Arooreessu Woradi Eote Biilloonyi Sinu Borro Mini Qoola

Arooreessu Woradi Eote Biilloonyi Sinu Borro Mini Qoola

Share

Eo Latishshaho!

12/02/2024
21/06/2019

ለመጠየቅ ከመሄድህ በፊት እንደምትጠየቅ አስበህ መሄድ እንዳለብህ ከዚህ ስብሰባ ተምሬአለሁ አብያተክርስቲያናት የቤት ስራችንን እንስራ ዶክተሩ ጥሩ የቤት ስራ ሰጥተውናል
======================================
በቤተመንግስት ከታዳሚዎች የተነሱ ጥያቄዎች እና የዶ/ር አብይ አስገራሚ መልሶች እና ምክሮች በከፊል!
መንደርደሪያ:-መልሶች በሜይን እስትሪም ሚዲያ ስላልተቀረፁ የስገረሙኝን የጠ/ሚንስትራችንን ምላሾች እና ምክሮች በከፊል እንዲህ ላቋድሳችሁ ወደድኩ:-

1- እንዴት አንድ የቤ/ክ ላይሰንስ ለማውጣት አንድ ሺህ ሰው ይጠየቃል እኔ ስጀምር በ7 ሰው ነበር …" በሚል ለተነሳው ጥያቄ
ሲመልሱ :- ሰባት ሰው ቤት ነው የሚፀልየው ላይሰንስ አያስፈልገውም።

2 - ወንጌላዊያኑ በኢትዮጲያ የነበራቸውን ታሪካዊ ዳራ በጥሩ ሁኔታ በመተንተን ወንጌላዊያን ያደረጉት ነገር በቅጡ መታወቅ አለበት (በሚገባ ልንታወቅ ይገባል) ለሚለው ረገጥ ያለ ጥያቄ

ሲመልሱ:- " ወንጌላዊያን ያሳውቃሉ እንጂ አይታወቁም። ዋናው ስራቸው ደግሞም ተልዕኮዋቸው እርሱን መግለጥ ማሳወቅ ነው። የሚል አጭር በሳል ምላሽ ሰንዝረዋል።

2- በዓለማዊ ሚዲያዎች ለመንፈሳዊ አገልግሎቴ ይሰጠኝ የነበረ የአየር ሰዓት ሳተላይቱ ወደ ኢትዮ ሳት ሲዞር ታግዷል ስለዚህ ይህ ህግ ሊታረም ይገባል ለሚለው ጥያቄ

ሲመልሱ:- " እርሱን ተወው ኢትዮጲያ እንኳን ለዘመናት አንድ ቲቪ ነበራት። ገንዘብ አለኝ እያላችሁ ቲቪ ከምታበዙ፡ አንድ አንድ ሰዓትም ቢሆን በተለያየ ቋንቋ ተባብራችሁ ቁምነገር ያለው ነገር ብታቀርቡ ይሻላል። ማስታወቂያችሁ እየቀነሳችሁም ቢሆን።"
-------//-------
- " የወንጌላዊያን የሀብት እና የስልጣን እሽቅድድም እንኳንስ ለሰማይ ለምድርም አይጠቅም።. . .የስልጣን ጥማታችሁ ከእኛ(ከፖለቲከኞቹ) የባሰ እየሆነ ነው።

- " . . .መኪና ያላቸው ምዕመናኖቻችሁ በዝተው መኪና ቢሰጡዋችሁ ምንም አይደል እንዴት ግን ያለ ርህራሄ ባስ የሚከፍለው ከሌለው ምዕመን ሰብስባችሁ መኪና ትገዛላችሁ?……እናንተ የሚያስፈልጋችሁ ከመነጋገርም በላይ ንስሃ እና ይቅርታ ነው።"

- ". . .እነዚህ ሰዎች ዝቅታ አይወዱም ተራራ ላይ መገኘት ነው የሚወዱት ተራራ ቀዝቃዛ ነው። እውቀትም ሙቀትም ታች ነው ያለው። "

- ስለ ቤ/ክ ውስጥ ዘረኝነት ለወንጌላዊያን ሞጋች ጥያቄ አዘል አስተያየት ሲሰነዝሩ " አባት ቀየራችሁ? በየትኛው አባታችሁ ነው የምትጠሩት?" ብለዋል።. . .
🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽
እርእሱ የኔ ነው ፅሁፉ ግን የአክሊሉ ተስፋዬ ነው በቦታው ተገኝቶ ያየውን የሰማውን ነው የፃፈልን

Photos 16/10/2015
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Hawassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Aroressa
Hawassa