20/11/2024
🎁Earn ETB10,700.00 in just two hours🎁
Esubalew Muche Zerihun invites you to earn money together! No investment required, everyone can withdraw money!
Nice
20/11/2024
🎁Earn ETB10,700.00 in just two hours🎁
Esubalew Muche Zerihun invites you to earn money together! No investment required, everyone can withdraw money!
እማዬ ስሚኝማ ፦ በራስ ወዳድነት አባዜ ታውሬ፣ ከንቱ ሀሳብ በህሊናዬ ደንቅሬ። የጊዜን ግልቢያ ፍፁም ዘንግቼ፣ በይዋል ይደር ደዌ ባጅቼ። ዛሬ ፣ነገ፣ከርሞ ስል ሳመነታ፣ ራሴን ለራሴ ብቻ ሰውቼ ሳንገላታ። ከእውር ድንብሬ ሳልባንንና ሳልነቃ፣ ፍቅርሽን ጠግቤው እንኳን ገና ሳልጠረቃ። ለእናትነትሽ፣ለስስትሽ፣ለማህፀንሽ ጓዳ፣ ሳልከፍል የልጅነቴን ታላቅ እዳ። ሞት ደርሶ ኖሮ ከአምስት ዓመት በፊት ከደጄ፣ ከጧት ከማታ ሳላስበው እናቴን ቀማኝ ከእጄ። እማዬ ሁሌም፦ ትዝታሽ፣ ጥንካሬሽ፣ ጽናትሽ፣ ልፋትሽ፣ ደግነትሽ፣ መልካም ንግግርሽ፣ የእናትነት እንክብካቤሽ እና አስተዳደግሽ፣ ልዩ የሆነው የእናትነት ፍቅርሽ፣ ቢወራም ቢጻፍም አያልቅም መልካምነትሽ፣ ከህሊና በላይ ነው ያንች እኮ ሁሉ ነገርሽ። እማዬ አንችን ካጣሁሽ በኋላ፦ አየሁት ሁሉንም ለካ ሰው የለኝም፣ እማ ካንች ሌላ ዘመድ አይገኝም። ልብሽ ያልተከፋ ፊትሽ ያልጠቆረ፣ በችግር በደስታ አብሮኝ የነበረ። በእውነተኛ ፍቅር ከፊቴ የቆምሽው፣ ያንችን ኑሮ ትተሽ ስለኔ የኖርሽው። አብዝቼ ብወድሽ ብወድሽ ብወድሽ፣ እማ ለውለታሽ ወደር አጣሁልሽ። እናማ እማዬ፦ መሬት ተዘቅዝቃ፤እኔ ብሸከማት፣ ውቅያኖስ ቢዘንቡ፤ቢወርዱብኝ ካናት፣ ያብርሃምን እድሜ፤ ብኖር ስታዘዛት፣ እግሮቿን እያጠብኩ፤ሺ ጊዜ ብስማት፣ መቼም አልክሳትም፤ የእኔ እናት ልዩ ናት። አዝያት ዓለምን ብዞር ብሽከረከር፣ አክናፋት ተችሬ ተሸክሜያት ብበር፣ በወርቅ አልማዝ እንቁ አድሎኝ ባኖራት፣ መቼም አልክሳትም የእኔ እናት ልዩ ናት። ምንም ድሃ ብትሆን ፊደሉም ባይገባት፣ ለእኛ ብላ ፊቷም ቢለዋወጥ ቢረታትም ማጣት፣ ከሠው ሳታሳንስ ለራስዋ እንኳን ሳትጎርስ አሳድጋኛለች፣ የእኔን ቀን ለማየት እራሱዋን ገድላለች። ዘመድ ወገኖቼ አንዴ ስሙኝማ፦ ከሀዘን ሁሉ የከፋው አጥንት ሰባሪ ሀዘን፣ እናትን በሞት መነጠቅ ጉዳቱ የሌለው ወሰን። ሕመሙ ጥልቅ ነው ሩቅ ከሲኦል እጅግ ይጠቁራል፣ በበረዶ ቤት ያልባል በእኩለ ፀሐይ ይበርዳል፣ የቀኑ ብርሃን ያስጠላል ማታ ሲጨልም ያስፈራል፣ ከጥርሳችን ሳቅ ይሸሻል ልባችን ሀዘን ላይ ያመሻል፣ ከውስጣችን ፍቅር ይረግፋል የቃላችን ውሉ ይጠፋል፣ የእናት ሀዘን ክፉ ነው ይህንን ሁሉ ይወልዳል። የዚህ መከራ ገፈታ ቀማሽ አንዱ እኔ ነኝና፣ አምስት ዓመት ሙሉ እያዘንኩ ኑሬያለሁ ሁሌ በጎዳና፣ ደግሞም ይቀጥላል የእናት ሀዘን አያልቅምና። እስኪ ዝም በሉኝ እንባዬን ላፍሰው፣ በድንገት አደለም ሆዴን ሆድ የባሰው፣ ጥልቅ ሀዘን ገብቶ ውስጤን አቁስሎት ነው፣ ደንዳና ነበረ ልቤማ ሲፈጥረው፣ አንዳንድ ጊዜማ መድኃኒት ነው እንባ፣ ጭንቀትን ያጥበዋል እንዲህ ግራ ስትጋባ። ደጋግሜ ላልቅስ እንባዬ ጎርፍ ሆኖ እኔኑ ይውሰደኝ፣ ሁሌ በቁጭት ከመኖር አንብቼ ይውጣልኝ። ሞትስ ብርቅ አይደለም ስው ሁሉ ይሞታል፣
ፍቅር ግን ታላቅ ነው ዘላለም ይኖራል።
አደራ ትላለች እማዬ የኛ እናት፣
ለወገን ለትውልድ ፍቅሬን አስተላልፉት። እማዬ የኔና እናት እንደዚህ ነበረች ፣ ከአምላክ ፈጣሪዋ ጋር የተነጋገረች፣
ቃሉን በሚገባ ጠንቅቃ ያወቀች፣
ፈጣሪዋን ፈሪ ደግ ሰው ነበረች።
መድኀኔዓለም በቀኝ ሚካኤል በግራ፣
ነፍስሽን ያኑሩት ከነአብርሃም ከቅዱሳን ጋራ።
21/05/2019