ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC

ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC, Sports Club, 1265, Mizan Teferi.

17/01/2022

የዳኒ ጉዳይ በዚህ ሳምንት እልባት ካላገኘ ከፍተኛ ሊጉ ሁለተኛ ዙር ሲጀምር ሚሰማን አይኖርም
ስለዚህ የጀመርነውን ዘመቻ በዚህ ሳምንት በደምብ በማሰማት የሚመለከተው አካል ጋር ደርሶ የተበደሉ ተጨዋቾቻችን እንዲመለሱና የጨዋታ ጊዜ እንዲሰጣቸው እናርግ
ክለቡንም ከሴረኞች እንታደገው
ከሚገዙት ተጫዋቾች 10 እጥፍ ችሎታ ያላቸው ልጆች አሉን
የሚዛን ልጆች ቲሙ ውስጥ በብዛት ይካተቱ
የጨዋታ ጊዜም ይሰጣቸዉ
ዳኒም ይመለስ

04/11/2019

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ድልድል ታወቀ
በከፍተኛ ሊግ የሚወዳደሩት ቡድኖች በየትኛው ቡድን እንደሚጫወቱ ለየቡድኖቹ በተላከ ደብዳቤ ማወቅ ችለዋል።
ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊጉ የወረዱት ሦስቱ ቡድኖች ደደቢት፣ መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ በሶስቱ ምድብ ላይ የምድብ አባት ሆነው የገቡ ሲሆን ከአንደኛ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደጉት ስድስት ቡድኖች የቦታ ርቀታቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ በየምድቡ ሁለት ሁለት ቦታ በመያዝ ተመድበዎል።
ምድብ ሀ
ደደቢት
ሶሎዳ ዓድዎ
ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን
አክሱም ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ደሴ ከተማ
ፌዴራል ፖሊስ
ገላን ከተማ
አቃቂ ቃሊቲ
ወልዲያ
ወሎ ኮምበልቻ
ምድብ ለ
ደቡብ ፖሊስ
ኮልፊ ቀራንዮ
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
ኢትዮጵያ መድን
ኢኮስኮ
ሀምበሪቾ
ሀላባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ
ነገሌ አርሲ
የካ ክፍለ ከተማ
ወላይታ ሶዶ
ዲላ ከተማ
ምድብ ሐ
መከላከያ
ጋሞ ጨንቻ
ባቱ ከተማ
አርባ ምንጭ ከተማ
ነቀምት ከተማ
ስልጤ ወራቤ
ቤንች ማጂ ቡና
ከምባታ ሺንሺቾ
ሻሸመኔ ከተማ
ጅማ አባ ቡና
ከፋ ቡና
ቡታጅራ ከተማ

07/10/2019

አዲስ ነገር
ሌላኛው የቤንች ቡና አጥቂ ተጫዋች የሆነው እና የቁርጥ ቀን ደራሻችን ወንዴ ኬራ አ.አ ውሃ ስራን ተቀላቅሏል።
ወንድዬ በሄድክበት ሁሉ መልካሙን ይግጠምህ
ውለታህን መቼም አንረሳም
በተለይ ደሞ ባለፈው አመት ከአርባምንጭ ጋር በነበረን ጨዋታ ከረፍት መልስ ተቀይረህ ገብተህ እነዛን 2 ሁለት ግቦች አስቆጥረህ በደስታ ያዘለልከንን መቼም አንረሳውም
በሌላ በኩል ግን ትልቅ ጥያቄ ተጭሮብኛል
የዘንድሮውን ቤንች ቡና በሀገራችን ልጆች አናየውም ወይም ክለቡ ውስጥ ቢኖሩ እንኳ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ነው ምናያቸው
ምክንያቱ ብትሉኝ ከዚ በፊት የነበሩ ቋሚ ሆነው ሚጫወቱ የሚዛን ልጆች ክለቡን ለቀው ሌላ ክለብ እየፈረሙ ነው
ታዳጊ ሚባል ነገርም እንደሌለ ሁላችንም ምናውቀው ነው
እና ጨዋታ ሲጀምር
የሚዛን ልጆች ይኖራሉ?? አላውቅም
ቋሚ ሚጫወትስስ?? አለውቅም
ያለ ሚዛን ልጆች ቤንች ቡናን ከሌላ ቦታ በመጡ ልጆች ልናይና ልንደግፍ ነውው?? አላውቅም
ጨዋታው ጀምሮ እነዚህ ጥያቄዎች እስኪፈቱልኝ በጉጉት......

