፈጻጸሞችና የወደፊት ስትራቴጂዎችን የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት በተሞክሮ አቅርበዋል።

በአማካሪው አቶ አለማየሁ አርጋው የቀረበው ሰፊ ሪፖርት የባህልና ስፖርት ዘርፍ ለማህበራዊ መስተጋብር፣ ለዲፕሎማሲ፣ ለስራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያለውን ዕምቅ አቅም በጥልቀት አብራርቷል።

ቋንቋንና ባህልን መሠረት ያደረገ የልምድ ልውውጥ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠናከር ያለውን ፋይዳ ያመላከቱት አማካሪው ኢትዮጵያ ያሏትን በርካታ ቋንቋዎችና ባህሎች እንደ ሀገራዊ ጸጋ በመጠቀም፣ ለማኅበራዊ ትስስርና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

በተለይም "የብርቱካናማ ኢኮኖሚ" (Orange Economy) ተብሎ የሚጠራውን የኪነጥበብ፣ የፊልም፣ የሙዚቃ እና የፈጠራ ዘርፍ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መሰጠቱም ተገልጿል።

ስፖርት ለዲፕሎማሲ እና ለማኅበራዊ ትስስር ያለው ሚናን ጨምሮ ​የመሠረተ ልማት መስፋፋት ያመጣው ውጤት በተሞክሮ ቀርበዋል።

አርቲስቶች ከሥራዎቻቸው የሚገኘውን የአዕምሮ ንብረት መብት (Intellectual Property) በአግባቡ እንዲያስከብሩና ተገቢውን የኢኮኖሚ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት ሥለመዘርጋቱም ለልምድ ልውውጡ ቀርቧል።

​ የታሪክና የዘመናዊነት ውህደት በተመለከተም ​እንደ ገና፣ ትግል እና ፈረስ ጉግስ ያሉ ባህላዊ ስፖርቶች ከጥንታዊ የታሪክ መሠረታቸው ሳይወጡ፣ ዘመናዊ ሕጋዊ መዋቅር ተበጅቶላቸው እንደ ብሔራዊ ውድድር እንዲካሄዱ መደረጉ ለናይጄሪያውያን ተመራማሪዎች ቀርቧል።

​የሚኒስቴሩ የስፖርት ልማት ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ አማረ በበኩላቸው የቋንቋና የባህል ብዝሃነትን ለሀገራዊ አንድነትና ለሰላም ግንባታ የመጠቀምን ስትራቴጂ ለልዑክ ቡድኑ አብራርተዋል።

ወ/ሮ አበባ አክለውም፣ "የብርቱካናማ ኢኮኖሚ" (Orange Economy) ተብሎ የሚጠራውን የኪነጥበብ፣ የፊልም እና የሙዚቃ ዘርፍ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ የተሰሩ ሥራዎችን ገልጸዋል።

​በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የናይጄሪያ ከፍተኛ የፖሊሲ አውጪዎችና አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ የባህልና ስፖርት አሠራር ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

አጥኚዎቹ በተለይም ፖሊሲዎችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የዘርፉ ተጨባጭ አስተዋጽኦ በአገሪቱ አጠቃላይ ምርት (GDP) ላይ ያለው ድርሻ፣ እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የታደሱና የተገነቡ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ዘላቂነትን በተመለከተ ማብራሪያ ጠይቀው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

​የልዑክ ቡድኑ አባላት በሰጡት አስተያየት፤ ኢትዮጵያ ያላትን የበለፀገ የባህል ሀብት ወደ ኢኮኖሚ ዕድል ለመለወጥ የምታደርገው ጥረት ለናይጄሪያ የፖሊሲ ቀረጻ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ መድረክ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ተግባራዊ የልምድ ልውውጥ ያሸጋገረና የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ዕውቀት ለጋራ እድገት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል ትልቅ እርምጃ መሆኑም ተጠቁሟል።

ግንቦት 4፣ 2018 ዓ.ም

ምንጭ፦ MoCS

Mesrak Sport ምስራቅ ስፖርት

Photos from Saint George S.A's post 12/05/2026
12/05/2026

የሀዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በአትሌት የብርጓል መለሰ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ፣ ለአትሌቷ ቤተሰቦች እና ለመላው የአትሌቲክስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

12/05/2026

አሳዛኝ ዜና

አትሌት የብርጓል መለሰ ልምምድ ላይ እያለች በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም መለየቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የ37 አመቷ አትሌት ሀገሯን በልዩልዩ ውድድሮች የወከለች ጠንካራ የማራቶን ሯጭ ስትሆን ከሁለት ሳምንት በኋላ በኦታዋ ለሚደረግ ማራቶን ዝግጅት ላይ እንደነበረች መረጃወች ያመላክታሉ።

አትሌት የብርጓል ባለትዳር እና የሁለት ልጆች እናትም ነበረች።

ልዩ ስፖርት በአትሌቷ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማትን ከፍተኛ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰብ እና ወዳጆች ልባዊ መፅናናትን ትመኛለች።

ነፍስ ይማር!

Photos from Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት's post 12/05/2026

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በተመሳሳይ ሰዓት ጨዋታቸውን ያደረጉት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ፉክክር አጥብቀዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእሙሽ ዳንኤል ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ድል ቀንቶታል።

በተመሳሳይ ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማን የገጠመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ ማህሌት ምትኩ እና በሻዱ ረጋሳ ከመረብ ባሳረፏቸው ሁለት ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ይህንን ውጤት ተከትሎ ሁለቱም ክለቦች በእኩል 66 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሊጉን በከፍተኛ ፉክክር እየመሩ ይገኛሉ።

የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ የተቀመጡት እነዚህ ሁለት ክለቦች በሊጉ መዝጊያ መርሐ-ግብር እርስ በእርስ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታም የሻምፒዮናነቱን ክብር ለመወሰን የሚያስችል በመሆኑ ከወዲሁ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Dire Dawa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Dire Dawa