Dirar Abohoy

Dirar Abohoy

Share

እዚ ዕላዊ ገፅ ዓለም-ለኻዊ ስፖርተኛን ወናኒ ፍሉያት ክእለታትን ድራር ኣቦሆይ እዩ፡፡ Follow, Like, Comment & Share ብምግባር ቤተሰብና ይኹኑ!

Photos from Dirar Abohoy's post 17/05/2024

Dirar Abohoy #ማነው?

ኮርያ ካላት የማርሻል አርት መካከል #ቴኳንዶ አንዱ ነው። ይህም ከ2000 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) በኃላ የኦሎምፒክ ስፖርት ሆኖ ተመዝግቧል። ስለሆነም ከኮርያ አልፎ የዓለም ስፖርት በመሆን ታውቆ በዘርፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እየሰጠ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያም በስሟ ተመዝግቦ በ''ኦሎምፒክ ጌም'' ዓለም-አቀፋዊ ለመሆን የበቃ የስፖርት ዓይነት ባይኖሯትም በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች በተለይ በአትሌቲክስ ስፖርት የዓለም ራስ ሆና መዝለቅ የቻለች የዓለም ፈርጥ ነች።

ቢሰራበት ግን በየክልሉሉ የሚዘወተሩ ከራስ አልፈው ለዓለም የሚተርፉ ብዙ የስፖርት ባህላዊ ጸጋዎች እንዳሉን እሙን ነው። ጥናት እና ዝግጁነት ቢፈልጉም የገቢ ምንጭ ከመሆን ባሻገር አገሪቷን ለማስተዋወቅ ታላቅ ድርሻ መጫወት የሚችሉ ሀብቶች እንዳሉን አያጠራጥርም።

ከነዚህ አንዱ በአገር ደረጃ (በኢትዮጵያ የአእምሮ ንብረት ጥበቃ ባለስልጣን) ለስፖርተኛ ድራር ኣቦሆይ እና ለዶት ስፖርት የባለቤትነት ምስክር ወረቀት የተሰጠው አዲሱ ስፖርት ነው። ይህ ስፖርት አዲስ እንደመሆኑ መጠን ከማስተዋወቅ ጀምሮ የስፖርቱ ተሳታፊዎች ለመፍጠር ጊዜ የሚፈጅ ቢሆንም በትግራይ ክልል የወረዳዎች ውድድር መካሄድ ተችሏል። በቅርቡም ከአዲስአበባ አስተዳደር ጋር በመተባበር የክፍለ-ከተሞች ውድድር የሚዘጋጅ ሲሆን በቀጣይም በመላው ኢትዮጵያ ውድድሩ እንዲካሄድ ለማድረግ ታስቧል።

የብዙ ተሰጥኦዎች ባለቤት በሆነው ዓለም-አቀፋዊ ስፖርተኛ ስም በአገር ደረጃ የተመዘገበው ይህ ከኢትዮጵያ አልፎ ዓለም-አቀፋዊ ቅርፅ በመያዝ በኢትዮጵያ ስም በኦሎምፒክ ጌም ተመዝግቦ ለውድድር እንዲቀርብም ይሰራል። ይህም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ የሁሉም ደጋፊ እጅ የሚፈልግ የሕብረት ስራ ነው እና ሁሉም የሚመለከተው በበጎ ዓይን ተመልከቶ እንዲደግፍ ይጋበዛል።

ምክንያቱም ይህ ስፖርት እውን ከሆነ የማይታመን ገቢ ከማስገባት አልፎ የእርስ በእርስ ትስስር እና ዝምድና በማጉላት ሰላምን ከማስፈኑ በተጨማሪ የኢትዮጵያን ስም እና ሰንደቅ ከፍ እንዲል አድርጎ የብዙ ኢንቨስተሮች ቀልብ በመሳብ የብዙ ዜጎች ህይወት መቀየር የሚችል የስራ ዕድል ይፈጥራልና ነው።

ስለ ስፖርተኛ ድራር ኣቦሆይ ብዙ ማውራት ቢቻልም የማያውቀው ሰው የለም እና ጊዜ ለማሳጠር ያኽል :-
=> መቐለ በሚገኙት የጮምዓ ተራራ 1.2 ኪ/ሜ ፣ ባለ 8 ወለል ኖርዘርን ስታር ሆቴል ፥ ባለ 10 ወለል ፕላኔት ሆቴል ተገልብጦ በእጁ የወረደና የወጣ ሲሆን ከዚ በመቀጠልም በመዲናችን አዲስአበባ ከሚገኘው ባለ 37 ወለል የሕብረት ባንክ ህንፃ በ18 ደቂቃ ተገልብጦ በእጁ በመውረድ ክብረ-ወሰኑን ጠብቋል።

ይህም በዓለም-አቀፉ የተሰጥኦዎች ማህደር (Guinness Book Of World Records) የሚያዝመዘግበው ቢሆንም ከዚህ የተሻለ ስምና ዝና ለማግኘት የራሱን ክብረ-ወሰን አሻሽሎ ለዓለም ለማሳየት በማሠብ ቀጣይ ከሚባለው UAE ዱባይ ከሚገኘው የዓለማችን ትልቁ ህንፃ እና የዓለማችን ትልቁ ተራራ ኤቨረስት በእጁ ለመውረድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው። ለዚህም ከፍተኛ ወጪ ይጠይቀዋል እና የሚመለከታችሁ ሁሉ ከስፖርተኛው ጎን በመሆን ለሕልሙ መሳካት ትሰሩ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ድርጅቱ
PLC

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Mekelle?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Kedemay Weyane
Mekelle
7000