29/08/2019

ደስ የሚል ዜና
ከፍተኛ ሊግ | ዲላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የስያሜ ለውጥ ማድረጉንም አሳውቋል
 August 29, 2019  አምሀ ተስፋዬ
ደረጀ በላይን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ዲላ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ መቀላቀል ጀምሯል።
በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ለበርካታ ጊዜ ከቡድኖች ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ በማደግ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሰለሞን ብሩ ዲላን ተቀላቅሏል። ሰለሞን በዳሽን ቢራ፣ ወሎ ኮምቦልቻ፣ ደደቢት፣ ጅማ አባጅፋር፣ ባህር ዳር እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ከደደቢት እና ወሎ ኮምቦልቻ በቀር አራቱ ቡድኖች ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድጉ የየቡድኖቹ አባል ነበር።
ከወልቂጤ አማካዩ ሀምዲ ሶፊ ሌላኛው ቡድኑን የተቀላቀለ ተጫዋች ሲሆን ከዚህ ቀደም በዲላ ሲጫወት የነበረው መና በቀለ ከኢኮስኮ ወደ ቀድሞ ቡድኑ ተመልሷል። ከቤንች ማጂ ቡናም የተከላካይ አማካዩ ዳንኤል ቡድኑን ተቀላቅሏል።
በተያያዘ ዜና ዲላ ከተማ ለእግርኳስ ፌዴሬሽን ባሳወቀው መሰረት የክለቡን ስያሜ ወደ ጌዴኦ ዲላ መቀየሩን የቡድኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተዘራ ጌታሁን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። “ቡድኑ ሥያሜውን ከዲላ ከተማ ወደ ጌዴኦ ዲላ ከቀየረ ቆየት ብሏል። ይህን ካሳወቅን ቆየት ብንልም አንዳድንድ ሚዲያዎች በዲላ ከተማ ነው የሚጠሩት፤ ይህ መስተካከል አለበት። ስፖርቱ በዞኑ ያሉትን ሁሉንም አካላት ማሳተፍ ስላለበት እና የኔነት ስሜት ይበልጥ ለመፍጠር በማሰብ የስያሜ ለውጥ ማድረግ አስፈልጓል።” በማለት ዲላ ከተማ ወደ ጌዴኦ ዲላ የስያሜ ለውጥ ማድረጉን ገልፀዋል።
የቤንች ቡናው ቅመም ዳኒ ዲላን ተቀላቅሏል

ዳኒዬ በሄድክበት ሁሉ መልካሙን ይግጠምህ
እንወድሀለን

Photos from ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC's post 26/05/2019

የዛሬው ከከፋ ቡና ጋር ላለው ደርቢ የደጋፊው ድባብ በዚሁ ቀጥሉ አይቶ ማለፉ ይከብዳል

Photos from ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC's post 07/04/2019

ቡንዬ(አረንጓዴ ጎርፎች) ከ ሀዲያ ሆሳዕና(ነብሮቹ)
9:00 ሰዓት
የዛሬው ጨዋታ ለሁለቱም ከባድና ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል
በመጀመሪያው ዙር ቤንች ቡና በወንዴ ኬራና በከማል አቶም ጎሎች ሆሳዕናን 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል
ያም እንዳለ ሆኖ ሆሳዕናዎች መሪነታቸውን ለማስጠበቅ ነው ሚፋለሙት
በተመሳሳይም ቤንች ቡና ከተሸነፈ የውጤት መቀራረብ ስላለ ከደረጃው ወደታች ይወርደል ካሸነፈ ደግሞ ከሌሎች ክለቦች ውጤት በኃላ ደረጃውን የሚያሻሽል ይሆናል
ስለዚህ ቡንዬ የዛሬውን ጨዋታ የግድ ማሸነፍ ወይም ውጤት ማስጠበቅ ይኖርበታል
ድል ለቡንዬ💪⚽⚽

Photos from ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC's post 06/04/2019

ቡናችን ነገ በሆሳዕና ሰታዲየም ከሆሳዕና ጋር ላለበት ጨዋታ በዝግጅት ላይ
ምንጭ:

Photos from ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC's post 31/03/2019

ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው
9:00 ሰዓት ላይ
ቤንች ቡና ነቀምት ከተማን ያስተናግዳል
እኛም ከዚ በፊት የነበረውን ቅራኔና ብስጭት በመተው በአዲስ መንፈስ በ2ኛው ዙር ቤንች ቡናን በሙሉ ልባችን በመደገፍ ወደ ድል እንመልሰዋለን💪💪💪
ድል ለቤንች ቡና

29/03/2019

Ehud bemnch buna ke Nekemt ketema gar bemedaw wesagn chewata yadergal

Photos from ቤንች ማጂ ቡና /Bench Maji Coffee FC's post 29/03/2019

Betechemarim ketachgnaw budn wanawn yetekelakelew
Enkuan lezi abekash berchilgn kanchi bzu ngr entebkalen
Betemesasaym lelaw tesfegna yhonal yalnew teamu wust takfual ketay amet sichawet endemnay tesfa alegn

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Mizan Teferi?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


1265
Mizan Teferi